gram news
ግጥም ብቻ channel avatar

ግጥም ብቻ

@getem

✔በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን። ✔ @getem @serenity13 ✔ @wegoch @Words19 ✔ @seiloch ✔ @zefenbicha @leul_mekonnen1

ProjectsENOther

63,200subscribers

Open the Channel

Latest posts

  • ግጥም ብቻ

    27 Sept, 18:10

    የሰይጣን ጆሮን ማን ደፈነልኝ? አይነ ጥላዬን ማን ገፈፈልኝ? የማን ተማፅኖ ጎሁን ቀደደው? በማን ተማልዶ እግዜር ፈቀደው?አይገባም አንዱም ከሰውጋር ውለው ምን ቢላመዱም በመውደድ ብቻ በመኖር ብቻ - ከቆንጆ አይወልዱም እናም ይሄ ዘር ከምን በቀለ? ከማንጋር አድሮ እሸት ደቀለ?በሚል ጥያቄ ግርምቱን ታጥቆ ስልቻ ልቡን ደስታ ጠቅጥቆ ካለልማዱ ሸክም ቢከብደው ከትዝታው ላይ ህመም ህመሙን - መርጦ ይካደው?አዎ ይካደው!ከሀዲ መባል ስምን ቢያውክም ሰባራ ቅስምን ደባብሶ ሚያክም ፀበል አፍልቆ ጅኒ 'ሚያዳክም ፈውስ አግኝቶ ሰው - ደዌ አያመልክምእኔም እንዲሁቀኔን በብርሀን መዳፉ ዳብሶት ፊቴን የደስታ ፀዳል አልብሶት እንደ ቁም ነገር ቸገረኝ ብሶትደስታዬም ሰፍቶ አይመስልም ልኬ ማኩረፍ ከበደኝ ሳቅ ሆነ መልኬ መልመድ አቃተኝ ላንድቀ'ንንኳ? ለካስ ችግር ነው ህልምም ሲሳካ?By Tadios Alemayehu@getem @getem
    1,85034931Open in Telegram
  • ግጥም ብቻ

    24 Sept, 07:12

    አልገባህም እንጂ የነገርኩህ ሁሉ ታድነኝ ነበረ ‘ራስህ በቀላሉ በመታየት ብቻ በተራ ሰላምታ በትንሽ ንግግር በቁጥብ ፈገግታ ባታስተውል እንጂ እየጠፋች ያለች ቀስ በቀስ ከምድር ደጅህ በቅላ ነበር ‘ምታሳዝን ፍቅር አላሳዝንህም?By Meleti Kiros@getem @getem @paappii
    3,59065553Open in Telegram
  • ግጥም ብቻ

    24 Sept, 07:12

    "ስለበላች ፣ ከማርህ"የሙጫህ ወለላ ፣ የግንድህ ወዘና ማርኮኛል ውዴ ፣ ሕይወቴ ነውና መቆረጤን ፣ ደምቶ አክሟልናጦር ባያፈሰው ፣ የጎንህን ደም ውሃ ነፍሴ በተራበች ፣ ሆና ወይራ በኦና በረሃ ግና ተመስገን ፣ ትፈልቃለች እንደ ጮራስለበላች ፣ ከ "መ" ማርህ ጠግባለች ፣ በማስማርህ ወደሃት ፣ አልፈህ ከሚስማርህ ክድን አይኗ ፣ የታወረ ረሃቧ ፣ ሆድ የሞረሞረ መዛሏ ፣ ጥልፍ የተጣመረ ግና ደምተህላት አንዴ ጠገበችብህ ውዴ አለችህም መንገዴ በማጉረስህ ፣ ደም ስጋ የዘላለምን ፣ ሕያው ጸጋ ረጋች ካንተ ፣ በርትታ ላትሰጋእያየችህ አለች ፣ዘወትር በቀኝህ ለመዳኗ ሁሌ ፣ ስታመካኝህ "አቅምሽ?" ሲሉ ፣ አንተን ስታስቃኝህBy #ናትናኤል_አበበ (Hiyaw_Kidan)@getem @getem @getem
    3,480182Open in Telegram
  • ግጥም ብቻ

    19 Sept, 08:03

    @mypoems396 @getem @getem @getem
    Image from a post by ግጥም ብቻImage from a post by ግጥም ብቻ
    3,400206431Open in Telegram
  • ግጥም ብቻ

    17 Sept, 18:47

    ያመሻሽ ስንኞች (በእውቀቱ ስዩም)በቀዝቃዛ ጎጆ፤ በደብዛዛ ኩራዝ እንባ እያጣቀስኩኝ ፤ በምገልጠው ጥራዝ፤ ኑሮየን ባጠናው፤ ፍቺው አይገለጥ ሊቅ ሆኘ ተፈጠርሁ፤ በቂል ለመበለጥ፤“”””” እሳቴን አንድጄ ጭራሮ ማግጄ ሰታቴየን ጥጄ ሺ ጊዜ ባማስል፣ ራት አላበሰልሁ እኔ ከማገዶው፤ ቀድሜ እየከሰልሁ፤By Bewketu seyoum@getem @getem @paappii
    4,990677542Open in Telegram
  • ግጥም ብቻ

    17 Sept, 16:05

    A SPARKLEREven if that sun never rises, I'm already bright with your lights. The night becomes darker and darker, but can't destroy your smile, a sparkler.No way! The black fog centered me like a core? oh, I'm safer than ever before. And if it's not going to end, I'll choose to stay dead. smelling your fragrance instead.If this night finally decides to go away, I still won't miss the sun anyway! [ዓለም]@mypoems396 @getem
    4,86016103Open in Telegram
  • ግጥም ብቻ

    16 Sept, 18:28edited

    ግዜ ደጉ . . . ልክ ለመሆን ላለመሳሳት ወርቅ ዘመኔን መፈተን በ'ሳትበፍጡር ይዘት በሰው ትከሻ ፍፁም ካልሆንኩ ይሉት ንክሻገጥሜ ትግል ውድቀት ሳላምጥ ሰው እንኳን መሆን ሲያቅተኝ በቅጥ...ጊዜ ደግ አይደል...?ካጓጉል ቅዠት ነክቶ ያባንናል ወደቀ ያሉት በድሜ ይቃናል ነብር ነኝ ባዩም ግልገል ይሆናልከሆዴ አራግፎ የጅል ኩራቴን
    5,6305887Open in Telegram
  • ግጥም ብቻ

    16 Sept, 06:14

    ሳይፀልዩ ማደር ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨የተራበ ነብር ከሩቅ ተመልክታ ሚዳቆ ፀለየች "አውጣኝ አውጣኝ" አለች ለፈጠራት ጌታ ነብሩም ተርቦ ወደ አምላኩ ቀርቦ አንጀቱ ከሆዱ እንደተጣበቀ ፈቅዶ እንዲሰጠው አምላኩን ጠየቀ የሁላችን ሰሪ ፀሎታቸውንም ሰማቸው ፈጣሪ አምላክም በድምጹ ሚዳቆዋን አላት "እሩጠሽ አምልጪ ከበረታው ጠላት።" ነብሩንም አለው "እሩጥ ተከተላት ምግብ አድርገህም ብላት" ሚዳቆዋ ስትሮጥ ከነብር ለማምለጥ ነብሩም ሲከተላት ሆዱን ሊሞላባት ቋጥኙን ስትዘል እግሯ ተስፈንጥሮ
    6,220137312071Open in Telegram
  • ግጥም ብቻ

    12 Sept, 10:10

    ደርሷል ትዕዛዛችን ፣ እንብላ ከእህሉ አዘን አዘን የተቀመጥን ፣ ዳስዳስ ያለን ሁሉእንደአበሻ ገበሬ ፣ አርሶ እንዳጨደ ነዶን ከምረን ፣ እጃችን ሰብል ያዘ የመብቃትን ማዕረግ ፣ የመድረስን ከፍታ እጃችን ጨብጦ ፣ ክንዳችን ባይገታግና ግና ሆዳችን ፣ አልጠገበም ሞልቶ ሰው ሰው ተርቧል ፣ ወዳጁን አጥቶ የእራሱ ራስ ከዳ ፣ የሆዱን ሆድ ፈጀ ፍቅር እየዘራ ፣ አሜከላ አጨደሰውን ሰው ራበው ፣ ሰውን ሰው ተጠማ አበሻ በታሪኩ ፣ ዛሬ ብቸኝነት ደማ።By ናትናኤል_አበበ@getem
    8,480385Open in Telegram
  • ግጥም ብቻ

    11 Sept, 05:51edited

    ብንሥቅም ፡ ባንሥቅም አደይ ቀርታ አታውቅም።by Seifu Workuመልካም አዲስ ዓመት@getem @getem @paappii
    8,5908116112Open in Telegram
  • ግጥም ብቻ

    11 Sept, 05:49

    ትዝ ይልሻል?የዛሬው ዋዜማ በጳጉሜ 5 አምናከበርሽ ነበርኩኝ የሀሳቤን ልኖር ደጅሽን ስጠናአይገርምም?ድሮ ልንል በቃን እኒያ ቀናት አልፈውትዝብት ሊሆኑን በፊደል ተጽፈውይሄውልሽ አለሜ ይሄንን እወቂ ፡ እንዳለፈው ዘመን ለእኔ ኑሪ እያለ ደጅ ይጠናል ብለሽ እንዳትጠብቂ። ፡ ባይሆን
    8,6704311Open in Telegram
  • ግጥም ብቻ

    10 Sept, 18:57

    አዲስ አመት . . ያ...ጠቢብ ሰለሞን.......... ያማረ ቀለበት ከእጅሽ ያጠለቀዉ፤ ምን ያክል ዉበትሽ ልቡን ቢገዛዉ ነው?ከአደይቷ ይልቅ ደምቀሽ ብትታይዉ፤ ሽንፈት የማያዉቀዉ ፍቅርሽ አሸነፈው።ትዋቢበት ዘንዳ ዉብ እንቁን ለጣትሽ፤ ችግር ሲያገኝሽ ማለፊያ ለጣጣሽ፤ አንድም ለልብሽ ነዉ ማሰሪያ ለቃልሽ፤ ለቅድስቷ ምድር አንድም ለሀገርሽ።የካም እድል ፈንታ እንቁ ዕጣ ለወጣች፤ ጸሎቷን ለማድረስ እጇን ለዘረጋች፤ህመምሽ ለሆነች ፈዋሽሽም እሷዉ፤ ለቅድስቷ ምድር አንድም ለሀገርሽ ነው።
    7,5205711Open in Telegram
  • ግጥም ብቻ

    10 Sept, 06:45

    "እኔ ባዲስ ቀን አላምንም ቀን ከቀን አልለይም አሮጌ መሆን ነው የቀረኝ አንድ አቅም!" የሚል ድባቴያም ሰምተህ ግን አታውቅም?!ካደፈ ልብሱ አልፎ ከርሞ ልቡናውን እያስተባበረ መስኮት ግድግዳውን እያሰማመረ ድባብ የሚጨምር ደርሶ ባያየውም እንዲህ ያለውንስ አላስተዋልኸውም?!ግን ከዚ ሁሉ ረቅቀን መጠቅ ነጠቅ ብለን፣ ከአይደለም እና አዎ መሃል ወጥተን፣ ካዲስነት ጀርባ ምን ታምር ታይቶሃል?፣ እውነትም ብርሃን ያለው ይመስልሃል?!... መልስ ያበጀህ እንደው ያጣህም እንደሆን ወዴት ትሸሻለህ ተቀባይ ከመሆን?!
    Image from a post by ግጥም ብቻImage from a post by ግጥም ብቻ
    8,2504682Open in Telegram
  • ግጥም ብቻ

    8 Sept, 13:14edited

    ድልድይ ናት ጳጉሜ ከዝያ ወደዚኛው፣ ከመጨረሽኛው~ወደ~መጀመሪያው ሲታደል አይደል ወይ ቋጭቶም ለመደምደም፣ የዓመት ቆይታን በ5 ቀን መገምገም!@mypoems396 @getem @getem @getem
    8,97057166Open in Telegram
  • ግጥም ብቻ

    1 Sept, 07:24

    @mypoems396 @getem @getem @getem
    Image from a post by ግጥም ብቻImage from a post by ግጥም ብቻ
    13,600501471Open in Telegram
  • ግጥም ብቻ

    30 Aug, 20:50

    @mypoems396 @getem @getem @getem
    Image from a post by ግጥም ብቻImage from a post by ግጥም ብቻ
    12,700611311Open in Telegram
  • ግጥም ብቻ

    30 Aug, 05:48

    «ናፈቅሽኝ አቦ !» ብዬ የፃፍኩት ኩራት ሲሰማኝ - ቀድጄ ጣልኩት ።«ናፈቅከኝ በጣም» ብለሽ የፃፍሽው ልምምጥ መስሎሽ ወርውረሽ ጣልሽው ።የፍቅር ብርሃን እንዳልተሰማን ቅር እንዳላለን እንዳልናፈቅን በአዲስ ወረቀት - ፀብ ተላላክን ።እንበልና ...እኒያ ወረቀቶች ... ቀደን የጣልናቸው የክረምት ጎርፍ አገናኛቸው ።እስኪ አስቢያቸው ...ደራሽ ተሳፍረው
    12,1001345443Open in Telegram
  • ግጥም ብቻ

    30 Aug, 05:48edited

    ๘ ቃና አልባ ህይወቴ የፈሰሰ ሀሞቴ ጣዕም ፣ መልኩ ጠፍቶ ፡ የጠቆረ ወተቴ ያ ‛መት ሙት አመቴ 𓏸 𓏸 𓏸 ተሰርዮልኛል ! ! ....ተሰርዞልኛል... እናትነት ፍቅርሽ ፡ ያለፍኩትን አይቶ ፤ አዝኖ ራርቶልኛል ከአዘቅት እመቃት ፡ከባርያነት ግዞት ለይቶ አንስቶኛል ⨳ఎማህፀንሽ ሳለሁ ኪዳን ገብተሽልኝ ያንቺን መልከ ስጋ ˔ ከእግዜር ገዝተሽልኝ . . . አገልግለሽኛል ተርበሽ ተጠምተሽ አሳድገሽኛል ꨄ 𓏲 አፈር ግፈሽ ቅመሽ
    11,100297Open in Telegram
  • ግጥም ብቻ

    27 Aug, 20:23

    ታግሼ እንዳላልፈው ፥ ክህደት ስላጠቃኝ አበባ እሰጥ ብዬ ፥ እሾህ ስለወጋኝ ሁሉንም ለመተው ፥ ትንሽ ነው ሚበቃኝBy ሲራክ ወንድሙ@getem @getem @paappii
    11,400124299521Open in Telegram
  • ግጥም ብቻ

    27 Aug, 17:18edited

    🔔 ውድ የቻናላችን አባላት፣ አዲስ የምስራች አለን!የተመረጡ ግጥሞችን እና ሀሳቦችን, ወጎችን የምናጋራበትን ጉዞአችንን የበለጠ ለማሳደግ እና ጽሁፎቻችንን ባማረ ሁኔታ ለማቅረብ አዲስ Substack ገጽ ከፍተናል!📌 ግጥሞች ለማንበብ እና አዳዲስ ጽሁፎቻችን በኢሜይል እንዲደርሷችሁ ከታች ያለውን ሊንክ ተጭነው Substack ገጻችንን Subscribe ያድርጉ፡ https://substack.com/@getembichaአብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን!! @getem
    Substackግጥም ብቻ | Substack
    16,300234Open in Telegram