gram news
Ethiopian Enterprise Development (የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት) channel avatar

Ethiopian Enterprise Development (የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት)

@ethiopianenterprisedevelopment

Ethiopian Enterprise Developmen (የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት)

ProjectsENBusiness

9,773subscribers

Open the Channel

Latest posts

  • Ethiopian Enterprise Development (የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት)

    22 Sept, 18:10

    Image from a post by Ethiopian Enterprise Development (የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት)Image from a post by Ethiopian Enterprise Development (የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት)Image from a post by Ethiopian Enterprise Development (የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት)Image from a post by Ethiopian Enterprise Development (የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት)
  • Ethiopian Enterprise Development (የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት)

    22 Sept, 18:10

    ተኪ ምርቶች፤ የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥEED መስከረም 12/2019ከውጭ በሚገቡ ምርቶች ላይ ያለውን ጥገኝነት ለመቀነስና የሀገር ውስጥ ምርትን በበቂ ሁኔታ ለማሳደግ ተኪ ምርቶች ላይ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል።የውጭ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ምርቶች የመተካት ሥራ እየተጠናከረ መምጣቱ የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ በእጅጉ ጠቃሚ ነው፡፡የመደመር መንግሥት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ እድገት ዋና ማሳያ የምርት እድገት መሆኑን በውል በመገንዘብ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ በርካታ ተግባራትን በልዩ ትኩረት በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡ዛሬ ኢትዮጵያ በራሷ አቅም የምታመርታቸውን ምርቶች ለራሷና ለዓለም በማቅረብ ታሪካዊ ምዕራፍ ላይ ትገኛለች።ለአብነትም በግብርናው ዘርፍ ስንዴ እንዲሁም በመድኃኒትና ሌሎች መሰረታዊ ምርቶች ራሷን ለመቻል በርካታ ተግባራትን እያከናወነች ነው፡፡ተኪ ምርቶች ላይ ትኩረት አድርጎ መስራት የውጭ ምንዛሪ አቅምን ከማሳደግ ባለፈ ሰፊ የስራ እድል በመፍጠርና ዜጎች ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ማግኘት እንዲችሉ እያደረገ ይገኛል።በ2018 በጀት ዓመት ብቻ በተኪ ምርት 5 ነጥብ 96 ቢሊየን ዶላር ማዳን የተቻለ ሲሆን፤ ለ448 ሺህ 717 ዜጎች የስራ ዕድል መፍጠር መቻሉን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡ኢትዮጵያ ለገቢ ምርቶች የምታወጣውን ወጪ ለመቀነስ ተኪ ምርቶችን በብዛት፣ በጥራትና በተመጣጣኝ ዋጋ ማቅረብ ላይ ትኩረት ተደርጎ እየተሰራ ሲሆን፤ ይህም ዘላቂ የኢኮኖሚ እድገት እንዲመዘገብ ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል፡፡
  • Ethiopian Enterprise Development (የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት)

    22 Sept, 06:32

    የምርጥ ተሞክሮ ቅመራና ማስፋት የአሠራር ሥርዓትEED መስከረም 12/2018 ዓ.ምየኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ከመላው ሀገሪቱ ለተውጣጡ የአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ አመራሮችና ባለሙያዎች የሚሰጠውን ሀገራዊ የአቅም ግንባታ ስልጠና አጠናክሮ ቀጥሏል። በስልጠና ውሎውም “የምርጥ ተሞክሮ ቅመራና ማስፋት የአሠራር ሥርዓት” ቀርቦ ሰፊ ስልጠናና ውይይት ተካሂዶበታል።ምርጥ ተሞክሮ ማለት የሚፈለገውን ውጤት በዘላቂነት ለማስመዝገብ እንዲያስችል በጥናትና በልምድ የተረጋገጠ ውጤታማ የአሠራር ስርዓት ነው።አነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞች በሀገሪቱ የመዋቅራዊ ኢኮኖሚ ሽግግር ውስጥ የሚኖራቸውን ከፍተኛ አበርክቶ በዘላቂነት ለማስቀጠል፣ ውጤታማ የሆኑ የመንግስት ድጋፍ አሰጣጥና የኢንተርፕራይዝ አሰራር ስርዓቶችን መለየት፣ መቀመርና ማስፋት ከፍተኛ ሀገራዊ ፋይዳ አለው። ይህንን ታሳቢ በማድረግም የምርጥ ተሞክሮ ልየታ፣ ቅመራና ማስፋት የአሰራር ስርዓት ተዘጋጅቷል።👉የአሠራር ስርዓቱ ዋና ዓላማውጤታማነቱ በጥናት የተረጋገጠ የመንግስት ድጋፍ አሠጣጥን እና የአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞችን አሰራር ለመለየት፣ ለመሰነድና ለማስፋት የሚያስችል ስርዓት መዘርጋት ነው። ይህም ለዘላቂ የኢንተርፕራይዝ ምርታማነትና ተወዳዳሪነት መሻሻል ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል።👉የምርጥ ተሞክሮ ዋነኛ ጥቅሞችምርታማነትን ማሳደግ፡ የኢንተርፕራይዞችን ልዩ ውጤታማነትና አፈጻጻም ማጎልበት፣ዕውቀትና በራስ መተማመንን ማዳበር፡ የባለሙያዎችንና የአመራሩን የፈጠራና የችግር መፍታት አቅም
  • Ethiopian Enterprise Development (የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት)

    22 Sept, 06:31

    የምርጥ ተሞክሮ ቅመራና ማስፋት የአሠራር ሥርዓት ስልጠና
    Image from a post by Ethiopian Enterprise Development (የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት)Image from a post by Ethiopian Enterprise Development (የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት)Image from a post by Ethiopian Enterprise Development (የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት)Image from a post by Ethiopian Enterprise Development (የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት)
  • Ethiopian Enterprise Development (የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት)

    21 Sept, 11:45

    https://youtu.be/CYM_GAFFTiw?si=f0VXUVTad-FeDdZ8#የአምራች_ስነ_ልቦና (ክፍል አስራ_ዘጠኝ) - #ቱምሃ_ሳሙና ===========///////==============ቱምሃ ሳሙና በ5 አባላት (አቶ ዘመኑ፣ ታከለና ጓደኞቻቸው) ሽርክና ማህበር በ2010 ዓ.ም ፈሳሽ ሳሙና በማምረት ወደ ስራ የገባ መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዝ ነው፡፡የኢንተርፕራይዙ መስራች አባልና ስራ አስኪያጅ አቶ ዘመኑ መለሠ "ቱምሃ ሳሙና" ስራውን ለመጀመር በኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት በኩል የተገኘው የሙያ ስልጠናና ሁሉን አቀፍ ድጋፍ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደነበረው ገልፀዋል፡፡ በተለይም በተቋሙ የተገኘው የሙያ ክህሎት ስልጠና አባላቱ ከተለያየ የስራ ዘርፍ የመጡ በመሆናቸው ስራውን ለመጀመር መሰረት እንደሆናቸው የገለፁት አቶ ዘመኑ፤ ከሙያ ስልጠና በተጨማሪ ከምርት አመራረት እስከ ገበያ አጠቃቀምና ተወዳዳሪነት ድረስ በተቋሙ የተደረገላቸው ድጋፍ ትልቅ አቅም እንደሆናቸው ተናግረዋል፡፡ ይህም ኢንተርፕራይዙ ጥራት ያላቸውን የጽዳትና የዲተርጀንት ምርቶች በስፋት እንዲያመርትና በዘርፉ ውጤታማ እንዲሆን ያስቻለው መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ሙሉ መረጃውን በቅርብ ቀናት ይጠብቁን!​#ኢትዮጵያ_ታምርት #እኛም_እንሸምት!ለተጨማሪ መረጃ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችንን ይጎብኙ፡https://linktr.ee/ethiopianenterprisedevelopment
    YouTube#የአምራች_ስነ_ልቦና (ክፍል አስራ_ዘጠኝ) - #ቱምሃ_ሳሙና#የአምራች_ስነ_ልቦና (ክፍል አስራ_ዘጠኝ) - #ቱምሃ_ሳሙና ===========///////============== ቱምሃ ሳሙና በ5 አባላት (አቶ ዘመኑ፣ ታከለና ጓደኞቻቸው) ሽርክና ማህበር በ2010 ዓ.ም ፈሳሽ ሳሙና በማምረት ወደ ስራ የገባ መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዝ ነው፡፡ የኢንተርፕራይዙ መስራች አባልና ስራ አስኪያጅ አቶ ዘመኑ መለሠ "ቱምሃ ሳሙና" ስራውን ለመጀመር በኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ…
  • Ethiopian Enterprise Development (የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት)

    21 Sept, 11:37

    ስርዓተ-ፆታና አካታችነት በአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዝ ዘርፍEED መስከረም 11/2018 ዓ.ምየኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ከመላው ሀገሪቱ ለተውጣጡ የአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ አመራርና ባለሙያዎች የሚሰጠው ሀገራዊ የአቅም ግንባታ ስልጠና ቀጥሎ ውሏል። በኢንዱስትሪው ዕድገትና ውጤታማነት ውስጥ ከፍተኛ ድርሻ ያለው «ስርዓተ-ፆታና አካታችነት» (Gender and Inclusivity) ርዕስ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተካሂዶበታል።ስርዓተ-ፆታ (Gender) በወንዶችና በሴቶች መካከል ያሉ ማህበራዊ ሚናዎችንና ግንኙነቶችን የሚያመለክት ሲሆን፤ በማህበረሰብ ደረጃ የተቀመጡ አመለካከቶች፣ ልምዶችና ተግባራት በሁለቱም ፆታዎች እንዲተገበሩ የሚጠበቁበትን ሂደት ያጠቃልላል።በስልጠናው የተዳሰሱ የስርዓተ-ፆታ የግንዛቤ ደረጃዎች (Levels of Gender Awareness)፦የስርዓተ-ፆታ ግንዛቤ እጦት (Gender Blind)፦ በወንዶችና ሴቶች መካከል ያሉ ልዩነቶችንና ፍላጎቶችን ያላገናዘበ አሰራር፤ስርዓተ-ፆታ ተኮር (Gender Sensitive)፦ በወንዶችና ሴቶች መካከል ልዩነቶች መኖራቸውን መገንዘብና መረዳት፤ለስርዓተ-ፆታ ጉዳይ ምላሽ ሰጪ (Gender Responsive)፦ የተለዩ ፍላጎቶችንና ክፍተቶችን ለመድፈን በተግባር የተደገፈ ምላሽ መስጠት፤ስርዓተ-ፆታዊ ለውጥ (Gender Transformative)፦ አድሏዊ አሰራሮችንና አመለካከቶችን በመቀየር ዘላቂ እኩልነትን ማረጋገጥ።አካታችነት (Inclusivity) ምንድን ነው?
  • Ethiopian Enterprise Development (የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት)

    21 Sept, 11:36

    Image from a post by Ethiopian Enterprise Development (የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት)Image from a post by Ethiopian Enterprise Development (የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት)Image from a post by Ethiopian Enterprise Development (የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት)Image from a post by Ethiopian Enterprise Development (የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት)
  • Ethiopian Enterprise Development (የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት)

    21 Sept, 08:28

    የማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዝ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት አሰጣጥEED መስከረም 11/2018 ዓ.ምየኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ከመላው ሀገሪቱ ለተውጣጡ የአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ አመራርና ባለሙያዎች የሚሰጠው ሀገራዊ የአቅም ግንባታ ስልጠና ቀጥሎ ውሏል።የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ያተኮረ ውይይትና ስልጠና ተሰጥቷል።ከዚህ ቀደም የነበረውን አሰራር በማሻሻልና የአለም አቀፍ ምርጥ ተሞክሮዎችን በማካተት፣ ለአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞች ፍላጎትና ደረጃ የሚመጥን ግልፅ ስትራቴጅውን መነሻ ያደረገ የማስፈጸሚያ ማንዋል ተዘጋጅቷል።👥 የማንዋሉ ተጠቃሚዎች·👉ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞች:በዕድገት ተኮር ንዑስ ዘርፎች የተሰማሩ ጥቃቅን፣ አነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞች (እንደ ዕድገት ደረጃቸው በፍላጎት ላይ የተመሰረተ ድጋፍ ያገኛሉ)።👉አስፈጻሚና ባለድርሻ አካላትበየደረጃው የሚገኙ የዘርፉ ልማት አስፈጻሚዎች፣ ድጋፍ ሰጪ ተቋማትና አመራሮች የተጣለባቸውን ኃላፊነት በብቃት እንዲወጡ ያስችላቸዋል።
  • Ethiopian Enterprise Development (የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት)

    21 Sept, 08:27

    የማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዝ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት አሰጣጥ ስልጠና
    Image from a post by Ethiopian Enterprise Development (የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት)Image from a post by Ethiopian Enterprise Development (የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት)Image from a post by Ethiopian Enterprise Development (የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት)Image from a post by Ethiopian Enterprise Development (የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት)
  • Ethiopian Enterprise Development (የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት)

    21 Sept, 07:15edited

    የአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ዘርፍን የግብዓት አቅርቦትና የኢንዱስትሪ ትስስር ማጎልበት ለምን አስፈለገ?EED መስከረም 11/2018 ዓ.ምየኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ከመላው ሀገሪቱ ለተውጣጡ የአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ አመራርና ባለሙያዎች የሚሰጠው ሀገራዊ የአቅም ግንባታ ስልጠና እንደቀጠለ ነው።የአምራች ኢንዱስትሪ ትስስር ስትራቴጂን መሰረት በማድረግ በተለይም በአምራች ዘርፉ የሚስተዋሉ የግብዓት አቅርቦት ማነቆዎችን መፍታት እና የኢንዱስትሪ ትስስር ማጠናከር ላይ ሰፊ ስልጠናና ውይይት ተደርጓል።ትኩረት የተሰጣቸው የኢንዱስትሪ ትስስር ዓይነቶች፦· የኋልዮሽ ትስስር (Backward Linkage)አምራች ኢንተርፕራይዞች ለምርት ሂደታቸው የሚሆኑ ጥሬ ዕቃዎችንና ግብዓቶችን ከሀገር ውስጥ አቅራቢዎችና አርሶ አደሮች ጋር በመተሳሰር የሚያገኙበት አሰራር፤·የፊትዮሽ ትስስር (Forward Linkage)ኢንተርፕራይዞች ያመረቷቸውን ምርቶች ለሚያከፋፍሉ፣ ለሚሸጡ ወይም ተጨማሪ እሴት ለሚጨምሩ ሌሎች ድርጅቶች የሚያቀርቡበት የገበያ ትስስር፤·የጎንዮሽ ትስስር (Horizontal Linkage)
  • Ethiopian Enterprise Development (የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት)

    21 Sept, 07:15

    Image from a post by Ethiopian Enterprise Development (የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት)Image from a post by Ethiopian Enterprise Development (የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት)Image from a post by Ethiopian Enterprise Development (የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት)Image from a post by Ethiopian Enterprise Development (የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት)
  • Ethiopian Enterprise Development (የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት)

    19 Sept, 07:44

    ለአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ አመራርና ባለሙያዎች መሰጠት የጀመረው ሀገራዊ የአቅም ግንባታ ስልጠና
    Image from a post by Ethiopian Enterprise Development (የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት)Image from a post by Ethiopian Enterprise Development (የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት)Image from a post by Ethiopian Enterprise Development (የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት)Image from a post by Ethiopian Enterprise Development (የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት)
  • Ethiopian Enterprise Development (የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት)

    19 Sept, 07:42edited

    በ2018 በጀት ዓመት በአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞች 270 ሺህ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድል ተፈጥሯል!ለአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ አመራርና ባለሙያዎች ሀገራዊ የአቅም ግንባታ ስልጠና መሰጠት ተጀመረEED መስከረም 9/2019 ዓ.ም (አዳማ)የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት በተጠናቀቀው የ2018 በጀት ዓመት አዲስ በተቋቋሙና በተጠናከሩ አነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞች 270 ሺህ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድል መፈጠሩን አስታወቀ::ይህ የተገለጸው ከመላው ኢትዮጵያ ለተወጣጡ 160 ለሚሆኑ የአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ አመራርና ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት በተጀመረበት ወቀት ነው።የልማት መስሪያ ቤቱ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዱልፈታህ የሱፍ በስልጠናው መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር፤ ተቋሙ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 526/2015 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት አነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞች ተወዳዳሪ ሆነው በሀገሪቱ ኢኮኖሚያዊ ሽግግር፣ በተኪ ምርት፣ በሥራ ዕድል ፈጠራና በኤክስፖርት እድገት ላይ ጉልህ ሚና እንዲጫወቱ በትኩረት እየሰራ ይገኛል ብለዋል።በተጠናቀቀው የ2018 በጀት ዓመት 4 ሺህ 233 አዳዲስ አነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞች መቋቋማቸውንና በዚህም ለ270,546 ዜጎች የስራ እድል መፈጠሩን ገልጸዋል::ከዚህም በተጨማሪ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ለመተካት በተሰራው ስራ 1 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር የሚያወጡ ምርቶችን መተካት መቻሉንና ወደውጭ በተላኩ ምርቶች
  • Ethiopian Enterprise Development (የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት)

    19 Sept, 06:01

    https://www.facebook.com/share/18pe7ZaV9E/
    FacebookAMN-Addis Media Networkየአምራች ኢንዱስትሪውን ዘርፍ ዕድገት ማረጋገጥ የሉዓላዊነት ጉዳይ ነው AMN- መስከረም 9/2019 ዓ.ም አምራች ኢንዱስትሪዎች ለአንድ ሃገር አጠቃላይ የውስጥ ምርት እድገት ያላቸው ድርሻ የላቀ ነው፡፡ በርካታ የዓለም ሃገራትም ለዘርፉ በሰጡት ልዩ ትኩረት የሃገራቸውን ሁለንተናዊ እድገት ከማረጋገጣቸውም በላይ...
  • Ethiopian Enterprise Development (የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት)

    19 Sept, 05:13edited

    #ኢትዮጵያ_ታምርት #እኛም_እንሸምት!ለተጨማሪ መረጃ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችንን ይጎብኙ፡https://linktr.ee/ethiopianenterprisedevelopment
    Image from a post by Ethiopian Enterprise Development (የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት)Image from a post by Ethiopian Enterprise Development (የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት)
  • Ethiopian Enterprise Development (የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት)

    17 Sept, 11:37edited

    https://www.youtube.com/@ethiopiaenterpriseማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞችን እና ስራ ፈጠራን ይደግፋሉ? በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ተሰማርተዋል? ወይንስ ለመሰማራት አስበዋል?የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት የዩቲዩብ ቻናልን በመቀላቀል የሀገራችንን አነስተኛ እና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞች የስኬት ጉዞ ይከታተሉ!📌 ቻናላችንን Subscribe በማድረግ፡· «የአምራች ሥነ-ልቦና» ፕሮግራሞችን እና የኢንተርፕራይዞችን የልምድ ልውውጥ ያገኛሉ · አዳዲስ የቴክኖሎጂ፣ የፈጠራ እና የሙያ ዕውቀቶችን ይሸምታሉ!· የሀገር ውስጥ አምራቾችን የስኬት ታሪክ በመመልከት ለራስዎ ተነሳሽነት ይፈጥራሉ!· የሀገር ውስጥ ምርቶችን ያስተዋውቃሉ፤ አዳዲስ የገበያ እና የንግድ ትስስሮችን ይፈጥራሉ!🔗 አሁኑኑ የዩቲዩብ ገጻችንን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!https://www.youtube.com/@ethiopiaenterprise#ኢትዮጵያ_ታምርት #እኛም_እንሸምት!
    Image from a post by Ethiopian Enterprise Development (የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት)Image from a post by Ethiopian Enterprise Development (የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት)
    91521Open in Telegram
  • Ethiopian Enterprise Development (የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት)

    17 Sept, 08:23edited

    https://www.youtube.com/watch?v=CkfShJ_Q3Ww#ኢትዮጵያ_ታምርት #እኛም_እንሸምት!ለተጨማሪ መረጃ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችንን ይጎብኙ፡https://linktr.ee/ethiopianenterprisedevelopment
    YouTubeየመጨረሻ በተባለ ቴክኖሎጂ የሚመረቱ አልባሳት#ፋና #አዲስ_አበባ #Ethiopia #ኢትዮጵያ #FANA_TV #FANA_NEWS #ፋና_ዜና