Latest posts

Ewunet Media
26 Sept, 10:09
የአሜሪካዊቷ ጋጋሪ የዓይን ብሌን እና የፍርሃት ኬኮችአንዲት አሜሪካዊት የኬክ ባለሙያ በህመም እና በፍርሃት የተጣመሙ፣ አስፈሪ የሰው ፊቶችን የሚመስሉ እጅግ የሚዘገንኑ ፒሳዎችን በመጋገር የብዙዎችን ቀልብ ስባለች።ኬኮቹ ሲታዩ የሚያስፈሩና እና በፍርሃት እጅግ የሚንጠራወጡ ቢመስሉም፣ ሙሉ በሙሉ ሊበሉ የሚችሉ እና በውስጣቸው ጣፋጭ ክሬም የተሞሉ ናቸው።ተመልካቾች በምፀት "ነፍስህን (ወይም የሌላ ሰውን ነፍስ) ሙሉ በሙሉ መጋገር ላይ ስታውለው!" በማለት የፈጠራ ችሎታዋን ያደንቃሉ።እነዚህ የሚያደነግጡ ነገር ግን ጣፋጭ የሆኑ የምግብ ጥበቦች በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ከፍተኛ ትኩረት አግኝተዋል።



Ewunet Media
26 Sept, 07:47
🚨 #እንድታውቁትየኢትዮጵያ የምግብ እና መድኃኒት ባለሥልጣን /EFDA በካንሰር ሕክምና ላይ የሚውለው "Avastin 400 mg/16 mL" የተሰኘው መድኃኒት ሐሰተኛ ቅጅ በሀገሪቱ ገበያ ውስጥ መገኘቱን በማረጋገጥ ማስጠንቀቂያ አውጥቷል።የካንሰር ሕክምና መድኃኒቱን ሕጋዊ አምራች ከሆነው «F. Hoffmann-La Roche Ltd» ከተገኘው መረጃና ከተደረገው የድህረ-ገበያ ቁጥጥር በተገኘው ግኝት መሠረት፤ የፓኬጁ ባች ቁጥር H1180A34 የሆነውና የምርት እንዲሁም የማብቂያ ቀኑ 01/2026 እና 05/2029 ተብሎ የተጻፈበት መድኃኒት ሐሰተኛ መሆኑ ተረጋግጧል ብሏል።ትክክለኛው «Avastin 400 mg/16 mL» መድኃኒት በውስጡ «bevacizumab» የተሰኘውን ይዘት የያዘና የአንጀት፣ የጡት፣ የኦቫሪ እንዲሁም የኩላሊት ካንሰር ሕክምናዎች ላይ የሚውል ነው።ይህንን የተጭበረበረ ምርት መጠቀም በሕሙማን ላይ ከፍተኛ የጤና አደጋና የሕይወት ስጋት የሚያስከትል በመሆኑ የሕክምና ተቋማት፣ የጤና ባለሙያዎችና ሕሙማን ከስርጭትና ጥቅም ላይ ከመዋል እንዲያግዱት ባለሥልጣኑ ጥሪ አቅርቧል።ኅብረተሰቡ ወይም የጤና ባለሙያዎች ይህን ምርት ሲያገኙ ወይም ጉዳት ሲያጋጥማቸው በነፃ ስልክ መስመር 8482፣ በኢሜይል pharmacovigilance@efda.gov.et፣ በ«Med Safety» ሞባይል መተግበሪያ ወይም በባለሥልጣኑ ድረ-ገጽ (www.efda.gov.et) ጥቆማ መስጠት ይችላሉ ተብሏል።



Ewunet Media
25 Sept, 05:05
የ8 አመት ልጅ በመሸሸግ 3 ሚሊዮን ብር የጠየቀችዋ የቤት ሰራተኛየወንጀል ድርጊቱ የተፈፀመው መስከረም 13 ቀን 2019 ዓ/ም ከምሽቱ 4፡00 ሠዓት በልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 8 ካርል አደባባይ ከሚገኝ አንድ መኖሪያ ቤት ነው፡፡ሰናይት አየለ የተባለች ግለሰብ በግል ተበዳይ መኖሪያ ቤት በቤት ሰራተኝነት ተቀጥራ መስራት ከጀመረች 8 ወራት ያህል አስቆጥራለች፡፡ተጠርጣሪዋ በተገለፀው ቀንና ሠዓት ዘዊ ጠንክር የተባለች የ8 አመት ህፃን ልጅ የግል ተበዳይ ከሚኖሩበት አፓርታማ ሁለተኛው ፎቅ ላይ ለኪራይ ተብሎ በተዘጋጀ ክፍል ውስጥ ህፃኗን ሸሽጋ እንድትቀመጥ አድርጋለች፡፡ተከሳሽ ህፃኗን ከሸሸገች በኋላም ለአባቷ በመደወልና ልጃቸው መታገቷን በመግለፅ ለማስለቀቅ 3 ሚሊየን ብር እንዲከፍሉ ጠይቃለች፡፡የግል ተበዳይም የወንጀል ድርጊቱ ከተፈፀመ በኋላ ለፖሊስ በሰጡት መረጃ ፖሊስ ጉዳዩን ሲከታተል ቆይቶ 24 ሠዓት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ተከሳሽን በቁጥጥር ስር ሊያውልም ችሏል፡፡




Ewunet Media
25 Sept, 03:39
በቱርክ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ምስል በመጠቀም ስልጣን እንዳለው ለማስመሰል የሞከረው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለበቱርክ አንካራ የሚኖር አንድ ግለሰብ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂን በመጠቀም የተሰሩ ሀሰተኛ ምስሎችን በማህበራዊ ሚዲያ በማሰራጨቱ በቁጥጥር ስር መዋሉን የሀገሪቱ የመገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።ግለሰቡ በኒውራል ኔትወርክ በመታገዝ ከቱርኩ ፕሬዝዳንት ረሲፕ ታይፕ ኤርዶጋን እና ከፍትህ ሚኒስትሩ ጎን እንደቆመ የሚያሳዩ ምስሎችን ፈጥሮ አሰራጭቷል።የመርማሪዎች ቡድን እንደገለጸው፣ ግለሰቡ ይህንን ያደረገው ከመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር ቅርብ ግንኙነት እንዳለው እና ተጽዕኖ ፈጣሪ እንደሆነ አስመስሎ ለመታየት በማሰብ ነው።በአሁኑ ወቅት በግለሰቡ ላይ ተጽዕኖ የመሸጥ እና ሀሰተኛ መረጃ የመንዛት ወንጀል ክስ ተመስርቶበት ምርመራ እየተካሄደበት ይገኛል።



Ewunet Media
24 Sept, 18:23
በሰሜን ወሎ #በተኩላሽ #በበቅሎ_ማንቂያ እና #ሳንቃ በኩል የወልዲያን መንገድ ለመቁረጥ የሞከረው የህወሓት ተዋጊ ሀይል አብዛኛው መማረኩ ይፋ ሆኗል።
Ewunet Media
24 Sept, 18:20edited
በአላማጣ ከተማ ከባድ የተባለ የድሮን ጥቃት ተፈፀመ‼️ህወሃት በአላማጣ ከተማ ፋጫ አንደኛ ትምህርት ቤት ውስጥ አስቀምጠዋቸው የነበሩ ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች ላይ ዛሬ መስከረም 14 8:00 ላይ የድሮን ጥቃት ተፈፅሞባቸዋል።ከዚህ በተጨማሪ በአላማጣ ከተማ ጅሃን 1ኛ ደረጃ ትም/ት ቤት አጠገብ የጥይት መጋዘን የነበረ ቢሆንም 7:50 ላይ በድሮን ጥቃት ተፈፅሞበታል።


Ewunet Media
24 Sept, 13:51edited
የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የመስቀል ደመራና የኢሬቻ በዓላት አከባበርን አስመልክቶ መግለጫ ሰጠየጋዜጣዊ መግለጫውን የሰጡት የአዲስ አበባ ከተማ ሠላምና ፀጥታ አስተዳደር ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ፍስሀ ጥበቡ ሲሆኑ በመግለጫው ላይም የተለያዩ ጥሪ የተደረገላቸው ሚዲያዎች ተገኝተዋል።የመስቀል ደመራና ኢሬቻ በዓላት ለኢትዮጵያ የዕድገት ግስጋሴ ያላቸው አንድምታ ስንመለከት ከኃይማኖታዊና ባህላዊ እሴቶቻቸው ባሻገር ለማህበራዊ ትስስርና ለሠላም ግንባታ የሚያበረክቱት አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው ብለዋል። ሰዎች በአንድ ላይ ተሰባስበው ባህላቸውን ሲያከብሩ፣ ለሌላው ባህልና እምነት ክብር ሲሰጡ አንድነታችንን ለማጠናከርን ይረዳል ብለዋል በመግለጫቸው፡፡በያዝነው መስከረም ወር በከተማችን በርካታ ህዝብ የሚታደምባቸው የአደባባይ በዓላት በሠላም እንዲከበሩ ልዩ ልዩ ቅድመ ዝግጅቶች የተደረጉ ሲሆን በተለይ ከፀጥታ አካላት፣ ከተቋማት እና ከህብረተሰቡ ጋር ሰፊ ውይይቶች መደረጋቸው በመግለጫው ተገልጿል።ሚዲያዎች የበዓላቱን ባህላዊና ማህበራዊ እሴት በማጉላት፣ የሠላምና የመቻቻል መልዕክቶችን በማስተጋባት እንዲሁም ህዝቡ ሊያደርጋቸው የሚገቡ የጥንቃቄ እርምጃዎችን በማሳወቅ፣ ሠላም እና ሕብረትን የሚያጠናክሩ ትክክለኛ መረጃዎችን ሙያዊ ሥነ-ምግባር በተላበሰ መልኩ እንዲያቀርቡ ኃላፊው ጥሪ አቀርበዋል።ሁሉም የከተማችን ነዋሪዎች የአደባባይ በዓላት የአንድነታችን እና የአብሮነታችን መገለጫ መሆኑን በመረዳት የተለመደውን መልካም ትብብሩን ማድረግ ይጠበቅበታል ያለው መግለጫው በተለይ ደግሞ ህገ-ወጥ እንቅስቃሴና አጠራጣሪ ጉዳዮችን ሲያይ ለሚመለከተው የፀጥታ አካል በማሳወቅ የራሱን ድርሻ እንዲወጣም ጥሪ ቀርቧል።


Ewunet Media
24 Sept, 06:15
#Alamataትናንት በአላማጣ ከተማ አካባቢ በተፈጸሙ የድሮን እና የአውሮፕላን ጥቃቶች #14_ሰዎች_መገደላቸውን እና ሌሎች በርካቶች መቁሰላቸውን የከተማዋ ከንቲባ አቶ ሞገስ ሽፈራው ለቢቢሲ ተናግረዋል።አላማጣ በትግራይና አማራ ክልሎች የወሰን ጥያቄ የሚነሳበት አካባቢ ነው።ከንቲባው አቶ ሞገስ፣ "የተገደሉት በሙሉ ሰላማዊ ሰዎች" መሆናቸውን፣ በታጣቂም ሆነ በጦር መሳሪያ ላይ የደረሰ ጥቃት እንደሌለ ገልጸዋል። ቢቢሲ ትግርኛ ያነጋገራቸው ሦስት የአካባቢው ነዋሪዎች ግን ከተጎጂዎች መካከል በርካታ ታጣቂዎች ተመልክተዋል።ጥቃቱ መለስ ዜናዊ እና ኢያሱ በርሄ በሚባሉ ትምህርት ቤቶች ላይ እንደተፈጸሙ ነዋሪዎችና የከተማዋ ከንቲባ አስረድተዋል። ከ10 ያላነሱ የድሮን ምልልስ ጥቃቶች መፈጸማቸውን ከነዋሪዎቹ ገልጸዋል።ለአላማጣ ከተማ በየጊዜው ከንቲባ ሆነው ብቅ የሚሉላት አመራሮች ነገር፦ከዓመታት በፊት የአላማጣ ከተማ ከንቲባ ሆነው በአማራ ክልል በኩል የወሎ ራያ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ አካል የሆኑት አቶ ኃይሉ አዱኛ ተሾመው ነበር።አቶ ጌታቸው ረዳ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር በነበሩበት ወቅት ደግሞ፣ አቶ ዝናቡ ደስታ የተባሉ አካል የከተማዋ ከንቲባ መሆናቸው ተገልጸ። በዚህ ወቅት አቶ ኃይሉ በበኩላቸው፣ "የከተማዋ ከንቲባ እኔ ነኝ" ብለው ሲሞግቱ ነበር።በኋላ ደግሞ አካባቢውን ለቀው እንደወጡ ቲቃህ በአንድ ወቅት ተረድቶ ነበር። ቲቃህ ጉዳዩን ገና ባያጣራም፣ ቢቢሲ ይዞት በወጣው ዘገባ ደግሞ፣ የከተማዋ ከንቲባ አቶ ሞገስ ሽፈራው መሆናቸውን ጠቅሷል።


Ewunet Media
22 Sept, 12:57
የዘንድሮው የኢሬቻ በዓል መስከረም 23 እና 24 ይከበራል‼️በዚህም መሠረት “ኢሬቻ ለሀገራዊ መግባባት” በሚል መሪ ሀሳብ፤ ኢሬቻ ሆረ ፊንፊኔ መስከረም 23 እንዲሁም ኢሬቻ ሆረ ሀርሰዴ መስከረም 24 በቢሾፍቱ ከተማ ይከበራል።የምስጋና፣ የአንድነትና የፍቅር በዓል የሆነው ኢሬቻ የሀገርን ገፅታ በሚገነባ መልኩ እንደሚከበር ተገልጿል፡፡


Ewunet Media
22 Sept, 04:54
በወለጋ ታግተው የነበሩ አሽከርካሪዎች በሙሉ በሰላም መለቀቃቸው ተገለጸበኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን ጊምቢ ከተማ "ቢላ" በተባለ አካባቢ ጳጉሜ 1/2018 ዓ.ም በታጣቂዎች ተታግተው የነበሩ አሽከርካሪዎች በሙሉ ከእገታ መለቀቃቸውን የኢትዮጵያ ከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማህበር አስታወቀ።በወቅቱ የነዳጅ ጫኝ ተሽከርካሪዎች ከተቃጠሉበት ጥቃት በኋላ ዘጠኝ የከባድ መኪና አሽከርካሪዎችን ጨምሮ እስከ 14 የሚደርሱ የኮንስትራክሽንና የሌሎች ተሽከርካሪዎች ሾፌሮች ተወስደው እንደነበር ይታወሳል።የማህበሩ አመራር እንደገለጹት፣ ታጋቾቹ ከቀናት በፊት በሰላም ተለቀው ወደ ቤተሰቦቻቸው ተመልሰዋል።አሽከርካሪዎቹ የተለቀቁት ገንዘብ ተከፍሎ ስለመሆኑ ለተነሳው ጥያቄ የማህበሩ አመራር ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ቢቆጠቡም፣ "ዋናው ነገር አሽከርካሪዎቹ ሕይወታቸው ሳይጎዳ በቤተሰቦቻቸው ጥረት በሰላም መለቀቃቸው ነው" ሲሉ ተናግረዋል።ቲክቫህ


Ewunet Media
21 Sept, 16:30
ሐሰተኛ ፖሊሶች ደሙ የፈሰሰን ሰው አፍነው ወሰዱበስፔን ባርሴሎና አቅራቢያ በሚገኝ አውራ ጎዳና ላይ ራሳቸውን እንደ ፖሊስ ያስመሰሉ አምስት ታጣቂዎች በአንድ መኪና ላይ ጥቃት በመሰንዘር አንድ መንገደኛን በኃይል አፍነው ወስደዋል።በቪዲዮ ተቀርጾ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የተሰራጨው ይህ ድርጊት በአካባቢው አሽከርካሪዎች ላይ ትልቅ ድንጋጤን ፈጥሯል።አጋቾቹ የፖሊስ ምልከት ያለው ቬስት የለበሱና ፊታቸውን የሸፈኑ ሲሆን፣ ተጎጂውን ደሙ እየፈሰሰና ልብሱ የተገፈፈ ሆኖ ሳለ በግፍ እየጎተቱ ወደ ሌላ መኪና ሲከቱት ታይቷል።ድርጊቱ የተፈጸመው በነጭ ቀን በብዙ አሽከርካሪዎች ፊት በመሆኑ፣ አያሌ የዓይን እይታ ምስክሮች ወዲያውኑ ለፖሊስ ጥቆማ ሰጥተዋል።
Ewunet Media
21 Sept, 16:30
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን በትግራይ ቴሌቪዥን ላይ ላልተወሰነ ጊዜ እገዳ መጣሉን ገለፀባለሥልጣኑ ቀደም ሲል ከፕሬቶሪያው የሰላም ስምምነት በኋላ ተጥሎበት የነበረው እገዳ ተንስቶ ወደ ሥራ መመለሱን አውስታው፣ ለባለሙያዎቹም የሰላም ግንባታ ሥልጠናዎች ሲሰጡ መቆየታቸውን ገልጿል።ሆኖም የይዘት ክትትል ግምገማው እንደሚያሳየው ጣቢያው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሀገርና ህዝብ ደህንነትን አደጋ ላይ የሚጥሉ፣ ወደ ግጭት የሚገፋፉና ፅንፈኝነትን የሚያበረታቱ መልእክቶችን በተከታታይ ሲያስተላልፍ መቆየቱን አስታውቋል።በዚህም ምክንያት ከዛሬ ጀምሮ ጣቢያው መታገዱን የገለፀው ባለሥልጣኑ፣ ማንኛውም ዲጂታል፣ ብሮድካስት ወይም የሕትመት ሚዲያ የትግራይ ቴሌቪዥንን እንደ መረጃ ምንጭ መጠቀም ወይም ይዘቶቹን ማሰራጨት በጥብቅ መከልከሉን አሳስቧል።ይህንን መመሪያ በሚተላለፉ ሚዲያዎች ላይ አስፈላጊው ህጋዊና አስተዳደራዊ እርምጃ እንደሚወሰድም አስጠንቅቋል።
2,160Open in Telegram
Ewunet Media
21 Sept, 07:15
በኢትዮጵያ ስምንት የትጥቅና የፖለቲካ ድርጅቶች “የኢትዮጵያ ህዝባዊ ኃይሎች ትብብር ለህልውና” የተሰኘ አዲስ ህብረት መመስረታቸውን ገለጹህወሓት፣ አፋብን፣ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት፣ ኦህነግ፣ አፋር፣ ቤንሻንጉል እና ጉሙዝን ያካተተው የጋራ ትብብር ሊቀመንበር አቶ ዘመነ ካሴ እንዳስታወቁት፣ የትብብሩ ዋና አላማ በሽግግር ቻርተር የሚመራ አካታች የሽግግር መንግስት ማቋቋም ነው።



Ewunet Media
20 Sept, 16:36
በደቡብ አፍሪካ የዘጠኝ ሴቶች አስከሬን መገኘት ቅጥረኛ ገዳይ አለ የሚል ስጋት ፈጠረበደቡብ አፍሪካ ጆሃንስበርግ ምስራቃዊ ክፍል በሚገኘው ኤኩርሁሌኒ ማዘጋጃ ቤት ባለፉት ሁለት ወራት ውስጥ የዘጠኝ ሴቶች አስከሬን በግፍ ተገድለው መገኘቱ በአካባቢው ነዋሪዎች ዘንድ ከፍተኛ ፍርሃትና ስጋት ጥሏል።የመጨረሻዋ ተጎጂ ዕድሜዋ 30 ገደማ የሆነች ሴት አስከሬን በግንባታ ቦታ አቅራቢያ በላንቃዋ ታርዳና በወገቧ ላይ በቢላዋ ተወግታ ሆና መንገደኞች አግኝተዋታል።የፖሊስ መርማሪ ፍሬድ ኬካና እንደገለጹት፣ የወንጀሎቹ ተመሳሳይነት በአንድ ቅጥረኛ ነፍሰ ገዳይ የተፈፀሙ ሊሆኑ ይችላሉ የሚል ጥርጣሬ አሳድሯል ሲሉ የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።ጉዳዩን የሚያጣራ ልዩ የፖሊስ ቡድን የተዋቀረ ሲሆን፣ የጋውቴንግ ግዛት አስተዳዳሪ ፓንያዛ ሌሱፊ በምርመራው ላይ ተስፋ ሰጪ ፍንጮች መኖራቸውን ገልጸዋል።ፖሊስ ህዝቡ የፍርሃት ወሬዎችን ከመነዛት እንዲቆጠብና የተጠረጠሩ ሁኔታዎችን በፍጥነት እንዲጠቁም አሳስቧል።


Ewunet Media
18 Sept, 14:50
ከጥቅምት አጋማሽ ጀምሮ ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ እንደሚኖር ገለጸበጥቅምት ወር የሚጥለው ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ ሰብሎች ላይ ጉዳት እንዳያደርስ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚያስፈልግ የኢትዮጵያ ሜትሮሎጂ ኢንስቲትዩት ለአሐዱ አስታውቋል።በተለይም በሰሜን በሰሜን ምስራቅ በሰሜን ምዕራብ የሀገሪቱ ክፍሎች ከመደበኛ በላይ ዝናብ መጠን እንደሚኖር እና በመካከለኛው የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ እንደሚኖር ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አሳምነው ተሾመ ተናግረዋል።በተለይም በሰሜን፣ በሰሜን ምስራቅ እና በምስራቅ አካባቢዎች በሚጥለው ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ በደረሱ ሰብሎች ላይ ጉዳት ሊያደርስ ስለሚችል፣ አርሶ አደሮች ሰብላቸውን በፍጥነት እንዲሰበስቡ እና የምርት ብክነት እንዳይከሰት ቅድመ ጥንቃቄ ማድረግ አለባቸው ነው ያሉት። አክለውም የሚመለከታቸው አካላት የጎርፍ መውረጃ ቦዮችን በማጽዳት እና ማህበረሰቡን በማንቃት አስፈላጊውን ቅድመ ጥንቃቄ ማድረግ አለባቸው ሲሉ ገልፀዋል።በደቡብ አጋማሽ የሀገሪቱ አካባቢዎች ሁለተኛ በጋ በመሆኑ ከመደበኛ በላይ የሆነ ዝናብ መኖሩ ለአርብቶ አደሩ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንደሚኖረው አንስተው ለግብርና እንቅስቃሴው ጠቀሜታ ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል።ዓመታዊ የዝናብ መጠኑ እስከ 45 በመቶ የሚሆን የዝናብ መጠን ስርጭት በጉጂ እና ቦረና ዞን እንዲሁም ሲዳማ፤ ደቡብ የኢትዮጵያ የሀገሪቱ አካባቢዎች በበጋ ወቅት የሚጥለው የዝናብ መጠን ከፍተኛ መሆኑ ተጠቀሜታው ከፍተኛ እንደሆነ አስታውቀዋል።


Ewunet Media
18 Sept, 10:36
የፓርላማ አባል በሽንት ቤት ውስጥ ለ13 ሰዓታት ተቆልፎባቸው አደሩየቤልጂየም የፓርላማ አባል ፍሬደሪክ ኤረንስ በፓርላማው መጸዳጃ ቤት በር መቆለፊያ ብልሽት ምክንያት ተቆልፎባቸው ማደራቸው ተሰማ።ፓርላማ አባሉ ስልካቸውን ቢሯቸው ጠረጴዛ ላይ ትተው በመውጣታቸው እርዳታ ለመጠየቅ አልቻሉም።በሩን ቢደልቁም እና ቢጮሁም ድምፃቸውን የሚሰማቸው ሰው አልነበረም።በማግስቱ ጠዋት በጽዳት ሰራተኛ አማካኝነት የተገኙት ኤረንስ፣ ቦታው በቂ አየር የሌለው በመሆኑ የትንፋሽ እጥረት እና የማዞር ስሜት አጋጥሟቸዋል።በመሆኑም ከደረሰላቸው የህክምና እርዳታ በኋላ ለተጨማሪ ምርመራ ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸውን የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።


Ewunet Media
18 Sept, 08:48
የፓርላማ አባል በሽንት ቤት ውስጥ ለ13 ሰዓታት ተቆልፎባቸው አደሩየቤልጂየም የፓርላማ አባል ፍሬደሪክ ኤረንስ በፓርላማው መጸዳጃ ቤት በር መቆለፊያ ብልሽት ምክንያት ተቆልፎባቸው ማደራቸው ተሰማ።ፓርላማ አባሉ ስልካቸውን ቢሯቸው ጠረጴዛ ላይ ትተው በመውጣታቸው እርዳታ ለመጠየቅ አልቻሉም።በሩን ቢደልቁም እና ቢጮሁም ድምፃቸውን የሚሰማቸው ሰው አልነበረም።በማግስቱ ጠዋት በጽዳት ሰራተኛ አማካኝነት የተገኙት ኤረንስ፣ ቦታው በቂ አየር የሌለው በመሆኑ የትንፋሽ እጥረት እና የማዞር ስሜት አጋጥሟቸዋል።በመሆኑም ከደረሰላቸው የህክምና እርዳታ በኋላ ለተጨማሪ ምርመራ ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸውን የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።


Ewunet Media
17 Sept, 09:00
በቀን 130 ሺህ ሜትር ኪዩብ ውሃ መስጠት የሚያስችል የከርሰ ምድር ውሃ የማልማት ስራ እየተከናወነ መሆኑ ተገለጸበአዲስ አበባ ከተማ እያደገ የመጣውን የንጹህ መጠጥ ውሃ ፍላጎት እና ያለውን የአቅርቦት ክፍተት ለማሻሻል የአጭርና የረጅም ጊዜ ፕሮጀክቶችን ቀርጾ እየሰራ መሆኑን የአዲስ አበባ ውሃ እና ፍሳሽ ባለስልጣን ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታውቋል።በ2018 በጀት ዓመት በቦሌ አራብሳ የጋራ መኖሪያ ቤቶች እና በሌሎች አካባቢዎች 20 አዳዲስ ጉድጓዶች ተቆፍረው ስራ በመጀመራቸው በቀን 60 ሺህ ሜትር ኪዩብ ተጨማሪ ውሃ ወደ ሲስተም ማስገባት መቻሉን የባለስልጣኑ የህዝብ ግንኙነት እና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰርካለም ጌታቸው ተናግረዋል፡፡በ2019 በጀት ዓመት 130 ሺህ ሜትር ኪዩብ ውሃ መስጠት የሚያስችል የከርሰ ምድር ውሃ የማልማት ስራ እየተከናወነ እንደሚገኝ የጠቀሱት ዳይሬክተሯ፤ 100 ሺህ ሜትር ኪዩብ ያህሉ ባለፉት 2 ዓመታት ሲገነባ የቆየው የጨቋላ የውሃ ፕሮጀክት እንደሆነና ቀሪው 30 ሺህ ሜትር ኪዩብ ደግሞ በሌሎች አካባቢዎች ከሚቆፈሩ ጉድጓዶች የሚገኝ መሆኑን ገልጸዋል፡፡በቀን ከ500 ሺህ እስከ 600 ሺህ ሜትር ኪዩብ ውሃ የማመንጨት አቅም ያላቸው የሲቢሉ እና የአለልቱ ችዳሮቤ የገጸ ምድር ውሃ ፕሮጀክቶች ጥናት ተጠናቆ ገንዘብ የማፈላለግ ስራዎች በተጎዳኝ እየተከናወኑ መሆናቸውን ወ/ሮ ሰርካለም ገልጸዋል፡፡የከተማዋን የውሃ ፍላጎት በዘላቂነት ለማሟላት አዳዲስ ምንጮችን ከማልማት ጎን ለጎን የሚመረተው ውሃ እንዳይባክን የመጠበቅና የውሃ ሀብቱን በአግባቡ የመጠቀም ስራ በትኩረት ሊሰራበት



Ewunet Media pinned «በኢትዮጵያውያን ተጓዦች ላይ የታይላንድ መንግስት አዲስ የቪዛ መመሪያ ስራ ላይ ማዋሉን አሳወቀ በአዲሱ መመሪያ መሰረት ከዚህ ቀደም ለበርካታ ሀገራት ይሰጥ የነበረው ያለቪዛ የመግባት እና የመዳረሻ ቪዛ (Visa on Arrival) አሰራር ድጋሚ ተከልሶ ለተወሰኑ ሀገራት ብቻ እንዲሆን ተደርጓል። በዚሁ መሰረት እስከ መስከረም 5/2019 ዓ.ም ድረስ ወደ ታይላንድ ለሚጓዙ ኢትዮጵያውያን ይሰጥ የነበረው…»
17 Sept, 09:00

Ewunet Media
17 Sept, 08:28
በኢትዮጵያውያን ተጓዦች ላይ የታይላንድ መንግስት አዲስ የቪዛ መመሪያ ስራ ላይ ማዋሉን አሳወቀበአዲሱ መመሪያ መሰረት ከዚህ ቀደም ለበርካታ ሀገራት ይሰጥ የነበረው ያለቪዛ የመግባት እና የመዳረሻ ቪዛ (Visa on Arrival) አሰራር ድጋሚ ተከልሶ ለተወሰኑ ሀገራት ብቻ እንዲሆን ተደርጓል።በዚሁ መሰረት እስከ መስከረም 5/2019 ዓ.ም ድረስ ወደ ታይላንድ ለሚጓዙ ኢትዮጵያውያን ይሰጥ የነበረው የመዳረሻ ቪዛ የተሰረዘ ሲሆን፣ ከአሁን በኋላ ማናቸውም መንገደኞች ከሀገራቸው ከመነሳታቸው በፊት የኦንላይን ቪዛ (E-Visa) ማመልከት ይኖርባቸዋል።ተጓዦች thaievisa.go.th በተሰኘው ይፋዊ ድረ-ገጽ ላይ በማመልከት ፈቃድ ሲያገኙ ብቻ ወደ ሀገሪቱ መግባት እንደሚችሉ በኒው ዴልሂ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ የታይላንድ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን ጠቅሶ አስታውቋል።
Related Channels
Other channels in the same section of the catalogue.
