Latest posts

Ethio Book Review
21 Sept, 07:56
የጊዜያችንን Industrial Revolution የሆነውን Artificial Intelligenceን የአለማችን በተለይም ደግሞ የሀገራችን ሰዎች ሊሰጠው የሚገባውን ትኩረት ያልሰጡትን የሆነ ያክል ደረጃ ሚናውን ሊጫወት የሚችል መጽሐፍ ስለሰጠን ሶል እናመሰግናለን። ሁላችንም በተቻላችሁ መጠን ቢያንስ ምን እንደሆነና እንዴት መጠቀም እንደምትችሉና መጠንቀቅ እንደምትችሉ ብታውቁ መልካም ነው እንላለን።ደግሞ AI ከ Nuclear ጋር ተቀራራቢ የሆነ ስጋት አለማችን ላይ እንደደቀነ ባለሙያዎችና እራሳችሀው ፈጣሪዎቹ ያምናሉ!



Ethio Book Review
13 Sept, 12:04
forwarded from @tikvahethiopia
AI የሰውን ልጅ ሊገድል/ሊያጠፋ ይችላል?ከፍተኛ አቅም ያለው ሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ከሰው ልጅ አቅም በላይ ከደረሰና በቂ ቁጥጥር ካልተደረገበት ለሰው ልጅ ህልውና ከባድ አደጋ ሊሆን እንደሚችል የAI ተመራማሪዎችና የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች እያስጠነቀቁ ነው።በአሜሪካዊው የAI ኩባንያ Anthropic የሚሰሩ ተመራማሪዎች ኃይለኛ AI በዚህ አስር ዓመት ውስጥ ለሰው ልጅ ህልውና አደጋ ሊሆን እንደሚችል ገልጸዋል።ከኩባንያው የለቀቀው ጃኮብ ኮክሰን የተባለ ተመራማሪ፣ AI እስከ 2030 መጨረሻ ድረስ የሰው ልጅን ሙሉ በሙሉ ሊያጠፋ/ሊገድል የሚችልበት እድል እንዳለ ሲገልጽ፣ አንድ የአሁኑ የAnthropic ተመራማሪም የዚህ አደጋ ዕድል ከ10 በመቶ በላይ ሊሆን እንደሚችል ጠቅሷል።እንደ የAI ተመራማሪዎቹ ገለጻ፣ እጅግ የላቀ AI ከሰው ልጅ ጥቅም ጋር ተጣጥሞ እንዲሰራ የሚያረጋግጥ በቂ የደህንነት ዕቅድ አሁን የለም።ይህ ስጋት በብሪታንያ ፓርላማም ተነስቷል። የቀድሞ የመከላከያ ሚኒስትር ዴዝ ብራውን እና የኮምፒውተር ሳይንስ ተመራማሪው ፕሮፌሰር ስቱዋርት ራሰል፣ እጅግ የላቀ AI ከኑክሌር መሣሪያዎች ጋር ተመጣጣኝ ወይም ከዚያ የሚበልጥ ለሰው ልጅ ስጋት ሊሆን እንደሚችል አስጠንቅቀዋል።ሆኖም ሁሉም ባለሙያዎች በዚህ ላይ አይስማሙም። የAI እና ማኅበረሰብ ባለሙያ ፕሮፌሰር ኬት ዴቭሊን እንደሚሉት፣ " AI የሰው ልጅን ሊያጠፋ ይችላል " የሚለው ትንበያ የተረጋገጠ እውነታ ሳይሆን የአደጋ ግምት ነው።በአሁኑ ወቅት እጅግ የላቀ " ሱፐር ኢንተሊጀንት " AI እንደሌለን እና መቼ እንደሚኖርም



Ethio Book Review
28 Aug, 05:35edited
🔥🌟 በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የዶ/ር ኤልያስ ገብሩ አዲስ መጽሐፍ በቅርቡ ለንባብ ይበቃል! 🔥🌟የመጀመሪያው «አርምሞ» መጽሐፍ በወጣ በጥቂት ጊዜያት ውስጥ በተደጋጋሚ ታትሞ በአንባቢዎች ዘንድ ከፍተኛ አድናቆትንና ተወዳጅነትን ማትረፉ ይታወሳል። አሁን ደግሞ የዚያ ድንቅ መጽሐፍ ቀጣይ ክፍል የሆነው «አርምሞ 2» መጽሐፍ በቅርቡ በጃዕፈር መጻሕፍት አሳታሚነት ታትሞ ለናንተ ውድ ደምበኞቻችን ሊቀርብ መሆኑን ስናበስር በታላቅ ደስታ ነው! 📖✨ደራሲው የሥነ-አእምሮ ስፔሻሊስት፣ የሳይኮቴራፒስት እና የሂፕኖቴራፒስት ባለሙያ የሆኑት ዶ/ር ኤልያስ ገብሩ አእምሮ፤ በዚህ አዲስ መጽሐፍ እንደተለመደው ወደ ስለ ጥልቅ የውስጥ ጉዞ ፣ ስለራስ ምሕንድስና (Self-Engineering) እና ወደ የአእምሮ ሰላም የሚወስደን ሌላ ድንቅ ጥበባዊ ስራ ይዞልን ቀርቧል ።የነፍስዎን ጥያቄዎች የሚመልስ፣ አእምሮን የሚያድስና በዝምታ ውስጥ ያለውን ታላቅ ኃይል የሚያስተምር ልዩ መጽሐፍ! 💯🏪 በቅርቡ በሁሉም ቅርንጫፎቻችን ያገኙታል፦📍 ለገሃር (Leghar) 📍 አራት ኪሎ (4 Kilo) 📍 ሜክሲኮ (Mexico) 📍 ጀሞ (Jemo) 📍 ጥቁር አንበሳ (Tikur Anbessa) 📍 ሳሪስ (Saris) 📍 መሪ (Meri)➡️ Telegram / Facebook / Website


Ethio Book Review
6 Aug, 06:04
በስታንፎርድ ዩኒቨርሲቲ '2026 AI Index Report' የወጣው አንድ አስደናቂም አስፈሪም እውነታ አለ!በታዋቂው 'New England Journal of Medicine' ላይ የቀረቡ እጅግ ውስብስብ የሕክምና እንቆቅልሾችን ለመፍታት በተደረገ ሙከራ፣ የዓለማችን ምርጥ ሐኪሞች ለብቻቸው ትክክለኛውን በሽታ መለየት የቻሉት ከ10ሩ 2ቱን (20%) ብቻ ነበር። በተቃራኒው እንደ OpenAI o3 ባሉ አዳዲስ Reasoning ቴክኖሎጂዎች የተገነባው 'Diagnostic Orchestrator' የተባለው የAI ሲስተም 85.5% የሚሆኑትን በከፍተኛ ትክክለኛነት በመለየት የሰው ሐኪሞችን በ4 እጥፍ የሚበልጥ አስደናቂ ውጤት አስመዝግቧል።ይህ አስገራሚ ስኬት ሊገኝ የቻለው AIው እንደ አንድ ግለሰብ ሳይሆን እንደ 'የዲጂታል አማካሪዎች ስብስብ' (Multi-agent AI system) ተደራጅቶ መስራት በመጀመሩ ነው። አዲሱ አሰራር አንዱ AI መረጃ ሲፈልግ፣ ሌላው ምርመራ እንዲያነብና እርስ በርስ በመከራከር ስህተታቸውን እንዲያርሙ (Self-correction) ያደርጋቸዋል። ይህም ቴክኖሎጂው ሳያስብ የሚሰጣቸውን የተሳሳቱ መልሶች በ60% በመቀነስ፣ ልክ በሆስፒታል ውስጥ ያሉ ልዩ ልዩ ባለሙያዎች ተባብረው እንደሚሰሩት ሁሉ በከፍተኛ ቅንጅት እንዲሰራ አስችሎታል።AIው በሰከንዶች ውስጥ በሺዎች የሚቆጠሩ የሕክምና መጻሕፍትን አጣርቶ የምርመራ ግብዓት ሲያቀርብ፣ ሐኪሙ ደግሞ ዋናውን የሕክምና ውሳኔ፣ ርህራሄና የሞራል ኃላፊነት ይወስዳል። ወደፊት AIን በትክክል መጠየቅ (Prompting) የሕክምናው አካል የሚሆን ሲሆን፣


Ethio Book Review
3 Aug, 08:14
በተለይ AIን በትክክል መጠቀም ፈልጋችሁ መነሻ ሀሳብ ለምትፈልጉ ሰዎች በጣም ጥሩ ቪድዮ ነው:https://youtu.be/nMwYtkMKVvUYouTubeChatGPTን እንዴት በትክክል እንጠቀም? | How to use ChatGPT Amharic TutorialAI መጠቀም መጀመር ፈልገው ከየት መጀመር እንዳለባችሁ ግራ ገብቷችኋል? እንግዲያውስ ይህ የቻትጂፒቲ ሙሉ ስልጠና አካውንት ከመክፈት ጀምሮ ሁሉንም መሰረታዊ የሚባሉትን ነገሮች በደንብ የሚያስረዳ ቪድዮ ነው። ቪድዮውን እያያችሁ ሀሳብ፣ አስተያየት፣ ወይም ጥያቄ ካላችሁ comment ላይ ጻፉልን። ሌሎች ጥሩ ጥሩ የAI ቪድዮዎችን እንድንሰራላችሁ ቻናሉን subscribe ማድረግ እንዳይረሳ። Like |…
Ethio Book Review
28 Jul, 19:07
የፎዶር ዶስቶየቭስኪ ድንቅ የስነ-ልቦና ልብወለድ የሆነው ወንጀል እና ቅጣት (Crime and Punishment) በ3ኛ ዕትም በሙሉ-ብርሃን ጥላሁን ተተርጉሞ በደማቅ ሁኔታ ለንባብ በቅቷል። በጥፋት፣ በበደል እና በንስሃ መካከል ያለውን ጥልቅ የሰው ልጅ ህሊና ውጊያ በምርጥ አማርኛ የተረከውን ይህን ዓለም አቀፍ ድንቅ መጽሐፍ አሁኑኑ ያንብቡት!


Ethio Book Review
23 Jul, 04:58
አዲስ መጽሐፍ በገበያ ላይከዚህ ቀደም ሶስት ወጥ ረጅም ልብወለዶች እና አንድ የአጫጭር ልብወለዶች ስብስብ (በድምሩ አራት መጻሕፍት) ለንባብ ያበቃው ደራሲ ቃልኪዳን ኃይሉ ገብሬ፣ ከአምስት ዓመታት የጽሕፈት ማቆም (ዝምታ) በኋላ «ፌርማታ» የተሰኘውን አምስተኛ መጽሐፉን ለአንባቢዎች አቅርቧል!


Ethio Book Review
4 Jul, 16:24
አዲስ መጽሐፍ በገበያ ላይ፦ "እነሆ መቆያ" (ቅጽ 1) በጋዜጠኛ እሸቴ አሰፋለዓመታት በሸገር ኤፍኤም 102.1 የሬዲዮ ሞገድ በሚያማልለውና ጥልቅ በሆነው የአተራረክ ስልቱ በሚሊዮን የሚቆጠሩ አድማጮችን ልብ ሲገዛ የቆየው ዝነኛው ጋዜጠኛ እና ተራኪ እሸቴ አሰፋ፣ አሁን ደግሞ በብዙሃን ዘንድ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረውን "እነሆ መቆያ" (ቅጽ 1) መጽሐፉን በይፋ ለንባብ አብቅቷል።ይህ አዲስ መጽሐፍ በዓለም ታሪክ፣ በዓለም አቀፍ ፖለቲካ፣ በስለላ ድርጊቶች እና በታዋቂ ግለሰቦች ዙሪያ በሬዲዮ ሲተላለፉ የነበሩትን እጅግ ማራኪ ታሪኮች በጽሑፍ አቀናጅቶ የያዘ በመሆኑ፣ ለአንባቢያን አዲስና ጥልቅ የሆነ የንባብ ልምድ ያበረክታል።የታሪክ፣ የፖለቲካ እና የጥበብ ወዳጆች የሆናችሁ ሁሉ ይህንን ልዩ የሥነ-ጽሑፍ ስራ በማንበብ የዓለምን አስገራሚ ሁነቶች በምርጥ የአማርኛ ስነ-ቃል መቃኘት እንድትችሉ መጽሐፉን ገዝታችሁ እንድታነቡ እንጋብዛለን።መጽሀፍን ማንበብን መለማመድ ለሚፈልጉም ይህ መጽሀፍ በጣም ጥሩ ነው ብለን እናስባለን!


Ethio Book Review
26 Jun, 13:18
°°° ደግሞ እንደ ገና በእግዚአብሔር ቸርነት በሦስተኛ የልብ ወለድ ድርሰት ተመልሰናል። ምስጋናው የቤተሰብ፥ የወዳጅ እና የእናንተ የአንባቢያን ነው። «ጠይም ፡ ትውስታዎች» ቀጣይ ሳምንት ሐሙስ (ሰኔ 11) በጃዕፈር መጻሕፍት አሳታሚና አከፋፋይ በኩል በገበያ ላይ ይውላል።


Ethio Book Review
14 Jun, 13:44
ሰሞኑን ብዙ የቴሌግራም ተጠቃሚዎች ጉድ ተሰራን ብሎ በጣም የሚያስደነግጥ ሁኔታ ውስጥ ይገኛሉ። ካልታወቀ ሰው ሊንክ ተልኮላቸው አንዴ ያንን ሊንክ ከከፈቱ በኋላ አካውንታቸው ተጠልፈው በነሱ ስም ለብዙ ሰዎች እነሱ ያላሰቡትን የብልግና ቪድዮና ፎቶ እየላከባቸው ይገኛል።ይህንን ነገር ከዘመኑ የAI ቴክኖሎጂ ጋር ተያይዘው እንዴት አደጋው እየሰፋ እንደመጣና መከላከያ ዘዴዎቹን ከዚህ ቪድዮ መመልከት ትችላላችሁ።ሁሌም ቢሆን በማህበራዊ ሚድያ የሚላክላችሁን ሊንክ በፍጹም አትክፈቱ!https://youtu.be/hOUg-2GaewYYouTubeሰሞኑን የTelegram ተጠቃሚዎችን ምን አጋጠማቸው? | Telegram AI Scams 2026ብዙ ሰዎች በተለይ በቴሌግራም "ፎቶአችሁን እዚህ ሊንክ ላይ አየሁት" እና ሌሎች መሰል ጽሁፎችን እየላኩ በጣም ብዙ ማጭበርበሮችን እያደረገ ይገኛሉ። በዚህ የ AI ዘመን የኦንላይን Privacy (የግላዊነት ደህንነት) ጉዳይ ከመቸውም ጊዜ በላይ አሳሳቢ ጉዳይ ሆኗል። በዚህ ቪድዮ ውስጥ ሶሻል ሚዲያዎች (Facebook, Telegram, TikTok) እንዴት እንደሚከታተሉን፣ የባንክ እና የኢሜይል መረጃዎቻችን…
Ethio Book Review
11 Jun, 05:10
አዲስ መጽሐፍ ጥቆማየቀድሞው ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊ የክቡር አቶ አባዱላ ገመዳን የሕይወት ታሪክ አጠቃልሎ የያዘ ና በልጃቸው በቤኪ አባዱላ እና በዐቢይ ፈቅይበሉ አጋዥነት የተዘጋጀው የዚህ መጽሐፍ የመጀመሪያ ቅጽ በአማርኛ፣ በኦሮምኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋዎች ታትሟል።መጽሐፉ የአቶ አባዱላን የቤተሰብ ታሪክ፣ የሥራ ዘመን ተሞክሮ እና የፖለቲካ የሕይወት ውጣ ውረድ ከቅርብ ወዳጆቻቸውና የትግል አጋሮቻቸው ምስክርነት ጋር በማዋሃድ በሰፊው ይተርካል።https://www.ethiobookreview.com/book/abadula-gemeda-legacy-and-indentity-through-the-lens-of-others-beki-abadula-gemeda


Ethio Book Review
7 Jun, 18:08
ደረሰ ደረሰ!AAU: Where Readers become Leaders#AAUBookFair2026


Ethio Book Review
29 May, 16:31
ባለፈው April 2026 Anthropic የተባለ የAI ካምፓኒ 4ኛ version AI ሞዴላቸውን እየሰሩ ባሉበት ሁኔታ በታሪክ ታይቶ የማይታወቅ በጣም ጠንካራ AI model ሰራ። ሞዴሉም አስደንጋጭ ውጤት አሳየ።ከዛም ለህዝቡ የመልቀቅ ሀሳባቸውን ተውት። አሜሪካንና የአሜሪካ ካምፓኒዎችን ጥቅም ሊያስከብሩበት ወሰኑ ፣ ይህ ውሳኔ ደግሞ ቻይናን ጨምሮ ሌሎችን አለማት ጭንቅ ውስጥ ከተታቸው። አስደንጋጭነቱ ከሲስተሙ ጉድለት ወይም ችግር ኖሮበት ሳይሆን ካሰቡት በላይ በጣም "ጎበዝ" ሞዴል መሆኑ ነው። በተለይ ደግሞ የአለማችንን top የሚባሉ ሶፍትዌሮች ውስጥ ያለውን ክፍተት እና ድክመቶችን በሚገርም ሁኔታ መለየት ማስቻሉ ተወዳዳሪ ያልተገኘለት አደረገው።ይህ እየነገርኳቸው ያለሁት Theory ወይም scifi አይደለም። ስለዚህና እንደዚህ አይነት መረጃዎች ላይ ፍላጎት ይኖራችሁ ይሆን? ካላችሁ እባካችሁ አሳውቁኝ!


Ethio Book Review
23 May, 13:35edited
“ዮቶር”የተሰኘዉ “የአለማየዉ ደመቀ” መጸሀፍ በድጋሜ ታትሞ ለንባብ ቀርቧል


Ethio Book Review
11 May, 15:12
Kitaabni Zufaan Urgaatiin barreeffame kun seenaa jireenyaa fi qabsoo Leencoo Lataa, bu’uureessaa fi hayyuu siyaasaa Oromoo gameessa irratti xiyyeeffata. Jireenya isaa isa ijoollummaa magaalaa Dambi Doollootti eegale irraa kaasee, hanga falmii dippiloomaasii fi siyaasaa Adda Bilisummaa Oromoo (ABO) keessatti taasiseetti gadi fageenyan dhiyeessa. Keessattuu, garaagarummaa ilaalchaa fi rakkina hogganummaa bara 1990moota keessa ABO keessatti uumamee fi deemsa inni qabsoo hidhannoo irraa gara falmii dimookiraasii hunda- galeessaatti itti jijjiirame dhalootaaf ibsa.https://www.ethiobookreview.com/book/lencho-leta-zufan-urga


Ethio Book Review
10 May, 13:21edited
ChatGPTንም ሆነ ሌሎች AI ሲስተሞችን በነጻ ነው የምንጠቀመው ብላችሁ የምታስቡ ሰዎች እስቲ እቺን የ 5 ደቂቃ ቪድዮ ተመልከቱ!https://youtu.be/rFg8pHizUPkYouTubeምን ቢጠቀሙ ነው ግን? | ከ ነጻ AI ጀርባ ያለው ሚስጥር ሲገለጥ! | Why AI is Free?ብዙዎቻችን ChatGPT፣ Gemini እና Claude በነጻ እንጠቀማለን። ነገር ግን እነዚህን ግዙፍ ሲስተሞች ለማንቀሳቀስ OpenAI, Google እና Anthropic በቀን በሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር ወጪ ያደርጋሉ። ታዲያ ለምን ነጻ እንድንጠቀም ፈቀዱልን? በዚህ ቪዲዮ፣ በቴክኖሎጂው ዓለም ውስጥ "ነጻ" የሚባል ነገር እንደሌለና የ AI ኩባንያዎች ዳታችንን እንዴት እንደሚጠቀሙ፣ "Model Collapse"…
Ethio Book Review
30 Apr, 14:15
🔥 ዘጠነኛው የመጽሐፍት ጥቆማ ኢትዮጵያ ቡክ ፎረም የምዕራፍ 8ን የመጻሕፍት ዳሰሳ አጠናቀቆ እረፍት ላይ መሆኑ ይታወቃል። በቅርቡ ምዕራፍ 9ን የምንጀምር ሲሆን ተከታዩን ማስፈንጠሪያ በመጫን የመጻሕፍት ምርጫዎን ከእሮብ፣ ሚያዝያ 21 እስከ እሮብ፣ ሚያዝያ 28 ድረስ ያከናውኑ። 👉🏾 የሚጠቁሟቸው መጻሕፍት ስለ ኢትዮጵያ ወይም በኢትዮጵያውያን የተጻፉ መሆን አለባቸው። 👉🏾 የሚጠቁሟቸው መጻሕፍት አማርኛ ከሆኑ በአማርኛ ይጻፉ። 👉🏾 የፈለጉትን ያህል መጻሕፍት መጠቆም ይችላሉ። 👉🏾 የተነነበቡ መጻሕፍትን ማየት እንዲሁም ፈልገው ማግኘት ይችላሉ። የመጠቆሚያ ሊንክ ፡ https://cutt.ly/UtLWnvXq


Ethio Book Review
28 Apr, 12:14
ማንም ሰዉ ድሀ እንዲሆን ወይም የሌሎች ባሪያ ተከታይ እንዲሆን የተበየነበት እጣ ፋንታ የለም። የውድቀቱም ሆነ ስኬቱ ሙሉ ምክንያት ራሱ ነው። በራሱ ላይ ያለው መረዳት አናሳ በመሆኑ እንጂ ማንም የሆነውን እንዲሆን ቀድሞ የወሰነበት ነገር የለም።የትናንት ግንኙነታችን የሚናፍቀንን ያህል ደግመን ማሰብና ማስታወስ የማንፈልገው የምንፈራዉና የምንጠላውም ትዝታ ይኖረናል። የታሰርንበትን የተደበደብንበትን የምንወደውን ሰው ያጣንበትን የታመምንበትን ተቸግረን የተሰበርንበትን የመሳሰሉ ብዙ የተጎዳንባቸው ትናንቶችን ለማስታወስ አንደፍርም። በተቃራኒው ደስ የሚለንንና ብልጫ ያየንባቸውን ትናንቶች ደግሞ እንናፍቃለን ለሰዎች ብናወራቸው ሞላ ያለ ክብር የሚያጎናጽፉን ለመሳሰሉት ትዝታዎች ናፍቆት ይኖረናል።እንደ ሀሳብ ደግሞ ተሽለን ያለፍንበት የእውቀትና የሙያ ጊዜ ይኖራል በሙያም ጥሩ የሰራንበት በእውቀትም የተሻለ መረዳት እንዳለን ማስታወስ የምንችለው የትናንት ልምድ ይኖረናል። እርሱንም ማሰባችን አይቀርም ሁለቱም የትናንታችን እኛነቶች ናቸው። ዛሬን ያደረጉን የየግል እድሜዎቻችን ናቸው።ሰዉ በተፈጥሮው በእነዚህ ሁለት የትናንት እሴቶቹ ይገነባል። ከሰዎች ጋር በኖራቸው ትዝታዎቹ ውስጥ የማኅበራዊነት ተፈጥሮውን ይማራል። በኖራቸው የየእለት ልምዶቹ ደግሞ በእውቀት ራሱን የሚያሳድግ አሳቢ ፍጡር መሆኑን ይመለከታል።


Ethio Book Review
17 Apr, 14:18
በአሁኑ ሰዓት ዓለምን እያነጋገረ ያለውና Altera በተባለ የቴክኖሎጂ ኩባንያ የተሰረው Project Sid AI አለማችንን ወዴት እየወሰደ እንደሆነ ቁልጭ አድርጎ ያሳየ Research ነው። ሙሉውን አስገራሚ መረጃ በዚህ ቪዲዮ ይመልከቱ። እርግጠኛ ነኝ ትገረማላችሁ! https://youtu.be/IDQYtTsEVD8 👇YouTubeAI ጉድ አፈላ! | አረ ወዴት እየሄደን ነው? | ለማመን የሚከብደው የ1000 AIዎች Research ውጤት!የ Altera ተመራማሪዎች 1,000 AI ኤጀንቶችን በMinecraft ውስጥ በማሰማራት ያደረጉት አዲስ የጥናት ውጤት። እነዚህ ኤጀንቶች የራሳቸውን ሀይማኖት ከመመስረት ጀምሮ እንደ ሰው ማሰብ፣ መገበያየት እና ማህበራዊ ስርዓት መፍጠር የሚችሉ ናቸው። ቪዲዮው AIዎች እንዴት በራሳቸው ፍቃድ ስልጣኔን እንደሚገነቡ እና ወደፊት በሰው ልጅ ህይወት ላይ ሊኖራቸው የሚችለውን ተፅእኖ ይተነትናል። ስለ አርቲፊሻል…
Ethio Book Review
9 Apr, 05:57
የ Robert Kiyosaki "Rich Dad Poor Dad" ቁልፍ ሃሳቦች በቀጣይ ይትኛውን መጽሐፍ እንስራላችሁ?

Related Channels
Other channels in the same section of the catalogue.
