Latest posts

EvaSUE |ኢቫሱ
19 Sept, 04:20
አብዛኛውን ጊዜ፣አንድን ሰው ስናጣ፣ ችግር ውስጥ ስንገባ፣ውጤት አልመጣ ሲለን፣ ብቸኝነት ሲሰማን እና ነገሮች እንዳሰብነው ሳይሆኑ ሲቀሩ፣ እግዚአብሔር እንደተወን እናስባለን፤ ተስፋ እንቆርጣለን። አምላካችን ማን እንደሆነ እንረሳለን።ይህ በእኛ አልተጀመረም። በኢሳይያስ ምዕራፍ 40:27ን ብናይ፣ እስራኤላውያን መብታቸው በእግዚአብሔር እንደተዘነጋ፣ እንደተተዉ እና እንደተረሱ ስለተሰማቸው፣ በእግዚአብሔር ላይ ተስፋ መቁረጣቸውን እናያለን።እኔም ብዙ ጊዜ ይህን አድርጌያለሁ። ዓለም በዙሪያዬ እየፈራረሰ እንደሆነ ፣ እግዚአብሔር ግን የትም እንደሌለ የተሰማኝ ወቅቶች ነበሩ። እግዚአብሔር ግን ለእስራኤላውያን የሰጠውን መልስ ቁጥር 28 ላይ እዩ።የእስራኤላውያን ትኩረት ሁኔታቸው ላይ ስለነበር፣ እግዚአብሔር ትኩረታቸውን ወደ እርሱ ማንነት መለሰ። ስለ ታላቅነቱ በማስታወስ፣ እርሱ የምድር ፈጣሪ መሆኑን፣ የማይደክም፣ የማይታክት፣ ብርታት ሰጪ አምላክ እንደሆነ ዘርዝሮ፣ ተስፋ የሚጣልበት አምላክ መሆኑን አሳያቸው።


EvaSUE |ኢቫሱ
11 Sept, 06:35
@HEYAWE_TESFA_bot በመጠቀም እንኳን አደረሳቹ ዲጂታል ፖስትካርድ እንላላክ!


EvaSUE |ኢቫሱ
11 Sept, 03:45
አደይ አበባ ሳይ መጀመሪያ ትዝ የሚለኝ እንቁጣጣሽ ነው። ቀኑ ሲደርስ እንኳን አደረሰህ! እንኳን አደረሰሽ! እየተባባልን በማዕድ ዙሪያ አንድ ላይ እንቀርባለን። በጨዋታውም መሃል ስለሚመጣው ዓመት ብዙ ተስፋ እንሰንቃለን፤ ከፊት ያለውንም እያሰብን እራሳችንን እናበረታለን።ታዲያ ስለ ተስፋ ሲነሳ፣ በሐዋርያት ሥራ ላይ ውብ በተባለው ደጅ ጴጥሮስ ለሽባው ለማኝ ያደረገው ትዝ አለኝ። ተስፋው መንምኖ ጴጥሮስን ለአንዳች ነገር እየጠበቀ ነበር፤ እርሱም ገንዘብ! አልፈርድበትም! ጴጥሮስ ግን ከገንዘብ ይልቅ የተሻለ ነገርን ለማካፈል ወደደ። በደንብ ስናጠና ጴጥሮስ ገንዘብ ቸግሮት እንዳልነበር እንረዳለን። ለለማኙ ገንዘብ ከመስጠት ይልቅ ግን ፣ በጌታው የተስፋ ቃል ታምኖ፣ “ተነስ እና ተመላለስ” ማለትን መረጠ። ቁርጭምጭሚቶቹም ፀንተው ቀሩ!ከጠበቀው እና ካሰበው፣ ተስፋም ሊያደርገው ከሚችለው በላይ ሆነለት። ከዚያም ሕይወቱን ሙሉ እያየው ያላገኘው፣ እየተመኘው ተስፋ የቆረጠበት፣ ቤተ መቅደስ መግባት ቻለ! እግዚአብሔርንም አመሰገነ! ሕይወቱን ሙሉ ከተቀበለው ገንዘብም በላይ ሆነለት።ዛሬስ እኛ ለዚህ ተስፋ ለቆረጠ ትውልድ ምንድነው የምንሰጠው? ብር? ወርቅ? ልብስ? ቤት? ጌጥ?ከእነዚህ ጊዜያዊ ነገሮች በላይ፣ ነፍስን የሚያድስ፣ ከጨለማ የሚያወጣ ሕያው የሆነ ተስፋ ተቀብለናል። ስለዚህ፣ አዲሱን ዓመት ይህን ተስፋ በጨለማ ላሉት ሁሉ የምናጋራበት፣ ስለማይጠፋው እና ስለማይበላሸው በሰማይ ላለው ርስት የምናወራበት፣ እንዲሁም የትውልዱን ትኩረት እንደገና ወደ የኢየሱስ መምጣት የምናዞርበት ዓመት ይሁንልን።


EvaSUE |ኢቫሱ
29 Aug, 04:13
ተስፋ የሕይወት ሽታ የሚሆነው ምንጭ እና መሠረቱ እግዚአብሔር ሲሆን ነው ። ተስፋ የሕይወት ሽታ ብቻ ሳይሆን የሕይወት ውሃ ወንዝ ነው ። ወንዝ ደግሞ ምንጭ አለው ። ምንጩም እግዚአብሔር ነው ። ወንዝ የተጓዘበት መንገድ ሁሉ ልምላሜን ይቸራል ። ከወንዝ አጠገብ ያለ ተክል ፍሬያማ ፣ ቅጠሉም እንደማይረግፍ ሁሉ በተስፋ የሚደረግ ጉዞ ሕይወት እና ስኬታማነትን ይጎናጸፋል ። መሠረቱ ምንጭ የሆነ ወንዝ የማይቆም ወንዝ ነው ። የማይቆም ወንዝ ደግሞ ድንጋዩን ሰንጥቆ ያልፋል ። ድንጋዩን ሰንጥቆ የሚያልፈው ግን በጉልበቱ ሳይሆን በጽናቱ ነው ። ለዚህም ጽናትን ወልደ ተስፋ ልንለው እንችላለን ። ያለተስፋ ጽናት እንዲሁ የሚመጣ ነገር አይደለም ። የምንጸናው በተስፋ ነውና ። ተስፋ ከእግዚአብሔር ስለሚመነጭ ተስፋ ቢስ ሆኖ ለደከመው የሰው ልጅ ልምላሜ እንዲሆን እግዚአብሔር አስቀድሞ የማይጠፋ ተስፋን ሰጠው ።...የቀረውን ለማንበብ 👇 https://telegra.ph/%E1%89%B0%E1%88%B5%E1%8D%8B--%E1%8A%AD%E1%8D%8D%E1%88%8D-4-08-29


EvaSUE |ኢቫሱ
22 Aug, 03:43edited
#National_Leadership_Summit_2026 #HOPE_of_the_kingdom#seeing#Living#witnessing


EvaSUE |ኢቫሱ
22 Aug, 03:42
#National_Leadership_Summit_2026 #HOPE_of_the_kingdom#seeing#Living#witnessing


EvaSUE |ኢቫሱ
18 Aug, 05:34edited
Thank you to our amazing volunteers #NLS26 #HOPE_of_the_kingdom #EvaSUE


EvaSUE |ኢቫሱ
17 Aug, 12:01
#ድምፅ_አልባው_ሞገድ #The_Silent_Wave #መጽሐፍ_ምረቃ




EvaSUE |ኢቫሱ
17 Aug, 12:00
#ድምፅ_አልባው_ሞገድ #The_Silent_Wave #መጽሐፍ_ምረቃ




EvaSUE |ኢቫሱ
17 Aug, 11:59
#ድምፅ_አልባው_ሞገድ #The_Silent_Wave #መጽሐፍ_ምረቃ




EvaSUE |ኢቫሱ
17 Aug, 11:58
#ድምፅ_አልባው_ሞገድ #The_Silent_Wave #መጽሐፍ_ምረቃ




EvaSUE |ኢቫሱ
17 Aug, 11:57
#ድምፅ_አልባው_ሞገድ #The_Silent_Wave #መጽሐፍ_ምረቃ



Related Channels
Other channels in the same section of the catalogue.
