gram news
ESAT (ኢሳት🇪🇹)® channel avatar

ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

@esat_tv1

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot 🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

ProjectsENNews

205,518subscribers

Open the Channel

Latest posts

  • ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

    24 Sept, 10:17edited

    የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ላሊበላ የሚያደርገው በረራ ሙሉ ለሙሉ ማቆሙን አስታወቀ‼️ላሊበላ ዙሪያ ትናንት ጀምሮ የከባድ መሳሪያ ተኩስ እየተሰማ ይገኛል። ይህንን ተከትሎ ከትናንት ጀምሮ ወደ ላሊበላ በረራ አለመደረጉን ከፍላይት ራዳር ለማረጋገጥ ተችሏል።@Esat_tv1 @Esat_tv1
    Image from a post by ESAT (ኢሳት🇪🇹)®Image from a post by ESAT (ኢሳት🇪🇹)®
    10,8003114962Open in Telegram
  • ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

    24 Sept, 03:40

    የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሸን ሊቀ መንበር የሰሜን ኢትዮጵያው ግጭት በአፋጣኝ እንዲቆም ጠየቁ‼️የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ማሕሙድ አሊ ዩሱፍ በሰሜን ኢትዮጵያ የተቀሰቀሰው ውጥረት እና ወታደራዊ መካረር "እጅግ እንዳሳሰባቸው" ገለጹ። ግጭቱ "በአፋጣኝ እንዲቆምም" አሳስበዋል።ዛሬ ረቡዕ መስከረም 13/2019 ዓ. ም. ማምሻውን ባወጡት መግለጫ፤ የመቀለ፣ የአክሱም እና ሽረ አውሮፕላን ማረፊያዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸው፣ ህወሓት የፌደራል መንግሥት ሠራተኞችን መያዙ እና የሕዝብ አገልግሎት መስጫዎች መቋረጣቸው እንዳሰጋቸው አስታውቀዋል።ረቡዕ ማለዳ ላይ የትግራይ ኃይሎች መቀለ የሚገኘውን አውሮፕላን ማረፊያ መቆጣጠራቸው ከተገለጸ በኋላ ከፌደራል መንግሥቱ ሠራዊት ጋር ጦርነት መቀስቀሱ ተሰምቷል።የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምሥራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ እና የቀድሞው የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ በኤክስ ገጻቸው ላይ ባጋሩት ጽሑፍ የህወሓት ኃይሎች "ጦርነት መክፈታቸውን" ገልጸዋል።@Esat_tv1 @Esat_tv1
    Image from a post by ESAT (ኢሳት🇪🇹)®Image from a post by ESAT (ኢሳት🇪🇹)®
    20,70073133Open in Telegram
  • ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

    24 Sept, 03:39

    💥በመገናኛ የካ ክፍለ ከተማ (ዲያስፖራ አደባባይ) የሚገኘውን የቴምር ፕሮፐርቲስ ዘመናዊ አፓርትመንት ሽያጭ መረጃ;​የክፍያ አማራጭ፦ በ40/60 አከፋፈል (40% አሁን፣ ቀሪውን 60% ቤት ሲረከቡ) ወይም ቀሪውን 80% እስከ 15 ዙር ያለምንም ወለድና የዕቃዎች ጭማሪ መክፈል ይቻላል። ለ40% ከፋዮች የ10% ቅናሽ አለ እንዲሁም 100% ለከፈለ 35%ቅናሽ አለው👉 1መኝታ 69ካሬ =ሙሉ ክፍያ 8,280,000ብር ይሆናል። 👉40%=3,312,000ብር ይሆናል ሌላው 60% ቤቱን ሲረከቡ የሚከፈል 👉100%ሲከፈል=5,382,000ብር ይሆናል።👉 1መኝታ(73 ካሬ):ሙሉ ክፍያ 8,760,000ብር|20%ቅድመ ክፍያ 1,752,000ብር። 40% 3,504,000ብር ቀሪውን ሲረከቡ 100% ሲክፈሉ 35% ቅናሽ 5,694,000 ብር ይሆናል።​2 መኝታ (90 ካሬ)፦ ሙሉ ክፍያ 11,700,000 ብር | 20% ቅድመ ክፍያ 2,340,000 ብር። 100% ሲከፍሉ 35% ቅናሽ=7,605,000 ብር ይሆናል ።​3 መኝታ (112 ካሬ)፦ ሙሉ ክፍያ 14,560,000 ብር | 20% ቅድመ ክፍያ 2,912,000 ብር። 100% ሲከፍሉ 35% ቅናሽ =9,464,000ብር።3 መኝት (123ካሬ);ሙሉ ክፍያ 14,760,000 ብር | 20% 2,952,000ብር። 100%ሲከፍሉ35%ቅናሽ=9,594,000 ብር ይሆናል ። 👉​ሌሎች ሳይቶች፦ በሳርቤት፣ አዋሬ፣ ቡልጋሪያ፣ ፒያሳ እና ገላን የመኖሪያና የንግድ ሱቆች/ቢሮዎች ይገኛሉ።ለበለጠ መረጃ +251978791342 ይደውሉልን::
    Image from a post by ESAT (ኢሳት🇪🇹)®Image from a post by ESAT (ኢሳት🇪🇹)®
    5,5401321Open in Telegram
  • ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

    23 Sept, 19:22

    የትግራይ ክልላዊ መንግሥት ፖሊስ ኮሚሽነር ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት ሜጀር ጀኔራል ገብረ አድሃና የህወሓትን አጥፊ መንገድ በመቃወም ወደ ፌዴራል መንግሥት ገቡ ‼️የትግራይ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት የህወሓት ነባር አመራር ሜጀር ጄኔራል ገብረ አድሃና የህወሓትን ከታሪካዊ ጠላቶቻችን ጋር በማበር ሀገር የማፍረስ ተልዕኮ እና የጦርነት አባዜ በመቃወም ወደ ፌዴራል መንግሥት ገብተዋል።ጄኔራል መኮንኑ በሀገር መከላከያ ሠራዊት ውስጥ በከፍተኛ የአመራር እርከን ላይ ያገለገሉ ሲሆን፣ ህወሓት በሀገር ላይ ክህደት እስኪፈጽም ድረስ የመከላከያ መረጃ እና ዘመቻ ዋና መምሪያዎች ኃላፊ ሆነው አገልግለዋል።ዕድሜያቸው ለውጊያ ያልደረሱ ሕፃናትን አስገድዶ በመመልመል ለጦርነት በመማገድ፣ የትግራይ ሕዝብን ስቃይ እያባዛ ያለውን የህወሓት እኩይ ሴራ በመቃወም ጄኔራሉ ከድርጅቱ መለየታቸው የሕገ-ወጡን የህወሓት ቡድን ሕልውና ማክተሙን ያሳያል። #EBC@Esat_tv1 @Esat_tv1
    Image from a post by ESAT (ኢሳት🇪🇹)®Image from a post by ESAT (ኢሳት🇪🇹)®
    22,90010635162Open in Telegram
  • ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

    23 Sept, 18:09edited

    በህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) የሚመራው የትግራይ ክልል መንግስት፤ በፌደራል መንግስት “ተከፈተብኝ” ያለውን “ወረራ” ለመመከት የክልሉን “ሰራዊት” “መመሪያ ሰጥቶ” ማሰማራቱን አስታወቀ‼️በክልሉ የሚካሄዱ የወታደራዊ እንቅስቃሴዎችን፣ ዘመቻዎችን እና ኦፕሬሽኖችን የሚመለከቱ መረጃዎችን፤ ከሚመለከተው አካል ውጪ ማሰራጨት “ህጋዊ ተጠያቂነት የሚያስከትል” መሆኑንም የክልሉ መንግስት አስጠንቅቋል።በፌደራል መንግስት ዕውቅና የተነፈገው በዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል የሚመራው የትግራይ ክልል መንግስት ይህንን ያስታወቀው፤ ዛሬ ረቡዕ መስከረም 13፤ 2019 ባወጣው መግለጫ ነው። የክልሉ መንግስት መግለጫውን ያወጣው፤ በትግራይ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ከትላንትና ጀምሮ “ጥቃቶች” እና “ውጊያዎች” እየተካሄዱ መሆኑ በተለያዩ የመረጃ ምንጮች ይፋ መደረጉን ተከትሎ ነው።“ጥቃቶቹ” እና “ውጊያዎቹ” በአላማጣ ከተማ እና አካባቢው እንዲሁም በትግራይ እና በአፋር ክልሎች አዋሳኝ ቦታዎችን ያካለሉ እንደነበሩ ምንጮች ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል። የትግራይ ክልል መንግስት በዛሬው መግለጫው፤ በትላንትናው ዕለት “በአውሮፕላን፣ በድሮኖች እና መድፎች ከባድ ድብደባ ሲካሄድ ውሏል” ብሏል።የክልሉ መንግስት በዛሬው ዕለት “ተከፈተብኝ” ያለው ጥቃት፤ “በእግረኛ ወታደሮች የታጀበ ነው” ሲል ወንጅሏል። ይህን ውንጀላ በተመለከተ እስካሁን ድረስ በፌደራል መንግስት በኩል በይፋ የተሰጠ ምላሽ ባይኖርም፤ የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የአፍሪካ ቀንድ አማካሪ የሆኑት አቶ ጌታቸው ረዳ ግን የህወሓት አመራሮች በአፋር እና በአማራ በሚገኙ የመንግስት ይዞታዎች ላይ ዛሬ ጠዋት “የተቀናጀ ጥቃት” መክፈቱን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት አስታውቀዋል።#ኢትዮጵያ_ኢንሳይደር@Esat_tv1 @Esat_tv1
    Image from a post by ESAT (ኢሳት🇪🇹)®Image from a post by ESAT (ኢሳት🇪🇹)®
    25,4009114721Open in Telegram
  • ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

    23 Sept, 18:02

    በሰሜን ኢትዮጵያ በፌደራል ኃይሎች እና በትግራይ ታጣቂዎች መካከል ግጭት መቀስቀሱ ተገለጸ‼️በትግራይ ኃይሎች እና በፌደራል መንግሥቱ ሠራዊት መካከል ጦርነት መቀስቀሱ የተገለጸው ረቡዕ መስከረም 13/2019 ዓ. ም. ማለዳ የትግራይ ኃይሎች መቀለ የሚገኘውን አውሮፕላን ማረፊያ ተቆጣጥረው በረራዎች መቋረጣቸው ከተነገረ በኋላ ነው።የፌደራል መንግሥቱ ከፍተኛ ባለሥልጣን እና የቀድሞው የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ በኤክስ ገጻቸው ላይ ባጋሩት ጽሑፍ የህወሓት ኃይሎች ጦርነት መክፈታቸውን ገልጸዋል።ትግራይን የሚያስተዳድሩት የህወሓት መሪዎች በበኩላቸው ባወጡት መግለጫ፤ በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ተከፈተብን ያሉትን ጥቃት ለመከላከል ኃይሎቻቸው እርምጃ እንዲወስዱ መታዘዛቸውን ገልጸዋል።የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምሥራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪው አቶ ጌታቸው እንዳሉት "በትግራይ ሌላ ዙር ጦርነት እንዳይቀሰቀስ ብዙዎች ጥረት ቢያደርጉም፣ ዛሬ ጠዋት የህወሓት አመራር" ጦርነት መክፈቱን አመለክተዋል።አክለውም የህወሓት ኃይሎች በአፋር እና በአማራ ክልሎች በሚገኙ ቦታዎች በኩል ሙሉ ጥቃት መክፈታቸውን በመግለጽ ጦርነት መቀስቀሱ "እጅግ የሚያሳዝን" ክስተት ነው ብለዋል።የህወሓት መሪዎች በበኩላቸው ኃይሎቻቸው ወደ መከላከል ውጊያ እርምጃ መግባታቸውን ገልጸው፤ ውሳኔው የተላለፈው የመንግሥት ኃይሎች ቀደም ብለው ጥቃት ከፈጸሙ በኋላ ነው ሲሉ ከስሰዋል።የህወሓት አመራሮች የትግራይ ጊዜያዊ መንግሥትን በማፍረስ ሥልጣን ከተቆጣጠሩ በኋላ ከፌደራል መንግሥቱ ጋር ውዝግብ ውስጥ ገብተው የቆዩ ሲሆን፣ አልፎ አልፎም ግጭቶች ሲከሰቱ ነበር።@Esat_tv1 @Esat_tv1
    Image from a post by ESAT (ኢሳት🇪🇹)®Image from a post by ESAT (ኢሳት🇪🇹)®
    25,800775221Open in Telegram
  • ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

    23 Sept, 14:30

    የአፋር ክልል መግለጫ አውጥቷል‼️ህወሃት ከትናንት ሌሊት ጀምሮ በአፋር ህዝብ ላይ መጠነ-ሰፊ ጦርነት ከፍተው ማደራቸውን የአፋር ክልል መንግሥት አስታወቀ።ከትናንት ጥፋቱ የማይማር ለጥፋትና ለእልቂት የተደራጀው የህወሓት ተላላኪ ቡድን ለፈጸመው ወረራ መራር ምላሽ የሚያገኝ ይሆናል ብሏል።ከአሁኑ ሰአት ጀምሮ የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ዋነኛ ተግባሩ የህዝቦቹን ደህንነት እና ሰላም መጠበቅ ስለሆነ፣ ከሌሎች ወዳጅ ሀይሎች ጋር በመሆን አጸፋዊው ራስን የመከላከል እርምጃ የሚወስድ ይሆናል ሲል በመግለጫው ላይ አስፍሯል።@Esat_tv1 @Esat_tv1
    Image from a post by ESAT (ኢሳት🇪🇹)®Image from a post by ESAT (ኢሳት🇪🇹)®
    30,20012534131264Open in Telegram
  • ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

    23 Sept, 14:29

    💥በመገናኛ የካ ክፍለ ከተማ (ዲያስፖራ አደባባይ) የሚገኘውን የቴምር ፕሮፐርቲስ ዘመናዊ አፓርትመንት ሽያጭ መረጃ;​የክፍያ አማራጭ፦ በ40/60 አከፋፈል (40% አሁን፣ ቀሪውን 60% ቤት ሲረከቡ) ወይም ቀሪውን 80% እስከ 15 ዙር ያለምንም ወለድና የዕቃዎች ጭማሪ መክፈል ይቻላል። ለ40% ከፋዮች የ10% ቅናሽ አለ እንዲሁም 100% ለከፈለ 35%ቅናሽ አለው👉 1መኝታ 69ካሬ =ሙሉ ክፍያ 8,280,000ብር ይሆናል። 👉40%=3,312,000ብር ይሆናል ሌላው 60% ቤቱን ሲረከቡ የሚከፈል 👉100%ሲከፈል=5,382,000ብር ይሆናል።👉 1መኝታ(73 ካሬ):ሙሉ ክፍያ 8,760,000ብር|20%ቅድመ ክፍያ 1,752,000ብር። 40% 3,504,000ብር ቀሪውን ሲረከቡ 100% ሲክፈሉ 35% ቅናሽ 5,694,000 ብር ይሆናል።​2 መኝታ (90 ካሬ)፦ ሙሉ ክፍያ 11,700,000 ብር | 20% ቅድመ ክፍያ 2,340,000 ብር። 100% ሲከፍሉ 35% ቅናሽ=7,605,000 ብር ይሆናል ።​3 መኝታ (112 ካሬ)፦ ሙሉ ክፍያ 14,560,000 ብር | 20% ቅድመ ክፍያ 2,912,000 ብር። 100% ሲከፍሉ 35% ቅናሽ =9,464,000ብር።3 መኝት (123ካሬ);ሙሉ ክፍያ 14,760,000 ብር | 20% 2,952,000ብር። 100%ሲከፍሉ35%ቅናሽ=9,594,000 ብር ይሆናል ። 👉​ሌሎች ሳይቶች፦ በሳርቤት፣ አዋሬ፣ ቡልጋሪያ፣ ፒያሳ እና ገላን የመኖሪያና የንግድ ሱቆች/ቢሮዎች ይገኛሉ።ለበለጠ መረጃ +251978791342 ይደውሉልን::
    Image from a post by ESAT (ኢሳት🇪🇹)®Image from a post by ESAT (ኢሳት🇪🇹)®
    13,70031Open in Telegram
  • ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

    22 Sept, 11:40

    የዘንድሮው የኢሬቻ በዓል መስከረም 23 እና 24 ይከበራል‼️በዚህም መሠረት “ኢሬቻ ለሀገራዊ መግባባት” በሚል መሪ ሀሳብ፤ ኢሬቻ ሆረ ፊንፊኔ መስከረም 23 እንዲሁም ኢሬቻ ሆረ ሀርሰዴ መስከረም 24 በቢሾፍቱ ከተማ ይከበራል።የምስጋና፣ የአንድነትና የፍቅር በዓል የሆነው ኢሬቻ የሀገርን ገፅታ በሚገነባ መልኩ እንደሚከበር ተገልጿል፡፡@Esat_tv1 @Esat_tv1
    Image from a post by ESAT (ኢሳት🇪🇹)®Image from a post by ESAT (ኢሳት🇪🇹)®
    18,500715711Open in Telegram
  • ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

    22 Sept, 04:17

    የአሜሪካ ግምጃ ቤት ኃላፊ ስኮት ቤሳንት ከነገ ጀምሮ “ሁሉም የኢራን አየር መንገዶች በረራ ማከናወን አይችሉም” ሲሉ አስታወቁ‼️ከሁለት ሳምንት በፊት የአሜሪካ ግምጃ ቤት 27 የኢራን አየር መንገዶች ላይ ማዕቀብ መጣሉ ይታወሳል።የቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ጂንግፒንግ ከሁለት ቀናት በኋላ ወደ አሜሪካ ተጉዘው በተለያዩ ጉዳዮች ዙርያ ከፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር ይመክራሉ።የሁለቱ አገራት መሪዎች ኢራን ላይ ስለተጣለው ማዕቀብ እንዲወያዩ ለማመቻቸት የቻይና ምክትል ፕሬዝዳንት ዋንግ ይ እና የአሜሪካ ግምጃ ቤት ኃላፊ ስኮት ቤሳንት እንደሚነጋገሩ ተገልጿል።የአሜሪካ መንግሥት ኢራን ላይ የምጣኔ ሃብት ጫና ለማሳደር ባንኮች፣ የንግድ ተቋማት፣ የቴክኖሎጂ እና በረራ ዘርፎች ላይ ማዕቀብ እንደሚጥል ከሳምንታት በፊት ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።@Esat_tv1 @Esat_tv1
    Image from a post by ESAT (ኢሳት🇪🇹)®Image from a post by ESAT (ኢሳት🇪🇹)®
    25,500748332Open in Telegram
  • ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

    21 Sept, 09:07

    በኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሱ ሰባት ታጣቂ ቡድኖች ፀረ መንግሥት ጥምረት መመስረታቸውን አስታወቁ‼️ሰባት ታጣቂ ቡድኖችን ያካተተ "ትብብር ለኅልውና" የተሰኘ ጥምረት መመስረቱን የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ዘመነ ካሴ በትግራይ መገናኛ ብዙኃን ቀርበው ተናገሩ።አቶ ዘመነ ካሴ ትናንት መስከረም 10/2019 ዓ.ም. አመሻሽ ላይ በትግራይ መገናኛ ብዙኀን ላይ ባነበቡት መግለጫ መሠረት ትብብሩ ህወሓትን፣ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊትን እና የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄን ጨምሮ ሰባት ታጣቂ ቡድኖችን ያካተተ ነው።የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ዘመነ በትግራይ ቴሌቭዥን በሰጡት መግለጫ የብልጽግና አገዛዝ ከተወገደ በኋላ "አካታች የሽግግር መንግሥት" እንደሚመሰረት ተናግረዋል።ይፋ በሆነው ትብብር አፋብን፣ ህወሓት፣ የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ፣ የጉሙዝ ሕዝቦች ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ፣ የቤንሻንጉል ሕዝቦች ነፃነት ንቅናቄ፣ የኦጋዴን ሕዝብ ነፃነት ግንባርና የአፋር ብሄራዊ አንድነት ግንባር አባላት መሆናቸው ተነግሯል።አቶ ዘመነ በመግለጫቸው ትብብሩ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይን መንግሥት ለመጣል እና "በሽግግር ቻርተር የሚመራ አካታች የሽግግር መንግሥት" ለመመስረት ዓላማ እንዳለውም አስረድተዋል።ትብብር ለኅልውናን በሰብሳቢነት የሚመሩት አቶ ዘመነ ካሴ "አዲስ የሽግግር ምዕራፍ" ሲሉ በመግለጫቸው የጠሩት ይህ ሂደት፤ የሁሉንም ኢትዮጵያውያን ሰብዓዊ እና ዲሞክራሲያዊ መብቶች "ሳይሸራረፉ እንዲረጋግጡ የሚያስችል" እንደሆነም አስታውቀዋል።ይህ "አዲስ ምዕራፍ" የሚከፈተው፤
    Image from a post by ESAT (ኢሳት🇪🇹)®Image from a post by ESAT (ኢሳት🇪🇹)®
    31,9002949332211613Open in Telegram
  • ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

    21 Sept, 09:06

    💥በመገናኛ የካ ክፍለ ከተማ (ዲያስፖራ አደባባይ) የሚገኘውን የቴምር ፕሮፐርቲስ ዘመናዊ አፓርትመንት ሽያጭ መረጃ;​የክፍያ አማራጭ፦ በ40/60 አከፋፈል (40% አሁን፣ ቀሪውን 60% ቤት ሲረከቡ) ወይም ቀሪውን 80% እስከ 15 ዙር ያለምንም ወለድና የዕቃዎች ጭማሪ መክፈል ይቻላል። ለ40% ከፋዮች የ10% ቅናሽ አለ እንዲሁም 100% ለከፈለ 35%ቅናሽ አለው👉 1መኝታ 69ካሬ =ሙሉ ክፍያ 8,280,000ብር ይሆናል። 👉40%=3,312,000ብር ይሆናል ሌላው 60% ቤቱን ሲረከቡ የሚከፈል 👉100%ሲከፈል=5,382,000ብር ይሆናል።👉 1መኝታ(73 ካሬ):ሙሉ ክፍያ 8,760,000ብር|20%ቅድመ ክፍያ 1,752,000ብር። 40% 3,504,000ብር ቀሪውን ሲረከቡ 100% ሲክፈሉ 35% ቅናሽ 5,694,000 ብር ይሆናል።​2 መኝታ (90 ካሬ)፦ ሙሉ ክፍያ 11,700,000 ብር | 20% ቅድመ ክፍያ 2,340,000 ብር። 100% ሲከፍሉ 35% ቅናሽ=7,605,000 ብር ይሆናል ።​3 መኝታ (112 ካሬ)፦ ሙሉ ክፍያ 14,560,000 ብር | 20% ቅድመ ክፍያ 2,912,000 ብር። 100% ሲከፍሉ 35% ቅናሽ =9,464,000ብር።3 መኝት (123ካሬ);ሙሉ ክፍያ 14,760,000 ብር | 20% 2,952,000ብር። 100%ሲከፍሉ35%ቅናሽ=9,594,000 ብር ይሆናል ።
    Image from a post by ESAT (ኢሳት🇪🇹)®Image from a post by ESAT (ኢሳት🇪🇹)®
    18,100261Open in Telegram
  • ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

    21 Sept, 09:06

    forwarded from @esat_tv1

    ለአዳማ ነዋሪዎች በሙሉ❗️ለልዩ ቀንዎ እና ለልዩ ዝግጅትዎ ውብና ማራኪ መሆን ይፈልጋሉ? 💕በሙያው ብቃት ባለው Makeup Artist የሚያምርና የሚመጥንዎትን Makeup በጥራት እንሰራለን። 💄✨✨ የምንሰጣቸው አገልግሎቶች፦👉 Simple Makeup 👉 Bridal & Bridesmaid Makeup 👉 Full Wedding Package 👉 Special Events Touch-up 👉 Henna & Mesh (Eyebrow)🌸 ደንበኞቻችንን በፍቅርና በጥራት እናገለግላለን!📍 አድራሻ፦ አዳማ 💄 Makeup Artist፦ Neb 📞 ስልክ፦ 0920393924
    Image from a post by ESAT (ኢሳት🇪🇹)®Image from a post by ESAT (ኢሳት🇪🇹)®
    17,800231Open in Telegram
  • ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

    20 Sept, 14:56

    ግብጽ በዓለም ላይ ደካማ የውሃ አስተዳደር ካላቸው ሀገራት መካከል አንዷ ናት‼️አቶ ጌታቸው ረዳአቶ ጌታቸው ረዳ እንዳሉት፤ የግብጽ አቋም የወንዙን እውነተኛ ምንጭ ጨምሮ ፍጹም ሐቅን የሚክድ የድፍረት አካሄድ መሆኑን ጠቅሰው፤ ይህ ደግሞ ፈጽሞ ተቀባይነት የለውም፡፡ግብጽ ሳይንስን በተቃረነ መልኩ በዓባይ አጠቃቀም ዙሪያ የምታራምደው የተሳሳተ አካሄድ ግብፃዊያን “ታሪካዊ መብቶች” በሚል የተሳሳተ የባለቤትነት ስሜት እንዲሰማቸው አድርጓል ብለዋል።“ታሪካዊ መብት” የሚለው ሀሳብ ውሃውን ቀድሞ መጠቀም የጀመረ አካል ለዘላለም መቆጣጠር አለበት ከሚል ስግብግብ አስተሳሰብ የመነጨ መሆኑን አመልክተዋል።ግብጽ በዓለም አቀፍ መድረኮች የምታራምደው የ“ውሃ ደህንነት” ጽንሰ ሀሳብ ጊዜ ያለፈበት የአንድ ወገን የበላይነት ፍላጎት አካል መሆኑንም አብራርተዋል።ግብጽ በዓለም ላይ ደካማ የውሃ አስተዳደር ካላቸው ሀገራት መካከል አንዷ ናት ያሉት አቶ ጌታቸው በበረሃማ አካባቢዎች የሚገኙት እንደ ቱሽካ ያሉ ከፍተኛ የውሃ መጠን የሚጠይቁ ፕሮጀክቶች የዚሁ ብክነት የተሞላበት አጠቃቀም ማሳያ ናቸው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።በግብጽ በሚገኘው የአስዋን ግድብ የሚከሰተው ዓመታዊ የውሃ ትነት መጠን፣ በኢትዮጵያ የውሃ ማከማቻዎች ውስጥ ከሚቀመጠው የውሃ መጠን በእጅጉ የሚበልጥ መሆኑንም ተናግረዋል።የዓባይ ወንዝ ዋና ምንጭ በሆነችው ኢትዮጵያ እና ሰፊ የመስኖ አቅም ያላት ሱዳን መካከል ሰላም እንዳይኖር ግብጽ ስትሰራ መቆየቷን አንስተው፤ በሱዳን ያለው ቀውስ ሀገሪቱ ውሃውን እንዳትጠቀም ለማድረግ ግብጽ የምታራምደው ስትራቴጂ
    Image from a post by ESAT (ኢሳት🇪🇹)®Image from a post by ESAT (ኢሳት🇪🇹)®
    33,000174351813Open in Telegram
  • ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

    20 Sept, 12:13

    ሁቲዎች የሳዑዲ አረቢያን ዋና ከተማ በባሊስቲክ ሚሳይሎች ማጥቃታቸውን ተናገሩ‼️በኢራን የሚደገፉት የየመን ሁቲ ተዋጊዎች በሳዑዲ አረቢያ ዋና ከተማ ሪያድ ላይ የድሮን እና የባሊስቲክ ሚሳይል ጥቃት መፈጸማቸውን ገለፁ።በተጨማሪም በአገሪቱ የቀይ ባሕር ዳርቻ ላይ ባሉ የኃይል ተቋማት ላይ መሰል ጥቃት መፈፀማቸውን ገልፀዋል።የሳዑዲ ባለሥልጣናት ቅዳሜ ዕለት ወደ ሪያድ የተወነጨፈ አንድ ባሊስቲክ ሚሳይል ማክሸፋቸውን የተናገሩ ቢሆንም ሌሎች ጥቃቶች ወይም ጉዳቶች ስለመኖራቸው አላረጋገጡም።ባለሥልጣናቱ ይህን ከማለታቸው አስቀድሞ፣ ቅዳሜ ዕለት በሳዑዲ ዋና ከተማ አቅራቢያ ባለው ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ አካባቢ ካሉ የነዳጅ ማጠራቀሚያዎች ጥቁር ጭስ ሲነሳ ታይቷል። ይህም በረራዎች ለአጭር ጊዜ እንዲስተጓጎሉ አድርጓል።ሁቲዎች በሐምሌ ወር በሳዑዲ አረቢያላይ የሚፈጽሙትን ጥቃት ካጠናከሩ በኋላ፣ በሪያድ የአየር ጥቃት ማስጠንቀቂያ ደወሎች ለመጀመሪያ ጊዜ ተሰምተዋል።የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ በመካከለኛው ምሥራቅ ያሉ አሜሪካውያን “ጥንቃቄ እንዲያደርጉ እና ሊኖሩ ለሚችሉ የበረራ ስረዛዎች እና ሌሎች የጉዞ መስተጓጎሎች ዝግጁ እንዲሆኑ” አሳስቧል።@Esat_tv1 @Esat_tv1
    Image from a post by ESAT (ኢሳት🇪🇹)®Image from a post by ESAT (ኢሳት🇪🇹)®
    33,1001051441Open in Telegram
  • ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

    19 Sept, 06:26

    41,400222252212103Open in Telegram
  • ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

    19 Sept, 06:24

    Image from a post by ESAT (ኢሳት🇪🇹)®Image from a post by ESAT (ኢሳት🇪🇹)®
    38,000106Open in Telegram
  • ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

    17 Sept, 13:22

    ከ46.4 ሚሊዮን ብር በላይ የማታለል ወንጀል ፈጽሞ ከሀገር ተሰውሯል የተባለ ተጠርጣሪ በኢንተርፖል ትብብር በቁጥጥር ሥር ዋለ❗️ከ46.4 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸውን 12 የ«BYD Seagull» ኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች በውክልና ለመሸጥ ከተረከበ በኋላ ገንዘቡን ለተበዳይ ሳያስረክብ ከባድ የማታለል ወንጀል ፈጽሞ ከሀገር ተሰውሯል የተባለ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ሥር ማዋሉን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታወቀ።ተጠርጣሪው ከግል ተበዳይ አቶ ዮናስ ገብረመስቀል ጋር በነበረው የውክልና ስምምነት ተሽከርካሪዎቹን ከተረከበ በኋላ፣ የተገኘውን ገንዘብ ይዞ ከሀገር በመውጣት በታይላንድ፣ በሲንጋፖር፣ በፊሊፒንስ እና በኢንዶኔዥያ ሀገራት ከሕግ ተጠያቂነት ለማምለጥ ሲዘዋወር ቆይቷል።የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከዓለም አቀፉ የፖሊስ ኅብረት ድርጅት (ኢንተርፖል) ጋር ባደረገው የቅርብ ትብብር በግለሰቡ ላይ ዓለም አቀፍ የቀይ ማስታወቂያ (Red Notice) እንዲወጣበት አድርጓል። በዚህም መሠረት ተጠርጣሪው መስከረም 3 ቀን 2019 ዓ.ም በኢንዶኔዥያ ኢንተርፖል በቁጥጥር ሥር የዋለ ሲሆን፣ መስከረም 5 ቀን 2019 ዓ.ም ለኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ተላልፎ መሰጠቱ ተጠቅሷል።ፖሊስ በተጠርጣሪው ላይ የምርመራ መዝገብ አደራጅቶ ያጠናቀቀ ሲሆን፣ ከዚህ በተጨማሪም በሌሎች ሁለት ከባድ የማታለል ወንጀሎች ተጠርጥሮ ተጨማሪ ምርመራ እየተጣራበት እንደሚገኝ አስታውቋል።የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በተለያዩ የሽብርና ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎች የሚፈለጉ አካላትን በቁጥጥር ሥር አውሎ ለሕግ ለማቅረብ ከሀገራት የፖሊስ ተቋማትና
    Image from a post by ESAT (ኢሳት🇪🇹)®Image from a post by ESAT (ኢሳት🇪🇹)®Image from a post by ESAT (ኢሳት🇪🇹)®
    50,30018227121073Open in Telegram
  • ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

    16 Sept, 17:34

    የትምህርት ሚኒስቴር የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎችን የዩኒቨርሲቲ ምደባ ማጠናቀቁን አስታወቀ‼️ምደባው የተማሪዎችን ውጤትና ምርጫ፣ የዩኒቨርሲቲዎችን የቅበላ አቅም፣ የክልል፣ የወረዳ፣ የዞን እና የትምህርት ቤት ስርጭት እንዲሁም የፆታ ሚዛን ታሳቢ በማድረግ መከናወኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል።በተጨማሪም ከ600 ነጥብ 500 እና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡ ተማሪዎች በመጀመሪያ ምርጫቸው መመደባቸውን አስታውቋል።ተማሪዎች የምደባ ውጤታቸውን በተዘጋጀው የኦንላይን ሥርዓት https://student.ethernet.edu.et/view-placement ማየት ይችላሉ ብሏል።ቅሬታ ያላቸው ምደባው ይፋ ከሆነበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ በኦንላይን ፦ https://student.ethernet.edu.et/complaints ብቻ ቅሬታ ማቅረብ እንደሚችሉ ተገልጿል።@Esat_tv1 @Esat_tv1
    Image from a post by ESAT (ኢሳት🇪🇹)®Image from a post by ESAT (ኢሳት🇪🇹)®
    54,30093245411Open in Telegram
  • ESAT (ኢሳት🇪🇹)®

    16 Sept, 06:09

    በአበሽጌ 13 ሰዎች ተገደሉ ‼️በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን አበሽጌ ወረዳ ውስጥ በሚገኘው እና ልዩ ስሙ "ዋልጋ" ተብሎ በሚጠራው ስፍራ፣ ትላንት መስከረም 4/2019 ዓ.ም ምሽት 3 ሰዓት ገደማ ታጣቂዎች በከፈቱት አሰቃቂ ጥቃት ቢያንስ 13 ንጹሃን ዜጎች መገደላቸው ተሰማ። የአካባቢው ነዋሪዎች በሰጡት ምስክርነት፣ ታጣቂዎቹ ንጹሃኑን ከመግደል ባለፈ 16 ያህል ሴቶችን በአስገዳጅ ሁኔታ አፍነው ወስደዋል።ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ታፍነው የተወሰዱት ሴቶች የት እንዳሉ እና በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ማወቅ አልተቻለም።@Esat_tv1 @Esat_tv1
    Image from a post by ESAT (ኢሳት🇪🇹)®Image from a post by ESAT (ኢሳት🇪🇹)®Image from a post by ESAT (ኢሳት🇪🇹)®
    48,9001897523843Open in Telegram