Latest posts

እንማር
22 Sept, 17:07edited
✅እናቴ ሁሌ እንዲህ ትለኝ ነበር፦“አባትህ ወደ ቤቱ ሲመለስ ፊትህን ፈገግ አድርግለት፤ ውጭ ያለው አለም ልብ በሚሰብሩ አውሬዎች የተሞላ ነው!።”―ዶይስቶቭስኪ✈️@Enmare1988 ✈️@Enmare1988
እንማር
21 Sept, 17:33edited
" ጥላቻ የሚያምር ነገር መሆኑን አላውቅም፡፡ ጥላቻን የተሸከመ ልብ ንፁህ መባሉም አይገባኝም፡፡” አልኳት::“አያምርም፡፡ አዎን ጥላቻ አያምርም፡፡ አየህ እውነትህን? ሁሉም ሰው በልቡ ለማንም ማሳየት የማይፈልገው ቆሻሻ ይኖረዋል፡፡ ጥላቻ፣ ክፋት፣ ግልፍተኝነት፣ ራስን መውደድ….. አንዱ ይኖርበታል፡፡ልዩነቱ ብዙዎቻችን ያ ባሕሪያችን በአስገዳጅ ሁኔታ ፈንቅሎ ካልተገለጠ በስተቀር ንጹሕ፣ ቅን እና ሁኔታ እንደሆንን እናስመስላለን፡፡ አንተ እንደዛ አይደለህም፡፡የተሰማህንና የሆንከውን ብቻ ነው የምትኖረው፡፡ የኖርከው ሕይወት የፈጠረብህን ጥላቻና ሽሽት አትደብቀውም፡፡ ያ ደግሞ እንድትድን ያደርግሃል። አንተ ክፉ ልብ የለህም፡፡ ማንንም መጉዳት አስበህ አትጎዳም። "ጠበኛ እውነቶች በሜሪ ፈለቀ✈️@Enmare1988 ✈️@Enmare1988
እንማር
21 Sept, 14:41edited
" ሁሉም ሰው በልቡ ለማንም ማሳየት የማይፈልገው ቆሻሻ ይኖረዋል፡፡ ጥላቻ፣ ክፋት፣ ግልፍተኝነት፣ ራስን መውደድ ….. ብቻ አንዱ ይኖርበታል፡፡ ልዩነቱ ብዙዎቻችን ያ ባህሪያችን በአስገዳጅ ሁኔታ ፈንቅሎን ካልተገለጠ በስተቀር ንፁህ፣ ቅን እና ፍፁም እንደሆንን እናስመስላለን፡፡ "ጠበኛ እውነቶች በሜሪ ፈለቀ❤❤@Enmare1988 ❤❤@Enmare1988
እንማር
20 Sept, 17:56edited
📚ርዕስ :- ኦሪጅን (Origin ✔️ደራሲ :- Dan Brown 👤ትርጉም:- ሃኒም ኤልያስ 📖የገፅ ብዛት:- 468እኛ ማን ነን? ከወዴት መጣን? ወደፊትስ ወዴት እንሄዳለን?"✅ለሺህ ዓመታት የሰው ልጅን ሲያወዛግብና ሃይማኖቶችን ሲያንቀጠቅጥ የኖረው ታላቁ ሚስጥር... በመጨረሻ ምላሽ ሊያገኝ ነው!✅በስፔን ቢልቦ ሙዚየም፤ በሺዎች የሚቆጠሩ ታዳሚዎችና በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የዓለም ህዝቦች በቀጥታ ስርጭት በሚከታተሉት ታሪካዊ ምሽት... ታዋቂው የነገሮች ተንባይ ኤድመንድ ኪርሽ የሰው ልጅን አመጣጥና እጣ-ፈንታ የሚቀይረውን ግኝት ይፋ ሊያደርግ ሰከንዶች ሲቀሩት… የጥይት ድምፅ ተሰማ!✅ደም በረበበበት መድረክ ላይ ሚስጥሩ ከሬሳው ጋር አብሮ ሊቀበር ሲል፣ የኪርሽ መምህር—የምልክቶች ተመራማሪው ፕሮፌሰር ሮበርት ላንግደን—እና የሙዚየሙ ዳይሬክተር ውቧ አምብራ ቪዳል፣ የይለፍ ቃሉን ለመክፈት ከጊዜ ጋር አደገኛ የሞትና የሽረት እሽቅድድም ውስጥ ይገባሉ። ነገር ግን ጠላታቸው ጊዜ ብቻ አይደለም!✅የሃይማኖት መሪዎች ጥቁር ጥላ፣ የስፔን ንጉሳዊ ቤተሰብ ሚስጥሮች፣ እና ጨካኝ አደኖች በየመጠምዘዣው ደብቀው ይጠብቋቸዋል። በዚህ አስፈሪ ፍልሚያ
እንማር
20 Sept, 11:06
ምን መማር ይፈልጋሉ👍ፎሬክስ ትሬዲንግ 👍Adobe Photoshop 👍ዲጂታል ማርኬቲንግ👍Website አሰራር 👍 የሞባይል ጥገና 👍 Computer ጥገና👍Gaming አሰራር 👍Hacking 👍 Graphics design👍 YouTube masterclass 👍Logo design 👍ድሮፕሺፒንግሁሉንም ኮርስ አንድ ላይ Telegram Channel ይቀላቀላሉ
እንማር
20 Sept, 09:38edited
✅ርዕስ:- አልገባኝም ✅ደራሲ:- ዮናስ ዘውዴ (የፍልስፍና መምህር)✅የገፅ ብዛት:- 135✅ ባለማውቅ ጨለማ ስትኖሩ ነፍሳችሁ ትጨነቃለች ሁሉ ነገር ያስፈራችሁ ዐይኖቻችሁ እየተጠበረበሩ የሚያዩትን አይምኑም ።ዋሻ ውስጥ የአንድ ክብሪት ብርሃን በላይ የምትፈልጉት አይኖረም ።ማንነትን መረዳት ዙሪያችሁን በውል መለየት ነወ። መማር ብርሃን ነው ፤✅በአለማወቅ ዋሻው ውስጥ ለተጣለ ሰው እውቀት ይገልጥለታል። አብዛኛ ሰው ይማራል የሚማረው ግን በማወቅ የሚገኘውን ሐሴት ፍለጋ አይደለም መማራቸውን የሚገለፅ ወረቀት ለመፈለግ ነው ።📔አልገባኝም ዬናስ ዘውዴ❤❤@Enmare1988 ❤❤@Enmare1988
እንማር
19 Sept, 15:50edited
📚ርዕስ:- አልገባኝም 👍ደራሲ:- ዮናስ ዘውዴ (የፍልስፍና መምህር) 👍የገፅ ብዛት:- 135 👍አቅራቢ:- ነቢል እንድሪስ====-----ከመጽሐፉ የተወሰደ -----====✅ የተሳሳተ አረዳድ ውስጥ የሚታዘዘው ታማኝ ተደርጎ ይወሰዳል። 'አይ" የሚለው ደግሞ ከአመጸኞች ጎራ ተፈርጆ ይገፋል። ተለጣፊ ስም በመፍራት ያላመኑበትን ነገር አድርጉ ሲባሉ ሰዎች ያደርጋሉ።✅ አሮጌ ልብና የበሬ ወለደ ትርክት ማንንም አያራምድም ባለበት የሚረግጥ ትውልድ አዲስ ብሔራዊ ጀግና አይፈጥርም✅ስኬታማ ሰዎች አዕምሯቸውን የመቆጣጠር አቅም ያላቸው ናቸው ከአንደበታችሁ ይልቅ ጆሮዎቻችሁ ክፍት መሆንን መልመድ አለባቸው። በሰማችሁት ሳይሆን በተናገራችሁት ነገር ሰውን ታስቀይማላችሁ። የልቡና ስፋት ሳይሆን የምላስ መርዘም አገር ያጠፋል። ሁሉም ሲናገር ያን ጊዜ ዝም በሉ። በጸጥታችሁ ሰላም ይፈጠራል፩. ገባኝ' የሚጀምረው ከ'አልገባኝም' ነው።፪.እምነት የሚጀምረው ከመጠራጠር ነው፫. የጥበብ ሁሉ መጀመሪያ ማሰብን መፍራት ሳይሆን ማሰብ መጀመር ነው( አልገባኝም...ከተለያዩ ገጽ የተወሰደ )
እንማር
18 Sept, 06:13
"ምን እያሰብሽ ነው?""ጊዜን ስለማቆም ስለምንፈለገው ስለምንወደው ምቾት በሚሰጠን ስፍራ ሁሉ!""ሃሳብሽ ማነው ጋር ነው?"ከቡና ወዝ ፡ ከመፅሃፍት ሽታ፤ እንደ ድካም እንቅልፍ ፡ እንደ እናት እቅፍ፤ ባዶ እግርን እንደመጓዝ ፡ ዕፅ እንደመጠብዘዝ፤ በአስቴር ዘፈን ፍሰት ፡ እንደ አዳም ድርሰት፤ አላውቅም አላውቅም መንፈሱን አልርቅም።"ሃሳብሽ ስለምንድነው?"እርጋታን በዝምታ ከቀይ ሰማይ ስር ማጥለል .. በፀዐይ መውጣትና መጥለቅ ያለህ እድሜ እንደ መኖር ..❤❤@Enmare1988 ❤❤@Enmare1988
እንማር
17 Sept, 06:24
✅⇲⇲ ✘ የውበት ወጥመድ ✘ ⇲ ⇲ ❏ ❐ ❑ ❒ ❏ ❐ ❏ ❐ ❑ ❒ ❏ ❐✅ ደራሲ ፦ ከርታ ክሌይ ✅ትርጉም ፦ ዮሐንስ ገ/ጻድቅ📖 ✈️@Enmare1988 ✈️@Enmare1988
እንማር
16 Sept, 15:58
✅ዳያን ትባላለች። በመንደሩ አለች የተባለች ውብ ነበረች። ያገባችው ወዳ ፈቅዳ አይደለም። ውበቷ አንድ ገበሬ አጥምዶ እንጂ። ትዳሩ ከጅምሩ አላቻ ጋብቻ ነበር። ዳያን በትዳር ህይወቷ ደስተኛ ባትሆንም አንድ ልጅ ወለደች። ይህ ልጅ የመኖሯ ምክንያት ሆነ።✅ነገር ግን ይህ ልጅ ታመመ ፤ በጠና ታመመ። በመጨረሻ ሞተ―ወይም ለዳያን የሞተ መሰላት። አሁን ዳያን እዚህ የምትኖርለት ምክንያት ሞቷል። ስለዚህ ማቄን ፣ ጨርቄን ሳትል ወደ ለንደን ተሰደደች።✅ብዙ አመታት አለፉ። ዳያን አሁን ከትልቅ ሰው ጋር ግንኙነት መስርታለች። ይህ ሰው ያለፈ ታሪኳን አያውቅም። ዳያን ከምታዘወትርበት የስእል ጋለሪ አንድ ልጅ እግር ሰአሊ ጋር ተግባባች። ከብዙ ምልልስ በኋላ ይህ ከፊቷ ቆሞ የምታየው የ19 አመት ወጣት ልጇ ፣ መሆኑን ተረዳች። ተደሰተች ፣ ደነገጠች። ልጇን በተደጋጋሚ ለማየት ወደ ስእል ጋለሪው መመላለስ አዘወተረች።✅በአንድ የተረገመ ቀን ግን ከቀድሞ ባሏ ብሩኖ ጋር በመንገድ ተገጣጠሙ። ብሩኖ የቀድሞ ሚስቴን አገኘሁ ብሎ ሲንሰፈሰፍ ፣ ዳያን ጭራሽ አላውቅህም ብላ ካደች።✅ብሩኖ ዳያንን ፍርድ ቤት ከሰሳት። ምስኪን ዳያን! መስካሪዎች አንድ በአንድ እየቀረቡ ሀሰተኝነቷን አረጋገጡባት። በመጨረሻ እራሷም አመነች። ጓደኛዋ የዋህነቷን እና ድንቁርናዋን ይቅር
እንማር
15 Sept, 17:36edited
«ፍቅረኛዬ ልደቷ ደርሷል። ምን ልስጣት » አለኝ«ለምን አትነቀስላትም» አልኩት።«ምን ልነቀስ? ስሟን? »«አይ እሱማ የተለመደ ነው። »«የተወለደችበትን ቀን? ወይ የተገናኘንበትን?»«እሱም አዲስ ነገር አይደለም!»«ታዲያ?»«ለየት ያለ ነገር። መጀመሪያ ከተገናኛችሁበት ቦታ... ወይ አብራችሁ ካደራችሁበት ጋር የተያያዘ ነገር ካለህ... » አልኩት...«ምርጥ ሀሳብ ! መጀመሪያ አብረን ያደርንበትን እንደውም!» ተቻኩሎ ሳይነግረኝ ጥሎኝ ሄደ። በሳምንቱ ጥቁርቁር ብሎ አገኘሁት።«ምነው?» አልኩት።
እንማር
14 Sept, 16:55edited
ዶይስቶይቭስኪ አንድ እውነት ልንገራችሁ ብሎ ይጀምራል፦‹‹ዓለም እንደ እናታችሁ አይደለችም ንዴታችሁን የመታገስ አመል የላትም፤ ቢርባችሁ ደርቃችሁ ትቀራላችሁ እንጂ ማንም ግድ አይሰጠውም!። እናት ግን ቀን ላይ ተናዳችሁ ትጮኹባታላችሁ፤ እናም ማታ በቀኑ መጨረሻ ሁሉንም እረስታ እራት ታቀርብላችኋለች..›› ❤🩹💬💬@Enmare1988 💬💬@Enmare1988
እንማር
14 Sept, 13:34
📢በ 2019 ህይወቴን እቀይራለውተረጋጋ Brooooooo 🤣🎉 yango ላይ ተመዝገበህ ስራ ካልጀመርክ አይቀየረም🌻 አዲሱን ዓመት ከYango ጋር በበለጠ ገቢ ይጀምሩ!🎉 የYango አጋር ሹፌር ይሁኑ ብዙ ተሳፋሪዎችን ያግኙ ብዙ ጉዞዎችን ያድርጉ ገቢዎንም ያሳድጉ!🎉 2019 ከያንጎ ጋር ልዩ የስኬት ዓመት ነው🌻 መልካም አዲስ ዐመት 2019የያንጎ ፕሮ መተግበርያን ለማውረድ ሊንኩን ይጫኑ👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇https://ya.cc/t/3nVOkmT99fvrCa
እንማር
14 Sept, 13:34

እንማር
14 Sept, 05:09edited
እንደምን አደራችሁ!⭐️ የዛሬዋ ቀን ውብ ቀን ትሁንላችሁ! ሰላማችሁ የበዛ ይሁን! እናንተና የእናንተ የሆነው ሁሉ ይጠበቅ! ለምልሙ! አብቡ! ይመርባችሁ! ያቀዳችሁት ይሳካላችሁ! ምንም ክፉ አጠገባችሁ አይቅረብ!⭐️ ይህንን ሁሉ ፈጣሪ ያድርግላችሁ! እነዚህና ሌሎችም መልካም ነገሮች ሁሉ ሲሆኑላችሁ ግን ሞልቶ ለሌሎች መትረፉንና ማካፈላችሁን አትዘንጉ!ዶክተር Eyob-Mamo💬💬@Enmare1988 💬💬@Enmare1988
እንማር
13 Sept, 18:02edited
✅ድሮ... ቆንጆ ስለሆነች ብቻ ነበር የወደድኳት ። ስቀርባት አራዳ ናት! አንድ ቀን በፀሃይ ተገናኝተን ስንቃደድ፥ ስንጫወት አስተናጋጇ መጥታ ይቅርታ ልወጣ ነው ሂሳብ አለችን ...ፈረቃዋን ጨርሳ ልትሄድ መስሎን ነበር፤ ለካ መሽቶ ሊዘጋ ነው። የምንወደው ሰው እንደኛው መለክያ ስናገኘው ሰዓቱ አልመጎተቱ ነው አይደል?ያልተመቸን ቦታ ሁሉ ሰዓቱ አይበርም!! ተፈጥሮ እንደ ምላስ We had an amazing time!! ብሎ አይዋሽም!!ስቀርባት መልኳን ትበልጠዋለች ...!ከሚሰማት 'ርቃ አታስመስልም፤ ጥላቻ አያሳድዳትም ፣ የበታቾቿ ላይ አትቀማጠልም። የወደቀ ላይ አትንጠራራም... ደስታዋ ቁስ ላይ አልተንጠለጠለም...።ትወጂኛለሽ እላታለሁ...?አስከሰማይ ነው የምወድህ ትላለች...አንገቴ ስር እየተወሸቀች። አወዳደዷ ስር አለው...ድንገት ተገንብሮ ውድቅ ሊል ይችላል የሚባል አይነት አይደለም።እዚህ ጋ...መዋደድ ባይኖር መኖር ይሰለቻል ብለን መኖርን እናበሽቀዋለን!!💬💬@Enmare1988 💬💬@Enmare1988
እንማር
13 Sept, 07:42edited
አንድ ቀን አንድ ታዳጊ ለፋርማሲስቱ እንዲህ አለው፦“መዳኒቶች ውጤት አላመጡም የእናቴን ጣቶች ስጠኝ!”ፋርማሲስቱ፡- የእናትህ ጣቶች ምንድናቸው?ታዳጊው፡-“ለብዙ ዓመታት እንቅልፍ ማጣት ነበረብኝ፤ እናቴ ድንገት ተነስታ ካየችኝ ጭንቅላቴን መዳበስ ትጀምራለች። በዚህ እጅ ውስጥ ምን አይነት ተአምር እንዳለ ባላውቅም የሰላም እንቅልፍ እተኛለሁ”💬💬@Enmare1988 💬💬@Enmare1988
እንማር
12 Sept, 15:35edited
ያዘዝነው ቡና ከፊታችን ተቀምጧል፤ እና ጥቂት ቀመስንለት ስኳር የለውም። አስተናጋጁን ጠርተን ለመውቀስ ግን ድፍረቱ የለንም። በራስ መተማመናችን ጠፍቷል፤ ጠንክሮ የመከራከር ኃይላችን ሞቷል።ስኳሩ የእኛ መብት አይደለም። ምንአልባት ስኬታማ ሰዎች ብቻ ናቸው ቡና ውስጥ ስኳር ለማድረግ የተፈቀደላቸው።እናንተ ግን አንድ ጊዜ ላይ ስኬታማ ነበራችሁ። በክፍል ውስጥ ጎበዝ ተማሪ ነበራችሁ። አፋችሁን ከፍታችሁ ማውራት ስትጀምሩ አስተማሪዎቻችሁ በዝምታ ነበር የሚያዳምጧችሁ።ታድያ ምንድነው የተከሰተው?፤ ምን እየተካሄደ ነው?። የሕይወት መንገዳችን በድንገት ለምን ቆመ?። ለነገሮች ያለን ጉጉት እና ፍላጎት በጠቅላላ ወዴት ተሰወሩ?።—ዶ/ር አሕመድ ካሊድ ታውፊቅ💬💬@Enmare1988 💬💬@Enmare1988
እንማር
12 Sept, 13:01
📢በ 2019 ህይወቴን እቀይራለውተረጋጋ Brooooooo 🤣🎉 yango ላይ ተመዝገበህ ስራ ካልጀመርክ አይቀየረም🌻 አዲሱን ዓመት ከYango ጋር በበለጠ ገቢ ይጀምሩ!🎉 የYango አጋር ሹፌር ይሁኑ ብዙ ተሳፋሪዎችን ያግኙ ብዙ ጉዞዎችን ያድርጉ ገቢዎንም ያሳድጉ!🎉 2019 ከያንጎ ጋር ልዩ የስኬት ዓመት ነው🌻 መልካም አዲስ ዐመት 2019የያንጎ ፕሮ መተግበርያን ለማውረድ ሊንኩን ይጫኑ👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇https://ya.cc/t/3nVOkmT99fvrCa
እንማር
12 Sept, 13:01
Followers write to the bot, you answer by reply, your account stays hidden. Created in one tap.
How it works →Related Channels
Other channels in the same section of the catalogue.
