Latest posts

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴
21 Sept, 09:38
ሂጃብ እንደ ደመና ነው ጨረቃዋን ይሸፍናታል እንጂ ብርሀኗን አያጠፋውም።
𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴
20 Sept, 14:35
የሞኝ ቀልድ አትቀልድ! ~ በጩቤ፣ በዱላ፣ በመጥረቢያ፣ በመኪና፣ በጦር፣ በጠመንጃ፣ በሰይፍ፣ … ሰዎች ለማስደንገጥ ከመቀለድ፣ ከመቃጣት ተጠንቀቅ። ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል:– من أشار إلى أخيه بحديدة فإن الملائكة تلعنه حتى ينتهي. "ወደ ወንድሙ በመሳሪያ የጠቆመ እስከሚታቀብ ድረስ መላእክት ይረግሙታል።" [ሙስሊም]በሌላም ሐዲሥ እንዲህ ብለዋል:– لا يحل لمسلم أن يروع مسلماً. "ሙስሊም ሙስሊምን ሊያስደነግጥ አይፈቀድለትም።" አልባኒይ ሶሒሕ ብለውታል።ሸይኽ ኢብኑ ዑሠይሚን ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ:– "አንድ ሰው የምሩንም ይሁን በቀልድ ወደ ወንድሙ ጠመንጃ ሊያዞር አይፈቀድለትም። መኪናም እንዲሁ (አይፈቀድም)። የከፋ ነውና።" [ሸርሑ ሶሒሒል ቡኻሪ: 9/ 502] ኢብኑ ሙነወር
𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴
19 Sept, 15:06edited
Even if we bought a car in 100 ብር በእናታችን እይታ ተበልተናል ተሸውደናል 😭
𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴
18 Sept, 06:34
ይሄ ወጣት ወደ አኼራ ሄዷል ቁርአኑን ስሙለት🥹
𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴
18 Sept, 06:05
🔖 ሸይኽ ሱሌይማን አሩሀይሊይ(ሀፊዘሁላህ) እንዲህ ይላሉ፦አንድ ሰው ልብሱን አውልቆ በሚራቆት ሰዓት ፦ "ቢስሚላህ" ይበል። ይህን በማለቱ ከሽይጣኖች እና ከጂኖች ዐይን መከለያ ይሆንለታል።"ሸርሁ አልወሲየቱ አሱግራ
𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴
16 Sept, 16:58

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴
16 Sept, 16:55

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴
16 Sept, 08:55
ኢብኑ ዑሠይሚን እንዲህ ይላሉ፦«فَمِنَ السَّفَهِ أَنْ تَأْتِيَ إِلَى قَبْرِ إِنْسَانٍ صَارَ رَمِيمًا، تَدْعُوهُ وَتَعْبُدَهُ، وَهُوَ بِحَاجَةٍ إِلَى دُعَائِكَ»."አካሉ ብስባሽ ወደ ሆነ ሰው ቀብር ሄደህ እርሱን መለመንህ እና እርሱን ማምለክህ ከሞኝነት ነው። እርሱኮ ያንተ ዱዓእ የሚያስፈልገው ነው።"[አልቀውሉል ሙፊድ ፡ 1/77
𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴
14 Sept, 20:05
ሼመኛ መጨረሻው ፀፀት ነው
𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴
14 Sept, 12:20
forwarded from @arisalah_charity
በቪድዮ😊
𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴
13 Sept, 12:08
forwarded from @arisalah_charity
አሰላሙ አለይኩም ወረህመቱላሂ ወበረካቱህአልሀምዱሊላህ!🤲 የ 3ኛ ዙር የቁርአን ልገሳ ተጠናቋል!😍በአላህ ፈቃድ 3ኛ ዙር የቁርአን ልገሳ ፕሮግራማችን በተሳካ ሁኔታ ተከናውኗል።ዛሬ መስከረም 3 ቀን 2019 ማህበራችን ፒያሳ በሚገኘው አወሊያ ትምህርት ቤት በመገኘት እሁድ እሁድ ከጠዋቱ 2:00 እስከ ቀን 6:00 ሰዓት ድረስ ትምህርታቸውን ለሚከታተሉ መስማት ለተሳናቸው ህፃናት እና አዋቂዎች ቁርዓኖችን አስረክቧል፦የተበረከቱ ቁርዓኖች፦ 100 ኑራኒያ ለጀማሪዎች 70 ባለ 30 ጁዝዕ ሙሉ ቁርአን 5 ትልቁን ባለ 30 ጁዝዕ ለሽማግሌዎችእኛ ሙሉ ጤና እያለንና የምንፈልገውን መስማትና መናገር እየቻልን በትንሽ ነገር እንማረራለን። ዛሬ ግን በዚህ ተቋም ያየናቸው መስማት የተሳናቸው ከእኛ በላይ ለቁርአን ያላቸው ፍቅር አስገርሞናል። ማማረር እንደሌለብንና አላህ በሰጠን ጸጋ ልናመሰግን እንደሚገባ አውቀናል።ይህ ተቋም እጅግ ልዩና ድጋፍ የሚሻ፣ ሊጎበኙትና ሊረዱት የሚገባ ቦታ ነው። ሌሎች አካላትና በጎ አድራጊዎችም ቦታው ድረስ በመሄድ እንዲጎበኙአቸው ጥሪያችንን እናስተላልፋለን። ተቋሙን መጎብኘትና መደገፍ ለምትፈልጉ በሙሉ በቴሌግራም ብታናግሩን አስፈላጊውን መረጃ የምናቀርብላችሁ ይሆናል።በዚህ ስራ የተሳተፋችሁ ወንድሞችና እህቶች በሙሉ ለሰራችሁት መልካም ስራና ለዚህ ኸይር ስራ መሳካት ከፊትለፊት ለነበራችሁ በሙሉ ዱዓ አስደርገናል።




𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴
12 Sept, 15:51
ወንጀል እንደመግባት መውጣቱ አይቀልም።
𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴
11 Sept, 04:41
ዛሬ በጥዋት ተነሳው 🌞 አየተነፈስኩ ነው😮💨 እግሮቼ ይንቀሳቀሳሉ 🚶♂ ልቤም እየመታ ነው ❤️🩹 ብርሀን እያየሁ ነው 👀 ከዚ በላይ ምን ቀረ🤷♀ አልሃምዱሊላህ ያ ረብ🙏አልሃምዱሊላህ ብለካል ወይስ እስክታስነጥስ እየጠበክ ነው✨✨አልሃምዱሊላሂ ረቢል ዓለሚን🥰
𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴
11 Sept, 04:41
አዲስ ንጋት ፤ ጭማሬ ቀን ... ከትንሹ ሞት (እንቅልፍ ) በኋላ ህያው ላረገን አሏህ ምስጋና ይገባው።ስንቶች አሉ የዛሬን መንጋት ለማየት ከጅለው ያልቻሉ። እኛ ግን አነጋን የዛሬዋን ፀሀይ አየን አልሃምዱሊላህ! ስንቶች አሉ ትላንት ሙሉ ጤነኛ የነበሩ ዛሬን ግን ያን ተነፍገው ያደሩ ። እኛ ግን በሙሉ ጤንነት አነጋን አልሃምዱሊላህ!!
𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴
9 Sept, 06:50
ከሐራም ነገር ከባዱ የመጀመሪያው ነው። ከዚያ ሲደጋገም እየቀለለ ይሄዳል። ከዚያ እንዲሁ ተራ ነገር ይሆናል። ከዚያ ልማድ ይሆናል። ከዚያ ይጣፍጣል። ከዚያ ልብ ይሸፈናል። ከዚያ ልብ ሌላ ሐራም መፈለግ ይጀምራል።አንድ ሷሊሕ ሰው እንዲህ ይላል፦ "ነፍስህ ወደ ወንጀል ከጋበዘችህ በዚች አንቀፅ አጭር ቃለ መጠይቅ አድርግላት :- { أَذَ ٰلِكَ خَیۡرٌ أَمۡ جَنَّةُ ٱلۡخُلۡدِ ٱلَّتِی وُعِدَ ٱلۡمُتَّقُونَۚ } "ይሄ ነው የሚሻለው ወይስ ጥንቁቆቹ ተስፋ የተሰጧት የዘለዓለሟ ጀነት?" [አልፉርቃን፡ 15]በዚህ ሐራም ነገሮችን መዳፈር በበዛበት ዘመን ይህቺን አንቀጽ ማስተዋል ምንኛ አንገብጋቢ ነው?!IbnuMunewor
𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴
6 Sept, 15:45
ደግነት መጠኑ ካለፈ መብት ሳይሆን ግዴታ ይመስላል 🙌
𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴
5 Sept, 18:51
ሰላም ለልባቹህ❤️🩹
𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴
4 Sept, 07:48edited
✅ የፈተና መብዛት!ረሱል (🤎) እንዲህ ብለዋል፦﴿إِنَّ أُمَّتَكُمْ هذه جُعِلَتْ عافِيَتُها في أولِها وإِنَّ آخِرَهُمْ يُصِيبُهُمْ بَلاَءٌ وأُمُورٌ تُنْكِرُونَها ثُمَّ تَجِيءُ فِتَنٌ يُرَقِّقُ بَعْضُها بَعْضًا فيقولُ المؤمنُ هذه مُهْلِكَتِي ثُمَّ تَنْكَشِفُ ثُمَّ تَجِيءُ فِتْنَةٌ فيقولُ المؤمنُ هذه مُهْلِكَتِي ثُمَّ تَنْكَشِفُ“ከዚህ ህዝበ ሙስሊም (ከተለያዩ ፈተናዎችና መከራዎች) አፊያ (ነፃ) የተደረገው በመጀመሪያው ዘመን ያለው ትውልድ ነው። የመጨረሻ ዘመን ላይ የሚመጡት መከራና የሚፀየፉትና (የማይወዱት) የሆነ ነገር ይገጥማቸዋል፤ ፈተናዎች ይከሰታሉ አንዷ ፈተና በሌላኛው ፈተና ላይ እየተደራረቡ ይመጣሉ፤ የዚህን ግዜ አማኝ የሆነ ሰው እንዲህ ይላል፦ ‘ይህቺ ፈተና መጥፊያዬ ናት’ ከዛም ፈተናው ይነሳል (ያልፋል) ሌላም ፈተና ይመጣል የዚህን ግዜ አማኝ የሆነ ሰው እንዲህ ይላል፦ ‘ይህቺ ፈተና መጥፊያዬ ናት’ ከዛም ፈተናው ይነሳል (ያልፋል)።”📚 ኢብኑ ማጃህ ሶሂህ ብለውታል፡ 3210
𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴
2 Sept, 14:38
አሰላሙ አለይኩም ወረህመቱላሂ ወበረካቱህአሪሳላህ በጎ አድራጎት ማህበር ባለፈው ከሰበሰብናቸው የተረፉ ቀሪ ቁርዓኖች አሉን የቁርዓን እጥረት አለበት የምትሉትን መድረሳ ወይም መርከዝ ጊዜው ሳይሄድ ጠቁሙን ለባሰበት እንሰጣለን🫶@arisalah_admin
𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴
1 Sept, 12:00
ታቢዒዩ ሶፍዋን ብኑ ሱለይማን እንዲህ ብለዋል፦ليأتين على الناس زمان ، تكون هِمّةُ أحدهم فيه : بطنُهُ، ودينُهُ : هواه."በሰዎች ላይ ሀሳባቸው ሁሉ ሆዳቸው፣ ሃይማኖታቸው ደግሞ ስሜታቸው የሚሆንበት ጊዜ ይመጣል።"[አልጁዕ፣ ኢብኑ አቢ ዱንያ ፡ 261]
Related Channels
Other channels in the same section of the catalogue.
