gram news
ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ channel avatar

ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

@eliasmeseret

Journalist-at-large

ProjectsENBlogsVerified by Telegram

133,000subscribers

Open the Channel

Latest posts

  • ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

    19 Sept, 16:50edited

    እነዚህን ስፖርተኞች እንደ ምሳሌ (role models) አድርገው ለሚመለከቱ ህፃናት እና ወጣቶች የምናስተላልፈው መልዕክት ምንድነው?https://www.meseretmedia.org/p/mma
    www.meseretmedia.orgከኤምኤምኤ (MMA) ስፖርት ጋር ተያይዞ ከሪንግ ውጭ የሚደረጉ ድብድቦች እና አምባጓሮዎች ለምን?በጋዜጠኛ ኤልያስ መሠረት ለመሠረት ሚድያ
    31,4001204436166Open in Telegram
  • ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

    17 Sept, 22:28edited

    የዛሬ 5 ወር ገደማ ለስራ ወደተዛወርኩበት ሜይን ግዛት በገባሁ በነጋታው ለቡና ቁጭ ባልኩበት ካፌ ሮቤልን ተዋወቅኩት፣ መልካም ሰው መሆኑን ለመረዳት ግዜ አልፈጀብኝም፣ በዛኑ ጠዋት ተወውቀን ለምሳ ቤቱ ይዞኝ ሄደ።በዚህ ወቅት ነበር የካንሰር ተጠቂ መሆኑን እንባ ባዘሉ አይኖቹ ያጫወተኝ። ከዛ ወዲህ በብዛት እንደዋወል ነበር። የዛሬ አንድ ወር ገደማ ግን "ዶክተሮች አንድ ወር ግዜ ብቻ ነው ያሉህ አለኝ" በማለት ነገረኝ፣ ወዲያው ቤቱ ሄጄም አገኘሁት። ኢትዮጵያ ሄዶ የህይወቱን መጨረሻ ቀናት ማሳለፍ እንደሚፈልግ ነግሮኝ ተሰነባበትን። ከዛ ወዲህ ስልኩ አይሰራም፣ ተጠፋፋን።ከኢትዮጵያ ተመልሶ እንደነበር እና እዚሁ ማረፉ ትናንት ተነገረኝ። ዛሬ ቀብሩ ፖርትላንድ ከተማ ውስጥ ተፈፀመ። ሮቤል በ19 አመቱ የዛሬ 20 አመት ገደማ ነበር ወደ አሜሪካ የመጣው፣ የሁለት ሴት ልጆች አባትም ነበር።ነብስህ በሰላም ትረፍ ወንድሜ!
    Image from a post by ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛImage from a post by ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ
    42,00089916665202012Open in Telegram
  • ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

    11 Sept, 11:49

    Me: “Just one lamb for Enkutatash.”Farmer: “Say no more.” Brings the excavator.ገመድ ፍለጋ የለ፣ እግር ያዝልኝ የለ 😊
    Image from a post by ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛImage from a post by ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ
    70,20071120717522169Open in Telegram
  • ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

    11 Sept, 03:08

    ፖርትላንድ፣ ሜይን ውስጥ ከኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያውያን ወዳጆች ጋር የአዲስ ዓመት ዋዜማን አሳለፍን።እንኳን አደረሳችሁ! መልካም አዲስ ዓመት!
    Image from a post by ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛImage from a post by ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ
    69,1004702613122102Open in Telegram
  • ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

    26 Aug, 18:35

    ሜርላንድ ግዛት እያለሁ በሐዋርድ ካውንቲ ውስጥ ባለ የጥቁሮች ታሪክ ዙርያ ለ 'Beacon' ሚድያ የፃፍኩት ትንታኔ የሰሜን አሜሪካ የአታሚዎች ማህበር (North American Mature Publishers Association- NAMPA) ሽልማት አስገኝቷል፣ ሽልማቱ በቴነሲ ግዛት በቅርቡ።That was a surprise! Thank you 🙏🏽ፅሁፉን ለማንበብ: https://www.thebeaconnewspapers.com/unearthing-howard-countys-black-history/
    Image from a post by ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛImage from a post by ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛImage from a post by ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ
    103,00099043370765Open in Telegram
  • ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

    25 Aug, 02:54

    አቶ ገዱ አንዳርጋቸውን ያሳያል የተባለ አንድ ቪድዮ ሲዘዋወር ተመለከትኩ፣ ቪድዮውን የለጠፉት ሰዎች ደግሞ 'የቀድሞው የክልል ፕሬዝደንት አሁን ላይ ይህን ስራ አሜሪካ እየሰሩ ነው' በሚል ለማሸማቀቅ ያሰቡ ይመስላል።ቪድዮው የእውነት ከሆነ ትክክለኛ መልዕክቱ ግለሰቡ እንደ ሌላው ሳይዘርፉ፣ በውጭ ሀብት ሳያካብቱ እንዲሁም በዱባይ፣ በናይሮቢ፣ በአውሮፓ እና በአሜሪካ የህዝብ ሀብት ይዘው እንዳልሸሹ፣ አሁን ላይ ደግሞ በነፃ ህሊና ስራ ሰርተው እየኖሩ እንደሆኑ የሚያሳይ ነው።ይህን መልዕክት የለቀቁ ሰዎች ስራ ሰርቶ ከሚኖር አንድ ባለስልጣን ከነበረ ግለሰብ ይልቅ የህዝብን ሀብት ዘርፎ ዱባይ ላይ ቪላ በመግዛት የሚንደላቀቅ ባለስልጣንን አክብረው እና አድንቀው የሚኖሩ ለመሆናቸው ምስክር አይሻም።@EliasMeseret
    98,2002,36084218230247Open in Telegram
  • ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

    10 Aug, 15:49

    ፎቷቸውን ትኩር ብዬ ተመለከትኩት፣ ህይወታቸው ገና ከፊታቸው የሚጠብቃቸው ወጣቶች እንደሆኑ ያስታውቃሉ። መሀል ላይ ያለው ወጣት ድንጋጤው ይጋባል፣ ሰው ባላጠፋው ጥፋት ሲከሰስ የሚሰማው ስሜት።ሁሉም 'ፋኖ ናችሁ' ተብለው ተረሸኑ፣ አስከሬናቸው እንኳን እንዳይነሳ ለቀናት ተከለከለ።ተመስገን ጌታቸው፣ ይታገሱ አሰግደው፣ ግዛው ግርማዬ!ነፍስ ይማር!https://www.meseretmedia.org/p/346
    www.meseretmedia.orgበጉራጌ ዞን አበሽጌ ወረዳ ሶስት ወጣቶች 'ፋኖ ናችሁ' ተብለው ከመኪና እንዲወርዱ ከተደረጉ በኋላ በአሰቃቂ ሁኔታ መረሸናቸው ታወቀ(መሠረት ሚድያ)- በማዕከላዊ ኢትዮጵያ በጉራጌ ዞን አበሽጌ ወረዳ ኢሰብአዊ እና ዘግናኝ ድርጊት መፈጸሙ ተሰምቷል።
    133,0001,4301265323227Open in Telegram
  • ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

    4 Aug, 01:20

    መንግስትን መቃወም እና የህዝብ ተቋማትን ማጥቃት ሙሉ በሙሉ የተለያዩ ነገሮች ናቸው!እንደ የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና ንግድ ባንክ ያሉ የህዝብ ሀብቶች ላይ ያተኮሩ ጥቃቶች ድንቁርና ካልሆኑ ምን ሊባሉ ይችላሉ? መንግስታት ይመጣሉ፣ ይሄዳሉ: ተቋማቱ ግን የህዝብ ሆነው ይኖራሉ። የሀገራችንን ሰንደቅ አላማ ይዞ አለምን የሚዞርን ታላቅ አየር መንገድ አርማ መሬት ላይ ጥሎ መርገጥ ከቀውስነት የዘለለ ትርጉም ያለው አይመስለኝም።@EliasMeseret
    Image from a post by ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛImage from a post by ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ
    132,00069037047342113Open in Telegram
  • ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

    28 Jul, 20:33

    ከአሜሪካዋ Maine ግዛት ዋና ገዢ (Governor) ጃኔት ሚልስ ጋር ትናንት በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ቃለ-መጠይቅ አርጌ ነበር፣ ዝርዝሩን ከታች ይገኛል ⤵️https://www.amjamboafrica.com/amjambo-exclusive-gov-mills-vows-to-protect-maines-immigrant-communities-after-fatal-ice-shooting/
    Image from a post by ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛImage from a post by ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ
    139,00018584171181Open in Telegram
  • ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

    27 Jul, 15:41edited

    የቀድሞው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ፣ አሁን ላይ ደግሞ በአሜሪካ የግዙፉ Delta Air Lines ስትራቴጂክ አማካሪ የሆኑት አቶ ተወልደ ገብረማርያም ከአየር መንገዳችን ከለቀቁ ወዲህ የመጀመርያውን ሰፊ ቃለ መጠይቅ ከ LTM- Network/Amjambo Africa ሚድያችን ጋር ቆይታ አድርገዋል።ሙሉው ቃለ መጠይቅ ከቀናት በኋላ በድረ-ገፃችን እና ሶሻል ሚድያ ገፆቻችን ላይ ይለቀቃል፣ ይጠብቁን amjamboafrica.comፌስቡክ: https://www.facebook.com/share/1JeWXnEfkK/ኤክስ: https://x.com/AmjamboAfricaዋትሳፕ: Follow the Amjambo Africa channel on WhatsApp: https://whatsapp.com/channel/0029VbCHMDG0AgWGXjzVk03Kኢንስታግራም: https://www.instagram.com/amjamboafrica?igsh=MWt2eDV1aWx0OHIyYg==
    Image from a post by ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛImage from a post by ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ
    125,000292160178Open in Telegram
  • ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

    23 Jul, 16:29

    'ሀገር እየመከረ ነው' በሚባልበት ወቅት ንፁሀን ዜጎች ላይ እንዲህ አይነት የጭካኔ ተግባር መፈፀም ምን ማለት ነው?https://t.me/meseretmedia/1787
    TelegramMeseret Media#ዜናመሠረት በአባይ ግዮን ቅድስት አርሴማ አንድነት ገዳም ላይ ዛሬ ጠዋት የድሮን ጥቃት ተፈፅሞ ምግብ ሲያዘጋጁ የነበሩ እናቶች መገደላቸው ተሰማ የአይን እማኞች ለሚድያችን ዛሬ ምሽት በስልክ እንደገለፁት ጠዋት 4:30 ላይ የተፈፀመው ጥቃት ያነጣጠረው በገዳሙ ውስጥ "ቤተ-እግዚአብሔር" በመባል በሚጠራው እና እናቶች ለምዕመናን ምግብ ለማብሰል በሚጠቀሙበት ክፍል ላይ ነበር። በዚህም ምክንያት የሰው ህይወት…
    101,000795574728129Open in Telegram
  • ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

    17 Jul, 18:53

    #የግልምልከታ"ጽምዶ" የተባለው ስብስብ በጋራ ጥቅምና በሰላም ላይ የተመሰረተ ሳይሆን የውስጥ ችግሮችን በኃይል ለመፍታት ከውጭ ኃይል ጋር መጣመርን የመረጠ ሀይል መሆኑን እያሳየ ነው፣ ይህ አካሄድ ደግሞ ታሪካዊ ስህተት እና የሕዝብ እልቂት ምንጭ መሆኑ የማይቀር ነው።የውስጥ የፖለቲካ ልዩነቶችንና ቅራኔዎችን በውይይት፣ በዕርቅና በሰላማዊ መንገድ በሀገር ውስጥ ከመፍታት ይልቅ የውጭ ኃይላትን ጦርና ጋሻ ጋብዞ የገዛ ወገንን ለማስጨፍለቅ ማሰብ እኩይ ተባር ነው።ቀደም ሲል የኢትዮጵያ መንግሥት ከኤርትራ ጋር በመጣመር በራሳችን ሕዝብ ላይ ያደረሰውን ሰብአዊ ቀውስና ስቃይ ስንተች የነበረውም ለዚሁ ነው ምክንያቱም እንዲህ ያሉ አሰላለፎች የሕዝብን ሕልውና የሚያጠፉ፣ ሀገርን ለባዕድ ጣልቃ ገብነት አሳልፈው የሚሰጡና ጠባሳቸው ለትውልድ የማይሻር በመሆኑ ነው።በመሆኑም አሁንም ሆነ ወደፊት ማንኛውም አካል በየትኛውም ስም “ጽምዶ” የሚል ስብስብ ፈጥሮ የሕዝብን ስቃይና መከራ የሚያበዛ ከሆነ በምንም ዓይነት መመዘኛ ተቀባይነት ሊኖረው አይችልም። የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት ሲባል የሰላማዊ ሰዎችን ሕይወት መገበሪያ ማድረግና ሀገርን ማፈራረስ የታሪክ ተጠያቂነትን ያስከትላል።እውነተኛ መፍትሔ ሊመጣ የሚችለው ከውጭ ኃይላት በሚገኝ የጦር ድጋፍ ሳይሆን በሀገር ውስጥ ኃይሎች መካከል በሚደረግ እውነተኛና ሁሉን አቀፍ ውይይት ብቻ እንደሆነ በጽኑ አምናለሁ፣ ሰላም የሚገነባው በጠመንጃ አፈሙዝ ሳይሆን በሰላማዊ ድርድር ነው።@EliasMeseret
    134,000784177166433930Open in Telegram
  • ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

    9 Jul, 14:43edited

    ካለፉት ሶስት ወራት ወዲህ በ Editor-in-Chief (ዋና አርታዒ) የስራ መደብ የሙሉ ግዜ ስራ የጀመርኩበት LTM-Network የአሜሪካዋ ሜይን ግዛት ውስጥ በሰባት ቋንቋዎች መረጃ የሚያቀርብ ብቸኛው እና በአይነቱ ትልቁ ጋዜጣ የሆነው የ Amjambo Africa አሳታሚ ነው። አሁን የተቋሙ ዋና ትኩረት የዲጂታል አቅሙን ማስፋት እንዲሆን አቅጣጫ አስቀምጠን እየሰራን ነው፣ አንዱ ደግሞ በወር ሁለት ግዜ በነፃ በቀጥታ ወደ አንባቢዎች ኢሜይል የምንልካቸው እና እኔ የማዘጋጃቸው Newsletter ናቸው።ዛሬውኑ ተመዝግበው መረጃዎቻችንን በነፃ ያንብቡ: ሊንክ ⤵️ https://www.amjamboafrica.com/newsletter/
    Image from a post by ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛImage from a post by ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ
    145,000256126312883Open in Telegram
  • ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

    4 Jul, 13:18

    Happy 250th Birthday, America! 🇺🇸Most of us are grateful to now call this great nation home. While no country is without its challenges, the United States remains a place where people can pursue opportunity, are treated with dignity, and enjoy freedoms that inspire hope.Here's to the enduring ideals that continue to bring people from around the world together.Happy Independence Day!@EliasMeseret
    Image from a post by ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛImage from a post by ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ
    148,0004411208219156Open in Telegram
  • ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

    22 Jun, 14:28

    Stepping into age 43 with gratitude!Thank you everyone for the warm birthday wishes 🙏🏽@EliasMeseret
    Image from a post by ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛImage from a post by ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ
    154,0001,47035143383517Open in Telegram
  • ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

    19 Jun, 23:02edited

    Having an incredible time at the Joe Russo's Almost Dead concert at Thompson's Point here in Portland, Maine!So grateful for all the amazing people stopping by to show love for our publication. Portland, you have a beautiful community!#PortME #AmjamboAfrica #Mainehttps://whatsapp.com/channel/0029VbCHMDG0AgWGXjzVk03K/216
    Image from a post by ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛImage from a post by ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ
    131,0001434111731Open in Telegram
  • ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

    19 Jun, 15:41

    ድሬዳዋ ላይ በግሉ ለፓርላማ ሊወዳደር እንቅስቃሴ ጀምሮ የነበረው ዶ/ር ሀብታሙ አለሙ በምስሉ ላይ በሚታየው መልኩ የስም ማጥፋት፣ ዛቻ እንዲሁም ማስፈራርያዎች ከደረሱት በኋላ ራሱን ከምርጫው አገለለ። ለምርጫ ቦርድ በተከታታይ አቤቱታ ቢያስገባም ምንም ሊፈይዱ አልቻሉም፣ አሁን ደግሞ ከምርጫው እንዲወጣ ያስገደዱት የከተማው አመራሮች ለስራ ወደ ድል ጮራ ሆስፒታል ሲያመራ አፍነው ወስደውታል።​ፖሊሶቹ ምንም አይነት የፍርድ ቤት የፍተሻም ሆነ የመያዣ ማዘዣ ሳይኖራቸው "በስልክ የተሰጠን የበላይ አመራር ትዕዛዝ ነው" የሚል ምላሽ ሰጥተዋል። ከሶስት ቀን በፊት ፍርድ ቤት አቅርበውት ዳኞቹ "አንተን ብሎ ዶክተር..." በማለት ሲያንቋሽሹት ነበር።እንኳን ሰው ምርጫ ተወዳድሮ ሊያሸንፍ ለመወዳደር በማሰቡ ብቻ ስቃይ የሚያይበት የድሬዳዋ አመራር አቶ ከድር ጁሀር ምላሽ ሊሰጥበት ይገባል።በስምሉ ላይ የሚታዩትን ቅንብሮች በመስራት ሲለቁ የነበሩት ከተማው ያደራጃቸው የቀን እና የለሊት የታክሲ ማህበራት አባላት የሆኑ ካድሬዎች ናቸው።@EliasMeseret
    Image from a post by ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛImage from a post by ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ
    118,0005201635623148Open in Telegram
  • ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

    16 Jun, 22:06

    ኢትዮጵያ እ.አ.አ በ2005፣ 2008፣ 2009፣ 2010፣ 2012 በቀድሞው ጠ/ሚር አቶ መለስ ዜናዊ ዘመን እንዲሁም በ2015 እና በ2017 በቀድሞው ጠ/ሚር አቶ ሐይለማርያም ደሳለኝ ዘመን በቡድን ሰባት (G 7) ሀገራት ስብሰባ ላይ ተሳትፋ ነበር። ዘንድሮ በፈረንሳይ እየተካሄደ ባለው ስብሰባ ኬንያ በፕሬዝደንቷ ስትወከል ግብፅ ደግሞ በታሪኳ ለሁለተኛ ግዜ በመሪዋ ተወክላ ተገኝታለች።ኢትዮጵያ በዚህ ጉባዔ ላይ አለመሳተፏ እና ሙሉ በሙሉ መቅረቷ በዲፕሎማሲውና በኢኮኖሚው ረገድ ስጋት ይፈጥራል። ይህ ይበልጥ አሳሳቢ የሚሆነው የዓለምን የፖለቲካና የኢኮኖሚ አቅጣጫ የሚወሰኑ ዋና ዋና ዓለም አቀፍ ውሳኔዎች፣ የዕዳ ቅነሳ ስትራቴጂዎችና የልማት አጀንዳዎች በሚቀረጹበት በዚህ ተፅዕኖ ፈጣሪ መድረክ ላይ የኢትዮጵያ ድምፅ ሳይሰማ በመቅረቱ ነው።ጎረቤት አገር ኬንያ በተደጋጋሚ የክብር እንግዳ ሆና ጥሪ እየተደረገላት ባለበት እና ሌላው ቀርቶ ግብፅ በታሪኳ ለሁለተኛ ጊዜ ብቻ በፈረንሳዩ የኤቪያን (Évian) የG7 ጉባኤ ላይ እንድትሳተፍ በተጋበዘችበት ወቅት ኢትዮጵያ አለመገኘቷ የዲፕሎማቲክ የቤት ስራ እንደሚጠብቀን አመላካች ነው።የኢትዮጵያ ከዚህ መድረክ መራቅ አገሪቱ ቀደም ሲል በአፍሪካ ቀንድ የነበራትን የጂኦፖለቲካዊ መሪነት ሚና እና በዓለም አቀፍ ደረጃ የነበራትን ዲፕሎማሲያዊ ተሰሚነት ዝቅ ማድረጉ አይቀርም። እንደ የአየር ንብረት ለውጥ፣ የፋይናንስ ድጋፍ እና የቀጣናው ደህንነት ባሉ ወሳኝ አጀንዳዎች ላይ ያላትን የመሰማት አቅም ይቀንሳል።የኢትዮጵያ ድምፅ ከፍ ብሎ እንዲሰማ የቤት ስራው በደንብ ይሰራ።@E
    Image from a post by ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛImage from a post by ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ
    109,0005522316736245Open in Telegram
  • ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

    14 Jun, 12:26edited

    ብዙ አትሌቶች የውጭ ሀገር ማናጀሮቻቸውን ይፈራሉ፣ በደል ሲፈፀምባቸው እንኳን ውጠው ያልፋሉ እንጂ መልሰው አይናገሩም። Not Kenenisa Bekele!ከጥቂት አመታት በፊት የቀነኒሳ ማናጀር ጆስ ሔርመንስ ለሚድያ የማይመጥን እና ወደ ሚድያ የማይወጣ ጉዳይ ሚድያ ላይ አወጣ። ቀነኒሳ ይህን አካሄድ ዝም ብሎ መመልከት አልፈለገም፣ እውነትም ከእርሱ ጋር ነበረች። በበርካቶች ዘንድ ግርምትን የፈጠረ እና በአትሌቲክስ ተንታኞች 'ደፋር' ያስባለ ቃለ መጠይቅ አድርጌለት በወቅቱ ትልቅ ዜና ሆነ፣ ጆስ ሔርመንስ ምላሽ አልሰጠም።"With those remarks, Jos Hermens acted like someone who lost a gamble."ቀነኒሳ ኋላ እንደነገረኝ ግንኙነታቸው ከዛ በኋላ ክብሮ (respectful) ሆኖ ቀጠለ (ዜናው: https://www.letsrun.com/news/2017/10/kenenisa-bekele-dismayed-jos-hermens-comments-professionalism-berlin-marathon-vows-break-world-record/)"ብዙ ደሀዎች መንገድ ላይ በበዙበት በዚህች ሀገር ውስጥ በጣም ውድ እና ውብ መኪና ይዞ ከቤት መውጣት እጅግ ከባድ ነው፣ ህሊናህ አይፈቅድም። ያንን መኪና ለማን ነው የማሳየው?። እዚያ መንገድ ላይ ፈስሰው ያሉት አባትህ፣እናትህ፣ወንድም እህትህ ፣ ዘመድ አዝማዶችህ ናቸው" ያለው ንግግሩም የብስለቱን ጥግ ያሳያል።መልካም ልደት አንበሳው!@EliasMeseret
    Image from a post by ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛImage from a post by ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ
    109,0001,36027168764Open in Telegram
  • ᴇʟɪᴀꜱ ᴍᴇꜱᴇʀᴇᴛ

    14 Jun, 02:16edited

    በአንዳንድ ጉዳዮች አስተያየት ስሰጥ 'በወያኔ ግዜ የት ነበርክ?' የሚሉ አስተያየቶችን አልፎ አልፎ አያለሁ። በወያኔ ግዜ አሁን ላይ በድምር 1 ሚልዮን ገደማ ተከታታይ ያላቸው የማህበራዊ ሚድያ ገፆቼ (ፌስቡክ፣ ኤክስ፣ ቴሌግራም እና ዋትሳፕ) አልነበሩኝም፣ ትንሽ ተከታይ ያለው አንድ የፌስቡክ ገፅ ነበረኝ።ታድያ በዛን ግዜ የሀገራችንን መልካም ዜናዎችም ሆነ የሚፈፀሙ ግድያዎችን፣ አፈናዎችን፣ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ወዘተ በአለም ዙርያ ለሚገኙ ቢሊዮኖች የማጋልጠው በሶሻል ሚድያ ሳይሆን በምሰራቸው ዜናዎች ነበር። ያኔ የት ነበርክ ለምትሉ ምላሹ በጥቂቱ ይኸው ⤵️1. Several dozen shot dead in weekend protests across Ethiopia https://apnews.com/general-news-6b3ca469c63941ebbfbbd321705aece12. Group: Ethiopia's security forces killed over 400 protesters https://www.ksl.com/article/40229325/group-ethiopias-security-forces-killed-over-400-protesters3. HRW: Media suppression in Ethiopia curbing democratic space https://www.sandiegouniontribune.com/2015/01/22/hrw-media-suppression-in-ethiopia-curbing-democratic-space/4. Ethiopia: At least 11 students killed in violence https://www.yahoo.com/ne
    92,900721325782443Open in Telegram