Latest posts

Fana Media Corporation S.C (FMC)
23 Sept, 17:52
የጽናትና የጀግንነት ምልክት፤ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትአዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የሀገር ድንበር ሲደፈር፣ የህዝብ ሰላምና ህልውና በጠላት ሴራ ሲፈተን፣ በግንባር ቀደምነት ደረቱን ሰጥቶ፣ ደሙን አፍስሶ አጥንቱን ከስክሶ ሀገር የሚያቆም ታላቅ ኃይል አለ እሱም የሀገር መከላከያ ሰራዊት ነው። ሰራዊቱ የሚከፍለው ዋጋ ለግል ጥቅም ወይም ለጊዜያዊ ክብር ሳይሆን፤ ለኢትዮጵያ ዘላቂ ህልውና እና ለህዝቧ ነጻነት ነው። በተለያየ ዘመን…https://www.fanamc.com/archives/323108


Fana Media Corporation S.C (FMC)
23 Sept, 17:05
የከተማ ልማት የነዋሪዎችን የኑሮ ክብር በሚጠብቅ መልኩ መከናወን አለበት – ከንቲባ አዳነች አቤቤአዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የከተማ ልማት የነዋሪዎችን የኑሮ ክብር በሚጠብቅ መልኩ መከናወን አለበት አሉ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፡፡ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በመልሶ ማልማት የተገነባውን የቅጠል ተራ የመኖሪያ ቤት በዛሬው ዕለት ለነዋሪዎች አስተላልፈዋል፡፡ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ ከተማ ለነዋሪዎች የተሻለ ኑሮ፣ ክብርና ምቹ የአኗኗር ሁኔታ የሚፈጥር…https://www.fanamc.com/archives/323104


Fana Media Corporation S.C (FMC)
23 Sept, 16:47edited
የትግራይ ክልላዊ መንግሥት ፖሊስ ኮሚሽነር ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት ሜጀር ጄኔራል ገብረ አድሃና ህገ ወጡን የህወሓት ቡድን በመቃወም ወደ ፌዴራል መንግሥት ገቡአዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የትግራይ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት የህወሓት ነባር አመራር ሜጀር ጄኔራል ገብረ አድሃና የህወሓትን ከታሪካዊ ጠላቶች ጋር በማበር ሀገር የማፍረስ ተልዕኮና የጦርነት አባዜ በመቃወም ወደ ፌደራል መንግሥት ገብተዋል። ጄኔራል መኮንኑ በሀገር መከላከያ ሠራዊት ውስጥ በከፍተኛ የአመራር እርከን ላይ ያገለገሉ ሲሆኑ፤ ህወሓት በሀገር ላይ ክህደት…https://www.fanamc.com/archives/323101


Fana Media Corporation S.C (FMC)
23 Sept, 16:24
ባዳም ተደነቀ፤ ባንዳም ተሸማቀቀሁለቱ ስፍራዎች የሀገር ስምና መልክ ናቸው! የዘመናዊት ኢትዮጵያን በተለይ ደግሞ የዚህን ትውልድ የሐሳብ፣ የተግባር እና የውጤት ተምሳሌት ሆነው ለዓለም የሚመሰክሩ ጉባና ቢሾፍቱ። ምሥራቅ እና ምዕራብ፤ የብርሃን መውጫም የብርሃን ማደሪያም። በጉባ ተራሮች ሥር ጳጉሜን 4 ቀን 2017 ዓ.ም የተካሄደውን የታሪክ እጥፋት የኢትዮጵያ ወይም የኢትዮጵያዊ ብቻ አይደለም፡፡ የጥቁርነት እና የነጻነት መንፈስን የሚጋራ የዓለም ሕዝብ ሁሉ…https://www.fanamc.com/archives/323098


Fana Media Corporation S.C (FMC)
23 Sept, 15:46
የሉዓላዊነት ምልክት፤ የኢትዮጵያ አየር ኃይልአዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ አየር ኃይል ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ ለዘጠኝ አሥርት ዓመታት ያህል የሀገሪቱን ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት በማስከበር ረገድ የማይተካ ታሪካዊ ሚና ሲጫወት ቆይቷል፤ አሁንም እተጫወተ ይገኛል፡፡ ተቋሙ በተለያዩ ዘመናት የተጋረጡበትን ውስብስብ ፈተናዎች በጽናት በማለፍ፣ ለሀገር ድንበር መከበርና ለሕዝብ ደህንነት ሲል የከፈለውን ከፍተኛ መስዋዕትነት ውጤት በማስጠበቅ እስከ ዛሬ…https://www.fanamc.com/archives/323095


Fana Media Corporation S.C (FMC)
23 Sept, 15:16
በዘመን ውስጥ ተወዳድረን የሚገባንን ለማግኘት ቴክኖሎጂ በጣም ወሳኝ ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)


Fana Media Corporation S.C (FMC)
23 Sept, 14:44
ኢትዮጵያ ዓባይ ወንዝን ለማልማት የማንንም ይሁንታ አትጠይቅም – አምባሳደር ዘሪሁን አበበአዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ የዓባይ ወንዝን ጨምሮ ሌሎች ወንዞቿን አልምታ ለመጠቀም የማንንም ይሁንታ አትጠይቅም አሉ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄነራል አምባሳደር ዘሪሁን አበበ፡፡ አምባሳደር ዘሪሁን አበበ እንዳሉት፤ ግብጽ በዓባይ ወንዝ ላይ ማስቀጠል የምትሻው የቅኝ ግዛት ፍላጎት ላይመለስ አክትሟል፡፡ ኢትዮጵያ ወንዞቿን አልምታ ለመጠቀም የማንንም ይሁንታ አትሻም ሲሉ…https://www.fanamc.com/archives/323092


Fana Media Corporation S.C (FMC)
23 Sept, 13:53edited
ኢትዮጵያ በሰው ሰራሽ አስተውሎት አማካኝነት የቱሪዝም ሀብቷን ለማልማት እየሰራች ነው – ሰላማዊት ካሳአዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ በሰው ሰራሽ አስተውሎት አማካኝነት የቱሪዝም ሀብቷን ለማስተዋወቅ እና ለማልማት እየሰራች ነው አሉ የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ፡፡ ሚኒስትሯ መስከረም 17 ቀን 2019 ዓ.ም የሚከበረውን የዓለም የቱሪዝም ቀን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ እንዳሉት ÷ የሰው ሰራሽ አስተውሎት በጎብኝዎች ፍላጎት ላይ የተመሰረተ እንዲሁም ጥራት ያለው እና የተደራጀ መረጃን…https://www.fanamc.com/archives/323086


Fana Media Corporation S.C (FMC)
22 Sept, 19:17
"ያለምንም ጥርጥር ኢትዮጵያ ትበለጽጋለች፥ የሚገባትን ቦታ ትይዛለች፤ ይህ ግን ከእኛ ጥረትና ድካም ውጪ ሊሳካ የሚችልበት ምንም መንገድ የለም" - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)


Fana Media Corporation S.C (FMC)
22 Sept, 16:48
የፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላን የሕይወትና የውትድርና ጉዞ የሚዳስሰው “ድል ቁርሱ” መጽሐፍ የምረቃ መርሐ ግብር እየተካሄደ ነውአዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላን የሕይወትና የውትድርና ጉዞ የሚዳስሰው “ድል ቁርሱ” የተሰኘ መጽሐፍ የምረቃ መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው፡፡ በመጽሐፉ የምረቃ ሥነ-ሥርዓት ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፣ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፣ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ (ዶ/ር)፣…https://www.fanamc.com/archives/323041


Fana Media Corporation S.C (FMC)
22 Sept, 16:44
"ከተሞቻችን እየዘመኑ፣ ፕሮጀክቶቻችን እያለቁ፤ ኢትዮጵያ በኢኮኖሚ እመርታ ከሚያሳዩ በጣት ከሚቆጠሩ ሀገራት ተርታ አንዷ ሆናለች" - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)


Fana Media Corporation S.C (FMC)
22 Sept, 15:59
ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በ81ኛው የተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ እየተሳተፉ ነውአዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ የተመራ ከፍተኛ ልዑክ ቡድን በኒውዮርክ እየተካሄደ በሚገኘው 81ኛው የተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ እየተሳተፈ ይገኛል። ጉባኤው “እምነትን መመለስ፣ ለውጥን መምራት፤ ለሁሉም የሚሰራ የተባበሩት መንግሥታት” በሚል መሪ ሐሳብ እየተካሄደ ይገኛል፡፡ በጉባኤው ላይ የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍፁም አሰፋ (ዶ/ር)፣ የምሥራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ…https://www.fanamc.com/archives/323036


Fana Media Corporation S.C (FMC)
22 Sept, 14:32
https://youtu.be/8X0JManjPkYYouTubeብርሃኑን ፍለጋ ...#ፋና #አዲስ_አበባ #Ethiopia #ኢትዮጵያ #FANA_TV #FANA_NEWS #ፋና_ዜና
Fana Media Corporation S.C (FMC)
22 Sept, 12:54
የመስቀል ደመራ በዓል በድምቀት እንዲከበር ዝግጀት ተደርጓል – ሌ/ጄኔራል አስራት ዴኔሮአዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የመስቀል ደመራ በዓል በድምቀት እንዲከበር በቂ ዝግጀት ተደርጓል አሉ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል አስራት ዴኔሮ፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ከአዲስ አበባ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ፣ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት እና ከአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ…https://www.fanamc.com/archives/323029


Fana Media Corporation S.C (FMC)
22 Sept, 12:53
የኢትዮጵያን የስንዴ ልማት ስኬት በዓይናችን አይተን አረጋግጠናል – አፍሪካውያን የዘርፉ ባለሙያዎችአዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያን የስንዴ ልማት ስኬት በዓይናችን አይተን አረጋግጠናል አሉ አፍሪካውያን ተመራማሪዎች እና የዘርፉ ባለሙያዎች። በአፍሪካ ዘላቂ የስንዴ ትራንስፎርሜሽን ማፋጠን፣ ቴክኖሎጂዎችን ማስፋፋት እና ብሔራዊ የዘር ሥርዓቶችን ማጠናከር ላይ ያተኮረ ዓለም አቀፍ ዐውደ ጥናት እየተካሄደ ነው። በዚህ ዐውደ ጥናት የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ተወካዮች፣ ተመራማሪዎች እና የዘርፉ ባለሙያዎች የተሳተፉ…https://www.fanamc.com/archives/323030


Fana Media Corporation S.C (FMC)
22 Sept, 12:36
ሚኬል አርቴታ ከአርሰናል ጋር ውሉን ለማደስ ተስማማአዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ከእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊጉ ሻምፒዮን ጋር የተሻሻለ አዲስ ውል ለመፈራረም ተስማምቷል። ስፔናዊው አሰልጣኝ ከአርሰናል ጋር ያለው ኮንትራት በዚህ የውድድር ዘመን መጨረሻ የሚያበቃ ሲሆን ከክለቡ ጋር ስለሚኖረው የወደፊት ቆይታ ላለፉት በርካታ ወራት ድርድር ሲካሄድ ቆይቷል። አሁን ላይ ታዲያ አሰልጣኝ ሚኬል…https://www.fanamc.com/archives/323026


Fana Media Corporation S.C (FMC)
22 Sept, 11:17
የዘንድሮው የኢሬቻ በዓል መስከረም 23 እና 24 ይከበራልአዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የዘንድሮው የኢሬቻ በዓል መስከረም 23 እና 24 ቀን 2019 ዓ.ም ይከበራል አለ የኦሮሞ አባገዳዎች ህብረት፡፡ በዚህም መሠረት “ኢሬቻ ለሀገራዊ መግባባት” በሚል መሪ ሀሳብ፤ ኢሬቻ ሆረ ፊንፊኔ መስከረም 23 እንዲሁም ኢሬቻ ሆረ ሀርሰዴ መስከረም 24 በቢሾፍቱ ከተማ ይከበራል። የምስጋና፣ የአንድነትና የፍቅር በዓል የሆነው ኢሬቻ የሀገርን ገፅታ…https://www.fanamc.com/archives/323020


Fana Media Corporation S.C (FMC)
22 Sept, 11:15
ከጓሮ ወደ ሉዓላዊነት – የሌማት ትሩፋት ታሪካዊ ስኬትአዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ግብርና ከተለመደው የአመራረት ልማድ ወጥቶ ወደ ተደራሽና ሁለንተናዊ የምግብ ዋስትና ለመሸጋገር በሚያደርገው ጉዞ በርካታ ስኬቶችን እያስመዘገበ ይገኛል። በዘርፉ ከተመዘገቡ ስኬቶች ውስጥ በ2015 ዓ.ም በይፋ የተጀመረው የሌማት ትሩፋት መርሐ ግብር ዋነኛ ተጠቃሽ ነው። መርሐ ግብሩ ዛሬ የኢትዮጵያውያን ጓሮ የልማት ማዕከል በመሆን የዕለት ተዕለት የምግብ ፍላጎትን…https://www.fanamc.com/archives/323018


Fana Media Corporation S.C (FMC)
22 Sept, 09:47
"አንድ ሀገር ከሚያቆማት ምሰሶዎች መካከል አንደኛው የኢኮኖሚ ለውጥ ነው፤ በኢኮኖሚ አሁን ሪፎርም እየተከፋፈተ በመሆኑ ገቢያችን እና የወጪ ንግዳችን በከፍተኛ ደረጃ እያደገ ነው" - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)


Fana Media Corporation S.C (FMC)
22 Sept, 09:46
አሜሪካ በኢራን ጥቃት ለተጎዱ የኃይል መሠረተ ልማቶች መልሶ ግንባታ የሚውል የ5 ቢሊየን ዶላር ፈንድ አቀረበችአዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) አሜሪካ የሰላጤው ሀገራት ንብረት የሆኑ እና በኢራን ጥቃት ጉዳት የደረሰባቸውን የኃይል መሠረተ ልማቶች መልሶ ለመገንባት የሚውል የ5 ቢሊየን ዶላር ፈንድ ይፋ አድርጋለች፡፡ የዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ይፋ ያደረገው የመልሶ ግንባታ ፈንድ የሰላጤው ሀገራት የነዳጅ ማጣሪያዎችን ጨምሮ የኃይል መሠረተ ልማቶቻቸውን መልሰው በመገንባት የኃይል አቅርቦት ደህንነታቸውን እንዲያረጋግጡ ያስችላል…https://www.fanamc.com/archives/323014

Related Channels
Other channels in the same section of the catalogue.
