gram news
Ministry of Education Ethiopia channel avatar

Ministry of Education Ethiopia

@ethio_moe

This is Ministry of Education's Official Telegram Channel. For more updates please visit www.facebook.com/fdremoe

ProjectsENOther

163,000subscribers

Open the Channel

Latest posts

  • Ministry of Education Ethiopia

    24 Sept, 12:11

    ማስታወቂያ ለወሊሶ ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ነባርና አዲስ ተማሪዎች በሙሉ፦በወሊሶ ፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ስትማሩ ለነበራችሁ ነባር ተማሪዎች እንዲሁም በ9ኛ እና 10ኛ ክፍል አዲስ ለተመደባችሁ ተማሪዎች ወደ ትምህርት የምትገቡበትን የመግቢያ ቀን በቀጣይ የምናሳውቅ መሆኑን እየገለጽን ተማሪዎች የመግቢያ ቀን እስኪገለጽ ድረስ በትዕግሥት እንድትጠብቁ እናሳስባለን።ማሳሰቢያ፦ በሌሎች አዳሪ ትምህርት ቤቶች የተመደባችሁ አዲስ ገቢ ተማሪዎች በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ተገኝታችሁ ሪፖርት ማድረግ የሚጠበቅባችሁ ሲሆን ወደ ትምህርት ቤቶቹ በምትገቡበት ጊዜ መረጃ በሚከተሉት ስልኮች እየደወላችሁ መጠየቅ የምትችሉ መሆኑ እንገልጻለን፣
    Image from a post by Ministry of Education EthiopiaImage from a post by Ministry of Education Ethiopia
  • Ministry of Education Ethiopia

    24 Sept, 11:55

    በትምህርት ዘርፍ የሥርዓተ-ጾታ እኩልነትና ፍትሐዊነትን ይበልጥ ለማረጋገጥ ትኩረት መስጠት እንደሚገባ ተጠቆመ።--------------------------//------------------------ (መስከረም 14/2019 ዓ.ም) በትምህርት ዘርፍ ያለውን የሥርዓተ-ጾታ እኩልነትና አካታችነት ሁኔታ የሚያሳይ አጠቃላይ ሀገራዊ የጥናት ውጤት ላይ ውይይት ተደረገ።በውይይት መድረኩ ንግግር ያደረጉት የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ አካቶ ትግበራ ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ምህረተክርስቶስ ታምሩ፣ ቀደም ሲል በዘርፉ የተሠሩ ሥራዎች በርካታ ለውጦችን ማምጣታቸውን አስታውሰው፣ ይህ ጥናት በትምህርት ዘርፉ የሚታዩ የጾታና የአካታች ትምህርት ክፍተቶችን በመለየት፣ በዘርፉ አዎንታዊና አካታች ለውጥ የሚያመጡ አሠራሮችን ለመዘርጋት መሆኑን ገልጸዋል።የሀገራዊ ጥናቱ ዋና ዓላማም በትምህርት ዘርፉ ያለውን የጾታ እኩልነትና አካታችነት በጥልቀት መገምገም፣ ዘላቂ ለውጥ ሊያመጡ የሚችሉ ምክረ-ሐሳቦችንና የድርጊት መርሃ-ግብሮችን ማዘጋጀት እንዲሁም ወደ ተግባር እንዲለወጡ ማድረግ መሆኑንም አብራርተዋል።በዚህም በጥናቱ ግኝቶች ላይ በመመሥረት የሚወጡ የውሳኔ ሐሳቦች ወደ ተግባር እንዲቀየሩ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ሙሉ ቁርጠኝነት እንዳለው ገልጸው የሥርዓተ-ጾታ እኩልነትና ፍትሐዊነትን ይበልጥ ለማረጋገጥ በትኩረት መሥራት እንደሚገባ ጠቁመዋል።በመድረኩ እንደተገለጸው፣ የጥናቱ ውጤት በትምህርት ዘርፉ ፖሊሲዎች፣ በመምህራን ማሻሻያ ፕሮግራሞች፣ በትምህርት ቤት ማሻሻያ፣ በሥርዓተ-ትምህርትና በጎልማሶች ትምህርት ውስጥ የጾታ እኩልነትን በዘላቂነት ለማካተት የሚያስችሉ ግልጽ ጠቋሚዎችንና ተግባራዊ የድርጊት መርሃ-ግብሮችን ለማዘጋጀት ትልቅ መሠረት ይሆናልም ተብሏል።
    Image from a post by Ministry of Education EthiopiaImage from a post by Ministry of Education EthiopiaImage from a post by Ministry of Education EthiopiaImage from a post by Ministry of Education Ethiopia
  • Ministry of Education Ethiopia

    23 Sept, 08:25

    ማስታወቂያ በፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመማር የመግቢያ ፈተና ወስዳችሁ በማለፍ በየትምህርት ቤቶቹ ለተመደባችሁ አዲስ ገቢ ተማሪዎች በሙሉ፤በፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመማር ተመዝግባችሁ የመግቢያ ፈተና በመውሰድ ያለፋችሁ በ9ኛ እና 10ኛ ክፍል በየትምህርት ቤቶቹ ለተመደባችሁ አዲስ ገቢ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤቶቹ የመግቢያ ቀን መስከረም 18 እና 19/2019 ዓ.ም መሆኑን እንገልጻለን። ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤቶቹ ሲመጡ ይዘው መምጣት ያለባቸው፤ 1. ለ9ኛ እና 10ኛ ክፍል ትምህርት የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶች፤ ለምሳሌ፡- ደብተር፣ እስክሪብቶ፣ ቦርሳ፣ የስፖርት ትጥቅ ወዘተ፣ 2. ለመኝታ አገልግሎት የሚያስፈልጉ አንሶላና ብርድ ልብስ፣ 3. እስካሁን ሲማሩበት ከነበረው ትምህርት ቤት የተሰጣቸውን መሸኛና የትምህርት ውጤታቸውን የሚገልጽ ትራንስክሪፕት ይዘው መገኘት ይጠበቅባቸዋል፤ 4. ተማሪዎች ወደ ተመደቡባቸው ትምህርት ቤቶች ከደረሱ በኋላ የሚያስፈልጋቸውን ዩኒፎርም በራሳቸው ወጪ የሚያስዘጋጁ በመሆኑ፣ ከወዲሁ አስፈላጊውን ዝግጅት እንድታደርጉ እናሳስባለን። ትምህርት ሚኒስቴር
    Image from a post by Ministry of Education EthiopiaImage from a post by Ministry of Education Ethiopia
  • Ministry of Education Ethiopia

    21 Sept, 14:29

    በኢትዮጵያ እና ሞሪሸየስ ዩኒቨርሲቲዎች መካከል ያለውን ትብብር አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ተገለጸ።…………………………………………. // ………………………………..(መስከረም 11/2019 ዓ.ም) የትምህርት ሚኒስቴር አማካሪ ሚኒስትር ዴኤታ ፕሮፌሰር ክንደያ ገብረህይወት ከሞሪሸየስ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ ሥራ አስፈጻሚዎች ጋር ውይይት አካሂደዋል።በውይይቱ ወቅት በሁለቱ ሀገራት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መካከል ያለውን የትምህርት፣ የምርምር እና የቴክኖሎጂ ልውውጥ ትብብር ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት አድርገዋል።ኢትዮጵያ በከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ የምታደርገውን ሪፎርም ለማስቀጠል ከቀጣናዊ እና አህጉራዊ ትምህርት ተቋማት ጋር የሚደረጉ የጋራ ትብብሮች ከፍተኛ ሚና እንዳላቸው ፕ/ር ክንደያ ገ/ህይወት ገልጸዋል።ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከሞሪሸየስ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር የሚደረጉ ግንኙነቶች ለሁለቱ ሀገራት ተመራማሪዎች እና ተማሪዎችያለውን የልምድ ልውውጥ ለማሳደግ ትልቅ እድል እንደሚፈጥር አስረድተዋል።አክለውም አሁን የተጀመረው የግንኙነት ፍላጎት ወደ ተግባር ለማውረድ በቀጣይ የመግባቢያ ስምምነት ለመፈራረም ፍላጎት ያለ መሆኑን አመላክተዋል።የሞሪሸየስ ዩኒቨርሲቲ ሥራ አስፈጻሚዎች በበኩላቸው ከኢትዮጵያ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር በጋራ ለመስራት እንደሚፈልጉ እና በተለይም በሳይንስ፣ በቴክኖሎጂ እንዲሁም የምርምር ስራዎች ላይ ትኩረት አድርጎ ለመስራት ከፍተኛ ፍላጎት ያላችው መሆኑን ገልጸዋል።
    Image from a post by Ministry of Education EthiopiaImage from a post by Ministry of Education EthiopiaImage from a post by Ministry of Education EthiopiaImage from a post by Ministry of Education Ethiopia
  • Ministry of Education Ethiopia

    21 Sept, 10:54

    በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በ2019 የትምህርት ዘመን የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ለተጀመሩ የሪፎርም ሥራዎች ትኩረት መሰጠቱ ገለጸ፤‎በክልሉ የ2019 የትምህርት ዘመን የመማር ማስተማር ሥራ ተጀምሯል።--------------------------- // ------------------------------ ‎ ‎(መስከረም 11/2019 ዓ.ም) የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር፣ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አንተነህ ፈቃዱ እንደገለጹት በ2019 በክልሉ የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ የሚያካሄዱ ተግባራት ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል።‎ ‎በባለፈው የትምህርት ዘመን በክልሉ በትምህርት መሠረተ ልማት ማሻሻል ፣ በመምህራን አቅም ግንባታ፣ በትምህርት ለትውልድ ንቅናቄ ስኬታማ ተግባራት መከናወናቸውን ኃላፊው ተናግረዋል‎ ‎በተለይም በትምህርት ለትውልድ ንቅናቄ ባለፉት ሦስት ዓመታት ብቻ በክልሉ ከ4.4 ቢሊዮን ብር በላይ ሀብት በማሰባሰብ የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ለማሻሻልና ምቹ የመማር ማስተማር ከባቢ ለመፍጠር የሚያስችሉ ሥራዎች መሰራታቸውን ጠቅሰዋል ።‎ ‎ከሥርዓተ ትምህርት ፣ ከግብዓት ማሟላት ፣ ከተማሪ መጽሀፍት ሥርጭት እንዲሁም የፈተና እና ምዘና ስርዓቱን ከማጠናከር አንጻርም ውጤታማ ሥራዎች መከናወናቸውን አብራርተዋል። ሙሉ መረጃውል ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://web.facebook.com/share/p/1BxFBirzav/
    Image from a post by Ministry of Education EthiopiaImage from a post by Ministry of Education Ethiopia
  • Ministry of Education Ethiopia

    21 Sept, 08:47

    ማስታወቂያለ2019 ዓ.ም በፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመማር ተመዝግባችሁ የመግቢያ ፈተና ወስዳችሁ ተጠባባቂ ለሆናችሁ ተማሪዎች በሙሉ፤በ2019 ዓ.ም በፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመማር ተመዝግባችሁ የመግቢያ ፈተና ወስዳችሁ ተጠባባቂ ለሆናችሁ ተማሪዎች፣ በተመዘገባችሁበት ሊንክ በመግባት ስማችሁንና ሪፈረንስ ቁጥራችሁን በማስገባት እስከ መስከረም 13 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ መመዝገብ እንደምትችሉ እንገልጻለን።ማሳሰቢያ ፦ ያሉን ቦታዎች ውስን በመሆናቸው በተጠባባቂነት ከተያዙ መካከል የተሻለ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች ቅድሚያ የሚሰጣቸው መሆኑን እየገለጽን ምደባ የሚካሄደው ክፍት ቦታዎች ባሏቸው ት/ቤቶች እንደሚሆን እናሳውቃለን።የትምህርት ሚኒስቴር
    Image from a post by Ministry of Education EthiopiaImage from a post by Ministry of Education Ethiopia
  • Ministry of Education Ethiopia

    18 Sept, 14:11edited

    ማስታወቂያ በ2019 ወደ ፌዴራል አዳሪ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለ9ኛና 10ኛ ክፍል ለመማር ተመዝግባችሁ ላለፋችሁ እና እስካሁን ድረስ ላልተመዘገባችሁ ተማሪዎች በሙሉ፣ ቀደም ሲል ለምዝገባ በተጠቀማችሁበት ሊንክ በመግባት እስከ እሁድ መስከረም 10/2019 ዓ.ም ድረስ እንድትመዘገቡ እናሳስባለን።
    Image from a post by Ministry of Education EthiopiaImage from a post by Ministry of Education Ethiopia
  • Ministry of Education Ethiopia

    18 Sept, 12:41

    የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም የሚያስጠብቅ ትውልድ ለመቅረጽ በትምህርት ዘርፉ ሰፊ የሪፎርም ስራዎች እየተከናወኑ ነው፦ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ-------------------------- // -------------------------የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም የሚያስጠብቅ፣ ብቁ፣ በቴክኖሎጂ የዳበረ፣ አገር ወዳድ እና ከግል ጥቅም ይልቅ ለጋራ ጥቅም የሚያስብ ትውልድ ለመፍጠር ያለመ የትምህርት ስርዓት አተገባበርን ባለፉት ሦስት ዓመታት ተኩል ውስጥ በትኩረት ስትተገብር ቆይታለች።የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከኢቲቪ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ አዳዲስ የስርዓተ-ትምህርት ማሻሻያዎችን ከመተግበር ጀምሮ፣ የብሔራዊ ፈተና አሰጣጥን በማጥበቅ የኩረጃን ልማድ ከመከላከል አንጻር ሰፊ ተግባራት መከናወናቸውን ገልጸዋል።በዚህም ባለፉት 3 ዓመታት ህብረተሰቡን በማሳተፍ በተሰበሰበ 146 ቢሊዮን ብር ወጪ ከ17 ሺህ በላይ አዳዲስ ትምህርት ቤቶች መገንባታቸውን የገለጹት ሚኒስትሩ፣ ከ36 ሺህ በላይ የሚሆኑ ነባር ትምህርት ቤቶችም እድሳት ተደርጎላቸዋል ብለዋል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ የቅድመ-መደበኛ ትምህርት ቤቶች ቁጥር ከነበረበት 4 ሺህ ወደ 36 ሺህ ከፍ ሊል ችሏል። ከትምህርት መሣሪያዎችና ከአቅም ግንባታ አንጻርም ከተካሄደው የስርዓተ-ትምህርት ማሻሻያ ከ45 ሚሊዮን በላይ የሁለተኛ ደረጃ መማሪያ መጻሕፍት ታትመው ለተማሪዎች የተዳረሱ ሲሆን፣ ከ120 ሺህ እስከ 130 ሺህ የሚጠጉ መምህራንም በዘመናዊ የሥልጠና አሰጣጥ ዘዴዎች አቅማቸውን የሚያሳድግ ስልጠና እንዲያገኙ ተደርጓል። ሙሉ
    Image from a post by Ministry of Education EthiopiaImage from a post by Ministry of Education EthiopiaImage from a post by Ministry of Education EthiopiaImage from a post by Ministry of Education Ethiopia
  • Ministry of Education Ethiopia

    17 Sept, 11:58

    ማስታወቂያ በ2018 ዓ.ም. የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ በሪሚዲያል (Remedial) መርሃ-ግብር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ውጤት ላስመዘገባችሁ ተማሪዎች በሙሉ፡-የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምደባ ምርጫችሁን ከመስከረም 7/ 2019 ዓ.ም. እስከ መስከረም 11 ቀን 2019 ዓ.ም. ድረስ ወደ ትምህርት ቤት መሄድ ሳይጠበቅባችሁ ባላችሁበት ቦታ ሆናችሁ ከታች የተቀመጠውን ማስፈንጠሪያ (Link) በመጠቀም እራሳችሁ እንድትሞሉ እንገልጻለን።የማስፈንጠሪያ ሊንክ (Link): https://student.ethernet.edu.et/preferences
    Image from a post by Ministry of Education EthiopiaImage from a post by Ministry of Education Ethiopia
  • Ministry of Education Ethiopia

    17 Sept, 11:36

    ማስታወቂያ በትግራይ ክልል በሚገኙ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች አዲስ ለተመደባችሁ ተማሪዎች ና ነባር ተማሪዎች በሙሉበትግራይ ክልል ካለው ወቅታዊ ሁኔታ አንጻር፣ የትምህርት ሂደታችሁ እንዳይስተጓጎልና ደህንነታችሁ ተጠብቆ ትምህርታችሁን በመደበኛነት እንድትቀጥሉ ለማስቻል፣ በጠየቃችሁት መሰርት ሁኔታዎች እስኪስተካከሉ ድረስ በጊዜያዊነት ከትግራይ ክልል ውጪ ወደሚገኙ ሌሎች የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች እንድትመደቡ የሚደረግ ሲሆን በዚህ ጉዳይ ቅሬታ ያላችሁ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ሚኒስቴር በአካል መምጣት የማይጠበቅባችሁ መሆኑን እየገለጽን በጊዚያዊነት የምትመደቡበትን ዩኒቨርስቲ በቅርቡ የሚገለፅላቹህ ሲሆን ያለው ነባራዊ ሁኔታ ሲስተካከል፣ መጀመሪያ በተመደባችሁባቸው ዩኒቨርሲቲዎች ተመልሳችሁ ትምህርታችሁን የምትቀጥሉ መሆኑን ከወዲሁ እናሳውቃለን። በተለያየ ምክንያት ትግራይ ባሉት ዩኒቨርስቲዎች መቀጠል የምትፈልጉ ነባርና አዲስ ተማሪዎች በሚመለከት ከዩኒቨርስቲዎቹ ጋር እየተነጋገርን ስለሆነ በትእግስት እንድትጠባበቁ እንጠይቃለን።የትምህርት ሚኒስቴር
    Image from a post by Ministry of Education EthiopiaImage from a post by Ministry of Education Ethiopia
  • Ministry of Education Ethiopia

    16 Sept, 15:56

    ማስታወቂያየ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የዩኒቨርሲቲ ምደባን ይመለከታልበትምህርት ሚኒስቴር በ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎችን ወደ መንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የመመደብ ሂደትን አጠናቋል። ምደባው ፍትሐዊነትን፣ ግልጽነትን፣ እኩል ዕድልን እና ሚዛናዊ ስርጭትን በሚያረጋግጥ መልኩ፣ የተማሪዎችን ውጤትና ምርጫ፣ የዩኒቨርሲቲዎችን የቅበላ አቅም እንዲሁም ሌሎች የምደባ መስፈርቶችን ታሳቢ በማድረግ ተከናውኗል።1. የምደባው ዋና መስፈርቶች1.1. የተማሪዎች አጠቃላይ ውጤት እና የዩኒቨርሲቲ ምርጫየተማሪዎች አጠቃላይ የብሔራዊ ፈተና ውጤት የምደባው ዋና የቅደም ተከተል መስፈርት ሆኖ ተወስዷል። በዚህም መሠረት ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች በምርጫቸው መሠረት የመመደብ ቅድሚያ እንዲያገኙ የተደረገ ሲሆን በተቻለ መጠን ከመረጧቸው የመጀመሪያ ሦስት ዩኒቨርሲቲዎች እንዲመደቡ ተደርጓል።1.2. የዩኒቨርስቲዎች የተማሪ ቅበላ አቅምየእያንዳንዱ ዩኒቨርስቲ የተማሪ ቅበላ አቅም በምደባው ሂደት ታሳቢ ተደርጓል። በመሆኑም የተማሪው ውጤትና ምርጫ ከዩኒቨርስቲዎች የቅበላ አቅም ጋር በማጣጣም ምደባው ተከናውኗል።1.3. የክልል፣ የዞን፣ የወረዳ እና የትምህርት ቤት ስርጭትበዩኒቨርሲቲዎቻችን ብዝሃነትን ለማጠናከር እና የተማሪዎችን ሚዛናዊ ስርጭት ለማረጋገጥ፦
    Image from a post by Ministry of Education EthiopiaImage from a post by Ministry of Education Ethiopia
  • Ministry of Education Ethiopia

    16 Sept, 14:22

    ኢትዮጵያና ስሎቫኪያ በትምህርት ዘርፍ ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር በሚችሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ተወያዩ ---------------------- // -------------------------(መስከረም 06/2019 ዓ.ም) የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የስሎቫኪያ ሪፐብሊክ አምባሳደር በኢትዮጵያ ራስቲስላቭ ክሪዛንን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው በሁለቱ ሀገራት መካከል በትምህርቱ ዘርፍ ሊኖር ስለሚችለው ትብብር ተወያይተዋል።በውይይቱ ወቅት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ኢትዮጵያ ከስሎቫኪያ ጋር በትምህርት ዘርፍ ያላትን ትብብር የበለጠ ማጠናከር እንደምትፈልግ ገልጸው፣ በሀገሪቱ እየተካሄዱ ስላሉ የትምህርት ሪፎርም ሥራዎች ለአምባሳደሩ አብራርተዋል።በተለይም በከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ ዩኒቨርሲቲዎችን በተልዕኮና በትኩረት መስክ በመለየት እንዲደራጁ እየተሠራ መሆኑን ጠቁመው፣ ዩኒቨርሲቲዎች የበለጠ አስተዳደራዊ ነፃነት እንዲኖራቸው ራስ ገዝ በሆነ መልኩ እንዲደራጁ እየተደረገ መሆኑንም አንስተዋል።የትምህርት ሪፎርሙ የበለጠ ውጤታማና ዘላቂ ውጤት እንዲያመጣ የተለያዩ የድጋፍና የትብብር አማራጮች እንደሚያስፈልጉ የገለጹት ሚኒስትሩ፣ ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት በአዲስ የኢኮኖሚ ሪፎርም ላይ በመገኘቷ ከዚህ ጋር በተያያዙ አዳዲስና ተፈላጊ የትምህርት መስኮች በትብብር መሥራት እንደምትፈልግ ጠቁመዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://web.facebook.com/share/p/1HF5jLJ5fu/
    Image from a post by Ministry of Education EthiopiaImage from a post by Ministry of Education EthiopiaImage from a post by Ministry of Education EthiopiaImage from a post by Ministry of Education Ethiopia
  • Ministry of Education Ethiopia

    16 Sept, 07:17edited

    በመላው ሀገራችን ለሚገኙ ተማሪዎቻችን አዲሱ የትምህርት ዘመን ስኬታማ እንዲሆን እንመኛለን! ‎ ‎ወጣቱ ትውልድ ለኢትዮጵያ ትልቁ ሀብቷ በመሆኑ የ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ጅማሮን ተከትሎ፤ እያንዳንዱ ተማሪ ለላቀ እውቀት በትጋትና ጉጉት ትምህርቱን እንዲከታተል፣ ለጥሩ ውጤት በጽናት እንዲተጋ፣ እንዲሁም የሀገራችንን የወደፊት ዕድል መቅረጽ በሚያስችሉ ክህሎቶች እንዲገነባ አበረታታለሁ።‎ ‎ዛሬ እየተገበርነው ያለው በርካታ የልማት ሥራዎች የነገን ትውልድ ታሳቢ ያደረጉ በመሆናቸው፣ የዚህ ቀጣይ ዕድል ተጠቃሚ እና ባለአደራ እንደመሆናችሁ መጠን፣ የኢትዮጵያን ታላቅ የስልጣኔ ታሪክ ወደፊት ለማስቀጠል የእናንተ ቁርጠኝነት መሠረት እንደሆነ ሙሉ እምነቴ ነው።‎ ‎ብቁ እና በራሱ የሚተማመን ትውልድ ለመገንባት በሚደረገው ጥረት ውስጥ የመምህራኖቻችን ትጋትና መሰጠት መሰረታዊ ምሰሶ ነው። ተማሪዎቻችንን ማነቃቃት፣ አቅማቸውን ማውጣት፣ እንዲሁም ነገ ተፎካካሪ ሆነው እንዲወጡ የሚያስችሏቸውን ዕውቀት፣ ክህሎትና እሴቶችን የማስታጠቅ አደራን ቀጥሉበት ስል በትህትና አሳስባለው።‎ ‎በትምህርት ዘርፉ ውስጥ ለምትገኙ ባለድርሻ አካላት በሙሉ፤ ስኬታማ እና ፍሬያማ የትምህርት ዘመን እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ።ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር)
    Image from a post by Ministry of Education EthiopiaImage from a post by Ministry of Education Ethiopia
  • Ministry of Education Ethiopia

    15 Sept, 14:43

    የፌዴራል ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች በሁሉም መስክ የወደፊቱ አገር መሪዎች የሚፈጠሩባቸው ተቋማት እንዲሆኑ እየተሰራ እንደሚገኝ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ አስታወቁ ።------------------------ // -------------------------‎ ‎(መስከረም 05/2019 ዓ.ም) የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ አዲስ ከተመደቡ የፌዴራል ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች መምህራን ጋር ውይይት ባደረጉበት ወቅት እንደገለጹት ‎ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች በሁሉም በኩል የወደፊቱ የአገር መሪ የሚሆኑ ዜጎች የሚፈልቁባቸው ተቋማት ይሆናሉ ብለዋል።‎ ‎ትምህርት ቤቶቹ የነገዋን ኢትዮጵያ በቴክኖሎጂ ፣ በሳይንስ፣ በፖለቲካ ፣በፍልስፍና በሌሎችም የሚገነቡ አገር ወዳድ ዜጎች መፍለቂያዎች እንደሚሆኑ ያላቸውን እምነት ሚኒስትሩ ገልጸዋል።‎ ‎አያይዘውም ለሁሉም እኩል የሚያስቡና ሁሉንም እኩል መምራትና ማገልገል የሚችሉና አገርን ከቅርቃርና ከችግር ማውጣት የሚችሉ ዜጎች የሚፈጠሩባቸው ተቋማት እንደሚሆኑም ጠቅሰዋል።‎ ‎ትምህርት ቤቶቹ ከሁሉም የኢትዮጵያ ክፍሎች የተውጣጡ ዜጎች የሚማሩባቸውና ከሁሉም ቦታ የተውጣጡ መምህራንና በችሎታ ተመርጠው የሚያስተምሩባቸው ተቋማት መሆናቸውንም ጠቁመዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://web.facebook.com/share/p/1Efqvo52qb/
    Image from a post by Ministry of Education EthiopiaImage from a post by Ministry of Education EthiopiaImage from a post by Ministry of Education EthiopiaImage from a post by Ministry of Education Ethiopia
  • Ministry of Education Ethiopia

    15 Sept, 11:34

    Image from a post by Ministry of Education EthiopiaImage from a post by Ministry of Education Ethiopia
  • Ministry of Education Ethiopia

    14 Sept, 15:04

    2018 ዓ.ም. በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች ይማሩ የነበሩ ተማሪዎች በሌሎች የመንግስት ኒቨርስቲዎች እንዲመደቡ መወሰኑን የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ አስታወቁ፤ ሚኒስትሩ በትግራይ ክልል ዩኒቨርስቲዎች ውስጥ ይማሩ የነበሩ ተማሪዎችን አነጋግረዋል፡፡ ………………………………….. // …………………………….‎(መስከረም 04/2018 ዓ.ም) የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከተማሪዎቹ ጋር ውይይት ባደረጉበት ወቅት እንደገለጹት በ2018 ዓ.ም. በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች ይማሩ የነበሩ ተማሪዎች ደህንነታቸው ወደሚጠበቁባቸው ሌሎች ዩኒቨርስቲዎች እንዲመደቡ ትምህርት ሚኒስቴር መወሰኑን ተናግረዋል፡፡‎ ‎ክቡር ሚኒስትሩ እንደገለጹት ጦርነትና ግጭት ሸሽተው ከትግራይ የወጡ ተማሪዎች ብቻ ሳይሆን ትግራይ ውስጥ የሚገኙ ተማሪዎች ትምህርት ሚኒስቴር መምጣት ሳይጠበቅባቸው ከቻሉ ከትግራይ ወጥተው አሊያም ባሉበት በኦንላይ ለመማር የሚችሉበት ቦታ ላይ እንደሚመዘገቡና ትምህርትታቸውን መማር እንደሚችሉ አስረድተዋል፡፡‎ ‎ተማሪዎቹን ምዝገባ ለማካሄድ ትምህርት ሚኒስቴር በበይነ መረብ የምዝገባ ስርዓት ማዘጋጀቱን የገለጹት ሚኒስትሩ ሁሉም በትግራይ ክልል ባሉ አራቱ ዩኒቨርስቲዎች ይማሩ የነበሩ ተማሪዎች ከዛሬ ማታ ጀምሮ ይፋ በሚደረገው የኦንላይን መተግበሪያ ፕላት ፎርም በመሙላት እንዲመዘገቡ አሳውቀዋል፡፡ ሙሉ መረጃውን ይህንን ሊንክ በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፤ https://web.facebook.com/share/p/1BgiGPjwXJ/
    Image from a post by Ministry of Education EthiopiaImage from a post by Ministry of Education EthiopiaImage from a post by Ministry of Education EthiopiaImage from a post by Ministry of Education Ethiopia
  • Ministry of Education Ethiopia

    14 Sept, 14:24

    📢 ማስታወቂያ የ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ነገ መስከረም 05 ቀን 2019 ዓ.ም ይጀምራል! ውድ ተማሪዎች፣ መምህራን፣ ወላጆች/አሳዳጊዎች እና መላው የትምህርት ማኅበረሰብ፤ እንኳን ለ2019 አዲሱ ዓመት እና የትምህርት ዘመን አደረሳችሁ!በትምህርት ካሌንደሩ መሠረት፣ የ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በመላ ሀገሪቱ ነገ፣ መስከረም 05 ቀን 2019 ዓ.ም፣ በይፋ ይጀምራል።በዚህም ትምህርት ቤቶች ለአዲሱ የትምህርት ዘመን የሚያስፈልጉ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን በማጠናቀቅ እናንተን ለመቀበልና የመማር–ማስተማር ሂደቱን በተቀመጠው የትምህርት ካሌንደር መሠረት ለመጀመር እየተጠባበቁ ይገኛል።ስለሆነም፣ ወላጆች/አሳዳጊዎች እና ሁላችሁም የሚመለከታችሁ አካላት ለትምህርት የደረሱ ልጆችን አስፈላጊውን የትምህርት ግብዓት በማሟላት ወደ ትምህርት ቤት እንዲሄዱ በማድረግ፣ የድርሻችሁን እንድትወጡ በዚህ አጋጣሚ መልዕክታችንን እናስተላልፋለን።🌟 መልካም የትምህርት ዘመን! ትምህርት ሚኒስቴር
    Image from a post by Ministry of Education EthiopiaImage from a post by Ministry of Education Ethiopia
  • Ministry of Education Ethiopia

    14 Sept, 11:30

    Image from a post by Ministry of Education EthiopiaImage from a post by Ministry of Education Ethiopia
  • Ministry of Education Ethiopia

    14 Sept, 07:05

    Image from a post by Ministry of Education EthiopiaImage from a post by Ministry of Education Ethiopia
  • Ministry of Education Ethiopia

    12 Sept, 13:43

    ማስታወቂያ ትምህርት ሚኒስቴር አዲስ ትምህርት በሚጀምርባቸውና እና ለነባር የፌደራል አዳሪ ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መምህራንን ለመልመል ባወጣው ማስታወቂያ መሰረት የጽሁፍ እና የቃል ፈተና ወስዳችሁ ያለፋችሁ መምህራን ዝርዝራችሁን መመልከት የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን። ያለፋችሁ መምህራን መስከረም 5/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ የትምህርት ቤት ምደባ እና ስልጠና የሚሰጣችሁ በመሆኑ ማንነታችሁን የሚገልጽ መታወቂያ በመያዝ በተጠቀሰው ቀን በትምህርት ሚኒስቴር ዋናው ግቢ የመሰብሰቢያ አዳራሽ እንድትገኙ እናሳውቃለን።ማሳሰቢያ፦ በዚህ ስልጠና እና ኦረንቴሽን የማይገኝ ማንኛውም መምህር ከምደባው የሚሰረዝ መሆኑን እንገልጻለን፡፡በተጨማሪም መስከረም 7 እና 8/2019 ዓ.ም በየተመደባችሁበት ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት (ዩኒቨርሲቲዎች)አስፈላጊውን መረጃ በመያዝ ሪፖርት ማድረግ የሚጠበቅባችሁ መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን።