Latest posts

EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
23 Sept, 18:02
የዳሞታ ተራራ የኢኮ-ቱሪዝም ልማት የመጀመሪያ ምዕራፍ ተጠናቅቆ ለጎብኚዎች ክፍት ሆነየታሪክ፣ የባህል እና የአካባቢው መለያ ስያሜ መገኛ የሆነው የዳሞታ ተራራ የመጀመሪያ ምዕራፍ የኢኮ-ቱሪዝም ልማት ፕሮጀክት ተጠናቅቆ ለጎብኚዎች ክፍት ሆኗል::የዳሞታ ተራራ በርካታ ብዝኃ ሕይወትን፣ ታሪካዊ፣ ባህላዊ እና ሃይማኖታዊ ይዘት ያላቸውን ብርቅዬ መስህቦች አቅፎ የያዘ ተፈጥሮአዊ ጸጋ ነው


EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
23 Sept, 17:29
“ቅጠል ተራ”ን ለዜጎች ክብር ወደሚመጥን ንፁህ፣ አረንጓዴ የመኖሪያ ስፍራ መቀየር ያስቻለን ፈጣሪ ይመስገን - ከንቲባ አዳነች አቤቤየአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ የከተማ አስተዳደሩ በቅጠል ተራ በ4 ወራት ውስጥ የገነባቸውን 960 ቤቶች ዛሬ ለልማት ተነሺዎቹ መልሰው አስተላልፈዋል::ከንቲባዋ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው ባጋሩት መልዕክት፣ የቀድሞው “ቅጠል ተራ” ለኑሮ እጅግ አስቸጋሪ፣ ለሰው ልጅ ክብር የማይመጥን፣ እጅግ የቆሸሸ፣ የተፋፈገ እና የተጨናነቀ በመሆኑ በእሳት አደጋ የነዋሪዎችን ሕይወት ጭምር አጥተናል ብለዋል


EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
23 Sept, 16:49
የትግራይ ክልላዊ መንግሥት ፖሊስ ኮሚሽነር ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት ሜጀር ጀኔራል ገብረ አድሃና የህወሓትን አጥፊ መንገድ በመቃወም ወደ ፌዴራል መንግሥት ገቡየትግራይ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት የህወሓት ነባር አመራር ሜጀር ጄኔራል ገብረ አድሃና የህወሓትን ከታሪካዊ ጠላቶቻችን ጋር በማበር ሀገር የማፍረስ ተልዕኮ እና የጦርነት አባዜ በመቃወም ወደ ፌዴራል መንግሥት ገብተዋል::ጄኔራል መኮንኑ በሀገር መከላከያ ሠራዊት ውስጥ በከፍተኛ የአመራር እርከን ላይ ያገለገሉ ሲሆን፣ ህወሓት በሀገር ላይ ክህደት እስኪፈጽም ድረስ የመከላከያ መረጃ እና ዘመቻ ዋና መምሪያዎች ኃላፊ ሆነው አገልግለዋል


EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
23 Sept, 12:38
የኢትዮጵያ የልማት እና የመፈጸም አቅም ከተግባራዊ ስኬት እስከ ሉዓላዊ ከፍታታሪክ እንደሚነግረን ሀገራት ከተጋረጡባቸው ውስብስብ ፈተናዎች ተላቅቀው ወደ ዘላቂ ብልጽግና ለመሸጋገር የሚያደርጉት ጥረት የሚመዘነው በወረቀት ላይ ባሰፈሯቸው ዕቅዶች ብቻ አይደለም::ይልቁንስ ዕቅዶቻቸውን በመሬት ላይ ለመተግበር በሚያስላቸው ተቋማዊ የማስፈጸም አቅም ነው


EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
23 Sept, 12:34
"የሀገር መከላከያ ሠራዊት ከኢትዮጵያ ያነሰ ዓላማ የለውም፤ የተደራጀው በኢትዮጵያውያን፣ የሚመራው በኢትዮጵያውያን፣ የሚሠራው ለኢትዮጵያ ነው"ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)


EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
23 Sept, 11:15
“ጀግኖች በሕይወት እያሉ ታሪካቸው ሊመዘገብ እና ለትውልድ ሊተላለፍ ይገባል” - ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላለቀጣዩ ትውልድ አርአያ የሚሆኑ ጀግኖችን ታሪክ መጻፍ እና ማሻገር ለሀገር ግንባታ ወሳኝ መሆኑን የኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ተናግረዋል::ኢታማዦር ሹሙ ይህንን የተናገሩት የሕይወት እና የውትድርና ጉዟቸውን የሚያስቃኘው “ድል ቁርሱ” የተሰኘ መጽሐፍ የምረቃ ሥነ-ሥርዓት ላይ ነው


EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
23 Sept, 10:23
የዲጂታል ኢትዮጵያ ጉዞ፡ ከዕውቀት ወደ ተጨባጭ ፈጠራየቴክኖሎጂ ለውጥ የዘመናዊ ዓለምን አቅጣጫ ከመቀየር ባለፈ የኢኮኖሚ ዕድገትን፣ የሥራ ፈጠራን እና የመንግሥት አገልግሎትን የሚወስን ዋነኛ ኃይል ሆኗል::ኢትዮጵያም ይህን የዓለም አቀፍ መነቃቃት ቀድማ በመረዳት ቴክኖሎጂን ከልማት ጋር በማስተሳሰር የዲጂታል ሽግግሯን ለማፋጠን ሰፊ የለውጥ ሥራዎችን እያከናወነች ትገኛለች


EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
23 Sept, 09:32
ጽኑ የሰማይ ላይ ዋስትና፦ የኢትዮጵያ አየር ኃይል የዘጠኝ አስርት ዓመታት የከፍታ ጉዞየአንድ ሉዓላዊ ግዛት የጽናት ማዕዘን የሚለካው ወሰኑን እና አየር ክልሉን በሚጠብቅበት አስተማማኝ አቅም ነው::ላለፉት ዘጠኝ አስርት ዓመታት የሀገራችንን አየር ክልል በንቃት የጠበቀው የኢትዮጵያ አየር ኃይል፤ ዛሬ ላይ ታሪካዊ ጀግንነቱን ከዘመኑ ቴክኖሎጂ ጋር አስተሳስሮ ወደ ላቀ ምዕራፍ ተሸጋግሯል


EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
22 Sept, 17:17
የፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላን የወታደራዊ ሕይወት ጉዞ እና ፅናት የሚያንፀባርቀው "ድል ቁርሱ" መጽሐፍ ተመረቀየኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የሕይወት ታሪክ፣ ልምድ፣ አመራር እና ጀግንነት ላይ የሚያጠነጥነው "ድል ቁርሱ" የተሰኘው መጽሐፍ በደማቅ ሥነ-ሥርዓት ተመረቀ::መጽሐፉ የግለሰብ ታሪክ ላይ ብቻ ሳይሆን፣ ከገጠሬዋ ኢትዮጵያ ክፍል ተነስቶ የወታደራዊ ሕይወትን በመቀላቀል ሀገር በፈተና ማዕበል በተናጠችበት ወቅት በፅናት የቆመ ታላቅ መሪን መንፈስ የሚያሳይ እና የሕይወት ውጣ ውረድን በጥልቀት የሚያስቃኝ ነው


EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
22 Sept, 16:51edited
የፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላን የወታደራዊ ሕይወት ጉዞ እና ፅናት የሚያንፀባርቀው "ድል ቁርሱ" መጽሐፍ ተመረቀየኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የሕይወት ታሪክ፣ ልምድ፣ አመራር እና ጀግንነት ላይ የሚያጠነጥነው "ድል ቁርሱ" የተሰኘው መጽሐፍ በደማቅ ሥነ-ሥርዓት ተመረቀ::መጽሐፉ የግለሰብ ታሪክ ላይ ብቻ ሳይሆን፣ ከገጠሪቱ ኢትዮጵያ ክፍል ተነስቶ የወታደራዊ ሕይወትን በመቀላቀል ሀገር በፈተና ማዕበል በተናጠችበት ወቅት በፅናት የቆመ ታላቅ መሪን መንፈስ የሚያሳይ እና የሕይወት ውጣ ውረድን በጥልቀት የሚያስቃኝ ነው


EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
22 Sept, 16:06
በፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ የተመራ የኢትዮጵያ ልዑክ በ81ኛው የተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ እየተሳተፈ ነው“መተማመንን ዳግም መገንባት እና አዳዲስ ለውጦችን በአግባቡ መምራት፤ ለሁሉም የሚሰራ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትን መፍጠር” በሚል መሪ ሐሳብ በኒውዮርክ እየተካሄደ የሚገኘው 81ኛው የተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ በፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ የተመራ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ልዑክ እየተሳተፈ ይገኛል፡፡በልዑክ ቡድኑ የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) እና የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምሥራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ ተሳትፈዋል፡፡ኢትዮጵያ በጉባኤው ብሔራዊ ጥቅሟን እንዲሁም የአፍሪካን ጥቅም በሚያስጠብቁ ጉዳዮች ላይ በሚደረጉ ውይይቶች በንቃት እንደምትሳተፍ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል::ኢትዮጵያ ከዋናው ጉባኤ ጎን ለጎን በሚደረጉ በርካታ የሁለትዮሽ እና የባለብዙ ወገን ስብሰባዎች ላይ እንደምትሳተፍም ተገልጿል


EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
22 Sept, 15:57
"የባህር በር የሌላቸው ሀገራት የልማትና የትራንስፖርት ትስስር የሕዝቦችን ሕይወት የመቀየር አቅሙ ከፍተኛ ነው"፦ የተባበሩት መንግሥታትየተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጠቅላላ ጉባኤ ፕሬዚዳንት ኻሊሉር ረህማን ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የሀብት ድልድሉንና አጠቃቀሙን በአግባቡ ማስተካከል እንዳለበት ጥሪ አቀረቡ::ፕሬዚዳንቱ እንዳመለከቱት ልማትን ለማፋጠንና ዘላቂ ለውጥ ለማምጣት የልማት እርዳታዎችን ማሳደግ፣ የዕዳ ጫናዎችን ማቃለል እንዲሁም የዓለም አቀፉን የፋይናንስ መዋቅር ማሻሻል ወሳኝና አስቸኳይ ጉዳይ ነው


EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
22 Sept, 14:44
"አፍሪካ ለመላው ዓለም ውይይት እና እርምጃ አስተዋጽኦ ማበርከት የምትችልባቸው ቋሚ መቀመጫዎች በተባበሩት መንግሥታት የጸጥታ ምክር ቤት ውስጥ ሊኖሯት ይገባል።" አንቶኒዮ ጉተሬዝ የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሐፊ


EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
22 Sept, 07:04
ቀይ ባሕር ኢትዮጵያን ለምን ይፈልጋል?የኢትዮጵያ የባሕር በር መዳረሻ ጥያቄ በተደጋጋሚ የሚነሳው ከአንድ ሀገር የኢኮኖሚና የንግድ ፍላጎት አንጻር ብቻ ነው::ሆኖም ጉዳዩን በጥልቀት ለሚመረምር አካል፣ የኢትዮጵያ ቀይ ባሕር ላይ መገኘት ለአንድ ወገን ብቻ የሚጠቅም ሳይሆን ለአጠቃላይ የቀይ ባሕር ቀጣና እና ዓለም አቀፍ የንግድ መስመር ዘላቂ ጥቅም የሚያስገኝ መሠረታዊ ጉዳይ ነው


EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
22 Sept, 06:55
ተመድ ሲፈተን፦ የኢትዮጵያ ፍትሐዊ የፖለቲካ ጥሪ፣ የማድረግ አቅም ልዕልና እና የዓለም አቀፍ ተፈላጊነት አዲስ ምዕራፍበኒውዮርክ በሚካሄደው የዓመቱ የተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የዓለም መሪዎች በተሰበሰቡበት በዚህ ወቅት፣ ድርጅቱ በታሪኩ ገጥሞት የማያውቅ ሁለንተናዊ ፈተና ውስጥ ይገኛል::የድርጅቱ ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ እንደሚያስጠነቅቁት የዓለማችን ሁኔታ ከቀን ወደ ቀን እየከፋ የመጣው በኃያላን ሀገራት መካከል ያለው የጂኦ-ፖለቲካ ክፍፍል የጸጥታው ምክር ቤቱን ውሳኔ መስጠት እንዳይችል "ሽባ" በማድረጉ ነው


EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
21 Sept, 18:17
ከኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ የተሻገረ ትርጉም ያለው የኩርሙክ ወርቅ ፋብሪካየማዕድን ክፍለ-ኢኮኖሚ ከጥሬ ሀብት ሻጭነት ወጥቶ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ዋና ምሰሶ የሚሆንበት ታሪካዊ መዋቅራዊ ሽግግር በተጨባጭ እየተረጋገጠ ይገኛል::በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ አሶሳ ዞን የሚገኘው የኩርሙክ የወርቅ ማዕድን ፕሮጀክት የዘመናዊ እና ግዙፍ የኢንዱስትሪ ደረጃ የወርቅ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ ግንባታን በማጠናቀቅ ወደ ምርት ምዕራፍ መሸጋገሩ በዘርፉ አዲስ የታሪክ ምዕራፍ ከፍቷል


EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
21 Sept, 17:54
ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የታዳሽ ኃይል ትኩረቱን ከማመንጨት ወደ ኤሌክትሪክ ተደራሽነት ሊያሸጋግር ይገባል - ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ የኢትዮጵያን ከፍተኛ ልዑካን በመምራት በኒውዮርክ እየተካሄደ ባለው የዓለም አቀፍ ታዳሽ ኃይል ጉባኤ ላይ እየተሳተፉ ነው፡፡ ፕሬዚዳንቱ በጉባኤው ላይ ባደረጉት ንግግር ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የታዳሽ ኃይል ትኩረቱን ኃይል ከማመንጨት ባሻገር ኤሌክትሪክን ለኢኮኖሚያዊ ሽግግር ለማዋል ወደሚያስችሉ መሠረተ ልማቶች ሊያሸጋግር እንደሚገባ ጥሪ አቅርበዋል፡፡የኃይል ማስተላለፊያ መስመሮች፣ የኃይል ማከማቻዎች እና ጠንካራ የኤሌክትሪክ አቅርቦት አቅም ሳይኖሩ ማመንጨት ብቻውን የኢኮኖሚ ሽግግርን ስለማያመጣ አዳጊ ሀገራት እምቅ አቅማቸውን ወደ አስተማማኝ ተደራሽነት እና የኢንዱስትሪ ዕድገት እንዲቀይሩ ጠንካራ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ድጋፍ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ካላት 9 ሺህ 761 ሜጋ ዋት አቅም ውስጥ ከ95 በመቶ በላይ የሚሆነው ከታዳሽ ኃይል የሚገኝ መሆኑን ያብራሩት ፕሬዚዳንቱ፤ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ እና ሌሎች የኃይል ማመንጫዎች ለኤሌክትሪክ ተደራሽነት እና ኢንዱስትሪ ልማት መሠረት መሆናቸውን አስገንዝበዋል፡፡ ግድቡ በሀገር ውስጥ አቅም እና በሰፊ የሕዝብ ተሳትፎ መገንባቱ የሀገር በቀል ባለቤትነት ማሳያ መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡ በተጨማሪም መንግሥት በአሁኑ ወቅት በአስር ሺዎች የሚቆጠር ሜጋ ዋት እምቅ አቅምን ለመጠቀም ሦስት ዐበይት ጉዳዮች ላይ እያተኮረ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ይኸውም በፈረንጆቹ 2030 የማመንጨት አቅምን


EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
21 Sept, 17:50
የአተካና ምሽት በመሳላ ዋዜማየከምባታ ብሔር የዘመን መለወጫ ‘መሳላ’ በዓል ዋዜማ በተለያዩ ሁነቶች እየተከበረ ይገኛል::በአካባቢው ባህል መሠረት ከእርድ ቀን አስቀድሞ የሚከበረው "የአተካና ምሽት" ወይም "የእናቶች መሳላ" በመባል የሚታወቀው የአተካና እራት የመብላት ሥነ-ሥርዓት በዱራሜ ከተማ፣ በኡቱቢ ወጋ አደባባይ እየተካሄደ ይገኛል


EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
21 Sept, 17:25
የማይበጠሰው የዳገታ ሰንሰለት፡ የፍቅር እና የይቅርታ ጥበብ“ዳገታ” በወላይታ ባህላዊ ሥርዓት ውስጥ ሁለት ሰዎችን “ከወንድማማችነት በላይ” በሆነ ፍጹም ታማኝነት ስና ፍቅር የሚያስተሳስር፣ እስከ ዕለተ ሞት የሚዘልቅ የማይፈርስ የፍቅር እና የአብሮነት ቃል-ኪዳን ነው::በጊፋታ በዓል ወቅት ሁለት ሰዎች በጋራ በመሆን የጊፋታ ልዩ ባህላዊ መጠጥ የሆነውን “ቦርዴ” በአንድ ቅል ይጋራሉ


EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
21 Sept, 17:04
የትግራይ ሕዝብ የሚፈልገው ሰላምን እና ልማትን እንጂ የቡድኖችን የፖለቲካ ሴራ አይደለም - ጋዜጠኛ ዳሞራ ያህያየትግራይ ሕዝብ ዘላቂ ጥቅም እና ሰላም እውን ሊሆን የሚችለው በኢትዮጵያ ማዕቀፍ ውስጥ ብቻ መሆኑን ጋዜጠኛ ዳሞራ ያህያ ተናግሯል::ጋዜጠኛው የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን እያከናወናቸው ያሉ ተግባራት እና በተለያዩ ከተሞች እየተተገበሩ የሚገኙት የኮሪደር ልማቶች፣ ኢትዮጵያውያን በጋራ ሲሠሩ የሚያመጡትን የላቀ ለውጥ እንደሚያሳዩ ገልጿል

Related Channels
Other channels in the same section of the catalogue.
