Latest posts

Halal Fkr
22 Sept, 17:36
በክርክር የተጠመደ ተግባርን ይከለከላል __ "ሰዎችን ከነበሩበት ቅናቻ መንገድ አይጠሙም ፣ ክርክርን የተሰጡ ቢሆን እንጂ" ሰዪዱና ሙሐመድﷺ __ ላለፉት ሺህ ዓመታት ሊቋጩ ያልቻሉ የሀሳብ ልዩነቶች ላይ ብዙ ጊዜዎች ባክነዋል፤ ይህን ውድ ጊዜ ማንነትን በሚያጎለብቱና ለማህበረሰቡ በሚፈይዱ ተግባራት ላይ ውሎ ቢሆን የተሻለ ለውጥ በተመለከትን ነበር ።
Halal Fkr
22 Sept, 10:33
የሰው ልጅ ትዕቢት ልቡን ሲወጥረው እራሱን እንደ ፈላጭ ቆራጭ ሲመለከት(በታሪክ'ማ እንደ አምላክ መመለክን ሽቶ አሰግዶም አልፏል)... እንዴት የለሊት እንቅልፉ ትዝ አይለውም? እንቅልፍ ሲወስደው አላጋው ላይ ሲያሸልብ በራሱ ላይ ስልጣን ያጣ ሚስኪን እንደሚሆን አላስተዋለም?...እንቅልፍ እኮ የሞት መልመጃ ፈተና ነው። የሰው ልጅ ሁሌ ለሰአታት እየሞተ ይነሳል... የፈለገ ሃያል ቢሆን እንቅልፉን ሊገታ አይችልም....ለምን ከሞት ቡሃላ ስላለ ህይወት መጨነቅ የፈላስፋ ጥያቄ ብቻ መሰለን?
Halal Fkr
22 Sept, 08:22
በስሜ ኮከብ የሚያሰይምልኝ ሰው ፍልጋለሁ😫
Halal Fkr
22 Sept, 07:29
በስሜ ኮከብ የሚያሰይምልኝ ሰው ፍልጋለሁ😫
Halal Fkr
22 Sept, 05:50
አስተውል…« ቀናቸውን በሙሉ በሥራ ተጠምደው የሚያሳልፉ፣ ነገር ግን ብዙም ወደ ግቦቻቸው የማይቀርቡ ሰዎች አሉ። ምክንያቱም የእንቅስቃሴ መብዛት በትክክለኛ አቅጣጫ ለመጓዝ ማረጋገጫ አይደለምና ።»(ዶ/ር ዐብደልከሪም በካ፟ር)በሥራዎች መወጠር ሁሉ እድገት አይደለም፤ እንቅስቃሴም ሁሉ መድረስ አይደለም።🤍
Halal Fkr
21 Sept, 16:30
"መኖር ማለት አለመሞት ከሆነ እስትንፋስ ያለው ሁሉ እየኖረ ነው። ግን መኖር ማለት እራስን መሆን፣ ለዓላማ መቆም፣ ህሊናን አለመዘንጋት፣ ፍርድን አለማጓደል፣ ለራስ ብቻ ሳይሆን ለሌላው እራስን መስዋዕት ማድረግ ብሎም አርአያ የሚሆን ነገር ጥሎ ማለፍ ከሆነ ስንቶቻችን ነን በህይወት ያለነው???"
Halal Fkr
21 Sept, 14:33
ዝንተዓለሙን ምርጥ የሆነ ሰው አይገኝም። በባህሪው ምሉዕ የሚባል ፍጡርም የለም። እዚህ… የሚሞላ ክፍት ቦታና የሚታከም ህመም አለ። እዚያ ደግሞ… የሚደበቅ ነውርና የሚሰረዝ ጥፋት አለ… አብሮ ለመኖር ስንል... መተራረም እንደሚያስተካክለን ሁሉ… መተላለፍም ውዴታችንን ያቆየዋል… ሳይበዛ።🖤
Halal Fkr
20 Sept, 20:21
👐😂


Halal Fkr
20 Sept, 16:11
ፍቅር ለድሆች_ነው፤ ሀብታሞችማ ያገባሉ😢ሲል ሰማሁት አንዱ ላጤ ከሰርግ እየወጣ😂
Halal Fkr
19 Sept, 23:46
እሹሩሩ እያለ አባብሎ ሚያስተኛ እንኳን እና ወዳጅ የለንም ጓደኛ ከወጣን በኋላ ከእናታችን ዕቅፍ ከገባን ወደ ዓለም የድካም ነው እንጂ የእረፍት እንቅልፍ የለም ከተኛን ቆየን😭
Halal Fkr
19 Sept, 17:44
የአለማችን ውሸታም ግጥምبعيني رأيت الذئب يحلب نملة ويشرب منها رائباً وحليبا ..ተኩላ ጉንዳንን እያለበ ወተቷን ሲጠጣ በአይን አየሁት 😭 ግን እወነት አለው?
Halal Fkr
19 Sept, 13:44
አኺሩ ዛማን ዘንድሮ ለፋው በትልቁ ብሷል ስልክሽን ስጭኝ ልሸኝሽ ምናምን አይባልም 🙌🏾ሀያ'ዕ አደብ የሚባል ነገር የለምዴ ኸረ እፈሩ!!
Halal Fkr
19 Sept, 11:03
ደስተኛ የሚለው ቃል በሀዘን ሚዛናዊ ካልሆነ ትርጉሙን ያጣል።🤎
Halal Fkr
18 Sept, 19:01
ሰውች በፊት የሆነ ሰው ከበደለው ወይም በፍቅር ጉዳይ ካልተሳካላቸው ወደ አሏህ ነበር ሚሸሹት ፣ እንዲሁም ዱአ በእንባ በማድረግ ነበር ሚታወቁት አሁንስ ወደ ጂም ቤት😁 ።ጂም ቤት ሀጃ ያወጣል እንዴ? ወይስ አብዛኛው ሰው የናቃቹ በቦርጫቹ ነው? ቦርጭ ማጥፍት ጥሩ ነው ሲክስ ፓክም አይከፍም ነገር ግን ሼፕና አቋምን እያስተካከሉ ጭንቅላትን እንደ ቦርጫሙ ቲቪ አሳብጦ መዞር ጥቅም የለውም ቅድሚያ አስተሳሰብህን ሼፕ አድርገው ከዛ አካልህን። 8ቁጥር ሆነሽ ዜሮ ጭንቅላት ካለሽ ምን ያደርጋል ? ከአካል በፊት አቅል ይቀድማል ከኃላ ይልቅ ከላይ ይቀድማል ።إن هذه تذكرة فمن شاء ذكره
Halal Fkr
18 Sept, 18:44
👐😂


Halal Fkr
18 Sept, 17:11edited
إِنَّمَآ أَشْكُوا۟ بَثِّى وَحُزْنِىٓ إِلَى ٱللَّهِ«ጭንቀቴንና ሐዘኔንና የማሰሙተው ወደ አላህ ብቻ ነው፡፡ 🤎
Halal Fkr
18 Sept, 16:05
የተወጋ ትዳር!በነገራችን ላይ ቆንጆ ሴት ስላገቡ ቆንጆ ልጆች መውለድ እንደሚችሉ የሚያስቡ ወንዶች አሉ። ስለዚህ ለትዳር ቆንጆ ሴት ያሳድዳሉ። በሰው ምርጫ መግባት አልፈልግም። ግን የአንድ ጓደኛየን ተሞክሮ ማካፈል እፈልጋለሁ። ለነገሩ የሱም ተሞክሮ ለህይወታችን ምንም አይጨምርም እንተወው። ዋናው ነገር ግን ልጆች ሲወለዱ ሜካፕ፣ሂውማን ሄር ፣የተወጋ ከንፈር፣ በሰርጀሪም ይሁን በኤክሰርሳይስ የተስተካከለ የሰውነት ቅርፅና የተጠና አማላይነት ከእናታቸው አይወርሱም። በኋላ የኔ አይደሉም እንዳትሉ!በዘር የሚተላለፉ የጤና ችግሮች፣ ደከም ያለ አዕምሮ፣ ባህሪ ወዘተ ግን ሊወርሱ ይችላሉ። እና ስትጋቡ ከፍቅር አልፋችሁ "ስለምርጥ ዘር" እስከማሰብ የደረሰ የከብት እርባታ መንፈስ ካደረባችሁ ቢያንስ ለትውልዱ ስትሉ ጤናና ባህሪ ላይ ላይ አተኩሩ።ሴቶችም እንደዛው "ከሚያምር ረዢም ወንድ የሚያምር ልጅ " የሚል መፎክር ውስጣችሁ ካደረ ፣ የምትመርጡት ለምርጥ ዘር የሚሆን ኮርማ እንጅ ባል አይደለም። መለሎው ኮርማ የቅድም አያቱን ስንዝሮ ቁመትና መጋፊያ እግር ለልጃችሁ ሊያወርስ ይችላል። ሆስፒታል አቀያይረውብኝ መሆን አለበት እስክትሉ የጀነቲክስ አልጎሪዝም እብድ ነው። የሆነ ሁኖ መሠረቱ ከተወጋ ትዳር ቆንጆ የምትሉትም ይወለድ መልከ ጥፉ ዋጋው ውድ ነው። ከምታፈቅሯቸው ውለዱ ፣ ከፍቅር የተወለዱ መልአክ ናቸው። ልጆች ምንጊዜም ውብ ናቸው። አስቀያሚ የሚያደርጓቸው አስቀያሚ ሒሳብ የሚሰሩ ወላጆች ፣ የእነዚህ ወላጆች ስብስብ የፈጠረው ማህበረሰብ ነው። የተወጋ ትዳር የተወጋ ማህበረሰብ ይፈጥራል። ©አሌክሶ
Halal Fkr
18 Sept, 13:07
🤔እኔ ብቻ ነኝ ግን አላህዬን አረ ባአላህ እያልኩ ምለምነው?🤎
Halal Fkr
18 Sept, 11:30
በቅርብ ቀን! ---------------------------------------- ♡ ㅤ ❍ㅤ ⎙ㅤ ⌲ ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ𝓗𝓪𝓵𝓪𝓵 𝓕𝓴𝓻 ™💞


Halal Fkr
18 Sept, 09:36edited
ስላንቺ.... እርግጥ ነው አንቺ አላህዬን አይደለሽምና ስላንቺ ለመፃፍ ባህሩ ቀለም፣ ደኑ መክተቢያ መድ ቢሆን ስላንቺ ከትቤ አልጨርስም __ አልልሽም። ግን ግን እንዲህ እልሻለሁ.... ጨረቃ ነሽ በ15ኛዋ ሌሊት ብቅ የምትለው ውብ ደማቅ ጨረቃ፣ ከሩቅ የምታበራ፣ መንገድ ለሳተ የምትመራ፣ ጨረቃ ብቻም አይደለሽም .... ሁለቱ ዓይኖችሽ በጨረቃዋ መሃል በውበቷ ላይ ውበት ሊጨምሩላት እንደተቀመጡ ፈርጥ ናቸው።
Related Channels
Other channels in the same section of the catalogue.
