Latest posts

Event Addis Media
21 Sept, 18:29
🔶የድምጻዊት ፌቨን ዮሴፍ አልበም ተለቀቀድምጻዊት ፌቨን ዮሴፍ «አዲስ ምዕራፍ» የሚል ርዕስ የተሰጠውን አዲስ አልበሟን በራሷ ይፋዊ የዩቲዩብ ቻናል በኩል ለአድማጮች አደረሰች።በዚህ አዲስ አልበሟ ውስጥ ጥልቅ መልዕክት ያላቸው የተለያዩ ሥራዎች ተካተዋል።በድምጻዊቷ «አዲስ ምዕራፍ» አልበም ውስጥ በአጠቃላይ 9 ዜማዎች የተካተቱ ሲሆን፣ ጥበብ፤ ኮብላይ ፤አለሁ፤ነይ ብራ፤ሀሳቤ፤ነፃነት ቁሳቁስ እና እናወሳስበው? የተሰኙ ርዕሶች የተሰጣቸው ሥራዎች ይገኙበታል።የሙዚቃ ወዳጆችም በድምጻዊቷ ዩቲዩብ ቻናል በመግባት አልበሙን ማዳመጥ ይችላሉ።አልበሟን ያድምጡ:-https://youtube.com/playlist?list=PLBoLT-QDY5uY&si=bjPScqvS0Hl4joIbለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1


Event Addis Media
21 Sept, 18:03
🔶አርቲስት አበበ ባልቻ ከፕሪስቴጅ አዲስ ጋርፕሪስቴጅ አዲስ ከአርቲስት አበበ ባልቻ ጋር የሚያገናኝ ልዩ የውይይት መርሃ ግብር አዘጋጀፕሪስቴጅ አዲስ (Prestige Addis) ከራዲያንት ፊልምስ እና በአዲስ አበባ ከሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ጋር በመተባበር፣ የታዋቂው አርቲስት አበበ ባልቻ ጋር ልዩ መርሃ ግብር ማዘጋጀቱን አስታወቀ።ይህ መርሃ ግብር ማክሰኞ መስከረም 12ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ጀምሮ በአሜሪካ ኤምባሲ ግቢ ውስጥ በሚገኘው ሳችሞ ሴንተር እንደሚካሄድ የተገለጸ ሲሆን፣ ፍላጎት ያላቸው ተሳታፊዎች አስቀድመው በተዘጋጀው የመመዝገቢያ ሊንክ አማካይነት መመዝገብ እንደሚችሉ አዘጋጆቹ አስታውቀዋል።🔗 አሁኑኑ ለመመዝገብ ይህንን ሊንክ ይጫኑ 👇https://jazzio.land/registerለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1


Event Addis Media
21 Sept, 18:03
🔶 "የቃል ሊቀ መኳስ" መጽሐፍ ነገ ይመረቃልየገጣሚ ጌራወርቅ ጥላዬ "የቃል ሊቀ መኳስ" መጽሐፍ ነገ መስከረም 12 ቀን 2019 ዓ፤ም ከቀኑ 10:30 ጀምሮ በወመዘክር ይመረቃል።በዕለቱም ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች ይገኛሉ። የዝግጅቱ መግቢያ በነፃ ነው።"የቃል ሊቀ መኳስ" መጽሐፍ በ128 ገጽ ታትሞ በ300 ብር የጀርባ ዋጋ ለአንባቢያን ቀርቧል።ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1


Event Addis Media
19 Sept, 08:33
forwarded from @kelematadshub
🌸እስከ መስቀል የሚቆይ 25% ቅናሽ!!🌸ቆንጆ የቁልፍ መያዛዎች እና የቦርሳ ቻርሞች ለራሳችሁ ወይም ለስጦታ ይዘን መተናል 🎀✨ትንሽ ስጦታ፣ ልዩ ትዝታ። ♡📩 ለማዘዝ DM ይላኩ! @Paracletezhelper💌 የእኛን ቤተሰብ ይቀላቀሉን! 🔗 https://t.me/mercy_allInstagram : https://www.instagram.com/mercyy._s?stkn=MWVlbGRjb3VlZnJpcQ== Tiktok : https://www.tiktok.com/@mercy._s?_r=1&_t=ZS-99rGsMI0OJx


Event Addis Media
11 Sept, 08:27

Event Addis Media
11 Sept, 08:27
🔶 የአዲስ ዓመት ልዩ ቆይታ!!የኤቨንት አዲስ፤ የአዲስ ዓመት ቆይታ ከጌራወርቅ ጋርጌራወርቅ ጥላዬ በገጣሚነት ብቅ ያለው 2015 ዓ.ም “እናርጅና እናውጋ” በሚል የግጥም መድበል ነው። ገደኛም ነበር። ተወዶለታል፣ ተሸልሞበታል። ቆይቶ ሃሌሉያ ተ/ጻዲቅ “4/28” በሚል የቁጥርመጠሪያ በለቀቀችው ገሚስ አልበም ‹‹የልቤ ቁምነገር›› በሚል በሙዚቃ ግጥም ብቅ አለ። በዚህም ገደኛ ነበር። ከገሚሱ አልበሙ የተደመጠውና ድምፃዊቷም በአፍሪማ አዋርድ የታጨችበት፤ በአይኮኒክ አዋርድ የተሸለመችበት እሱ በሰጣት ግጥም “የልቤ ቁምነገር” በሚለው ዘፈኗ ነበር።ጌራወርቅ በመጀመሪያ ሥራው ተቀባይነት ተቀብቶበታል። ከዚያም በኋላ “ሙሉ አካል ትዝታ” በሚል ልቦለድ መጣሁ ሲል ቆይቶ በሥነ ጽሑፉም፣ በሙዚቃው ለዓይንና ለጆሮ ራቀ። ሰነበተ፤ ቆዬ፤ ከረመ።ከተወሰኑ ዓመታት በኋላ ለመስከረም አዲስ ዓመትን (2019 ዓ.ም) ቀጠሮ አድርጎ ሐምሌ “የቃል ሊቀ መኳስ” በሚል የግጥም መጽሐፍ መጣሁ አለ። እኛም ከአዲሱ መጽሐፍ ንባብ በፊት እንደማናበቢያና እንኳን ደኅና መጣህ ለማለት ያህል “እናርጅና እናውጋ”ን የትዝታ ስንብት፣ “የቃል ሊቀ መኳስ” ደግሞ የተስፋ ቀጠሮ አድርገን ኤቨንት አዲስ ከጌራወርቅ ጥላዬ ጋርከዚህም ከዚያም የተወሰነ ቆይታ አድርጋለች። እነሆ ትጋበዙ ዘንድ መልካም ንባብ እንላለን።ሙሉ ቆይታውን ያንብቡ:-👇


Event Addis Media
9 Sept, 09:45
🔶ኮምፓስ ፕሮፐርቲስ ድጋፍ አደረገኮምፓስ ፕሮፐርቲስ የ2019 አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ የማኅበራዊ ተሳትፎ ኃላፊነቱን ለመወጣት ለሴት ተማሪዎች የንጽህና መጠበቂያ (ሞዴስ) ድጋፍ አደርጓል።ድርጅቱ ድጋፍ ያደረገው በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 ለሚገኘው የተባበሩት አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ነው።ድጋፉም በት/ቤቱ ለሚማሩ 200 ሴት ተማሪዎች ለአንድ ዓመት የሚሆን የንጽህና መጠበቂያ (ሞዴስ) ቁሳቁስ እንደሆነም ተገልጿል።በስጦታ ርክክብ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የኮምፓስ ፕሮፐርቲስ የገበያና ሽያጭ ክፍል ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ተኩ "ኮምፓስ ፕሮፐርቲስ ቃል በገባው መሠረት በዛሬው ዕለት ድጋፉን ያደረገ ሲሆን፣ ወደፊትም ማኅበራዊ ኃላፊነቱን አጠናክሮ ይቀጥላል" ብለዋል። አክለውም ድርጅታቸው አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ ለመኖሪያና ለንግድ ቤት ገዢዎች እስከ 30 በመቶ የሚደርስ ልዩ የበዓል ቅናሽ ማዘጋጀቱን ገልጸዋል።የወረዳ 03 ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዋኩማ ጎንፋ በበኩላቸው የተደረገውን ድጋፍ አድንቀው፣ ሌሎች ተቋማትም ተመሳሳይ ማኅበራዊ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።የትምህርት ቤቱ ም/ርዕሰ መምህር እህቴነሽ ተ/ያሬድ የተደረገውን ደጋፍ በተገቢ መንገድ ለሴት ተማሪዎች እናቀርባለን ብለዋል።ኮምፓስ ፕሮፐርቲስ በዘርፉ የካበተ ልምድ ያላቸውን ኢትዮጵያውያን እና አንቱታን ያተረፉ የቻይና ባለሙያዎችን በማጣመር፣ በጥራት እና በአጭር ጊዜ ግንባታዎችን በማጠናቀቅ በዘርፉ አዲስ መለኪያ ማስቀመጥ የቻለ ተቋም ነው።ለተጨማሪው: https://t.me/EventAd


Event Addis Media
9 Sept, 08:27
forwarded from @kelematadshub
🏙 የPENTHOUSES ሽያጭ በመገናኛ በይፋ ተጀምሯል!🔥 ከ10% እስከ 35% ቅናሽ! የህልምዎን ቤት አሁኑኑ ያግኙ! 🔥አዲስ ቤት ለመግዛት እያሰቡ ነው? ለመወሰን ጊዜው አሁን ነው! 🔥📍 መገናኛ 🏢 Penthouses — 209 ካሬ ጀምሮ 🛏 1–3 Bedroom — 69 ካሬ እስከ 145 ካሬ📍 ሳርቤት 🛏 1–3 Bedroom — 73 ካሬ እስከ 175 ካሬ📍 ቡልጋሪያ 🛏 1–3 Bedroom — 68 ካሬ እስከ 142 ካሬ📍 አዋሬ 🛏 1 እና 3 Bedroom — 80 ካሬ እስከ 157 ካሬ📍 አያት 49


Event Addis Media
7 Sept, 11:08
forwarded from @kelematadshub
ቆይ እንዳሰቡት አይደለም!የቀነስነው ጥራቱን አይደለም አላስፈላጊ ወጪውን እንጂ!ዌብሳይትዎን ለመገንባት በአንድ ጊዜ የሚሰሩ 7 የ-AI ኤጀንቶችን እንጠቀማለን። ዲዛይን፣ ጽሁፍ፣ ኮዲንግ ሁሉም በአንድ ጊዜ ይከናወናሉ። ትልቅ team፣ ተጨማሪ ክፍያ የለም ቅልጥፍና ብቻ! ዋጋችንን እጅግ ቅናሽ ያደረገው ይኸው ነው።ውጤቱስ?በ48 ሰዓታት ውስጥ ለስራ ዝግጁ የሆነ ፕሮፌሽናል ዌብሳይት። ቴምፕሌት አይደለም፤ የተቀጣጠለ ስራም አይደለም። ቡድናችን እረፍት ስለማያውቅ በከፍተኛ ፍጥነት የተገነባ እውነተኛ ዌብሳይት!7AI Studioዌብሳይታችን ላይ በመግባት ይዘዙ : https://sebat.oriix.netለበለጠ መረጃ☎️ Phone Number: +251957323634📱 Telegram @Oriix_Support


Event Addis Media
7 Sept, 06:00
🔶 "አዲሱን ዓመት በምስጋና”አዲሱን ዓመት በምስጋና፣ በተስፋ እና በመልካም ምኞት ለመቀበል የተዘጋጀ የምስጋና መርሃግብር ተካሄደ።መርሃግብሩ በቲኤች ሚድያ ግሩፕ (TH Media Group) እና በስዊት ላይፍ ፎር ኦል (Sweet Life for All) ትብብር የተዘጋጀ ነው።በስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙ ተሳታፊዎች በተጠናቀቀው ዓመት በተከናወኑ ስኬታማ ሥራዎች፣ በተገኙ ዕድሎች እና በነበሩ መልካም አጋጣሚዎች ላይ ምስጋና አቅርበዋል።በተጨማሪም መጪው አዲስ ዓመት የሰላም፣ የእድገት፣ የተሻለ ሕይወት እና የአዳዲስ ዕድሎች ዘመን እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን አስተላልፈዋል።"ያለፈውን በምስጋና፣ የሚመጣውን በተስፋ" በሚል መሪ ቃል በተካሄደው በዚህ መርሃግብር፤ ምስጋና ያለፈውን ጉዞ ለመገምገም እና ወደ ፊት በተስፋ ለመራመድ ትልቅ አቅም የሚሰጥ እሴት መሆኑ ተመልክቷል።በመጨረሻም ህብረተሰቡ አዲሱን ዓመት በአንድነት፣ በፍቅር፣ በምስጋና እና በተስፋ እንዲቀበል ጥሪ የቀረበ ሲሆን፣ መርሃግብሩ በታላቅ ደስታ ተጠናቋል።ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1




Event Addis Media
6 Sept, 19:04
🔶ጋዜጠኛ በላይ በቀለ በፅኑ ታሟልአንጋፋው ጋዜጠኛ በላይ በቀለ ድንገተኛ የስትሮክ አደጋ አጋጥሞት፣ በአሁኑ ወቅት ዳግማዊ ሚኒሊክ ሆስፒታል በፅኑ ሕሙማን መከታተያ ክፍል (ICU) ውስጥ እየታከመ ይገኛል።ጋዜጠኛ በላይ በቀለ በኢትዮጵያ የሚዲያ ታሪክ ውስጥ ለበርካታ ዓመታት በሬዲዮና በቴሌቪዥን በብቃት ያገለገለ አንጋፋ ባለሙያ ነው። በቅርብ ዓመታትም “በላይ ሚዲያ” የዩቲዩብ ቻናልን በመመስረት፣ በሥራ ፈጠራ፣ በቢዝነስና በግል ልማት ዙሪያ ለወጣቶች እውቀትና ልምድ ሲያካፍል ቆይቷል።ከጋዜጠኛው የቅርብ ወዳጅ አንጋፋው ጋዜጠኛ አለምነህ ዋሴ በተሰጠ መረጃ መሠረት፣ የስትሮክ አደጋው ከተከሰተ በኋላ ወደ ልዩ የስትሮክ ሕክምና ማዕከል ለማዛወር ጥረት ተደርጎ ነበር። ሆኖም ከአደጋው ጀምሮ ከ24 ሰዓት በላይ በመቆየቱ ምክንያት የቀዶ ሕክምና አማራጩ ወሳኝ ጊዜ ማለፉን ሐኪሞች እንደገለጹ ተገልጿል።በአሁኑ ወቅት በዳግማዊ ሚኒሊክ ሆስፒታል የሚገኙ የሕክምና ባለሙያዎች አስፈላጊውን የነፍስ አድን ሕክምናና የቅርብ ክትትል እያደረጉለት ነው።ይህ ሕይወቱን ሙሉ ለሕዝብ መረጃና እውቀት ሲያበረክት የኖረ አንጋፋ ባለሙያ ዛሬ የወገኖቹን እገዛ የሚሻበት ወቅት ላይ ይገኛል።የድጋፍ ጥሪለጋዜጠኛ በላይ በቀለ የሕክምና ወጪ ድጋፍ ማድረግ የምትፈልጉ፦የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (CBE) የአካውንት ቁጥር፦ 1000191873061 የአካውንት ስም፦ አለማየሁ በፍቃዱ


Event Addis Media
6 Sept, 18:58
🔶ፖለቲከኛው የዘፈን አልበም ሊለቅ ነውፖለቲከኛ ልደቱ አያሌው በኤአይ የተሰራ የዘፈን አልበም ሊለቅ ነው እንደሆነ ተሰምቷል።ፖለቲከኛ ልደቱ አያሌው በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) የታገዘ እና 12 ዘፈኖችን የያዘ አዲስ የሙዚቃ አልበም ለአድማጮች ለማቅረብ መዘጋጀቱን አስታወቀ።"ሀሳብን በዜማ" የተሰኘው ይህ አልበም የፖለቲከኛውን የፖለቲካ ፍልስፍና፣ ማህበራዊ አመለካከት እና የተለያዩ የሕይወት እይታዎችን በዘፈን መልክ የሚያቀርብ ነው። ፖለቲከኛው ስለ ጉዳዩ ሲናገር፦ "እኔ የኪነ-ጥበብ ሰው ባልሆንም፣ ትንሽ አንዳንድ ዝንባሌዎች አሉኝ፤ በመሆኑም 'ሀሳብን በዜማ' የሚል አልበም በኤ አይ ሰርቻለሁ" ብሏል።እንደ ፖለቲከኛ ገለፃ፣ የአልበሙ ዘፈኖች ለአዲሱ ዓመት መግቢያ ከመስከረም 1 ቀን ጀምሮ ለ12 ተከታታይ ቀናት በየእለቱ አንድ አንድ ዘፈን ለህዝብ የሚለቀቁ ይሆናል ተብሏል።ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1


Event Addis Media
4 Sept, 18:17
🔶3ኛው “ምሳሌ የቤተሰብ ሸልማት”“ምቹ ቤት ሚዲያ እና ኢቨንት” በየዓመቱ የሚያዘጋጀው “ምሳሌ የቤተሰብ ሸልማት” ዘንድሮ ለ3ኛ ጊዜ በደማቅ ሁኔታ ሊካሄድ መሆኑ ተገለጸ።መርሃ ግብሩ የቤተሰብን እሴት ለማክበርና ለትውልድ የሚሻገር አሻራ ለማስቀመጥ ያለመ ሲሆን፣ ተጋባዥ እንግዶችና የክብር አበጋዞች በተገኙበት በታላቅ ድምቀት እንደሚካሄድ አዘጋጆቹ አስታውቀዋል።የሽልማት ዝግጅቱ ነገ ቅዳሜ፣ ነሐሴ 30 ቀን 2018 ዓ.ም. 7:30 ጀምሮ በዓድዋ ድል መታሰቢያ ይካሄዳል ተብሏል።ዝግጅቱ የቤተሰብን ሚና የሚያጎሉ ጥሪ የተደረገላቸው ልዩ እንግዶች በሚገኝበት የሚካሄድ ልዩ የምስጋናና የእውቅና መድረክ መሆኑ ተመላክቷል።ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1


Event Addis Media
4 Sept, 17:30
🔶በሆሄ ምዕራፍ ቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሤ!የሆሄ ምዕራፍ የመጽሐፍ ውይይት መድረክ በደራሲ ዮሐንስ አድማሱ በተጻፈው “ቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሤ፤ አጭር የሕይወቱና የጽሑፉ ታሪክ” በተሰኘው መጽሐፍ ላይ ያተኮረ የውይይት መርሃ ግብር ማዘጋጀቱን አስታወቀ።ውይይቱ ነሐሴ 30 ቀን 2018 ዓ.ም. ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ጀምሮ በወመዘከር (የብሔራዊ ቤተ መጻሕፍትና ቤተ መዛግብት ኤጀንሲ) ይካሄዳል።የሆሄ ምዕራፍ የዚህ ወር መድረክ በሚከተሉት ዋና ዋና ነጥቦች ላይ ትኩረት ያደርጋል:- የኢትዮጵያ ዘመናዊ ትያትር አጀማመርና የቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሤ ድርሻ፣ የጽሑፍ፣ የድራማና የሙዚቃ ሥራዎች የዘመናቸውን ማኅበረሰብ የገለጹበት መንገድ፣የቀደምት ምሁራንና የሥነ ጥበብ ሰዎች ውርስ ለዛሬው ትውልድ የሚያስተላልፈው መልእክት ።በዕለቱም የሥነ ጽሑፍ፣ የትያትር፣ የሙዚቃና የመጽሐፍ አፍቃሪያን እንደሚታደሙ ከአዘጋጅዎቹ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1


Event Addis Media
4 Sept, 17:30edited
🔶"የእናቴ ሮሚዮ" መጽሐፍ ነገ ይመረቃልከእውነተኛው ሕይወት ገጽታዎች የተቀዱ ውብ ታሪኮች የተሰባሰቡበት የጋዜጠኛና ደራሲ ስመኝ ግዛው «የእናቴ ሮሚዮ» እና ሌሎች አጫጭር ታሪኮች መጽሐፍ ነገ ነሐሴ 30/2018 ዓ.ም ይመረቃል።መጽሐፉ ቀደም ብሎ ለአንባብያን መድረሱን ተከትሎ፣ በዕለቱ በሥራው ላይ ጥልቅ ግምገማና ዳሰሳ ይቀርባል።በምርቃት ሥነ ሥርዓቱ ላይ ታዋቂ የሥነ ጽሑፍ ባለሙያዎች፣ ምሁራን፣ አርቲስቶችና አንባብያን የሚገኙ ሲሆን፣ ከመጽሐፉ የተወሰዱ ታሪኮችም በታዋቂ ተዋንያን አማካኝነት በመድረክ ላይ ይቀርባሉ።ደራሲዋ መጽሐፍን አስቀድሞ ለንባብ ማብቃት አንባብያን ያዩትንና የተሰማቸውን በነፃነት እንዲገልጹ እንዲሁም ገንቢ ሂስና አስተያየት እንዲሰጡበት ሰፊ መድረክ የሚከፍት መሆኑን ተናግራለች።ምርቃቱ ከቀኑ 8:00 ጀምሮ በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም አዳራሽ ይካሄዳል።ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1


Event Addis Media
4 Sept, 17:30
🔶 "አዲሱን ዓመት በምስጋና”አዲስ ዓመትን ያለፉትን በጎ ተግባራት በማስታወስ እና የሚመጣውን ተስፋ በምስጋና በመቀበል ለማክበር የተዘጋጀ ልዩ የበጎነትና የምስጋና መርሃ ግብር ሊካሄድ ነው።ዝግጅቱ በTH Group እና በ Sweet Life For All ትብብር የተዘጋጀ ሲሆን፣ “አዲሱን ዓመት በምስጋና” በሚል መሪ ቃል በርካታ ወጣቶችን፣ ተፅዕኖ ፈጣሪዎችን፣ የሀገር ባለውለታዎችን እና የበጎነት ተምሳሌቶችን በአንድ መድረክ ያገናኛል ተብሏል።መርሃ ግብሩ የተለመደ የበዓል ግብዣ ሳይሆን፣ በሕይወታቸውና በስራቸው ለሌሎች መልካም አርአያ የሆኑ ሰዎችን ለማመስገን፣ የበጎነት ታሪኮችን ለማጋራት እና ተስፋን ለማደስ የተዘጋጀ ልዩ መድረክ መሆኑ ተገልጿል።በዚሁ መሠረት በማህበረሰብ ተሳትፏቸው እና በበጎ ሥራ ላይ ባሳዩት ቁርጠኝነት ተፅዕኖ የፈጠሩ አካላት የክብር እንግዳ ሆነው እንዲገኙ ጥሪ ቀርቧል።ዝግጅቱ ቅዳሜ፣ ነሐሴ 30 ቀን ከሰዓት በኋላ ከ7:30 ጀምሮ ቦሌ ኤድናሞል አካባቢ፣በሚገኘው ካሌብ ሆቴል ይካሄዳል።ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1


Event Addis Media
3 Sept, 10:34edited
🔶"ጎረቤቴ" የግጥም ዝግጅት በፊሊ ኮፊ"ጎረቤቴ" የተሠኘ የኪነጥበብ ዝግጅት የፊታችን እሁድ ጳጉሜ 1 2018 ዓ.ም ከ11:00 ጀምሮ ሜክሲኮ ቡናና ሻይ በሚገኘው ፊሊ ኮፊ እንደሚካሄድ አዘጋጆቹ አስታውቀዋል።የዝግጅቱ አሰናኞች " አዲስ ወቅት ለመቀበል የምናደርገውን ሽር ጉድ የሚያደምቅ እስካሁን ከሠራናቸው ሁሉ ለየት ያለ መድረክ ይዘን መጣን። ጉዱን ለማየት እሁድ 11 ሰዓት ሜክሲኮ ቡናናሻይ የሚገኘው ፊሊ ኮፊ መከሰት!" ብለዋል።ከታች ባለው ሊንክ ቀድማችሁ ተመዝገቡ!Register here https://gorebete.wassystem.com/customer/event/12ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1


Event Addis Media
3 Sept, 10:34
🔶"አውራ አምባ: በዓለም አዲስ ምዕራፍ"“አውራ አምባ ለዓለም አዲስ ምዕራፍ” የተሠኘውና 10 ዓመታትን የፈጀ ዘጋቢ ፊልም እሁድ ይመረቃል።በኢትዮጵያ ልዩ ታሪክ፣ ፍልስፍና እና ማኅበራዊ የአኗኗር ዘይቤ ያለውን የአውራ አምባ ማኅበረሰብ ታሪክና የሕይወት ተሞክሮ የሚዳስሰው “አውራ አምባ ለዓለም አዲስ ምዕራፍ” ዘጋቢ ፊልም ለመጀመሪያ ጊዜ ለእይታ ቀርቦ በይፋ ሊመረቅ ነው።10 ዓመታትን የፈጀው ዘጋቢ ፊልሙ፣ በታዋቂዋ ትውልደ ኢትዮጵያዊት የፊልም ባለሙያ፣ የቪዲዮ አርቲስት እና አስተማሪ ፕሮፌሰር ሳሌም መኩሪያ የተዘጋጀ ነው። ፕሮፌሰር ሳሌም መኩሪያ ከዚህ ቀደም ስደት እና የወንዝ ማዕበል የተሰኙ የፊልም ስራወች የሚታወቁ ሲሆን፣ ሥራዎቻቸው በቬኒስ ቢዬናሌ፣ በኒውዮርክ አፍሪካን ፊልም ፌስቲቫል እና በሌሎች ዓለም አቀፍ የኪነጥበብ መድረኮች ቀርበዋል።ዘጋቢ ፊልሙ እሁድ ጳጉሜ 1 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8:30 ጀምሮ ሰንጋተራ አካባቢ በሚገኘው የአዲስ አበባ ከተማ ሲኒማ ቤቶች ድርጅት አዳራሽ (አዲስ ሲኒማ ኮምፕሌክስ) በደመቀ ዝግጅት ይመረቃል።የፊልሙ ምረቃ ለፊልም ባለሙያዎች፣ ለባህልና ማኅበራዊ ጥናት ተመራማሪዎች፣ ለኪነ-ጥበብ ወዳጆች እንዲሁም የአውራ አምባን ማኅበረሰብ ልዩ የህይወት ተሞክሮ ለማወቅ ፍላጎት ላላቸው ሁሉ ጥሩ አጋጣሚ እንደሚሆን ይጠበቃል ተብሏል።ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1


Event Addis Media
2 Sept, 13:34edited
🔶ሙዚቀኛ ጆቫኒ ሪኮ ከፕሪስቴጅ አዲስ ጋርፕሪስቴጅ አዲስ ከሙዚቀኛ ጆቫኒ ሪኮ ጋር የሚያገናኝ ልዩ የመታሰቢያ እና የውይይት መርሃ ግብር አዘጋጀፕሪስቴጅ አዲስ (Prestige Addis) ከራዲያንት ፊልምስ እና በአዲስ አበባ ከሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ጋር በመተባበር፣ የታዋቂው የቤዝ ጊታር ተጫዋች እና የሮሃ ባንድ መስራች አባል ጆቫኒ ሪኮን የአምስት አስርት ዓመታት የሙዚቃ ጉዞ የሚያከብር ልዩ መርሃ ግብር ማዘጋጀቱን አስታወቀ።በመድረኩ ላይ ሙዚቀኛ ጆቫኒ ሪኮ ስለ ኢትዮጵያ ሙዚቃ ወርቃማ ዘመን፣ ስለ አሁኑ የሙዚቃ ኢንዱስትሪ ሁኔታ እንዲሁም ስለ ህይወትና ጥበብ ተሞክሮዎቹ ማብራሪያ የሚሰጥ ሲሆን፣ ከተሳታፊዎች ለሚነሱ ጥያቄዎችም ምላሽ እንደሚሰጥ ተገልጿል።ይህ መርሃ ግብር ማክሰኞ ጳጉሜን 3 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ጀምሮ በአሜሪካ ኤምባሲ ግቢ ውስጥ በሚገኘው ሳችሞ ሴንተር (Satchmo Center) እንደሚካሄድ የተገለጸ ሲሆን፣ ፍላጎት ያላቸው ተሳታፊዎች አስቀድመው በተዘጋጀው የመመዝገቢያ ሊንክ አማካይነት መመዝገብ እንደሚችሉ አዘጋጆቹ አስታውቀዋል።🔗 አሁኑኑ ለመመዝገብ ይህንን ሊንክ ይጫኑ 👇 https://jazzio.land/registerለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1


Event Addis Media
2 Sept, 13:34
🔶በአማን ፕሮፐርቲስ አማን አዲስ ኤክስፖአማን ፕሮፐርቲስ በሪል ስቴት እና በግንባታ ዘርፉ ባላፉት አምስት ዓመታት ሲንቀሳቀሱ የነበሩትን ላፍቶ ላይፍ፣ ኒው ላይፍ እና ስካይ ቪው ሪል ስቴቶችን በአንድ ስም በማጠቃለል በአዲስ የብራንድ ስም ወደ ገበያ መግባቱን አስታወቀ።ድርጅቱ እስካሁን ባደረገው እንቅስቃሴ ሦስት የቤት ግንባታ ቦታዎችን (ሳይቶችን) ሙሉ ለሙሉ በማጠናቀቅ 312 አባወራዎችን የቤትና የሱቅ ባለቤት ያደረገ ሲሆን፣ 64 ዘመናዊ ቪላዎችን ገንብቶ ማስረከቡን ገልጿል።የአማን ፕሮፐርቲስ እናት ኩባንያ የሆነው አማኔት ግሩፕ በንግድ፣ በማኑፋክቸሪንግ እና በቴክኖሎጂ ዘርፎች ላለፉት 10 ዓመታት ሲንቀሳቀስ የቆየ ሲሆን፣ በብረትና አሉሚኒየም አስመጪነት፣ በቡና ላኪነት እና በወንዝ ዳርቻ ልማት ግንባታዎች የሚታወቅ ነው።አማን ፕሮፐርቲስ በራሱ የኮንስትራክሽን ድርጅት የሚታገዝ በመሆኑ የግብዓት እጥረትን በማስወገድ ፕሮጀክቶችን በተያዘላቸው ጊዜ የማጠናቀቅ፣ የግንባታ ጥራትን የመጠበቅ እና አማራጭ የአከፋፈል መንገዶችን የማቅረብ አቅም እንዳለው አስታውቋል።ከዚሁ ጋር ተያይዞ ኩባንያው ከአርብ ነሐሴ 29 እስከ ጳጉሜን 1 ቀን 2018 ዓ.ም በላፍቶ ሞል ግቢ ውስጥ “አማን አዲስ ኤክስፖ” የተሰኘ ኤግዚቢሽን ያዘጋጀ ሲሆን፣ በብስራተ ገብርኤል እና በካዛንችስ የሚያስገነባቸውን ሚክስድ አፓርትመንቶች በልዩ የበዓል ቅናሽ፣ ለደንበኞች እንደሚያቀርብ ገልጿል።ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

Related Channels
Other channels in the same section of the catalogue.
