gram news
ኢትዮ መረጃ - NEWS channel avatar

ኢትዮ መረጃ - NEWS

@ethio_mereja_news

ኢትዮጵያን መውደድ ባትችል አትጥላት ማክበር ባትችል አታዋርዳት ማራመድ ባትችል አታዘግያት መጠበቅ ባትችል አትበትናት። ይህን በማድረግ ታሪክ ባትሠራም ታሪክ አታበላሽም። ለአስታየት @ethio_merjabot @B_promotor

ProjectsENNews

45,276subscribers

Open the Channel

Latest posts

  • ኢትዮ መረጃ - NEWS

    14 Nov, 15:22edited

    በአፄ ኃይለ ሥላሴ ዘመን 35 ሙስሊም ተወካዮች በፓርላማ ነበሩ‼️(በሙጃሒድ ካሊድ)[ ከስልሳ አመት በፊት , በ1959 ዓ.ል የአፄ ሀይለ ስላሴ የህዝብ እንደራሴ ፓርላማ ውስጥ 35 ሙስሊም ተወካዮች ነበሩ :: የደሴ ከተማ እንደራሴው ታዋቂው ፊት አውራሪ አመዴ ለማ አንዱ ናቸው ::በአፄ ኃ/ ስላሴ የስልጣን ዘመን ዘጠኝ መስጅድ ተሰርቷል ፤ አንድም መስጅድ ፈርሶ አያውቅም :: ለመጀመርያ ግዜ በአይሮፕላን ሀጅ ጉዞ የተጀመረው በእሳቸው ዘመን 1940 ነው , ይህም አድካሚ የሆነውን የእግር ጉዞ ከሶስት ወር ወደ ሶስት ሰአት ቀንሶታል ::ለመጀመርያ ግዜ ቁርአን ከአረብኛ ወደ አማርኛ ተተርጉም እንዲታተም ትዕዛዝ ሰተዋል :: በ1960 ለሸይኽ ሲራጅ ሙሀመድ እና አምስት ተማሪዎቻቸው ሙሉ ወጪ ሸፍነው ሀጅ ልከዋቸውል ... :: ]
  • ኢትዮ መረጃ - NEWS

    14 Nov, 15:21edited

    🎈 በየወሩ 1 ፐርሰንት በመክፈል ብቻ የሱቅ ባለቤት ይሁኑ!!!💫 የአዲስ አመት ስጦታ ከቴምር ፕሮፐርቲስ!!✅ገበያ በሚደራባቸው… ⚫️ሳርቤት ⚫️ቡልጋሪያ እና ⚫️ገላን✅በተመጣጣኝ ዋጋ በእውነተኛ ቅናሽ እና ከወለድ ነጻ አከፋፈል፤ ስርአቱ የሚታወቀው ቴምር ፕሮፐርቲስ🔔 በ2019 ተጨማሪ ብስራት ይዞ ብቅ ብሏል!🌟 ነጋዴው በአንድ ጊዜ ክፍያ ወረቱን ሳያጣ የሱቅ ባለቤት የሚሆንበትን እድል!! ሱቅዎን ከነገበያው ለመውሰድ የሚጠበቅብዎት✅25 በመቶ ቅድመ ክፍያ ✅ለ24 ወራት በየወሩ የሱቁን ዋጋ 1 በመቶ ብቻ መክፈል ነው! ✅ቀሪውን ክፍያ በ4 የግንባታ ምዕራፎች ሳይጨናነቁ ይከፍላሉ!✅ቴምር የህልምዎን ማረፊያ በአዲስ አበባ አራቱም አቅጣጫ እየገነባ ነው!☑️ የእርስዎ ትልቁ ህልም ቋሚ አድራሻ ስለሚያስፈልገው ምርጫዎን ብቻ ይንገሩን! በፈለጉት አካባቢና ካሬ ንግድ ሳይጀምሩ የሚያተርፉባቸው ሱቆች አሉን!☎️ለበለጠ መረጃ 09-81-85-88-35 ይደውሉልን
  • ኢትዮ መረጃ - NEWS

    14 Nov, 14:52

    የቅድስት አርሴማ ረድኤት እና ምልጃዋ አይለየን🙏ራሷን የክርስቶስ ሙሽራ አድርጋ የለየች የፊቷ መልክ እጅግ ልዩ፣ ደምግባቷ ያማረ ነበረች።ራሷን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ሙሽርነት ያጨችና ዓለምን የናቀች፣ ለመንፈሳዊ ሕይወቷ ፍጹም ራሷን አሳልፋ የሰጠችም ናት፡፡ ውብ ሚስት እንዲፈልጉለት መልእክተኞቹን የላከው ከሀዲው ንጉሡ ዲዮቅልጥያኖስ ሮሜ ውስጥ ባለ አንድ ገዳም ውስጥ ከሌሎች ደናግል ጋር ያገኟትን ቅድስት አርሴማ ሥዕል እንዳየ እጅግ ወደዳትና አምጡልኝ አለ፡፡ እርሷ ግን ከገዳሙ እመምኔትና ከሌሎቹ ደናግላን ጋር ወደ አርማንያ ሸሸች። አካባቢውን የሚገዛው ንጉሥ ድርጣድስ ከንጉሡ ዲዮቅልጥያኖስ መልእክት ደርሶት ሲያስፈልጋት ከደናግሉ ጋራ አገኛት። እርሱም በውበቷ በእጅጉ ተስቦ ለራሱ ሊያደርጋት ወስኖ ከደናግሉም ጋራ ካሠራት በኋላ እናታችን ቅድስት አርሴማን ሊያታልላት ይጥር ጀመር።አልሆን ሲለውም እመምኔቷን እንድታባብላት ቢልካትም እርሷ ግን እንዲህ ላለው ምድራዊ ኃላፊ ነገር እንዳትታለይ፤ ሰማያዊ ሙሽርነትሽንና ንጽሕናሽን አጽኚ” ብላ ይበልጥ አጸናቻት። ንጉሡም ቅድስት አርሴማን በግድ ይዟት ሊሄድ ሲል ኃይለ መንፈስ ቅዱስ አድሮባታልና ያንን በጦር የጎለመሰ ሰውነት ያለው ንጉስ ከመሬት ፈጠፈጠችው። አንዲት ትንሽ ወጣት እንደምን ጣለችኝ ብሎ እጅግ በማፈሩም እጅግ ተቆጥቶ ሥቃይዋን ሊያበዛባት ተነሳ በደናግሉ ሁሉ ፊትም አሠራትና እንድትሳቀቅ በፊቷ አንድ በአንድ አንገታቸውን ቀላቸው። እርሷ ግን ቅዱሳኑ ሰማያዊ አክሊልን ሲቀበሉ ትመለከት “አይዟችሁ!” እያለችም ታጽናናቸው ነበር። ይህን ሲጨርስም “አንቺን እንደሌሎቹ ቶሎ አልገድልሽም” ብሎ በብዙ መከራ እጅግ አሠቃያት። ሁለቱን ጡቶቿን ቆረጠ፤ ሁለት ዐይኖቿንም አወጣቸው፡፡ ንጽሕት ድንግል እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም ልዩ የብርሃን ዐይኖችን ሰጠቻት። በመጨረሻም ከቀሩት ሰባ አምስት ወንዶችና ሃያ ሰባት ደናግል ሴቶች ጋራ መስከረም ሃያ ዘጠኝ ቀን አንገታቸውን ሲሰይፋቸው የሰማዕትነትን የድል አክሊል ተቀዳጁ።የቅድስቲቱ ሰማዕት ቤተክርስትያኗ የከበረችበትና አብረዋት ከተጋደሉ 27 ደናግላን ጋር ሥጋቸው የፈለሰበት ዕለትም በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ይከበራል። ቅድስት አርሴማ ከሃያ ሰባቱ ደናግል ጋራ ሰማዕትነት ከተቀበለች በኋላ ንጉሡ ድርጣድስ ፈጽሞ ታመመ ታወከም። በትውፊት ታላቅ ወንድሟ እንደኾነ የሚነገርለት ቅዱስ ጎርጎርዮስ ሊቀ ጳጳሳትን አስቀድሞ አሥሮት ነበር። በኋላም ቅዱስ ጎርጎርዮስን ፈታውና ከደዌው ዳነ፡፡ የቅዱሳን ደናግልና የቅድስት አርሴማንም የቅዱሳን ሰማዕታቱን ዐፅመ ፍልሠታቸው ታኅሣሥ ስድስት ቀን በቅዱስ ጎርጎርዮስ ተደረገ፡፡ በስሟ ያማረ ቤተ ክርስቲያን ሠርተው አከበሩበት። ቅድስት አርሴማ በሰማዕትነት ስታርፍ ጌታችን ነፍሷን በክብር ተቀበላት ራሷን ለእርሱ በሙሽርነት አሳልፋ ሰጥታለችና ብዙ ቃል ኪዳንም ሰጣት፡፡ በዚህ ቃል ኪዳኗ የታመኑ ገዳማውያን ዘወትር አማልጂን ይሏታል፡፡ ገዳማቸውን ስንደግፍ በዓታቸውን ስናጸና ከበረከታቸው እንሳተፋለን፡፡ድጋፍ ለማድረግ፦ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳምኢትዮጲያ ንግድ ባንክ 1000442598391ወይምአቢሲኒያ ባንክ 141029444የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444
  • ኢትዮ መረጃ - NEWS

    14 Nov, 11:15

    ርብራብ ተደርምሶ የሦስት ሠራተኞች ሕይወት አለፈ‼ዛሬ ጠዋት 4:30 ሰዓት አካባቢ ከደምበል ወደ መስቀል ፍላወር በሚወስደው መንገድ፣ ጋዜቦ አደባባይ አቅራቢያ በግንባታ ላይ ያለ ሕንጻ ርብራብ በመደርመሱ የሦስት ሠራተኞች ሕይወት ማለፉን ጌጡ ተመስገን አጋርቷል።አደጋው የተከሰተው ሠራተኞቹ በሥራ ላይ እያሉ ርብራቡ ተደርምሶ ከ12ኛ ፎቅ በመውደቃቸው ሲሆን፣ ክስተቱ በአካባቢው በነበሩ መንገደኞችና ነዋሪዎች ዘንድ ከፍተኛ ድንጋጤና ሐዘን ፈጥሯል።ለሟች ቤተሰቦች መፅናናትን እመኛለሁ።
    2,32044Open in Telegram
  • ኢትዮ መረጃ - NEWS

    14 Nov, 11:01edited

    800 ሺህ" የሚደርሱ ወጣት የክልሉ ነዋሪዎች ወደ አዲስ አበባ እና ሌሎች የአገሪቱ አካባቢዎች ተሰደዋልትግራይ ውስጥ በነበረው የግዳጅ ወታደራዊ ምልመላ ምክንያት “እስከ 800 ሺህ" የሚደርሱ ወጣት የክልሉ ነዋሪዎች ወደ አዲስ አበባ እና ሌሎች የአገሪቱ አካባቢዎች መሸሻቸውን የኢትዮጵያ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ተናገሩ።መከላከያ ሠራዊት “ድሮ የኛ ምሽጎች የነበሩ ላይ ነው ያለው" ያሉት ጠቅላይ ኢታማዦር ሹሙ፣ "ጦርነቱን እንዲከፍቱ ታዝዘው ጦርነቱን ከፍተው የተሸነፉ ሰዎች ደግሞ እንዳጎርጊስ፣ አዲ ኳላ፣ መንደፈራ ነው ያሉት። አንዳንዶቹ አስመራ ነው ያሉት” ሲሉ ከስሰዋል።ፊልድ ማርሻሉ ይሄን ይበሉ እንጂ በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ስለሚደረገዉ የግዳጅ ወታደራዊ አፈሳ ምንም አላሉም ፡፡
    2,400821Open in Telegram
  • ኢትዮ መረጃ - NEWS

    14 Nov, 06:26

    #ዜና: በ #ኢትዮጵያና #ኤርትራ ድንበር #ባድመ አካባቢ ግጭቱ መባባሱን የዲፕሎማቲክ ምንጮች ገለጹ፤ ነዋሪዎች ከጥቃት ለመሸሽ አካባቢውን እየለቀቁ ነውበ #ኢትዮጵያ እና #ኤርትራ ድንበር አካባቢ ያለውን የጸጥታ ሁኔታ የሚከታተሉ የመረጃ ግምገማዎችን በቅርበት የሚያውቁ የዲፕሎማቲክ ምንጮች፣ በ #ባድመ ዙሪያ ግጭቶች መባባሳቸውን ገልጹ። በኢትዮጵያ በኩል የሚፈጸሙ የድሮን ጥቃቶች እና በኤርትራ በኩል የሚተኮሱ ከባድ መሣሪያዎች ወደ ሰፊ ወታደራዊ ግጭት ሊያመሩ ይችላሉ የሚል ስጋት የፈጠሩ ሲሆን፣ የአካባቢው ነዋሪዎችም በሌሊት የሚፈጸሙ ከባድ ድብደባዎች ሰላማዊ ዜጎችን ለመፈናቀል እያስገደዱ መሆኑን ተናግረዋል።አንድ የአካባቢው ነዋሪው፣ “ሌሊቶቹ በከፍተኛ ፍንዳታዎች እና በከባድ ድብደባዎች የተሞሉ በመሆናቸው እጅግ አስፈሪ ናቸው። ብዙ ሰዎች ሕይወታቸውን ለማዳን አካባቢውን ለቀው እየወጡ ነው” ያሉ ሲሆን፣ ሱቆችና ገበያዎች መዘጋታቸውን እንዲሁም ነዋሪዎች የአየር ላይ ጥቃት ይደርስብናል በሚል ከፍተኛ ፍርሃት ውስጥ መሆናቸውን አስረድተዋል።
    3,31091Open in Telegram
  • ኢትዮ መረጃ - NEWS

    14 Nov, 06:08

    እንኳን ለአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ዓመታዊ ክብረ በዓል አደረሳችሁ፤አደረሰን🙏መላእክትም ነፍሱን በታላቅ ዝማሬ አሳርገዋታልትውልዳቸው ግብጽ ንሒሳ ውስጥ ነው፡፡ አባታቸው ስምዖን እናታቸው አቅሌስያ 33 ዓመት በትዳር ሲቆዩ ልጅ ለማግኘት ሲሉ ሦስት ቀን ብቻ በሩካቤ ስጋ ቀዋውቀዋል፡፡ በመልአክ ብስራትም መጋቢት 29 ተጸንሰው ታኅሣሥ 29 በጌታችን ልደት ቀን ተወለዱ፡፡ ሕጻኑ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በተወለደበት ቅጽበት ቅድስት ሥላሴን አመሰገነ፤ የእናቱን ጡት ሳይጠባም ቅዱስ ገብርኤል ወሰደው፡፡ እግዚአብሔርም መልአኩን “ወደ እናቴ ወደ ማርያም ውሰደውና ትባርከው” አለው፡፡ ወስዶት እመቤታችንም ባረከችው፡፡ ከዚህም በኋላ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ሕፃኑን አባ ዘመደ ብርሃን የተባሉ አባት ላሉበት ገዳም ወስዶ ምግቡ የእግዚአብሔር ቃል እንደሆነ ነግሮ ሰጣቸው፡፡ አባ ዘመደ ብርሃንም ሕፃኑን የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት እያስተማረ አሳድጎ ዲቁና ሰጠው፡፡እንደ ቅዱስ እስጢፋኖስም ጸጋንና ሞገስን የተመላ ሥራው የተቃና ሆነ፡፡ አባ ዘመድ ብርሃንም እንደ ቅዱስ እንጦንስ አስኬማን ሰጠው፡፡ ከዚህ በኋላም አባታችን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቅስናን ተቀብለው በጾም በጸሎትና በታላቅ ተጋድሎ መኖር ጀመሩ፡፡ እንደ ሐዋርያትም የተአምራትና የፈውስ ሀብት ተሰጣቸውና ድውያንን የሚፈውሱ፣ ሙታንን የሚያነሡ፣ አጋንንትን የሚያወጡ ሆኑ፡፡ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ዳግመኛ ተገልጦላቸው ወደ ሰማይ አሳረጋቸው፡፡ እግዚአብሔርም ከባረካቸው በኋላም ከሰው ተለይተው ከአናብስትና ከአናብርት ጋር ይኖሩ ጀመር፡፡ ሰውነታቸውም ሁሉ በጠጉር ተሸፈነ፡፡ በፍጹም ተጋድሎም በቀንና በሌሊት የክርስቶስን መከራ እያሰቡ ስለ ኃጥአንም ጥፋት እንባቸውን እያፈሰሱ ይጸልዩ ነበር፡፡በጸሎታቸውም ብዙ እልፍ ነፍሳትን አስምረዋል፡፡ በ300 ዓመታቸውም ከ60 አንበሶችና ከ60 ነብሮች ጋር ወደ ኢትዮጵያ ያመጣቸው ቅዱስ ገብርኤል ምድረ ከብድንና ዝቋላን አሳይቷቸዋል፡፡ የኢትዮጵያን ሕዝብ ማርልኝ ብለው ለአንድ መቶ ዓመት ተዘቅዝቀው ስጋቸው እስኪያልቅ ጸልየው ጥቅምት 5 ቀን ታላቅ የምሕረት ቃልኪዳን ተቀብለዋል፡፡ በሀገራችንም 262 ዓመታት በጸሎትና በትምህር እየቀዱሱዋት፣ አጋንንትን እያሳደዱ ኖረው በተወለዱ በ562 ዓመታቸው መጋቢት 5 ቀን ምድረ ከብድ ላይ አርፈዋል፡፡ ቅዱሳን መላእክትም ነፍሳቸውን በታላቅ ዝማሬ አሳርገዋታል፡፡ የቅዱሳኑ በረከት እንዲድርብን ገዳማውያንን እንደግፍ በዓታቸውን እናጽና፡፡ ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳምኢትዮጲያ ንግድ ባንክ 1000442598391ወይምአቢሲኒያ ባንክ 141029444ለበለጠ መረጃ:- 09 38 64 44 44/0918077957
  • ኢትዮ መረጃ - NEWS

    13 Nov, 16:54edited

    በባንክ ጥበቃ በጥይታ የተመታው ወጣት ሕይወት ማለፉ ተሰማ።በዛሬው ዕለት ቀን በቦሌ አካባቢ (በካርን ሳፊል እና አስራት ህንፃዎች አጠገብ) በሚገኝ የባንክ ተቋም ፊት ለፊት በመኪና ማቆሚያ (ፓርኪንግ) ዙሪያ በተፈጠረ አሳዛኝ የተኩስ አደጋ የአንድ ወጣት ሕይወት ማለፉ ተረጋገጠ።እንደ ታዲያስ አዲስ ዘገባ፣ ክስተቱ መነሻውን ያደረገው አረንጓዴ ፒጆ ተሽከርካሪ ይዞ በመጣ ወጣት እና በባንክ ተቋሙ የጥበቃ ሰራተኛ መካከል በተነሳ ውዝግብ ነው። በወቅቱ «እዚህ ማቆም አትችልም» በሚል ቀላል በሚመስል ንትርክ የተነሳው አለመግባባት ወጣቱ ተሽከርካሪውን አቁሞ ወደ ስራው ጉዳይ ከሄደ በኋላ ሲመለስ ወደ ከፋ ግጭት አድጓል።ወጣቱ ተሽከርካሪውን ለማንሳት ሲመለስ የጥበቃ ሰራተኛው በከፍተኛ ቁጣና ንዴት ውስጥ ሆኖ ተከታታይ ተኩስ እንደከፈተበት የዓይን እማኞች ገልጸዋል።በጥይት ተመቶ ከባድ ጉዳት የደረሰበት ወጣት ወዲያውኑ ወደ አያት ሆስፒታል ቢወሰድም፣ የደረሰበት የከፋ ጉዳት ህይወቱን ለማትረፍ ባለመቻሉ ሕይወቱ አልፏል።በሌላ በኩል፣ ጥቃቱን የፈጸመው የጥበቃ ሰራተኛ ድርጊቱን ፈጽሞ በድንጋጤና በሁከት ውስጥ ሆኖ ፖሊስን ለመጥራት መሞከሩን እንዲሁም መሳሪያውን ጥሎ ለመሸሽ እንደተንቀሳቀሰ ተገልጿል።ቀላል በሚመስል የመኪና ማቆሚያ አለመግባባት የሰውን ሕይወት የቀጠፈው ይህ አሳዛኝ ድርጊት በአካባቢው ማህበረሰብ እና በዓይን እማኞች ዘንድ ከፍተኛ ሐዘንና ቁጣን ፈጥሯል።
    4,520321732Open in Telegram
  • ኢትዮ መረጃ - NEWS

    22 Sept, 18:56

    በቻይና ሰዎች ጭንቀታቸውን ለማስወገድ እንዲቧጨሩ የሚያደርግ ልዩ የቧጨራ ሳሎን ተከፈተ‼️በቻይና የ32 ዓመቱ ዣንግ ሺያኦቻኦ ሰዎች ጭንቀታቸውን ለማስታገስ በሰራተኞች በቀስታ የሚቧጨሩበትን ልዩ የአገልግሎት ሳሎን ከፍቶ በወር ወደ 100,000 ዩዋን ያህል ገቢ እያገኘ መሆኑ ተዘግቧል።ዣንግ ይህን ያልተለመደ የንግድ ሀሳብ ያገኘው በኢንተርኔት ላይ ባየው አጭር ቪዲዮ መሆኑን ገልጿል። በቪዲዮው ላይ አንዲት ሚስት የባለቤቷን ጀርባ በቀስታ ስትቧጭ ተመልክቶ አስተየየት ሰጪ የነበሩ ሰዎችም “እንዲህ ያለ አገልግሎት ቢኖር ገንዘብ እንከፍላለን” የሚሉ መልዕክቶቹን በመመልከቱ ወደዚህ ስራ መግባቱ ተናግሯል።የመጀመሪያው የቧጨራ ሳሎን ከተከፈተ ብዙም ሳይቆይ ሁለተኛ ሳሎን መክፈት ችሏል ሁለቱም ሳሎኖች በአጠቃላይ በወር ወደ 100,000 ዩዋን የሚጠጋ ገቢ እንደሚያገኝ ተነግሯል።ደንበኞች በጀርባቸው ተኝተው ሰራተኞች በልዩ የፕላስቲክ ጥፍሮች በመጠቀም ሰውነታቸውን በቀስታ ይቧጫሉ። ዣንግ ይህን ሥራ ለመጀመር ልዩ የቧጨራ ቴክኒኮችን ራሱ መመርመርና መፍጠር እንደነበረበት ገልጿል።አንድ ሰዓት የቧጨራ አገልግሎት 300 ዩዋን ያስከፍላል።የንግዱ ዋና ዓላማም ሰዎች የከተማ ሕይወት የሚያመጣውን ጭንቀት እንዲያስታግሱና የእንቅልፍ ጥራታቸውን ለማሻሻል ዘና የሚያደርግ ልምድ እንዲያገኙ ማድረግ እየሰራ መሆኑ ተነግሯል።ዣንግ የከተማ ነዋሪዎች የጭንቀት ደረጃ ከፍ ያለ በመሆኑ ለዚህ ዓይነቱ አገልግሎት ፍላጎት እንዳለ በመግለጽ አንዳንድ ደንበኞችም አገልግሎቱ ከማሳጅ ይልቅ የበለጠ ዘና እንደሚያደርጋቸው እንደነገሩት
    95883Open in Telegram
  • ኢትዮ መረጃ - NEWS

    22 Sept, 13:53

    በፊጂ የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ስርጭት በከፍተኛ ሁኔታ በመጨመሩ ብሔራዊ የአደጋ ጊዜ ታወጀ​የደቡብ ፓሲፊክ ደሴት ሀገር የሆነችው ፊጂ በኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ስርጭት ምክንያት ከፍተኛ የጤና ቀውስ ውስጥ በመውደቋ ብሔራዊ የአደጋ ጊዜ አውጃለች።​የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) እንደገለጸው፣ በሀገሪቱ የበሽታው ስርጭት በዓለም ላይ ካሉት በፍጥነት የሚያድጉት መካከል አንዱ ሆኗል።እ.ኤ.አ. በ2025 ብቻ ከ9,100 በላይ ሰዎች ከቫይረሱ ጋር እንደሚኖሩ የተገመተ ሲሆን፣ ይህም ከአዋቂው ህዝብ ውስጥ ከአርባ ስድስት አንዱ ተጋላጭ መሆኑን ያሳያል።በተጨማሪም ባለፈው ዓመት 59 ህፃናት ከቫይረሱ ጋር የተወለዱ ሲሆን፣ 18ቱ ህይወታቸው አልፏል።​ለበሽታው ፈጣን ስርጭት እንደ ዋና ምክንያት ከተጠቀሱት መካከል የመርፌ አደንዛዥ ዕፅ (በተለይም ሜታምፌታሚን) መጠቀም እና ደህንነቱ ያልተጠበቀ የጾታ ግንኙነት ናቸው።የጤና ባለስልጣናት እና የዓለም ጤና ድርጅት ነፃ የምርመራ አገልግሎቶችን፣ የመከላከያ መድኃኒቶችን እና የህክምና ተዳራሽነትን ለማስፋፋት የተቀናጀ እርምጃ እየወሰዱ ይገኛሉ።
  • ኢትዮ መረጃ - NEWS

    22 Sept, 13:49

    እንኳን ለቅዱስ ሚካኤል ወርሃዊ በዓል አደረሳችሁ፤ አደረሰን🙏 የቅዱስ ሚካኤል ምልጃ እና ረድኤት አይለየን!!!በጾርዓ ከተማ የሚኖር፣ ከዳን ወገን የሆነና ሚስቱም መካን የነበረች ማኑሄ የሚባል አንድ ሰው ነበረ፡፡ የእግዚአብሔር መልአክም ለሴቲቱ ተገልጦ “እነሆ ትጸንሻለሽ፤ አሁንም ተጠንቀቂ፤ የወይን ጠጅን የሚያሰክርም ነገር አትጠጪ፥ ርኩስም ነገር አትብዪ፤ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፤ ልጁም ከእናቱ ማኅፀን ጀምሮ ለእግዚአብሔር የተለየ ናዝራዊ ይሆናልና በራሱ ላይ ምላጭ አይድረስበት፤ እርሱም እስራኤልን ከፍልስጥኤማውያን እጅ ማዳን ይጀምራል” አላት። ሴቲቱም ለባልዋ የሆነውን ሁሉ ነገረችው፡፡ ማኑሄም የተላከው ሰው ዳግመኛ ወደኛ ይምጣ፤ ብሎ ወደ እግዚአብሔር ለመነ። እግዚአብሔርም የማኑሄን ድምፅ ሰማ፤ መልአኩም ሴቲቱ በእርሻ ውስጥ ተቀምጣ ሳለች እንደገና ተገለጠላት፤ ማኑሄ ግን አልነበረም።ሴቲቱም ፈጥና ሮጠች፤ ባልዋንም ጠራችው። ማኑሄም “ከዚህች ሴት ጋር የተነጋገርህ አንተ ነህን? ቃልህ በደረሰ ጊዜ የልጁ ሥርዓት ምንድን ነው? አለው። መልአኩም ማኑሄን “ሴቲቱ ከነገርኋት ሁሉ ትጠንቀቅ፣ በማለት ለሴቲቱ የነገራትን ደገመለት፡፡ ማኑሔም “የፍየል ጠቦት እስክናዘጋጅልህ ድረስ፤ እባክህ ቆይ” አለው። መልአኩም የሚቃጠለውንም መሥዋዕት ማዘጋጀት ብትወድድ ለእግዚአብሔር አቅርበው” አለው። ማኑሄም “ነገርህ በደረሰ ጊዜ እንድናከብርህ ስምህ ማን ነው?” አለው፡፡ መልአኩ “ስሜ ድንቅ ነውና ለምን ትጠይቃለህ?” ብሎ መለሰለት። ማኑሄም የፍየሉን ጠቦትና የእህሉን ቍርባን ወስዶ በድንጋይ ላይ ለእግዚአብሔር አቀረበው።መ
  • ኢትዮ መረጃ - NEWS

    22 Sept, 13:48

  • ኢትዮ መረጃ - NEWS

    22 Sept, 12:33

    የዘንድሮው የኢሬቻ በዓል መቼ ይከበራል ?የኦሮሞ አባገዳዎች ህብረት የዘንድሮው የኢሬቻ በዓል መስከረም 23 እና 24 ቀን 2019 ዓ.ም እንደሚከበር አሳውቋል።ኢሬቻ ሆረ ፊንፊኔ መስከረም 23 እንዲሁም ኢሬቻ ሆረ ሀርሰዴ መስከረም 24 በቢሾፍቱ ከተማ ይከበራል።
    3,00064Open in Telegram
  • ኢትዮ መረጃ - NEWS

    22 Sept, 11:51

    በኢትዮጵያ ያለው የታጣቂ ቡድኖች ጥምረት እና የድሮን ጥቃቶች አስቦኛል - የተባበሩት መንግስታትየተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአዲሱን የታጣቂ ቡድኖች ጥምረት መመሥረት፣ የቀጠለውን የጸጥታ ችግር እና የድሮን ጥቃት ዘገባዎችን በመጥቀስ በኢትዮጵያ እየተባባሰ የመጣው የጸጥታ ሁኔታ እንዳሳሰበው ገለፀ።ትላንት በተካሄደው የተመድ ዕለታዊ የዜና መግለጫ ላይ የተቋሙ ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ቃል አቀባይ እስቴፋን ዱጃሪክ እንደተናገሩት፣ ተመድ በኢትዮጵያ ውጥረት በተባባሰበት በዚህ ወቅት በተከሰቱ አዳዲስ ኩነቶች «ጥልቅ ስጋት» እንደገባው አስታውቀዋል።ቃል አቀባዩ «ውጥረት በነገሠበት በዚህ ወቅት፣ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ሁኔታውን ይበልጥ ሊያባብሱ ከሚችሉ ድርጊቶች ወይም ንግግሮች እንዲቆጠቡ እንጠይቃለን» ብለዋል።አክለውም «ወታደራዊ እርምጃ የፖለቲካ ልዩነቶችን አይፈታም፤ ወይም መሠረታዊ ቅሬታዎችን አይመልስም» ሲሉ አጽንኦት ሰጥተው የተናገሩ ሲሆን፣ ወገኖች ለውይይትና ለንግግር ዳግም ቁርጠኝነታቸውን እንዲያሳዩ ጥሪ አቅርበዋል።
    3,240122Open in Telegram
  • ኢትዮ መረጃ - NEWS

    22 Sept, 11:50

    እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከክፉ ነገር ሁሉ ትከልለን፤ ምልጃዋ እና ረድኤቷም አይለየን🙏እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ገና በቅድስት ሐና ማሕጸን ከነበረችበት ወቅት ጀምሮ ተአምራት ታደርግ ነበር፡፡ አንድ አይኗን ያጣች ቤርሳቤህ የተባለች ሴት የሀናን መጽነስ ስትሰማ በደስታ ልትጎበኛት መጣች፡፡ ቅድስት ሐናን እንኳን ደስ አለሽ ብላ ሆዷን ከዳሰሰቻት በኋላ በዚያው እጇ ዓይኗን ብትነካው ዐይኗ በርቶላታል፡፡ ይህን ምሳሌ አደርገው ድውያን እየመጡ ሆዷን ዳሰው ይፈወሱ ነበር፡፡ በመካንነት የነበሩት ወላጆቿ ልጅ ከሰጣቸው ለቤተ እግዚአብሔር ሊሰጡ ስዕለት ገብተው በቅድስት ድንግል ማርያም መወለድ ፍሬ ሲያገኙ ዓለም ደግሞ የመድኃኒቱን እናት አጊኝቷል፡፡ እናታችን ቅድስት ሐና ጸንሳ ሳለች የአጓቷ ልጅ አርፎ እጅግ የአልጋውን ሸንኮር እየዞረች ስታለቅስ ከሞተበት ተነስቶ “የሰማይና የምድር ፈጣሪ አያት ሆይ ላንቺ ክብር ይገባሻል” ብሎ መስክሮ ተመልሶ አርፏል፡፡አይሁድም “ቀድሞ የእነዚህ ዘር የነበሩ ዳዊትና ሰሎሞን አርባ፣ አርባ ዘመን ገዙን አሁን ከዚህች የሚወለድ ምን ሊያደርገን ነው?” ብለው በድንጋይ ሊወግሯት ተነሱ፡፡ የራማው ልዑል ቅዱሰ ገብርኤል ወደ ሊባኖስ ተራራ ወሰዳቸው፤ በእዚያም በጨለማ ውስጥ የነበረው ዓለም ብርሃን የሚያይባት፣ የእውነተኛው ጸሐይ እናቱ ቅድስት ድንግል ማርያም ተወለደች፡፡ ኢያቄምና ሐና የተሳሉትን ስእለታቸው አስታውሰው በሦስት ዓመቷ ወስደው ለቤተ እግዚአብሔር ሲሰጧትም ካህኑ ዘካርያስ ስለምግቧ ተጨንቆ፤ ሕዝቡን ሰብስቦ ሳለ መልአኩ ፋኑኤል ኅብስት ሰማያዊ ጽዋዕ ይዞ ከሰማይ
  • ኢትዮ መረጃ - NEWS

    22 Sept, 11:49

  • ኢትዮ መረጃ - NEWS

    22 Sept, 04:27

    ሳዲዮ ማኔ በሃገሩ ሴኔጋል በ20 ሚሊዮን ዶላር ወጪ ግዙፍ የግብርና እና ኢንዱስትሪ ፕሮጀክት አስጀመረI የሴኔጋል የእግር ኳስ ኮከብ ሳዲዮ ማኔ በደቡባዊ ሴኔጋል በሚገኘውና በተወለደበት ባምባሊ መንደር የ20 ሚሊዮን ዶላር ግዙፍ የግብርና ኢንዱስትሪ ፕሮጀክት መሠረት ድንጋይ አኖረ። እንደ DW Africa እና የአካባቢው መገናኛ ብዙኃን ዘገባ፣ ማኔ በራሱ ኩባንያ ‘SM10 Agro’ በኩል የሚመራውን ይህን ፕሮጀክት ሙሉ በሙሉ በራሱ የግል ገንዘብ የሚሸፍነው ነው።በ500 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈው ይህ ግዙፍ ፕሮጀክት የማንጎ እርሻዎችን፣ አራት የማቀናበሪያ ፋብሪካዎችን፣ የግብርና ሥልጠና ማዕከልን እንዲሁም የምርምርና ልማት ክፍሎችን ያካተተ ነው።ፕሮጀክቱ ሥራ ሲጀምር ከ1,000 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ቀጥተኛ የሥራ ዕድል እንደሚፈጥር የሚጠበቅ ሲሆን፣ በዓመት እስከ 8,500 ቶን ማንጎ የማቀናበር አቅም ይኖረዋል። ፋብሪካው ማንጎን ወደ ተለያዩ ተጨማሪ እሴት ያላቸው ምርቶች እንደ የማንጎ ጭማቂ፣ ደረቅ ማንጎ እና የማንጎ ቅቤ በመቀየር ለአገር ውስጥና ለውጭ ኤክስፖርት ገበያ ያቀርባል።ማኔ ቀደም ሲል በትውልድ መንደሩ ትምህርት ቤት፣ ሆስፒታል፣ መስጊድ፣ የነዳጅ ማደያ እና የዳቦ ቤት በመገንባት የሚታወቅ ሲሆን፤ አዲሱ የግብርና ፕሮጀክት ደግሞ ዘላቂ የሥራ ዕድልና ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ለህብረተሰቡ ለማስገኘት ያለመ ነው። ተጫዋቹ የባምባሊ አካባቢ የሚመረተው በርካታ ማንጎ ማቀናበሪያ በማጣቱ ምክንያት ይባክን እንደነበር ገልጾ፣ “የምድራችን ፍሬ እዚሁ እንዲቀር እና እሴት እንዲፈጠርበት እፈልጋለሁ” ሲል ስለ
    4,030357Open in Telegram
  • ኢትዮ መረጃ - NEWS

    22 Sept, 04:25

    እንኳን ለቅዱስ ሚካኤል ወርሃዊ በዓል አደረሳችሁ፤ አደረሰን🙏 የቅዱስ ሚካኤል ምልጃ እና ረድኤት አይለየን!!!ቅዱሳት መጻሕፍት እንደሚነግሩን የመላእክት ሁሉ አለቃቸው ቅዱስ ሚካኤል በፈጣሪው ኃይል ብዙ ድንቆችን ሠርቷል፡፡ ከመጀመሪያው ሰው አዳም ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ አምነው ለሚጠሩት ረዳት ነው፡፡ በመዝሙር 33÷7 እደተጻፈው ዘወትርም ያድናቸው ዘንድ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሠፍራል፡፡ እግራችን እንዳይሰናከል ዘወትር ይጠብቀናል፡፡ የቅዱስ ሚካኤል ስሙ ድንቅ ነው፡፡ ነቢዩ ቅዱስ ዳንኤል እንደተናገረው ከእርሱ በቀርስ የሚያጸና ማን አለና! ለሕዝቡም የሚቆም ታዳጊ መልአክ ነው፡፡ ይህ ድንቅ መልአክ ከሺህ ዓመታት በፊት በሮም ከተማ ይህንን ድንቅ ተአምር መስከረም ዘጠኝ ቀን መሥራቱን ቤተ ክርስቲያን ትመሰክራለች፡፡ በቀድሞው የሮም ግዛት 'ሩፍምያ' የምትባል ከተማ ነበረች፡፡ይህች ከተማ በእምነታቸው ጠንካሮች የሆኑ ጥቂት ክርስቲያኖችና በርካታ ኢአማንያን ተቀላቅለው የሚኖሩባት ናት፡፡ በተለይ ደግሞ የቤተ ክርስቲያኗ መጋቢ ፍጹም የእምነት ሰው ነበር፡፡ በቦታው የቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በመኖሩም ብዙ ተአምራት ይደረግ ስለነበር ተበለጥን የሚል ስሜት የተሰማቸው አሕዛብ “ዮናናውያን”ይሕንን ቤተ ክርስቲያን ለማጥፋት ተማማሉ፡፡ በቀጥታ ሔደው ቢያፈርሱት ወይም ቢያቃጥሉት በሕግ እንደሚጠየቁ ያውቃሉና በሥጋዊ ጭንቅላታቸው ዘዴ ያሉትን መከሩና ወሰኑ፡፡ በከተማዋ ዳር የሚያልፍ አንድ ትልቅ ወንዝ አለ፡፡ በሞላ ጊዜ ያገኘውን ሁሉ ጠርጐ የሚወስድም ነበር፡፡ ታዲያ ክፋተኞቹ ሌሊት ሌሊት እየተነሱ የሚሔድበትን
  • ኢትዮ መረጃ - NEWS

    22 Sept, 04:25

  • ኢትዮ መረጃ - NEWS

    21 Sept, 15:31

    ጋምቤላ ክልል በተከሰተ ግጭት የ12 ሰዎች ህይወት ማለፉን ድንበር የለሽ የሃኪሞች ቡድን ገለፀበጋምቤላ ክልል በደቡብ ሱዳን ድንበር አቅራቢያ በተከሰተ ግጭት ቢያንስ 12 ሰዎች መገደላቸዉንና በርካታ ሰዎች ቆስለዋል ሲል ድንበር የለሽ የሐኪሞች ቡድን አስታወቀ።ይህ የሰብዓዊ ረድኤት ድርጅት በትናንትናው ዕለት ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው ከሆነ ጥቃቱ በርካቶች የሞቱበት እና የቆሰሉበት እንደሆነ ነው።የተቋሙ ሰራተኞች ጋምቤላ ክልል በሚገኘው የኩሌ ጤና ጣቢያ ላይ እ.አ.አ መስከረም 18 ቀን 2026 በኢታንግ ልዩ ወረዳ ላይ በተከሰተው ግጭት ምክንያት የተጎዱ ታካሚዎችን በመቀበል እያገለገለ መሆኑንም አስታውቋል።ጤና ጣቢያው በግጭቱ የተጎዱ 88 ታካሚዎችን እንደተቀበለ በመግለፅ ስምንቱ ሰዎች ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን ሌሎች አራት ሰዎች ደግሞ የተቋሙ የህክምና ቡድን አባላት ጥረት ቢያደርጉም ወደ ኩሌ ጤና ጣቢያ በደረሱ ጊዜ ህይወታቸው አልፏል ብሏል።በተጨማሪም ቀሪዎቹ ታካሚዎች ከከባድ እስከ ቀላል ለሆኑ ጉዳቶች ህክምና ሲሰጣቸዉ አስራ ሶስት ታካሚዎች ተጨማሪ ህክምና እንዲያገኙ ወደ ጋምቤላ ሆስፒታሎች ወጭ እንዲባሉ መደረጉን ጠቅሷል፡፡“ቅድሚያ የምንሰጠው ለሁሉም ህክምና የሚያስፈልጋቸው ሰዎች አስቸኳይ የህክምና እርዳታ ማድረስ ነው፡፡ ይህም በህክምና ፍላጎት ላይ ብቻ ተመስርቶ፣ ማንነታቸው ወይም ዳራቸው ምንም ይሁን ምን” ሲሉ በናይሮቢ የሚገኙት በቡድኑ የኢትዮጵያ ኦፕሬሽንስ ማኔጀር የሆኑት ጉል ባድሻህ ተናግረዋል፡፡አክለዉም በግጭቱ የተሳተፉ ሁሉም አካላት ራሳቸውን እንዲገዙ ጥሪ በማቅረብ ንፁሀን
Download the series as CSV
A feedback bot for your channel — free

Followers write to the bot, you answer by reply, your account stays hidden. Created in one tap.

How it works →
Create the bot