Latest posts

Global Bank Ethiopia
24 Sept, 05:51
የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ኢንተርኔት ባንኪንግ – ደህንነቱ የተጠበቀ፣ ምቹና ፈጣን!በማንኛውም ጊዜ፤ ከየትኛውም ቦታ ምቹ፣ ፈጣን፣ አስተማማኝ፣ደህንነቱ የተጠበቀና ለአጠቃቀም ቀላል የሆነውን የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያን የኢንተርኔት ባንኪንግ አገልግሎት ይጠቀሙ፡፡በኢንተርኔት ባንኪንግ አገልግሎታችን፡- 👉 ገንዘበ ማስተላለፍ፣ 👉ቀሪ ሂሳብ ማየት፣ 👉 የአየር ሰዓት መሙላት፣ 👉 ወደ ቴሌብር ገንዘብ መላክ እንዲሁም ልዩ ልዩ ክፍያዎችን መፈፀም ያስችሎታል፡፡የባንካችንን ኢንተርኔት ባንኪንግ ሲጠቀሙ ደህንነትዎ የተጠበቀ ነው፣ ምቾትዎ ደግሞ ቅድሚያ የምንሰጠው ጉዳይ ነው፡፡አገልግሎቱን ለመጠቀም ቀጥሎ የተቀመጠውን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ፡- https://www.globalonline.com.et/?page=homeግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ለጋራ ስኬታችን!


Global Bank Ethiopia
23 Sept, 08:27
ዕለታዊ የውጭ ምንዛሪ መስከረም 13 ቀን 2019 ዓ.ምFOREIGN EXCHANGE RATE September 23, 2026
1,720Open in Telegram
Global Bank Ethiopia
22 Sept, 15:45
ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ አዳዲስ ከፍተኛ የማኔጅመንት አባላትን ተቀበለ፤ ስድስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችን በዶክትሬት ዲግሪ አስመረቀግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ባንኩን በቅርቡ የተቀላቀሉ ከፍተኛ የማኔጅመንት አባላትን የእንኳን ደህና መጣችሁ መርሃ ግብር የባንካችን የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ዮሴፍ ጌታቸው፣ ተ/ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሳኅለሚካኤል መኮንን (ዶ/ር) እና ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት መስከረም 12 ቀን 2019 ዓ.ም በባንካችን የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተካሂዷል፡፡ባንካችንን በአዲስ መልክ የተቀላቀሉት ወ/ሮ ሌንሴ ገለታ የሪቴል ባንኪንግ እና ሀብት ማሰባሰብ ቺፍ ኦፊሰር እንዲሁም ካሳ ሚኮሮ (ዶ/ር) የፋይናንስ እና ትሬዠሪ ቺፍ ኦፊሰር ሆነው ኃላፊነታቸውን ተረክበዋል።ባንኩ እያከናወነ ያለውን የለውጥ እና የዕድገት ስራዎች ለማሳካት ብቁ የሆኑ የማኔጅመንት አባላትን ማጠናከር ላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን በመርሃ ግብሩ ወቅት የጠቆሙት የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ዮሴፍ ጌታቸው፣ አዳዲሶቹ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች የባንኩን አጠቃላይ ተወዳዳሪነት እና አሰራር ይበልጥ በማጠናከር ለባንኩ ስኬት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ማበርከት እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡ለባንካችን ዕድገት የሰው ኃይሉን በዕውቀትና በክህሎት ማብቃት የማያቋርጥ ትኩረት ሆኖ እንደሚቀጥል የገለፁት ደግሞ የባንካችን ተ/ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሳኅለሚካኤል መኮንን(ዶ/ር) ናቸው፡፡ አዳዲሶቹ ኃላፊዎች ከነባሩ አመራር እና ሠራተኞች ጋር በመቀናጀት ባንካችንን ወደ ላቀ የስኬት ምዕራፍ ማሻገር እንደሚችሉ ያላቸውን እምነት ተ/ስራ አስፈፃሚው አክለዋል፡፡
Global Bank Ethiopia
22 Sept, 15:45





Global Bank Ethiopia
21 Sept, 05:36
EXTERNAL VACANCY ANNOUNCEMENT (September 21, 2026) Global Bank Ethiopia S.C wants to recruit the following professionals;1.Job Title: Manager - Relation & Communication Division Education (Minimum): MBA or BA in Communication/ Journalism/ Public Relations/ Marketing/ Business Administration/ Management or related field Experience: 6/8 years of relevant experience; preferably in Corporate Communication, Public Relation, Stakeholder Relation, Media Relations in the banking or financial service industry; 3years of which in senior position Number Required: 1 (One) Place of work: Head Office2. Job Title: Manager - Ethics & Anti-Corruption Division Education (Minimum): MSC or BSc in Law/ Business Administration/ Management/ Ethics/ Compliance/ Accounting/ Finance /Human Resource or related field Experience: 6/8 years of relevant experience; preferably in the banking or financial service
Global Bank Ethiopia
21 Sept, 05:36

2,320Open in Telegram
Global Bank Ethiopia
21 Sept, 03:52
መልካም የሥራ ሳምንት ይሁንልዎ!ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ለጋራ ስኬታችን


Global Bank Ethiopia
19 Sept, 06:32
9335# በማንኛውም ስልክ፣ ያለ ኢንተርኔት!በማንኛውም ሰዓት፣ ከየትኛውም ቦታ ሆነው የባንክ አገልግሎትዎን ማከናወን ይፈልጋሉ? ወደ ባንካችን አጭር ቁጥር (USSD) 9335# በመደወል የባንክ አገልግሎት ማግኘት ይችላሉ፡፡የባንካችን አጭር ቁጥር 9335# ከሚሰጣቸው ጥቅሞች መካከል፡- 👉ቀሪ ሂሳብ ማየት 👉የገንዘብ ዝውውር መፈፀም 👉የሒሳብ እንቅስቃሴ (Mini Statement) ማየት 👉ወደ ግሎባል ባንክ እና ወደ ሌሎች ባንኮች ገንዘብ ማስተላለፍ 👉የአየር ሰዓት (Airtime) መሙላት 👉እንዲሁም ሌሎች ተጨማሪ አገልግሎቶችን በቀላሉ መጠቀም ያስችሎታል፡፡ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ለጋራ ስኬታችን


Global Bank Ethiopia
18 Sept, 05:53
ሙዳረባ የልጆች የቁጠባ ሒሳብ ሙዳረባ የልጆች የቁጠባ ሂሳብ የሸሪዓ መርህን የተከተለ ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ከሚሰጣቸው ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎቶች መካከል አንዱ ነው፡፡ ለምን ይከፍታሉ? • ልጆችዎ የቁጠባ ባህል ያዳብራሉ፣ • ለትምህርት፣ ለህልማቸው እና ለወደፊት ዕቅዶች ዝግጁ ይሆናሉ፣ • ገንዘብዎ በሀላል ንግዶች ላይ ይውላል፣ • ልጅዎ ከሚገኘው ትርፍ ላይ ተጋሪ ይሆናል፡፡የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ለመሆን በአቅራቢያዎ ወደሚገኙ የባንካችን ቅርንጫፎች ጎራ ይበሉ፡፡ ለተጨማሪ መረጃ በደንበኞች የግንኙነት ማዕከል 8118 ይደውሉ፡፡ግሎባል ሐቂቃ፡- የሸሪዓ የፋይናንስ መርሆችን የተከተለ ከወለድ-ነፃ የባንክ አገልግሎት!ጁምዓ ሙባረክ!ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ለጋራ ስኬታችን!


Global Bank Ethiopia
17 Sept, 06:43edited
EXTERNAL VACANCY ANNOUNCEMENT (September 17, 2026) Global Bank Ethiopia S.C wants to recruit the following professionals;1. Job Title: Trainee Banker Education: BA in Accounting/ Banking/ Management or related fields Experience: None Number Required: 7 Work Place: Hirna, Dire Dawa Mariyam Sefer, Jigjiga, Taiwan, Aweday and Gelemso Branches Salary: Per the Bank’s Salary Scale CGPA - 3 & above Year of graduation- 23/24/25 & 26 Must have passed the exit examApplication Dead line: 5 Working days (September 15, 2026 – September 19, 2026) starting from the date of announcement on the job portalInterested applicants should submit their applications along with CV and other relevant documents through our Bank’s website job portal; https://globalbankethiopiaapps.com.et/jobs/loginglobalbankethiopiaapps.com.etGlobal Bank Job PortalFind your dream job
Global Bank Ethiopia
17 Sept, 06:43

3,300Open in Telegram
Global Bank Ethiopia
16 Sept, 14:05
የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች የሪሞን ጀነራል ትሬዲንግን የስራ እንቅስቃሴ ጎበኙበግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ተ/ሥራ አስፈፃሚ ዶ/ር ሳኅለሚካኤል መኮንን የተመራ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ልዑክ፣ የሪሞን ጀነራል ትሬዲንግን የሥራ እንቅስቃሴ የጉብኝት እና የውይይት መርሃ ግብር መስከረም 6 ቀን 2019 ዓ.ም አካሂደዋል፡፡የጉብኝቱ ዋና ዓላማ ባንካችን ከደንበኞች ጋር ያለውን ስትራቴጂካዊ አጋርነት ማጠናከር፣ የድርጅቱን ሁለገብ የሥራ እንቅስቃሴ በቅርበት መመልከት እና የጋራ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ መሆኑን ዶ/ር ሳኅለሚካኤል መኮንን በውይይቱ ወቅት ገልጸዋል።ሪሞን ጀነራል ትሬዲንግ በንግድ፣ በኢንቨስትመንት እና በተለያዩ የልማት ዘርፎች ላይ ተሰማርቶ እንደሚገኝ የገለጹት የድርጅቱ መስራችና ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አያሌው፤ ከግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ጋር ያላቸውን መልካም የሥራ ግንኙነት አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል።ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ከደንበኞቹ ጋር ያለውን መልካም የስራ ግንኙነት በዘላቂነት ለማስቀጠል እና የረጅም ጊዜ ስትራቴጂካዊ አጋርነት ለመፍጠር የሚያስችሉ የጉብኝት እና የውይይት መርሃ ግብሮችን አጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል፡፡ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ለጋራ ስኬታችን




Global Bank Ethiopia
15 Sept, 10:45
ለወጣቶች ብቻ የተዘጋጀ ልዩ የቁጠባ ሂሳብ!ከመደበኛው የቁጠባ ሂሳብ የተሻለ ወለድ የሚያስገኘውን የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ የወጣቶች የቁጠባ ሂሳብ ይክፈቱና ይቆጥቡ፡፡አገልግሎቱን ለማስጀመር በአቅራቢያዎ በሚገኙ የባንካችን ቅርንጫፎች ጎራ ይበሉ፡፡ ለተጨማሪ መረጃ ወደ 8118 በነፃ ይደውሉ፡፡ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ለጋራ ስኬታችን


Global Bank Ethiopia
14 Sept, 09:05
ዕለታዊ የውጭ ምንዛሪ መስከረም 4 ቀን 2019 ዓ.ምFOREIGN EXCHANGE RATE September 14, 2026
3,420Open in Telegram
Global Bank Ethiopia
14 Sept, 06:24
መልካም የስራ ሳምንት!የዘመን መለወጫ በዓላችንን በድምቀት አክብረን፣ ወደ አዲሱ ሳምንት እና የሥራ ከባቢ ስንገባ፤ በታደሰ መንፈስና ከፍተኛ ዝግጁነት ጉዟችንን እንቀጥላለን።ለባንካችን ታላቅ እሴት ለሆናችሁ ደንበኞቻችን እና አጋሮቻችን በአዲሱ ዓመት አዳዲስ ስኬቶችን እውን የሚያደርጉበት፣ ዕቅድዎ የሚሳካበት ይሁንልዎ!መልካም የስራ ሳምንት!ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ለጋራ ስኬታችን!


Global Bank Ethiopia
10 Sept, 16:11
🌼🌼ከባንካችን ተ/ሥራ አስፈፃሚ ሳኅለሚካኤል መኮንን (ዶ/ር) የተላለፈ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት፡-🌼🌼ክቡራን ባለድርሻ አካላት፣ ደንበኞቻችን፣ የሥራ አጋሮቻችንና የባንካችን ቤተሰቦች በቅድሚያ እንኳን ለአዲሱ ዓመት በሰላም እና በጤና አደረሳችሁ!አዲሱ ዓመት አዳዲስ ግቦችን የምንቀርፅበት፣ ተስፋችን የሚታደስበት እና የወደፊት ጉዟችንን በጠንካራ መሠረት ላይ የምንገነባበት የስራ ዘመን ነው። ባለፈው ዓመት ከእኛ ጋር ለነበራችሁ መልካም የሥራ ግንኙነት እና ላሳያችሁን እምነት በግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ስም የላቀ ምስጋናዬን እያቀረብኩ፤ ይህ ትብብር በአዲሱ ዓመትም አጠናክረን የምንቀጥል ይሆናል፡፡በአዲሱ ዓመት አገልግሎታችንን ይበልጥ ዘመናዊ፣ ቀልጣፋ እና ደንበኛ ተኮር በማድረግ እንደሁልጊዜው ሁሉ ለስኬታችሁ መዳረሻ ባንካችን ብርቱ አጋር መሆኑን አጠናክሮ ይቀጥላል፡፡አዲሱ ዓመት፡- 🌼የጋራ ስኬታችንን በጉልህ የምናይበት፣ 🌼የንግድና የኢኮኖሚ እድገታችሁ የሚፋጠንበት፣ 🌼የሰላም እና የጤና እንዲሆንላችሁ መልካም ምኞቴን እገልጻለሁ።ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ሁልጊዜም ለስኬታችሁ ብርቱ አጋር ሆኖ ይቀጥላል!መልካም አዲስ ዓመት! መልካም በዓል!ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ለጋራ ስኬታችን


Global Bank Ethiopia
10 Sept, 14:30
መልካም በዓል ይሁንላችሁ!ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ለጋራ ስኬታን!
Global Bank Ethiopia
10 Sept, 12:53
ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ አዲሱ ዓመትን ምክንያት በማድረግ ማዕድ የማጋራት መርሃ ግብር አካሄደግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ አዲሱን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 እና 7 ለሚገኙ አቅመ ደካሞች ማዕድ የማጋራት መርሃ ግብር ጳጉሜ 5 ቀን 2018 ዓ.ም በባንካችን ዋናው መ/ቤት አከናወነ።በመርሃ ግብሩ የባንካችን ቺፍ የሰው ሃብትና ኢንተርፕራይዝ ሰርቪስ ኦፊሰር አቶ ዳሳ ጎቤ፣ የኢንቨስተር ሪሌሽንና ኮምዩኒኬሽን ተጠባባቂ ዳይሬክተር አቶ ዘመላክ ብርሀኑ፣የመንግስት አመራሮች እንዲሁም የባንካችን አመራሮች እና ሰራተኞች ተገኝተዋል።ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ በተለያዩ የበጎ አድራጎት ስራዎች ላይ በንቃት በመሳተፍ ማህበራዊ ኃላፊነቱን በአግባቡ እየተወጣ እንደሚገኝ በመርሃ ግብሩ ወቅት የገለጹት የባንካችን ቺፍ የሰው ሃብትና ኢንተርፕራይዝ ሰርቪስ ኦፊሰር አቶ ዳሳ ጎቤ ባንኩ የሚያደርገውን ድጋፍ በቀጣይም አጠናክሮ እንደሚቀጥል አመላክተዋል፡፡አቅም የሌላቸው ወገኖቻችን አዲስ ዓመትን ከቤተሰቦቻቸው ጋር በደስታ እንዲያሳልፉ ለበዓሉ አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶች መበርከታቸውን የገለጹት ደግሞ የኢንቨስተር ሪሌሽንና ኮምዩኒኬሽን ተ/ዳይሬክተር አቶ ዘመላክ ብርሀኑ ናቸው፡፡ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ "ለጋራ ስኬታችን" በሚል መሪ ቃል ማህበራዊ ኃላፊነቱን መወጣት የባንኩ ዕሴት ዋና ማዕከል አድርጎ በትኩረት እየሰራ መሆኑን የተናገሩት አቶ ዘመላክ በቀጣይም ማህበረሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የበጎ አድራጎት እና የልማት ስራዎች ላይ በንቃት ይሳተፋል ብለዋል፡፡በመርሃ ግብሩ ላይ የታደሙት አቅመ




Global Bank Ethiopia
8 Sept, 15:05
የባንካችንን ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ



Global Bank Ethiopia
8 Sept, 06:38
የአዲስ ዓመት ስጦታዎን በግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ይመንዝሩ!የ2019 ዓ.ም አዲስ ዓመት በዓልን ምክንያት በማድረግ ከውጭ ሀገር የተላከልዎትን የውጪ ምንዛሬ በአቅራቢያዎ በሚገኙ የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ቅርንጫፎች ይመንዝሩ።👉ከፍተኛ ተመን 👉ፈጣን እና አስተማማኝ አገልግሎትግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ለጋራ ስኬታችን

Related Channels
Other channels in the same section of the catalogue.
