Latest posts

Hanna Tekle
7 Oct 2025, 10:18
ነፍሴ ተስፋ ያደረገችህ ምትውልብህ ምታድርብህ ህያው ተስፋዬ - ልቤ አንተን አምኖ ልቤ ልቤ ባንተ ፀና ልቤ! ጓዳዬን ሙላው አደባባዬን ልኑር አንተን ስል ቀሪ ዘመኔን


Hanna Tekle
21 Sept 2025, 16:53



Hanna Tekle
14 Sept 2025, 14:55edited
‘መሥዋዕት ለእግዚአብሔር’ በዴንቨር Sep 27 @ Ethiopian Evangelical Church of Denverጌታ ቢፈቅድና ብንኖር በዚህ ቀን ጌታን በዝማሬ ለማምለክ ቀጠሮ ይዘናል! በዴንቨርና አካባቢው የምትገኙ ሁሉ ከእኛ ጋር ጌታን ለማምለክ ተጋብዛችኃል!እስከዚያው በፀሎት ከጐናችን ሁኑ! ተባረኩ!


Hanna Tekle
27 Aug 2025, 12:03
ዜማ ለክርስቶስ 🎶🎶🎶 ዜማ ቤተሰብእግዚአብሔር ስለእኛ እጅግ መልካም ነው!በዘመናችን ሁሉ የእርሱን በጐነት እናወራለን!ገና በጠዋት እድሜ እውቀት ሳይኖረን ለአገልግሎቱ ታማኝ አድርጎ ከየስፍራችን የጠራን አምላክ እርሱን ለማገልገል ሕብረት ስላደረገን እጅግ ደስ ይለኛል! በብዙ ፍሬ እየባረከ እያስተማረ እያሳደገ እዚህ ጋር ላደረሰን አምላካችን እግዚአብሔር ክብር ይሁንለት! ከዝማሬ አገልግሎት ባለፈ ደግሞ በነዚህ ሁሉ አመታት ሳይለየን ቤተሰብ ስላደረገን ጌታችን ይመስገን! እኔ በግሌ የአገልግሎት ጅማሬዬንና የወጣትነት ዘመኔን በዚህ ሕብረት ውስጥ በማሳለፌ የተጠቀምኩትም የተማርኩትም ብዙ ነውና ጌታዬንም አመሰግናለሁ!እግዚአብሔር በእኛ ሕይወት ስላደረገው መልካምነት ምስጋናችን ብዙ ነው!ዜማዎችዬ እወዳችኃለሁ በረከቶቼ ናችሁ!እንደዘመርነው ጌታ እስከፍፃሜ በቤቱ ያዘምረን ይጠብቀን አይለየን! ውድ ወዳጆቻችን እንደጌታ ፈቃድ እንደዜማ ለክርስቶስ ከፊታችን የምናስባቸው የጋራ ፕሮጀክቶች አሉን በፀሎት አስቡን! ተባረኩ!




Hanna Tekle
5 Aug 2025, 11:45edited
ነሐሴ 10 | August 16At Beza International Churchበቤዛ ዓለም አቀፍ ቤተ ክርስቲያን ከ10 ሰዐት ጀምሮ#ማጽናናትህ


Hanna Tekle
17 Jul 2025, 16:14
የሕይወት ምስክርነት ምሽት ከዝማሬ ጋር!“በወንጌል አላፍርም፤ ምክንያቱም ለሚያምን ሁሉ ለድነት የሚሆን የእግዚአብሔር ኀይል ነው፤ ይህም በመጀመሪያ ለአይሁድ፣ ቀጥሎም ለአሕዛብ ነው።” ሮሜ 1 : 16 NASV


Hanna Tekle
27 May 2025, 10:38
የፃድቁን ቤት በግፍ አትነቅንቀው! 👉ሚደረመሰው አንተው ላይ ነው!‘ኃጢአተኛ ጻድቁን ይመለካከተዋል፥ ጥርሱንም በእርሱ ላይ ያንገጫግጫል። እግዚአብሔር ይሥቅበታል፥ ቀኑ እንደሚደርስ አይቶአልና።’መዝሙር 37፡12-13Channel photo updated
11 May 2025, 09:16

Hanna Tekle
28 Apr 2025, 15:46
‘ሕይወቴን አገኘህ’በቅርብ ቀን


Hanna Tekle
21 Apr 2025, 08:42
ትናንትና ዛሬ … OUT NOW❣️❣️❣️ መልካም የትንሳኤ በዓል ትንሳኤ ከሆነላት ነፍስ በወጣ የምስክርነት ዝማሬ ጋር።የተወደድሽ እህቴ ዘሪቱ እንኳን ጌታ ረዳሽ በሕይወት ፈተና ላይ በርትተሽ እንድትቆሚና እንደዚህ ቆመሽ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ሕይወትና የእርሱን በጐነት በዝማሬ እንድታውጂ ፀጋው ስለበዛልሽ እግዚአብሔር ይመስገን!ያፀናሽ እግዚአብሔር ድኖ በሚፀና ትውልድ ይባርክሽ!እወድሻለሁ!ትናንት በዚህ ጊዜ ትናንት በዚህ ሰዓት ትናንት በጨለማ ትናንት በክፋት ነበረ ሕይወቴ ከብርሀኑ ማዶ ጌታ እስኪታደገኝ ሊያስመልጠኝ ወዶ ትናንት ሽብር ነበር ያለመረጋጋት ለነፍሴ ማረፊያ ከለላ በማጣት ግን አለፈ ትናንት ላልመለስበት ኢየሱስ አገኘኝ በማይጥለው ምህረት ዛሬ እኔ ደህና እረፍት ያገኘው ሰው እግዚአብሔር ይመስገን ይህን ያደረገው!!!በዚህ በትክክለኛው https://youtu.be/h6szR48vovo?si=gctloLoax4rMfZLM ዝማሬውን ያገኙታል። Zeritu Kebede


Hanna Tekle
16 Apr 2025, 18:44
ኃጢአቱን የሚሰውር አይለማም፤ የሚናዘዝባትና የሚተዋት ግን ምሕረትን ያገኛል። ምሳሌ 28:13በዚህ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የሕማማት ሳምንት የተከፈለልንን የህይወት ዋጋ እያሰብን ለዚህ የከበረ የሕይወት ዋጋ የምስጋና ምላሽ ይሆን ዘንድ በምን አይነት የሕይወት መንገድ ላይ እንዳለን እየመረመርን ከየትኛውም እርሱ ከማይከብርበትና ካልከበረበት ከሚያዝንበትና ካዘነበት አካሔድ በንስሀ ለመመለስ ዛሬ እንወስን!ውለታውን በቃላት ከመናገርና ከመመስከር ባለፈ የተግባር ምላሽ ከእኛ ብዙ ከተከፈለልን ከውድ ልጆቹ ይጠበቃል!መልኩን በመምሰል በሕይወት በብርሀን በመመላለስ መዳናችንን ዕለት ዕለት እንድንፈፅም ተጠርተናል! እንደግለሰብ እንደቤተሰብ እንደቤተክርስቲያንና እንደሀገር ከየት እንደወደቅን እያሰብን በንስሐ ፊቱ በመቅረብ ለዚህ ሀገራዊ የንስሐ ጥሪ ምላሽ እንስጥ!ተራራው ዝቅ ይበል-ሸለቆው ከፍ ይበል ስርጓጉጡም ሜዳ ይሁን ጠማማውም ይቅና ስጋ ለባሽ ሁሉ የእግዚአብሔርን ማዳን እንዲያይ!!


Hanna Tekle
13 Apr 2025, 14:23
እግዚአብሔር ይመስገን!ማጽናናትህ New Live album Coming soon! Zeritu Kebede


Hanna Tekle
16 Feb 2025, 16:14
ለልቤ እንደመከራዋ ብዛት ማጽናናትህ ነፍሴን ደስ አሰኛት!ብርታቴ ሆይ እወድሀለሁ!


Hanna Tekle
9 Feb 2025, 05:42
Congratulations to Prophet tilahun tsegaye / ecrc🎊🎊🎊🎊🎊🎊🎊🎁🎁🎁🎁🎁🎁🎁🎁🎁በዚህች ቤተክርስቲያን ላይ ስለበዛው ደግነት እግዚአብሔር ይመስገን!እግዚአብሔር በእውነት ለሚጠሩት እጅግ ቅርብ ነው! የተወደድከው ወንድሜ ነብይ ጥሌ እና ውድ ባለቤቱ ፍሬ አንዲሁም የEverlasting Christ Revelation Church አባላትና መሪዎች ደስታችሁ ደስታችን ነው እንኳን ደስ አላችሁ! ይህች የምንወዳት ቤተክርስቲያን በእግዚአብሔር ደስታ ሀይል የሚሆንላት ፍቃዱን የምታስቀድም ነፍሳት የሚድኑባት የክርስቶስ መልክ ገኖ ሚታይባት የባዘኑትን የምትመልስ የጠፉትን የምትመልስ የተሰበሩትን የምትጠግን የደከሙትን የምታፅናና ሰውን ሁሉ በእኩል የምትወድ የክርስቶስ ቤተክርስቲያን ትሁንልን!!




Hanna Tekle
5 Feb 2025, 15:52
““ለታማኝ ሰው ታማኝ መሆንህን፣ ለፍጹም ሰው ፍጹም መሆንህን ታሳያለህ። ለንጹሕ ሰው አንተም ንጹሕ መሆንህን፣ ለጠማማ ሰው ግን አንተም ጠማማ መሆንህን ታሳያለህ።”2 ሳሙኤል 22 : 26 - 27
Hanna Tekle
28 Jan 2025, 14:51
እውነት እና ፍቅር! ፍቅር የሌለበት እውነት ያፈርሳል! እውነት የሌለበት ፍቅር ይፈርሳል!Unknown Source
Hanna Tekle
11 Jan 2025, 18:12
"መሥዋዕት ለእግዚአብሔር" ነገ ጥር 4 ከ7:00 ሰዓት ጀምሮበሚሊንየም አዳራሽውድ ቤተሰቦቼ ነገ እግዚአብሔርን በእውነትና በመንፈስ ለማምለክና ለማመስገን በተዘጋጀ መንፈስ እንገናኝ! አዳዲስ ሰዎችን በመጋበዝ እንድትገኙ ስል ሁላችሁንም በአክብሮት እጋብዛችኃለሁ ተባረኩ! ዮሐንስ 4:24 “እግዚአብሔር መንፈስ ነው፤ የሚሰግዱለትም በመንፈስና በእውነት ሊሰግዱለት ይገባል።”




Hanna Tekle
6 Jan 2025, 16:35
"መሥዋዕት ለእግዚአብሔር" ጥር 4 እሁድ ከሰዓት በሚሊንየም አዳራሽ "የሰማይ አምላክ ያከናውንልናል፥ እኛም ባሪያዎቹ ተነሥተን እንሠራለን፤" ነህምያ 2:20ጌታ ቢፈቅድና ብንኖር ጥር 4 በሚሊንየም አዳራሽ "መሥዋዕት ለእግዚአብሔር" በተሰኘ መሪ ቃል ምስጋናና አምልኮ የሚገባውን አምላካችንን እግዚአብሔርን ለማመስገንና ለማምለክ ቀጠሮ ይዘናል!እስከዚያው ሁላችሁም በፀሎት እንድታስቡን እንጠይቃለን!


Hanna Tekle
28 Dec 2024, 14:04
ዝም ብዬ እቆማለሁ ሰልፉን ላንተ እለቃለሁ!!ወገኖቼ የእግዚአብሔርን ጦርነት በስጋችሁ አትዋጉ እናንተ ዝም በሉ!


Hanna Tekle
26 Nov 2024, 16:18
"መሥዋዕት ለእግዚአብሔር"ጥር 4 እሁድ ከሰዓት በሚሊንየም አዳራሽ"የሰማይ አምላክ ያከናውንልናል፥ እኛም ባሪያዎቹ ተነሥተን እንሠራለን፤" ነህምያ 2:20 ጌታ ቢፈቅድና ብንኖር ጥር 4 በሚሊንየም አዳራሽ "መሥዋዕት ለእግዚአብሔር" በተሰኘ መሪ ቃል ምስጋናና አምልኮ የሚገባውን አምላካችንን እግዚአብሔርን ለማመስገንና ለማምለክ ቀጠሮ ይዘናል! እስከዚያው ሁላችሁም በፀሎት እንድታስቡን እንጠይቃለን!"ምስጋና የሚሠዋ ያከብረኛል፤ የእግዚአብሔርን ማዳን ለእርሱ የማሳይበት መንገድ ከዚያ አለ።” መዝሙር 50:23 በምስጋና የብዙ ጥያቄ ድል አለ በምስጋና ፊቱ እንቅረብ!የዚህን ፕሮግራም ሙሉ ወጪ በራስ ተነሳሽነትና ፍቃደኝነት በመሸፈን የተባበረኝ El-hadar Engineering PLC ሲሆን APEX Events ደግሞ ሙሉ ዝግጅቱን በማስተባበር ላይ ይገኛል!ስለእናንተ እግዚአብሔር ይመስገን!ክብር ሁሉ በነገር ሁሉ እየረዳኝ ላለ ለልዑል እግዚአብሔር ይሁን!እህታችሁ ዘማሪት ሀና ተክሌ ነኝ ተባረኩ!

Related Channels
Other channels in the same section of the catalogue.
