Latest posts

Ministry of Labor and Skills - Ethiopia
22 Sept, 06:51
በግብርና ዘርፍ ለወጣቶች ሰፊ የሥራ ዕድል ለመፍጠር የሚያስችል አበረታች ጅምርበሲዳማ ክልል የሥራና ክህሎት ቢሮ ከእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮና ከአጋር ተቋማት ጋር በመቀናጀት በግብርና ዘርፍ ለወጣቶች የሥራ ዕድልና የገቢ ምንጭ ለመፍጠር የሚያስችሉ ተግባራትን አከናውኗል።በዚህም በ10 ማህበራት ለተደራጁ 148 ወጣቶች የሥራ ዕድል ለመፍጠር በ32 ሚሊዮን ብር ወጪ 10 ትራክተሮች ተገዝተው ለተጠቃሚዎቹ ተላልፈዋል።ትራክተሮቹም የግብርና ሥራን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ለማስፋትና የወጣቶችን የሥራ ዕድል ለማሳደግ የሚያግዙ ናቸው።የመንግስትና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በትብብር መሥራት የወጣቶችን ተጠቃሚነት በማረጋገጥ ረገድ ወሳኝ መሆኑን የገለጹት የቢሮው አመራሮች፣ በISVCD ፕሮጀክት ድጋፍ የተገኙት ትራክተሮች የግብርና ዘርፉን ዘመናዊነት ከማሳደግ ባለፈ ለበርካታ ወጣቶች የሥራና የገቢ ዕድል እንደሚፈጥሩ ገልጸዋል።በፕሮጀክቱ ተጠቃሚ የሆኑ ወጣቶችም ከሙያዊ ስልጠናና ከተጨማሪ ድጋፍ በመጠቀም ወደ ሥራ እንዲገቡና ዘላቂ ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚያስችል አሠራር መዘርጋቱ ተጠቁሟል።ይህ ተግባር በሲዳማ ክልል የወጣቶችን የሥራ ዕድል ለማስፋት፣ የግብርና ምርታማነትን ለማሳደግና ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥ ከተወሰዱ ተግባራዊ እርምጃዎች መካከል የሚጠቀስ አመርቂ ሥራ መሆኑ ተገልጿል። መረጃው የክልሉ ሥራና ክህሎት ቢሮ ነው።መስከረም 13/2019 ዓ.ም፤ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
Ministry of Labor and Skills - Ethiopia
22 Sept, 06:44
በዓለም አቀፉ የክህሎት ውድድር ላይ የሚሳተፈው የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን የውድድር ዝግጅቱን ማጠናቀቁን አስታወቀየ48ኛው ዓለም አቀፍ የክህሎት ውድድር ከመስከረም 13–16 ቀን 2019 ዓ.ም በቻይና ሻንጋይ ይካሄዳል።በውድድሩ ላይ የሚሳተፈው የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድንም ሻንጋይ የገባ ሲሆን ለውድድሩ ሙሉ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን አስታውቋል፡፡በውድድሩ በ64 የሙያ አይነቶች ከ68 ከሀገራት የተወጣጡ 1380 በላይ ወጣቶች እንደሚሳተፉ የዓለም አቀፉ የክህሎት ውድድር መረጃ ያመለክታል፡፡በዓለም አቀፍ የክህሎት ውድድር የኢትዮጵያ የቴክኒክ ተወካይ ዶ/ር ሀፍቶም ገ/እግዚአብሔ እንደገለጹት፣ ውድድሩ የባለሙያዎቻችንን የክህሎት ብቃት በዓለም አቀፍ መድረክ ለማሳየትና ወጣቶች ወደ ሙያ እንዲገቡ ከማነሳሳት አኳያ ሚናው የላቀ ነው፡፡የሀገራችንን የክህሎት ልማት ሥርዓት ለማዘመን፣ ከዓለም አቀፍና ከኢንዱስትሪ መስፈርቶች ጋር ለማጣጣምም ዕድል የሚፈጥር እንደሆነ ገልፀው በውድድሩ ኢትዮጵያ በዘጠኝ የሙያ አይነቶች እንደምትሳተፍ ገልፀዋል፡፡በዓለም አቀፉ የክህሎት ውድድር የኢትዮጵያ ረዳት የቴክኒክ ተወካይ እና ተጠሪ በበኩላቸው አቶ አያሌው ሣህለ፤ የኢትዮጵያ ተሳትፎ በተወዳዳሪነት ብቻ ሳይሆን ባለሙያዎች በመዛኝነት ይሳተፋሉ፡፡ይህም የሀገራችንን የሙያ ሥልጠናና ምዘና ሥርዓታችንን ለማሻሻል ከፍተኛ አቅም የሚገኝበት መሆኑን አስረድተዋል፡፡ኢትዮጵያ እ.አ በ2024 የዓለም አቀፍ የክህሎት ውድድር ድርጅትን 88ኛ አባል ሀገር መሆኗ ይታወሳል፡፡ በዚያው ዓመት በፈረንሳይ ሊዮን በተካሄደው 47ኛው ዓለም አቀፍ የክህሎት
Ministry of Labor and Skills - Ethiopia
10 Sept, 21:00
እንኳን ለአዲሱ ዓመት በሰላም አደረሰን፣ አደረሳችሁ!


Ministry of Labor and Skills - Ethiopia
4 Sept, 17:45
የሲዳማ ክልል የሥራና ክህሎት ቢሮ የISO 9001:2015 ዓለም አቀፍ የጥራት ሰርተፊኬት አገኘየሲዳማ ክልል የሥራና ክህሎት ቢሮ የISO 9001:2015 ዓለም አቀፍ የጥራት ማኔጅመንት ሥርዓት ሰርተፊኬትን ከኢትዮጵያ ተስማሚነት ምዘና ድርጅት በይፋ ተረክቧል።ሰርተፊኬቱ እንደ ሀገር ለአንድ የክልል የሥራና ክህሎት ቢሮ የተሰጠ የመጀመሪያው መሆኑ ተገልጿል።የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ፣ ስኬቱ በክልሉ የመንግሥት ተቋማት ዘመናዊና ጥራት ያለው አገልግሎት የማስፈን ጥረትን የሚያፋጥን እና ለሌሎች ተቋማትም አርአያ የሚሆን መሆኑን ገልጸዋል።የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ነቢሃ መሀመድ በበኩላቸው፣ ሰርተፊኬቱ ቢሮው የጥራት አሠራሩን ለማጠናከር ያደረገውን ተነሳሽነት የሚያሳይ በመሆኑ፣ የተገኘውን ደረጃ በማስጠበቅ ለተገልጋዮች የተሻለ አገልግሎት እንዲሰጥ አሳስበዋል።የኢትዮጵያ ተስማሚነት ምዘና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ኢንጅነር ማዓዛ አበራ፣ ቢሮው የISO 9001:2015 መስፈርቶችን በአግባቡ በማሟላቱ ሰርተፊኬቱን ማግኘት መቻሉን ገልጸው፣ የተገኘውን የጥራት ደረጃ ለማስቀጠል ጥረቱ እንዲጠናከር አሳስበዋል።የቢሮው ኃላፊ ወ/ሮ ሀገረጽዮን አበበ ደግሞ ስኬቱ የተጠናከረ ቡድናዊ ሥራና ቀጣይነት ያለው ተቋማዊ ሪፎርም ውጤት መሆኑን ጠቅሰው፣ ሰርተፊኬቱ የተገልጋዮችን እርካታና የዜጎችን የሥራ ዕድልና የክህሎት ልማት ፍላጎት በተሻለ ደረጃ ለማሟላት ተጨማሪ ብርታት እንደሚሆን ገልጸዋል።ነሀሴ 29/2018 ዓ.ም፤ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር OffFacebookየሥራና ክህሎት ሚኒስቴር - ኢትዮጵያ / Ministry of Labor and Skills- Ethiopiaየሥራና ክህሎት ሚኒስቴር - ኢትዮጵያ / Ministry of Labor and Skills- Ethiopia. 246,394 likes · 7,198 talking about this. This is the Official Facebook Page of the Ministry of Labor and Skills of Ethiopia....
Ministry of Labor and Skills - Ethiopia
3 Sept, 17:56
በአምስት ዓመታት የልማት ጉዞ የተገኙ ውጤቶችን የበለጠ ማላቅየሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከሰኞ ነሐሴ 25 ጀምሮ ለተከታታይ አራት ቀናት ሲያካሄድ የቆየውን የአምስት ዓመታት የልማት ጉዞ የምክክር መድረክ ለዘርፉ ዕድገት አስተዋፅኦ ላበረከቱ ተጠሪ ተቋማት ፣ የክልል አስፈፃሚ አካላት፣ የስኪል ኢትዮጵያና ኢንተርፕራይዞች ዕውቅና በመስጠት ተጠናቋል፡፡አማራ ፣ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ፣ ድሬዳዋ አስተዳደር፣ ኦሮሚያና ሲዳማ ክልሎች፣ ድሬዳዋ አስተዳደርና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በዘርፉ ባስመዘገቡት ውጤት የዋንጫ ተሸላሚ ሆነዋል፡፡በዕውቅና እና ማጠቃለያ መድረኩ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ፣ አማካሪ ሚኒስትር ዴኤታ፣ ክብርት ነቢሃ መሃመድ በአምስት ዓመታት በዘርፉ የተገኙ ውጤቶችን በላቀ መልኩ ለማስቀጠል የሚያስችል ስንቅ ከመድረኩ መገኘቱን ጠቁመዋል፡፡በክህሎት ልማት ዘርፍ የስልጠና ደረጃና ጥራትን ለማሳደግ ፣ የተጀመሩ የዲጂታላይዜሽን ሥራዎችን ለማጠናከርና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሆኑ የክህሎት ባለቤቶችን በስፋት ለማፍራት የሚያስችሉ ጉልህ ተግባራት በትኩረት እንደሚከናወኑ ተናግረዋል፡፡ከሥራ ዕድል ፈጠራ አንፃር እንደ ሀገር ያለውን የሥራ ፍላጎት ምላሽ ለመስጠት በሚያስችል መልኩ በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር ለዜጎች ሰፊ የሥራ ዕድል ለመፍጠር የሚያስችሉ ሥራዎች በቀጣይ እንደሚሰሩም ጠቁመዋል፡፡በኢንዱስትሪ ሰላምና ጤንነት ላይ የሚታዩ ችግሮችን በመሰረታዊነት ለመፍታት ፣የምክክር ሥርዓትን በአግባቡ ማሳለጥ እንደሚገባም አሳስበዋል ።በተቋም ግንባታ አስቀድመው የተጀመሩFacebookየሥራና ክህሎት ሚኒስቴር - ኢትዮጵያ / Ministry of Labor and Skills- Ethiopiaየሥራና ክህሎት ሚኒስቴር - ኢትዮጵያ / Ministry of Labor and Skills- Ethiopia. 246,394 likes · 7,198 talking about this. This is the Official Facebook Page of the Ministry of Labor and Skills of Ethiopia....
Ministry of Labor and Skills - Ethiopia
2 Sept, 14:14
“የኢትዮጵያ ማንሰራራት”የ2018 ዓ.ም. የጳጉሜን ቀናት “የኢትዮጵያ ማንሰራራት” በሚል መሪ ሀሳብ ይከበራሉ።የዘንድሮ የጳጉሜን ቀናት ኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች ያስመዘገበቻቸውን እመርታዎች ለመዘከር፣ የማንሰራራቷን ጉዞ ለማጉላት እና የተሻለ ነገን ለመገንባት ያለንን የጋራ ተስፋና ቁርጠኝነት ለማጠናከር የተዘጋጁ ናቸው። እያንዳንዱ የጳጉሜን ቀን የራሱ ልዩ ትርጉምና ዓላማ አለው።🟢 ጳጉሜን 1 — የእመርታ ቀንጳጉሜን 1 ኢትዮጵያ ከአዝጋሚ የዕድገት ጉዞ በመውጣት በተለያዩ ዘርፎች ያስመዘገበቻቸው እመርታዎች የሚዘከሩበት ቀን ነው።በግብርና፣ በኢንዱስትሪ፣ በገቢ አሰባሰብ፣ በዕዳ ቅነሳ፣ በቱሪዝምና በውጭ ምንዛሬ ዘርፎች የተመዘገቡ እመርታዎች ይወሳሉ።🔵 ጳጉሜን 2 — የማንሰራራት ቀንጳጉሜን 2 ኢትዮጵያ ወደ ሁለንተናዊ ልማት የተሸጋገረችበትን፣ ከጎታች ማነቆዎች በመውጣት የማንሰራራቷን ጉዞ የሚያሳዩ ሁነቶች የሚቀርቡበት ቀን ነው።በኢኮኖሚ፣ በታዳሽ ኃይል፣ በከተሞች ገጽታና በገጠር ኮሪደር ልማት የተገኙ ውጤቶች ይገለጣሉ።🔴 ጳጉሜን 3 — የፅናት ቀንFacebookየሥራና ክህሎት ሚኒስቴር - ኢትዮጵያ / Ministry of Labor and Skills- Ethiopiaየሥራና ክህሎት ሚኒስቴር - ኢትዮጵያ / Ministry of Labor and Skills- Ethiopia. 246,394 likes · 7,198 talking about this. This is the Official Facebook Page of the Ministry of Labor and Skills of Ethiopia....
Ministry of Labor and Skills - Ethiopia
2 Sept, 14:14



Ministry of Labor and Skills - Ethiopia
2 Sept, 13:06
ከፈጠራ ሀሳብ ወደ ገበያ፦ ለስታርታፖች የሚያስፈልግ ምቹ ምህዳርአቤል ማስረሻ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በነበረው ቆይታ፣ የአካል ጉዳተኛ ጓደኛው ይገጥመው የነበረውን ፈታኝ ሁኔታ በመነሳት፣ የመንቀሳቀስ ችግር ላለባቸው ወገኖች መፍትሄ የሚሆን የኤሌክትሪክ ዊልቼር ፈጥሯል።ይህ ሀሳብ ወደ ተግባር ሊሸጋገር የቻለው የአቤል ንድፈ ሀሳብ እውቀትን ከተግባራዊ ክህሎት ጋር በማጣመር ነው።እንደ አቤል ማብራሪያ መሰል የፈጠራ ሥራዎች ወደ ዘላቂ ንግድ እንዲሸጋገሩ ፋይናንስ፣ የማምረቻ ቦታ፣ ጥሬ ዕቃ፣ የገበያ ትስስር፣ እንዲሁም ቀልጣፋ ሕግና አሠራር አይነተኛ ሚና ይጫወታሉ።የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የአምስት ዓመት የልማት ጉዞ የምክክር ጉባኤ ላይ አቤልን ጨምር ውጤታማ የሆኑ ሥራ ፈጣሪዎች የተሳተፉበት የፓናል ውይይት «ከሥልጠና ወደ ሥራ፣ ከፈጠራ ሀሳብ ወደ ንግድ ልማት» በሚል ርዕስ ተካሂዷል።ወጣቶች ፈጠራቸው ወደ ምርት፣ ምርታቸው ወደ ገበያ፣ ገበያቸውም ወደ ዘላቂ ንግድ የሚሸጋገርበትን ምቹ ምህዳር መፍጠር የሁሉም ባለድርሻ አካላት ቅንጅት ይፈልጋል።በቴክኒክና ሙያ ተቋማት የሚገኘው ተግባራዊ ክህሎት በስታርታፕ ምህዳር በተገቢው ሁኔታ ከተደገፈ፣ የወጣቶች ፈጠራ ከግል ስኬት ባሻገር ለሀገራዊ ኢኮኖሚ ዕድገትና ለሥራ ዕድል ፈጠራ ጉልህ አስተዋፅኦ ሊያበረክት እንደሚችል በውይይቱ ላይ በስፋት ተነስቷል፡፡ነሀሴ 27/2018 ዓ.ም፤ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር Official Website: mols.gov.et Facebook: https://web.facebook.com/MolsFFacebookየሥራና ክህሎት ሚኒስቴር - ኢትዮጵያ / Ministry of Labor and Skills- Ethiopiaየሥራና ክህሎት ሚኒስቴር - ኢትዮጵያ / Ministry of Labor and Skills- Ethiopia. 246,394 likes · 7,198 talking about this. This is the Official Facebook Page of the Ministry of Labor and Skills of Ethiopia....
Ministry of Labor and Skills - Ethiopia
2 Sept, 07:37
# አሁን የአምስት ዓመት ጉዞ ቅኝት የፓናል ውይይትየሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የአምስት ዓመት የልማት ጉዞውን አስመልክቶ እያካሄደው የሚገኘው የምክክር መድረክ በሦስተኛ ቀን ውሎውበዘርፉ ፖሊሲ፣ ተቋማዊ እሳቤና የሥርዓት እይታ ላይ ያተኮረ የፓናል ውይይትን እያስተናገደ ይገኛል፡፡የውይይት መድረኩን በንግግር የከፈቱት የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ፣ አማካሪ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ነቢሃ መሃመድ ያለፉት አምስት ዓመታት ዘላቂ አሰራሮችን በሥርዓታዊ እይታ ለመገንባት ጥረት የተደረገበት ጉልህ የመሸጋገሪያ ወቅት እንደነበር ገልፀዋል፡፡በአምስት ዓመት ጉዞ ውስጥ በርካታ አወንታዊ ውጤቶችን ማስመዝገብ መቻሉን የገለፁት ክብርት ሚኒስትር ዴኤታዋ ወደፊት ዘርፉ የሚጠበቅበትን ግቦች ለማሳካት ደግሞ ጥልቅ ግምገማና ተከታታይ ማሻሻያ ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ ውይይቱ ተዘጋጅቷል ብለዋል፡፡የፖሊሲውን ውጤታማነት መፈተሸና ባለፉት አመታት በተጨባጭ የተሠሩ ሥራዎችን መገምገም የውይይቱ ዋንኛ ትኩረት መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡ነሀሴ 27/2018 ዓ.ም፤ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር Official Website: mols.gov.et Facebook: https://web.facebook.com/MolsFDRE Telegram: https://t.me/FDRE_MoLSofficial TikTok: tiktok.com/@mols_official Twitter / X: twitter.com/Jobs_ሚኒስቴር WhatsApp: whatsapp.com/channel/0029VakCgcYIFacebookየሥራና ክህሎት ሚኒስቴር - ኢትዮጵያ / Ministry of Labor and Skills- Ethiopiaየሥራና ክህሎት ሚኒስቴር - ኢትዮጵያ / Ministry of Labor and Skills- Ethiopia. 246,394 likes · 7,198 talking about this. This is the Official Facebook Page of the Ministry of Labor and Skills of Ethiopia....
Ministry of Labor and Skills - Ethiopia
30 Aug, 14:13
የዘርፉ የአምስት ዓመታት የልማት ጉዞ ሀገር አቀፍ ጉባኤ ነገ ይጀምራልየሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የዘርፉን የአምስት ዓመታት የልማትና የሪፎርም ጉዞ በመገምገም፣ የቀጣይ የልማት ዘመን አቅጣጫዎችን የሚያስቀምጥበት ሀገር አቀፍ ጉባኤ ነገ በአዲስ አበባ መካሄድ ይጀምራል።ለአራት ተከታታይ ቀናት በሚቆየው በዚህ ሀገር አቀፍ መድረክ፣ ባለፉት አምስት ዓመታት በዘርፉ የተከናወኑ ዋና ዋና የልማት ሥራዎች በጥልቀት ይገመገማሉ፤ በዘርፉ አንኳር ጉዳዮች ዙሪያም የፓናል ውይይቶች ይካሄዳሉ።ከዚሁ ጎን ለጎን የክህሎት ኢትዮጵያ የሁለተኛው ዙር (2.0)ማጠቃለያ እና የቀጣዩ ዙር ይፋዊ ማብሰሪያ መርሃ ግብር እንዲሁም የቴክኖሎጂ ኤክስፖ ይካሄዳል።በኤክስፖው ሁለተኛው ዙር የክህሎት ኢትዮጵያ መርሃ ግብር ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ በመርሃ ግብሩ በታቀፉ ወጣቶች የተሰሩ፣ ችግር ፈቺ የሆኑና ወደ ምርትና አገልግሎት የተሸጋገሩ ውጤታማ ቴክኖሎጂዎች ለእይታ ይቀርባሉ።እንዲሁም ባለፉት አምስት ዓመታት በተተገበረው የክህሎት መር የሥራ ዕድል ፈጠራ አቅጣጫ ውጤት ያመጡና ማሳያ የሆኑ ኢንተርፕራይዞችና ሥራ ፈጣሪዎች፣ እንዲሁም የተመረጡ የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ምርትና አገልግሎቶቻቸውን ያስተዋውቃሉ።ጉባኤው ያለፉትን አምስት ዓመታት የሚዘክር ብቻ ሳይሆን፣ የተገኙ ውጤቶችን መነሻ በማድረግ የቀጣይ ዘመን የሥራ አቅጣጫዎችን የሚያስቀምጥ፣ ክህሎትን ከሥራ፣ ከፈጠራ፣ ከቴክኖሎጂ እና ከባለድርሻና አጋር አካላት ጋር የሚያስተሳስር ሀገር አቀፍ መድረክ ነው።በጉባኤው የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የዘርፉ ባለድርሻና አጋርFacebookየሥራና ክህሎት ሚኒስቴር - ኢትዮጵያ / Ministry of Labor and Skills- Ethiopiaየሥራና ክህሎት ሚኒስቴር - ኢትዮጵያ / Ministry of Labor and Skills- Ethiopia. 246,394 likes · 7,198 talking about this. This is the Official Facebook Page of the Ministry of Labor and Skills of Ethiopia....
Ministry of Labor and Skills - Ethiopia
28 Aug, 04:06
ሥራ ፈጣሪ እና ብቁ ዜጎችን ለማፍራት ያለመ የፋዌ (FAWE) የሁለተኛ ዙር ተማሪዎች ዓመታዊ ጉባኤ ተካሄደየሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አጋር የሆነው Forum for African women educationalist (FAWE) ከማስተርካርድ ፋውንዴሽን ጋር በመሆን የሁለተኛ ዙር የትምህርትና ስልጠና ፕሮግራም ተጠቃሚዎችን ዓመታዊ ጉባኤ አካሄደ፡፡ጉባኤው ትምህርት ፈልገው አቅም ላጡ ወጣቶች፣ ለሴቶች፣ ለአካል ጉዳተኞች፣ ለተፈናቃዮች እና ለስደተኞች በቴክኒክና ሙያ ተቋማት ገብተው ስልጠና እንዲያገኙ ማስቻልን ዓላማ ያደረገ ነው፡፡በዚሁ መሠረት በፕሮግራሙ ከታቀፉ 396 ተማሪዎች መካከል 326ቱ ሴቶች፣ 60ቹ በተለያዩ ምክንያቶች የተፈናቀሉ እና 40 የሚሆኑት ደግሞ የተለያዩ የአካል ጉዳት ያለባቸው ተማሪዎች መሆናቸው ተገልጿል፡፡በመክፈቻ መርሃ-ግብሩ ላይ የተገኙት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሥልጠናና የተቋማት አቅም ግንባታ መሪ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሙሁዲን አባሞጋ እንደገለጹት፤ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከአለም አቀፍ አጋር አካላት ጋር በቅንጅት እየሰራ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ ከእነዚህም መካከል FAWE አንዱ መሆኑን አንስተዋል፡፡ተማሪዎቹ በቴክኒክና ሙያ ተቋማት ስልጠና አግኝተው የተሻለ የሥራ ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማስቻል ከፌዴራል እስከ ክልል ሥራና ክህሎት ቢሮዎች የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመው በትብብር እየሰሩ እንደሚገኙም አስረድተዋል፡፡ተማሪዎቹ በመጪው ጊዜ ሥራ ፈጣሪ፣ ብቁ ተወዳዳሪ፣ ትጋት የተሞላባቸው እና ለሀገር የሚጠቅሙ ዜጎች እንዲሆኑ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አስፈላጊውን ትብብር እንደሚያደርግምFacebookየሥራና ክህሎት ሚኒስቴር - ኢትዮጵያ / Ministry of Labor and Skills- Ethiopiaየሥራና ክህሎት ሚኒስቴር - ኢትዮጵያ / Ministry of Labor and Skills- Ethiopia. 246,394 likes · 7,198 talking about this. This is the Official Facebook Page of the Ministry of Labor and Skills of Ethiopia....
Ministry of Labor and Skills - Ethiopia
14 Aug, 04:27
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የ2018 በጀት ዓመት የአሠሪና ሠራተኛ ዘርፍ አፈጻጸምን ገመገመየሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የ2018 በጀት ዓመት የአሠሪና ሠራተኛ ዘርፍ አፈጻጸምን በጋራ ገምግሟል።በመድረኩ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል፣ የአሠሪና ሠራተኛ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ዳንኤል ተሬሳን ጨምሮ የዘርፉ አመራሮችና ባለሙያዎች ተገኝተዋል።በመድረኩ በሚኒስትር ዴኤታው ክቡር አቶ ዳንኤል ተሬሳ የቀረበውን ሪፖርት መሠረት በማድረግ ሰፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን፣ በበጀት ዓመቱ የተገኙ ውጤቶች፣ ያጋጠሙ ተግዳሮቶች እና የቀጣይ የትኪረት አቅጣጫዎች ላይ ሰፊ ውይይት ተካሂዷል።ነሀሴ 8/2018 ዓ.ም፤ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር Official Website: mols.gov.et Facebook: https://web.facebook.com/MolsFDRE Telegram: https://t.me/FDRE_MoLSofficial TikTok: tiktok.com/@mols_official Twitter / X: twitter.com/Jobs_ሚኒስቴር WhatsApp: whatsapp.com/channel/0029VakCgcYIFacebookየሥራና ክህሎት ሚኒስቴር - ኢትዮጵያ / Ministry of Labor and Skills- Ethiopiaየሥራና ክህሎት ሚኒስቴር - ኢትዮጵያ / Ministry of Labor and Skills- Ethiopia. 246,394 likes · 7,198 talking about this. This is the Official Facebook Page of the Ministry of Labor and Skills of Ethiopia....
Ministry of Labor and Skills - Ethiopia
13 Aug, 11:36
ፅናትን፣ ትጋትንና ጥንካሬን የተላበሱ ወጣቶች የስኬት መንገድበደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ ኮንሶ ዞን፣ ካራት ከተማ ነዋሪ የሆነው ወጣት መንግስቱ ለጋ ከአመታት በፊት ነበር በኢንጂነሪንግ የትምህርት መስክ የተመረቀው፡፡ በተማረው ትምህርት ሥራ አለማግኘቱ ወደ ተስፋ መቁረጥ እንዲያመራው አልፈቀደም፡፡ከመሰል ጓደኞቹ ጋር በጋራ በመደራጀት "ኤግሊስ የእንቁላል ጣይ ዶሮ እርባታ ማህበር "ን አቋቋሙ፡፡ የማህበሩ ሰብሳቢ የሆነውን ወጣት መንግስቱ ለጋን ጨምሮ 6 አባላት ባዋጡት 6 መቶ ሺህ ብር ወደ ስራ የገባዉ የኤግል የእንቁላል ጣይ ዶሮ ማህበር ዛሬ ላይ የ6ሚሊዮን ብር ካፒታል ባለቤት ለመሆን በቅቷል።በማህበሩ ጊዜአዊ የሥራ ዕድል የተፈጠረላቸዉ አራት አባላት የተሻለ ገቢ ማመንጨት የቻሉ ሲሆን በተፈጠረላቸዉ የሥራ ዕድል ደስተኛ መሆናቸዉንም ይናገራሉ።1,600 እንቁላል ጣይ የ45 ቀን ጫጩትና እንቁላል በመጣል ላይ ያሉ 2000 ዶሮዎችን በማርባት ላይ የሚገኝ ማህበር በዋናነት የእንቁላል ምርትን ለትምህርት ቤቶችና ለተጠቃሚ ማህበረሰብ እያቀረበ ይገኛል፡፡ማህበሩ በቀጣይ ተጨማሪ የዶሮ ማርቢያ ሼድ በመገንባት የእንቁላል ጣይ ዶሮዎችን በስፋት የማምረትና ከእንቁላል ምርት በተጨማሪ የወተት ላም በማርባት ወተትና የወተት ተዋፅኦ ምርቶችን ለተጠቃሚ ማህበረሰብ የማቅረብ ዕቅድ እንዳለው አባላቱ ይገልፃሉ፡፡‹‹ችግርን ፈርቶ ሳይሆን በፅናትና ደጋግሞ በመሞከር ወደ ስኬት መድረስ ይቻላል›› የሚለው ወጣት መንግስቱ ወጣቶች የአካባቢያቸውን ፀጋ ተጠቅመው የራሳቸውን ሥራ ለመፍጠርና ህይወታቸውን ለመቀየር ትጋትና ጥንካሬንFacebookየሥራና ክህሎት ሚኒስቴር - ኢትዮጵያ / Ministry of Labor and Skills- Ethiopiaየሥራና ክህሎት ሚኒስቴር - ኢትዮጵያ / Ministry of Labor and Skills- Ethiopia. 246,394 likes · 7,198 talking about this. This is the Official Facebook Page of the Ministry of Labor and Skills of Ethiopia....
Ministry of Labor and Skills - Ethiopia
8 Aug, 07:26
ለኢንዱስትሪው ፍላጎት የተጣጣመ የቴክኒክና ሙያ ሥልጠናን ለመገንባት የሚያስችል ጠንካራ የአጋርነት መድረክ ተመሠረተበየዓመቱ ከ2 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች ወደ ሥራው ዓለም የሚቀላቀሉ ቢሆንም፣ ከግማሽ ሚሊዮን ያነሱት ብቻ ናቸው የክህሎት ሥልጠና የማግኘት ዕድል ያላቸው።የሥልጠና ዕድሉን አግኝተው ከሚመረቁት መካከልም ቢሆን፣ የቴክኒክና ሙያ ተቋማት የሚሰጡት ሥልጠና ከኢንዱስትሪው እውነተኛ የሰው ኃይል ፍላጎት ጋር አለመጣጣሙ ለሥራ ዕድል ፈጠራ፣ ለምርታማነትና ለንግድ ተወዳዳሪነት ትልቅ ማነቆ ሆኖ ቆይቷል።ይህንን መዋቅራዊ ችግር በመፍታት የሥልጠና ሥርዓቱ የሥራ ገበያውን እውነተኛ ፍላጎት ያገናዘበ እንዲሆን ለማድረግ በግል ባለሀብቶች፣ በቴክኒክና ሙያ ተቋማት እና በፖሊሲ አውጪዎች መካከል ጠንካራ አጋርነት መፍጠር ወሳኝ መሆኑ ታምኖበታል።ይህንን ዓላማ ስኬታማ ለማድረግም የኢትዮ-ጀርመን የዘላቂ ሥልጠናና ትምህርት ፕሮግራም (STEP IV) በክህሎት ልማት ዘርፍ ያለውን ትብብር ለማጠናከር የሚያስችል የምክክር መድረክ ዋና ዋና የመንግሥትና የግል ዘርፍ ባለድርሻ አካላትን በባህር ዳር ከተማ አሰባስቧል።በተካሄደው የምክክር መድረክም በመንግሥት ተቋማት፣ በቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች፣ በኢንዱስትሪዎች፣ በኩባንያዎች እና በንግድ ማህበራት መካከል በተግባር ላይ የተመሠረተ የሥራ ላይ ሥልጠና (Cooperative Training) ትስስርን የሚያጠናክር "የአማራ ክልል የቴክኒክና ሙያ የትብብር ሥልጠና ፎረም “ እንዲመሠረት ተደርጓል።በአማራ ክልል የሥራና ክህሎት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አማረTelegramMinistry of Labor and Skills - EthiopiaFDRE, Ministry of Labor and Skills
Ministry of Labor and Skills - Ethiopia
6 Aug, 06:26
የዘርፉን አዲስ እሳቤ በውጤታማነት ለመተግበር የሚስችል አቅም መፍጠርን ያለመ ስልጠናየአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፣የሥራና ክህሎት ቢሮ ከክልል፣ ከዞን፣ ከወረዳና ከቴክኒክና ሙያ ተቋማት ለተውጣጡ የዘርፉ አመራሮችና ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት ጀመረ፡፡በጣልያን ፕሮጀክትና በሴቭ ዘ ችልድረን የፋይናንስ ድጋፍ የተዘጋጀው ይህ ስልጠና በዘርፉ አዲስ እሳቤ፣ በባዮሜትርክስ ምዝገባና በዕቅድና ሪፖርት ዝግጅት ላይ ያተኩራል፡፡መድረኩን በንግግር የከፈቱት የአፋር ክልል፣ የሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ አህመድ ኢብራሂም ስልጠናው በዋነኛነት በየእርከኑ የሚገኙ አመራርና ባለሙያዎች የዘርፉን አዲስ እሳቤ በውጤታማነት ለመተግበር የሚስችላቸውን አቅም ለማጎልበት ያለመ መሆኑን ተናግረዋል፡፡በክልሉ በሚገኙ 30 የሥራ ማዕከላት የሥራ ፈላጊዎች የባዮ ሜትሪክስ ምዝገባ በመካሄድ ላይ እንደሚገኝ የገለፁት ቢሮ ኃላፊው የምዝገባ ሂደቱን በሚጠበቀው ደረጃ ሙሉ ለሙሉ ዲጂታላይዝ ለማድረግ የሚያስችል ዕውቀትን ቢሮው ተደራሽ ለማድረግ እየሠራ እንደሚገኝ አስረድተዋል፡፡በሥራና ክህሎት ዘርፍ በሀገር ዓቀፍ ደረጃ የተያዙ ግቦች እንዲሳኩ የሚከናወኑ ተግባራት ሁሉ ከዕቅድ ዝግጅት የሚጀምሩ እንደመሆናቸው ‹‹አንድ ዕቅድ፣ አንድ ሪፖርት›› የሚለውን የሚኒስቴር መ/ቤቱን መርህ ለመተግበርና የመረጃ ጥራትን ለማረጋገጥ ስልጠናው ጉልህ ሚና አንደሚኖረው ተመላክቷል፡፡የሥራ ማዕከላትን ለማጠናከር በተጀመሩ ሰፋፊ የሪፎርም ተግባራት ወጣቶችን ከአዳዲስ የሥራ ዕድል ዕድሎች ተጠቃሚ ለማድረግ የሚያስችሉ ተስፋ ሰጪ ለውጦችTelegramMinistry of Labor and Skills - EthiopiaFDRE, Ministry of Labor and Skills
Ministry of Labor and Skills - Ethiopia
5 Aug, 08:46edited
የበጎ ፈቃድና የልማት ሥራዎች ሕዝባዊ ትስስርን የሚያጠናክሩ ናቸው፡፡ክቡር ተሻለ በሬቻ(ዶ/ር) የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታየበጎ ፈቃድና የልማት ሥራዎች ቁሳቁሳዊና የመሠረተ ልማት ፋይዳ ከማስገኘታቸው ባሻገር በማህበረሰቡ መካከል የሚፈጥረው የእርስ በእርስ መተዋወቅ፣ ትስስርና አገራዊ ፍቅር ትልቅ መሆኑ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ተሻለ በሬቻ (ዶ/ር) ገለጹ።ሚኒስትር ዴኤታው በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል በቤንች ሸኮ እና በሸካ ዞኖች እየተከናወነ የሚገኘውን የክረምት የበጎ ፈቃድና የልማት መርሃ ግብር አስመልክተው መግለጫ ሰጥተዋል።ክቡር ተሻለ በሬቻ (ዶ/ር) በሰጡት መግለጫ፤ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ከአንድ አካባቢ ወደ ሌላ አካባቢ በመንቀሳቀስ የባህልና የልማት እቅዶችን ለመገንዘብ እንዲሁም የሕዝቦች እርስ በእርስ ትስስርንና አገራዊ ፍቅርን ለማጠናከር ከፍተኛ ሚና የሚጫወት ባህል እየሆነ መምጣቱን ገልጸዋል።በተከናወኑት ተግባራትም በአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በቤንች ሸኮ እና በሸካ ዞኖች እያንዳንዳቸው 10 ሺህ፣ በድምሩ 20 ሺህ የቡና ችግኞች መተከላቸውን ተናግረዋል።በተመሳሳይ በሁለቱም ዞኖች እያንዳንዳቸው 15 ሚሊዮን ብር፣ በድምሩ 30 ሚሊዮን ብር ገደማ ወጪ የሚደረግባቸው ሁለት የቅድመ-አንደኛ ደረጃ (ኪንደርጋርተን) ትምህርት ቤቶች ግንባታ ለማስጀመር የመሠረተ ድንጋይ መቀመጡ ጠቁመዋል።ከዚህ በተጨማሪ አቅም ለሌላቸው ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ የመስጠት መርሃ ግብር የተከናወነ ሲሆን፤ በቤንች ሸኮ እና በሸካ ዞኖች ከ400 በላይ


Ministry of Labor and Skills - Ethiopia
3 Aug, 17:47
ከመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት የተሰጠ መግለጫስንትባበር ምን ማድረግ እንደምንችል ደጋግመን ለዓለም ያሳየንበት የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ዛሬም በድል ተጠናቋል።ኢትዮጵያ የሚለው ስም በጋራ የመቻልና የጽኑ አቋም ተምሳሌት ነው። መንግሥት የሀገሪቱን ዘላቂ ጥቅም ለማረጋገጥ የሚያስፈልጉ ስትራቴጂካዊ አቅጣጫዎችን ሲያስቀምጥ፣ የኢትዮጵያ ሕዝብም ሀገራዊ ፍላጎቱን በጋራ ተነሣሽነት እውን የማድረግ የዘመናት ልምምድ አለው። በተለይም መንግሥት ለአረንጓዴ ልማትና ሀገራዊ ከፍታ ለሚያቀርበው ጥሪ ሕዝቡ በላቀ ተሳትፎ ምላሽ የመስጠት ቁርጠኝነቱ ለዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ አብነት የሚሆን ነው።መንግሥት በኢትዮጵያ የተራቆቱ አካባቢዎች በልጆቿ ብርቱ እጆች እንዲታከሙ፣ እየተስፋፋ የመጣው ድርቅና በረሃማነት በዘላቂነት እንዲገታ እና በአስተማማኝ መሠረት ላይ የተገነባ አረንጓዴ ኢኮኖሚ እውን እንዲሆን ግልጽና ጽኑ አቋም በመያዝ ጥሪ ሲያቀርብ ቆይቷል። በዚህም በላቀ የሕዝብ ተሳትፎና በመንግሥት መሪነት ታላቁን የሕዳሴ ግድብ እውን ማድረግ ተችሏል፤ ኢትዮጵያዊያን ዛሬ ላይ ምድራቸውን አረንጓዴ ማልበስ ባህላቸው አድረገውታል ፤ባለፉት ሰባት ዓመታት ብቻ በአረንጓዴ ዐሻራ ንቅናቄ ከ48 ቢሊዮን በላይ ችግኞች ተተክለው ኢትዮጵያ አረንጓዴ ሸማ ለብሳለች። ዘንድሮም በንቅናቄው 8ኛው ዓመት በአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን ችግኞችን፣ በክረምቱ ደግሞ በአጠቃላይ 8 ቢሊዮን ችግኞችን ለመትከል መንግሥት ቁርጠኛ አቋሙን በይፋ አሳውቋል።ለመንግሥት ሀገራዊ ጥሪ ቀናኢ የሆኑ ውድ የኢትዮጵያ ልጆችም ይህንን ጥሪ በሙሉ
Ministry of Labor and Skills - Ethiopia
3 Aug, 15:43
ኢትዮጵያ በአንድ ጀምበር 805.3 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል ለአፍሪካ ተምሳሌት ሆናለች - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)ኢትዮጵያ በአንድ ጀምበር 805.3 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል ለአፍሪካ ተምሳሌት መሆኗን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የአንድ ጀምበር የ800 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል ሀገራዊ መርሐ ግብር አፈጻጸምን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ፤ ኢትዮጵያ በያዘችው እቅድ መሰረት በአንድ ቀን ብቻ 805.3 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል ታሪካዊ ስኬት አስመዝግባለች ብለዋል።በዚህም ሀገራችን ከራሷ አልፋ ለመላው አፍሪካ ታላቅ ምሳሌ መሆን መቻሏን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አብስረዋል፡፡በዚህ ደማቅ ሀገራዊ የችግኝ ተከላ ንቅናቄ ላይ 26.2 ሚሊዮን ዜጎች በነቂስ ወጥተው እጅግ ከፍተኛ እና የነቃ ተሳትፎ ማድረጋቸውን በመግለጫቸው አብራርተዋል፡፡ኢትዮጵያውያን ላሳዩት አስደናቂ ርብርብ እና ቁርጠኝነት አድናቆታቸውን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ በዚሁ የአንድ ጀምበር ተሳትፎ 291.4 ሺህ ሄክታር መሬት የአረንጓዴ ዐሻራ መልበስ መቻሉን አስታውቀዋል፡፡


Ministry of Labor and Skills - Ethiopia
3 Aug, 15:37edited
በዛሬው የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር 805.3 ሚሊየን ችግኞች የተተከሉ ሲሆን፣ 26.2 ሚሊየን ሰዎች ተሳትፈዋል፤ በዚህም 291.4 ሺህ ሄክታር መሬት ተሸፍኗል።


Ministry of Labor and Skills - Ethiopia
3 Aug, 12:03
የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር አረንጓዴ አካባቢን ከመፍጠር ባሻገር ለወጣቶችና ሴቶች የሥራ ዕድልና የገቢ ምንጭ በመፍጠር የዜጎችን ተጠቃሚነት በማሳደግ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ ነው።ክቡር ዶ/ር ተሻለ በሬቻ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታየሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የ2018 ዓ.ም በአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል ሀገራዊ ዘመቻ አካል በመሆን፣ "ተስፋን እንትከል!" በሚል መሪ ሀሳብ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር እያካሄደ ይገኛል፡፡በመርሃ ግብሩ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታዎች ክቡር ዶ/ር ተሻለ በሬቻ እና ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካን ጨምሮ የክልሉ፣ የዞንና ወረዳው አመራሮች፣ የግብርና ኮሌጆች ከፍተኛ ኃላፊዎች፣ የሚኒስቴሩ አመራርና ሠራተኞች እንዲሁም የአካባቢው ህብረተሰብ በንቃት እየተሳተፉ ይገኛል፡፡የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ተሻለ በሬቻ በመርሃ ግብሩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ኢትዮጵያ ባለፉት ስምንት ዓመታት በአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ከ48 ቢሊዮን በላይ ችግኞችን መትከል መቻሏን ጠቅሰው፣ ዘንድሮም ወደ 56 ቢሊዮን ችግኞች ለማድረስ ግብ ተይዞ እየተሠራ መሆኑን ገልጸዋል።ክቡር ዶ/ር ተሻለ አክለውም የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር አረንጓዴ አካባቢዎችን በመፍጠር፣ አረንጓዴ ኢኮኖሚን በመገንባት፣ የፍራፍሬ ልማትን በማስፋፋት፣ የውጭ ምንዛሬ በማሳደግ እና ለCOP32 የኢትዮጵያን ዝግጁነት በማጠናከር ትልቅ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን ገልጸዋል።በተለይም የቡና፣ የአቮካዶና ሌሎች የፍራፍሬ ልማቶች ለወጣቶችናFacebookየሥራና ክህሎት ሚኒስቴር - ኢትዮጵያ / Ministry of Labor and Skills- Ethiopiaየሥራና ክህሎት ሚኒስቴር - ኢትዮጵያ / Ministry of Labor and Skills- Ethiopia. 246,394 likes · 7,198 talking about this. This is the Official Facebook Page of the Ministry of Labor and Skills of Ethiopia....
Related Channels
Other channels in the same section of the catalogue.
