Latest posts

Harun Media - ሀሩን ሚዲያ
21 Sept, 08:45
የመስጂደል ሐረም ሙአዚን የነበሩት ሸይኽ ኢብራሂም አል-መደኒ ወደ አኼራ ተሻገሩ።• ሀሩን ሚዲያ | መስከረም 11 ቀን 2019 ዓ.ል«ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን!»የተከበሩት የመስጂደል ሐረም ሙአዚን ሸይኽ ኢብራሂም አል-መደኒ ዛሬ ንጋት ላይ (በፈጅር ሰዓት) ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ተገለጸ።በመዲና ከተማ ተወልደው ነገር ግን በተቀደሰችው የመካ ከተማ በመስጂደል ሐረም ውስጥ ባላቸው ያማረና ማራኪ የአዛን ድምፃቸው በስፋት የሚታወቁት ሸይኽ ኢብራሂም አል-መደኒ፤ የጀናዛ ሶላታቸው ዛሬ ከዐስር ሶላት በኋላ እንደሚሰገድ ታውቋል።አላህ (ሱ.ወ) ከፍተኛውን የጀነት ደረጃ (ፊርደውስን) እንዲወፍቃቸው ዱዓ እናደርጋለን።📅 ረቢዑስ ሳኒ 10 ቀን 1448 ዓ.ሂ© ሀሩን ሚዲያ


Harun Media - ሀሩን ሚዲያ
19 Sept, 08:23
ሂጅራ ባንክ በእጅዎ መዳፍ! አሁን በኦንላይን ይመዝገቡ! Baankii Hijraa Harka Keessan Irraa! Ammuma Karaa Onlaayinaatiin Galmaayaa!ሁሌም የሚመኙት ከወለድ ያልተነካካ የባንክ አገልግሎት… አሁን በእጅ ስልክዎ ላይ እውን ሆኗል!ባንካችን ተደራሽነቱን ለማስፋት በመላው አገሪቱ እያደረገ ከሚገኘው የቅርንጫፍ ማስፋፍያ በተጨማሪ ወደ ቅርንጫፎቻችን በአካል መምጣት ሳይጠበቅብዎ ምቾትዎ እንደተጠበቀ ካሉበት ሆነው የባንክ ሂሳብዎን በኦንላይን የሚከፍቱበትን ዘመናዊ መፍትሄ አቅርቦልዎታል፡፡የሞባይል ስልክዎን፣ ኮምፒውተሮን፣ ወይም ታብሌትዎን እንዲሁም የፋይዳ መለያ ቁጥርዎን ብቻ በመጠቀም! ጊዜዎን ቆጥበው በመመዝገብ ከእሴትዎ ጋር የተጣጣሙ አገልግሎቶቻችንን ይጠቀሙ፡፡አሁኑኑ https://accounts.hijra-bank.com ን በመጫን ወይም በልጥፉ ላይ የሚገኘውን ኪው አር ኮድ ስካን አድርገው አስፈላጊው መረጃ በመሙላት በቀላሉ የሂጅራ ባንክ ቤተሰብ በመሆን ውደ ብሩህ ተስፋ አብረውን ይጓዙ፡፡ሂጅራ ባንክ ጉዞ ወደ ብሩህ ተስፋ!


Harun Media - ሀሩን ሚዲያ
18 Sept, 16:37
በወራቤ ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ነፃ የዓይን ምርመራ እና የሞራ ግርዶሽ ቀዶ ሕክምና ሊሰጥ ነው!• ሀሩን ሚዲያ | መስከረም 8 ቀን 2019 ዓ.ልአል-በስር ኢንተርናሽናል ፋውንዴሽን የተሰኘው የሳዑዲ ዓረቢያ ግብረ ሰናይ ድርጅት፤ ከወራቤ ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ጋር በመተባበር ነፃ የዓይን ምርመራ እና የዓይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ሕክምና አገልግሎት ሊሰጥ መሆኑን አስታወቀ።ድርጅቱ እንዳስታወቀው፤ ይህ ሰብዓዊ የሕክምና መርሃ ግብር ከመስከረም 18 ቀን 2019 ዓ.ል ጀምሮ ለተከታታይ 6 ቀናት በወራቤ ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ውስጥ የሚሰጥ ይሆናል።በመሆኑም በወራቤ ከተማና አካባቢው የምትገኙ ማንኛውም የዓይን ህመም ችግር ያለባችሁ የማኅበረሰብ ክፍሎች፤ በተጠቀሱት ቀናት በሆስፒታሉ በመገኘት የነፃ የዓይን ምርመራ እና የዓይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ሕክምና አገልግሎቱን ማግኘት የምትችሉ መሆኑን ሆስፒታሉ በአክብሮት ጥሪውን አስተላልፏል።📅 ረቢዑስ ሳኒ 7 ቀን 1448 ዓ.ሂ© ሀሩን ሚዲያ


Harun Media - ሀሩን ሚዲያ
18 Sept, 12:51
ክፍት የስራ ቦታ ማስታወቂያ #የሂሳብ ሰራተኛ (Accountant) የሚያስፈልጉ መስፈርቶች፦ • ጾታ ሴት • ቢያንስ 1 ዓመት የሂሳብ ትምህርት (Diploma) ያላት • Online E-Tax Report የማዘጋጀትና የመላክ እውቀት ያላት • በአዲሱ የግብር ህግ (New Tax Law) ላይ ጥሩ ግንዛቤ ያላት • መሰረታዊ የኮምፒውተር እውቀት ያላት • ሙሉ ጊዜ (Full-time) መስራት የምትችል • የመኖሪያ ቦታዋ ለስራ ቦታ ቅርብ የሆነ • የስራ ቦታ: አዲስ አበባ, ጀሞ3 አካባቢ ለማመልከት CV እና አስፈላጊ ሰነዶችን በTelegram @harunmedHr ይላኩ © ሀሩን ሚዲያ


Harun Media - ሀሩን ሚዲያ
15 Sept, 14:40
በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል መተከል ዞን ዳንጉር ወረዳ በሙስሊሞች ላይ የሚፈጸመው ጥቃት አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱ ተገለጸ!• ሀሩን ሚዲያ | መስከረም 5 ቀን 2019 ዓ.ልበቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል መተከል ዞን፣ ዳንጉር ወረዳ በእስልምና እምነት ተከታዮች ላይ የሚፈጸመው ጥቃት አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን የወረዳው መጅሊስና የአካባቢው ነዋሪዎች አስታወቁ።በተለይም ጳጉሜ 1 እና 2 ቀን 2018 ዓ.ል ሰብልና ከብቶችን ለመዝረፍ በሞከሩ ታጣቂዎች በተፈጸመ ጥቃት፤ 8 ንጹሐን ሲገደሉ 6 ሰዎች ደግሞ ቆስለው በባህር ዳርና በፓዊ ሆስፒታሎች ሕክምና እየተከታተሉ ይገኛሉ።በጥቃቱም ከ350 በላይ ከብቶች መዘረፋቸውን የገለጹት ነዋሪዎቹ፤ ከ2014 ዓ.ል ጀምሮ በጃቫ፣ ባምባ ጅሃ፣ ቡርጂ፣ ቦረንዳ ቀበሌዎችና ባኩስታን ጎጥ አካባቢዎች ዘረፋና ግድያዎች በመባባሳቸው በርካታ የእስልምና እምነት ተከታዮች ከመኖሪያቸው መፈናቀላቸውን ጠቁመዋል።በ2018 ዓ.ል መጀመሪያ አካባቢ በተፈጸመ ተመሳሳይ ጥቃት 6 ሰዎች መገደላቸውንና በመስጂዶች ላይም የማቃጠልና የማውደም ተግባር መፈጸሙን ያስታወሱት ነዋሪዎቹ፤ በቅርቡ የደረሰውን ጥቃት ተከትሎ የአካባቢው ሙስሊም ማኅበረሰብ ለ3 ቀናት የሥራ ማቆም አድማ በማድረግ ቁጣውን መግለጹንና ፍትሕ መጠየቁን አሳውቀዋል።የዳንጉር ወረዳ መጅሊስ በንጹሐን ላይ የሚደርሰው ጥቃት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ መምጣቱን የሚያሳይ ደብዳቤ ለዞንና ለክልል ጽ/ቤቶች የላከ ሲሆን፤ የአካባቢው ነዋሪዎችም በብሔርና በሃይማኖት ሽፋን በሙስሊሞች ላይ ያነጣጠሩ ጥቃቶች በአስቸኳይ እንዲቆሙና መንግሥት አፋጣኝ




Harun Media - ሀሩን ሚዲያ
15 Sept, 10:52
«የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የትምህርት ተሳትፎ ከትላንት እስከ ዛሬ» በሚል መሪ ቃል በደሴ ከተማ የፓናል ውይይትና የዳዕዋ መድረክ ተካሄደ!• ሀሩን ሚዲያ | መስከረም 5 ቀን 2019 ዓ.ልበደሴ ከተማ «የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የትምህርት ተሳትፎ ከትላንት እስከ ዛሬ» በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ልዩ የፓናል ውይይትና የዳዕዋ መድረክ ተካሂዷል።ይህ መድረክ በደሴ ሙስሊም ወጣቶች ካውንስልና በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት ትብብር የተዘጋጀ ሲሆን፤ የኢትዮጵያ ሙስሊም ማኅበረሰብ የትምህርት ጉዞ ከታሪካዊ ፈተናዎች አንስቶ እስከ ዛሬው ዘመን ያለው ዕድገት ምን እንደሚመስል ሰፊ ዳሰሳ ተደርጎበታል።በፓናል ውይይቱ ላይ የእስልምና ዕውቀትንና ዘመናዊ ትምህርትን ማቀናጀት፣ ወጣቱን ትውልድ በዕውቀትና በሥነ-ምግባር (ተርቢያ) ማነጽ፣ እንዲሁም የማኅበረሰቡን የትምህርት ተሳትፎ ይበልጥ ለማሳደግ የሚያስችሉ ቁልፍ አቅጣጫዎች በስፋት ተነስተዋል።በተጨማሪም ዕውቀት ለትውልድ ግንባታና ለማኅበረሰብ ዕድገት ያለውን ወሳኝ ሚና በማስገንዘብ፤ በቀጣይ የትምህርት ተሳትፎን በማሳደግ ረገድ ሁሉም አካል የጋራ ኃላፊነቱን እንዲወጣ ጠቃሚ ግንዛቤ የፈጠረ መድረክ መሆኑ ተመላክቷል።📅 ረቢዑስ ሳኒ 4 ቀን 1448 ዓ.ሂ© ሀሩን ሚዲያ




Harun Media - ሀሩን ሚዲያ
13 Sept, 16:31
ታላቁ የሸይኽ ሙሐመድ አሊ አደም የቁርኣን ሂፍዝና ኢስላማዊ ተርቢያ ማዕከል ከ50 በላይ ተማሪዎችን በድምቀት አስመረቀ!• ሀሩን ሚዲያ | መስከረም 3 ቀን 2019 ዓ.ልመርከዝ ሸይኽ ሙሐመድ አሊ አደም የቁርኣን ሂፍዝና ኢስላማዊ ተርቢያ ማዕከል በቁርኣን ሂፍዝ፣ ቃዒዳና ሌሎች የኢስላማዊ ትምህርቶች ሲያስተምራቸው የቆዩ 58 ተማሪዎችን በድምቀት አስመርቋል።ከተመራቂ ተማሪዎቹ መካከል 15ቱ ቁርኣንን ሙሉ ለሙሉ ያጠናቀቁ (ሐፊዞች) ሲሆኑ፣ ቀሪዎቹ 43 ተማሪዎች ደግሞ በክረምት መርሃ ግብር ቁርኣንና ሌሎች ኢስላማዊ ትምህርቶችን ሲከታተሉ የቆዩ መሆናቸው ተገልጿል።በምረቃ መርሃ ግብሩ ላይ በተማሪዎቹ የተዘጋጁ ውብ የቁርኣን ቲላዋዎች፣ የተጅዊድ ግጥሞች፣ ኹጥባዎች፣ ዳዕዋዎችና ልዩ ልዩ ኢስላማዊ ምክር አዘል ፕሮግራሞች ቀርበዋል። በተጨማሪም በተማሪዎቹ መካከል ከፍተኛ ፉክክር የታየበት የቁርኣን ውድድር ተካሂዷል።ሸይኽ ሙሐመድ አሊ አደም አል-ኢትዮጵያዊ ሀገራችንን በዓለም አቀፍ ደረጃ ያስተዋወቁ ታላቅ ዓሊም ሲሆኑ፤ ሸይኽ ኢብኑ ባዝ፣ ሸይኽ ፈውዛንና ሸይኽ ኢብኑ ዑሰይሚንን ጨምሮ ታላላቅ የዓለማችን ዑለማዎች በሐዲስና በኢስናድ ዕውቀታቸው የላቀ ደረጃ እንደነበራቸው የመሰከሩላቸው ታላቅ አባት ናቸው። ማዕከሉም በእኚህ ታላቅ ሸይኽ ስም ሲሰየም ይህንን ፈለግ የሚከተሉ ትውልዶችን ለማፍራት በማለም መሆኑ ተነግሯል።ታላላቅ ዑለማዎችና መሻይኾች በተገኙበት ይህ የ2018 ዓ.ል የአዳሪና የክረምት መርሃ ግብር የቁርኣን ተማሪዎች ምረቃ በከፍተኛ ክብርና ድምቀት በማጠናቀቅ ለ2019 አዲስ አዳሪ ተማሪዎች ምዝገባ




Harun Media - ሀሩን ሚዲያ
12 Sept, 17:44
በክረምት መርሃ ግብር የቁርኣን ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ ከ100 በላይ መስማት የተሳናቸው ሙስሊሞች በድምቀት ተመረቁ!• ሀሩን ሚዲያ | መስከረም 2 ቀን 2019 ዓ.ልየኢትዮጵያ መስማት የተሳናቸው ሙስሊሞች ማኅበር በክረምት መርሃ ግብር ሲያስተምራቸው የቆዩ 107 መስማት የተሳናቸው ተማሪዎችን በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አዳራሽ በድምቀት አስመርቋል።ማኅበሩ ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ሕጋዊ ፈቃድ ወስዶ እየተንቀሳቀሰ የሚገኝ ተቋም ሲሆን፤ በሀገራችን የሚገኙ መስማት የተሳናቸው ሙስሊሞችን ሸሪዓዊና አካዳሚያዊ ዕውቀቶችን ተደራሽ ለማድረግ በትኩረት እየሠራ ይገኛል።በዛሬው ዕለት በተካሄደው የምረቃ መርሃ ግብር ላይ የጠቅላይ ምክር ቤቱ የሥራ አስፈጻሚ አባላት፣ ኡስታዞች፣ የማኅበሩ የሥራ ኃላፊዎች፣ የተማሪ ወላጆችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።ማኅበሩ እንዳስታወቀው፤ የክረምት መርሃ ግብራቸውን በስኬት አጠናቅቀው ከተመረቁት 107 መስማት የተሳናቸው ሙስሊም ተማሪዎች መካከል 60ዎቹ ሴቶች ሲሆኑ፣ ቀሪዎቹ 47ቱ ደግሞ ወንዶች ናቸው።📅 ረቢዑስ ሳኒ 1 ቀን 1448 ዓ.ሂ© ሀሩን ሚዲያ




Harun Media - ሀሩን ሚዲያ
12 Sept, 11:57
ማኅበረሰቡንና መጅሊሱን ይበልጥ ለማጠናከር ያለመው የሀላባ ዞን ሙስሊም ወጣቶች ካውንስል በቁሊቶ ከተማ በደማቅ ሁኔታ ተመሠረተ!• ሀሩን ሚዲያ | መስከረም 2 ቀን 2019 ዓ.ልየማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሙስሊም ወጣቶች ካውንስል፤ የወጣቶችን አቅም በሕጋዊ ማዕቀፍ ለማስተባበር ያለመውን የሀላባ ዞን ሙስሊም ወጣቶች ካውንስል የምሥረታ ጉባኤ በቁሊቶ ከተማ በስኬት አካሂዷል።በምሥረታ መርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የሀላባ ዞን እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ዋና ሰብሳቢ ሸይኽ ሁሴን መሐመድ ቃበቶ፤ ወጣቶች ያላቸውን ሰፊ አቅምና ችሎታ በማኅበረሰቡ ልማትና ዕድገት ላይ በአግባቡ ሊያውሉት እንደሚገባ አሳስበዋል።የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ተወካይ ሸይኽ ዑመር ሙስጠፋ በበኩላቸው፤ ወጣቶች ጠንካራ ተቋም በመመሥረት መጅሊሱንና ማኅበረሰቡን በሚያጠናክር መልኩ በንቃት መንቀሳቀስ እንደሚገባቸው መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።የክልሉ ሙስሊም ወጣቶች ካውንስል ፕሬዚዳንት ወጣት አብዲከሪም ኑሪ እንዳብራሩት፤ የወጣቶችን ጉልበትና አቅም በሕጋዊ ተቋም ማደራጀትና ለማኅበረሰቡ ጠቃሚ በሆነ መልኩ መጠቀም ወሳኝ ነው። ለዚህም ሲባል በክልልና በፌዴራል ደረጃ የሙስሊም ወጣቶች ካውንስሎች ተጠናክረው እየተቋቋሙ መሆኑን ገልጸዋል።በዚህ ታሪካዊ የምሥረታ መርሃ ግብር ላይ የክልሉ የዑለማ ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት ሸይኽ ሐጂ ዩሱፍ ሁሴን፣ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ዑለማ ምክር ቤት አባልና የሀላባ ተወካይ ሸይኽ ሐጂ ሽፋ መሐመድ፣ የሀላባ ዞን እስልምና ጉዳዮች ዑለማ ምክር ቤት ዋና ጸሐፊ




Harun Media - ሀሩን ሚዲያ
12 Sept, 09:39
ሳዑዲ ዓረቢያ ያለ አሜሪካ ቀጥተኛ ተሳትፎ በሁቲዎች ላይ ሰፊ ወታደራዊ ዘመቻ ልትከፍት እንደምትችል ጠቆመች!• ሀሩን ሚዲያ | መስከረም 2 ቀን 2019 ዓ.ልሳዑዲ ዓረቢያ የአሜሪካ ቀጥተኛ ተሳትፎ ባይኖርም እንኳ በየመን ሁቲዎች ላይ ሰፊ ወታደራዊ ዘመቻ ልትከፍት እንደምትችል ፍንጭ መስጠቷን አንድ የአሜሪካ ባለስልጣን መግለጻቸውን ኤቢሲ ኒውስ ዘገበ።ሪያድ እስካሁን የመጨረሻ ውሳኔ ላይ ባትደርስም፤ አልጋ ወራሽ ልዑል ሙሐመድ ቢን ሳልማን ሐሙስ ዕለት ከዶናልድ ትራምፕ ጋር ባደረጓቸው ሁለት የስልክ ምልልሶች አሜሪካ ቀጥተኛ ወታደራዊ ጣልቃ ገብነት እንድታደርግ ከፍተኛ ግፊት ማድረጋቸው ተገልጿል።ለጊዜው ዋሽንግተን የደህንነት መረጃዎችን በማጋራት እና የኢላማ ጥቆማ ድጋፎችን በማቅረብ ላይ ብቻ የተገደበች ሲሆን፤ በየመን ውስጥ ቀጥተኛ ወታደራዊ ጥቃት ለማካሄድ እስካሁን ምንም ዓይነት ዕቅድ እንደሌላት ምንጮች አክለው ጠቁመዋል።📅 ረቢዑል አወል 30 ቀን 1448 ዓ.ሂ© ሀሩን ሚዲያ


Harun Media - ሀሩን ሚዲያ
11 Sept, 07:38
https://youtu.be/Iwo1adu5TfI?si=j2JadvJNIJRrjOP8YouTubeከአስመሳይ ሰው ራቁ!ኡስታዝ ካሚል ጣሀ| አደራ!||@haruntube2HARUN MEDIA የሙስሊሙ ዑማ ቀዳሚ ድምጽ !
Harun Media - ሀሩን ሚዲያ
10 Sept, 16:23
የየመን ሁቲዎች ስትራቴጂካዊቷን የሞኻ ወደብ ከተማን ጨምሮ በምዕራብ የመን ሰፊ ግዛቶችን በቁጥጥራቸው ሥር ማዋላቸው ተገለጸ!• ሀሩን ሚዲያ | ጳጉሜን 5 ቀን 2018 ዓ.ልየየመኑ የሁቲ ታጣቂ ቡድን እጅግ ፈጣን በሆነ ወታደራዊ ዘመቻ ስትራቴጂካዊቷን የሞኻ ወደብ ከተማን ጨምሮ በምዕራብ የመን ወደ 2,600 ካሬ ኪሎ ሜትር የሚጠጋ ሰፊ ግዛት በቁጥጥሩ ሥር ማዋሉ ተገለጸ።ይህ ወታደራዊ እርምጃ በምዕራባዊ ጣይዝና እንዲሁም በደቡባዊ አል-ሁዳይዳ ግዛቶች ላይ ያነጣጠረ ሲሆን፤ በጦርነቱ ታሪክ ውስጥ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ከታዩት እጅግ ፈጣን የግዛት ለውጦች አንዱ እንደሆነ ተነግሮለታል። በተቃራኒው የመንግሥትና የብሔራዊ ተቃውሞ ኃይሎች ከሰፊው ግንባር በመውጣት ወደ አደን ማፈግፈጋቸው ተዘግቧል።ሁቲዎች በዚሁ ዘመቻ በቁጥጥራቸው ሥር ካዋሏቸው ዋና ዋና ቦታዎች መካከል ሀይስ፣ አል-ኻውኻህ፣ አል-ዋዚዒያህ፣ ማውዛ እና ከፍተኛ ወታደራዊ ጠቀሜታ ያለው የኻሊድ ኢብኑ አል-ወሊድ ወታደራዊ ካምፕ ይገኙበታል። የዚህ ፈጣን ዘመቻ ማሳረጊያ የሆነው ደግሞ በቀይ ባሕር ዳርቻ በመንግሥት ቁጥጥር ሥር የነበረችውን ዋነኛዋን የሞኻ ወደብ ከተማ መያዛቸው ነው።የዚህ እርምጃ ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ ምንድን ነው?ሞኻ ከ2017 መጀመሪያ አንስቶ በመንግሥትና በጥምረት ኃይሎች እጅ የነበረችና የታሪቅ ሳላህ ብሔራዊ ተቃውሞ ኃይሎች ዋነኛ ማዕከል ሆና አገልግላለች። ይህች ስትራቴጂካዊ ከተማ በሁቲዎች ቁጥጥር ሥር መውደቋ፣ ቡድኑ ዓለም አቀፍ የንግድ መርከቦችን እያስተጓጎለበት ለሚገኘው የባሕር መተላለፊያ ይበልጥ ቅርብ እንዲሆን


Harun Media - ሀሩን ሚዲያ
10 Sept, 08:22





Harun Media - ሀሩን ሚዲያ
10 Sept, 08:22
በቄራ ሰላም መስጂድ የሚገኘው ሰላም በጎ አድራጎት ተቋም ከ1.5 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ ለ400 የቲም ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ!• ሀሩን ሚዲያ | ጳጉሜን 4 ቀን 2018 ዓ.ልበአዲስ አበባ ቄራ ሰላም መስጂድ የሚገኘው 'ሰላም ወላጆቻቸውን በሞት ያጡ ሕፃናትና አረጋውያን የልማትና መረዳጃ ተቋም'፤ ለ2019 አዲሱ የትምህርት ዘመን ለ400 የቲም ተማሪዎች ያዘጋጀውን የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ መርሃ ግብር ዛሬ ጳጉሜን 4 ቀን 2018 ዓ.ል አከናውኗል።የተቋሙ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሳዳም ሀሰን እንዳስታወቁት፤ ተቋሙ በያዝነው የ2019 በጀት ዓመት ዘርፈ ብዙ የበጎ አድራጎትና የማኅበረሰብ ድጋፍ ሥራዎችን እያከናወነ ይገኛል። በዛሬው ዕለትም ለ400 የወላጅ አልባ ሕፃናት ከ1.5 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ የተደረገ ሲሆን፤ ከሚማሩበት ትምህርት ቤት ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ 6 ተማሪዎችም ልዩ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።ከዚህ በተጨማሪም ተቋሙ በግል ትምህርት ቤት ለሚማሩ 18 የወላጅ አልባ ልጆች 750 ሺህ ብር የሚያወጣ ዓመታዊ የትምህርት ክፍያ መሸፈኑ ተገልጿል። በተመሳሳይ ባሳለፍነው ወር 1.1 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ የአስቤዛ ድጋፍ ለተለያዩ ተጠቃሚዎች መደረጉ ተጠቁሟልከነገ ጀምሮ ደግሞ የትምህርት ቁሳቁስ ወጪን መሸፈን ለማይችሉ አቅመ ደካማ ቤተሰቦች በማስረጃ ላይ የተመሠረተ ድጋፍ የማድረግ ሥራ እንደሚጀመር በመርሃ ግብሩ ላይ ተገልጿል። ዋና ሥራ አስኪያጁ በዚህ ፕሮጀክት ለተሳተፉና ድጋፍ ላደረጉ አካላት በሙሉ ከልብ የመነጨ ምስጋናቸውን አቅርበው፤ በቀጣይም ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን የተለያዩ የበጎ አድራጎትና የማኅበረሰብ ድጋፍ ሥራዎችን እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል📅 ረቢዑል አወል 27 ቀን 1448 ዓ.ሂ © ሀሩን ሚዲያ



Related Channels
Other channels in the same section of the catalogue.
