gram news
የሕይወት እምሻው አጫጭር ታሪኮች/ Hiwot Emishaw channel avatar

የሕይወት እምሻው አጫጭር ታሪኮች/ Hiwot Emishaw

@hiwotwog

ሕይወት እምሻው የተወዳጆቹ ባርቾ፣ ፍቅፋቂ፣ ማታ ማታ፣ ለእርቃን ሩብ ጉዳይ፣ የቡና ቁርስ እና ዥዋዥዌ መጽሐፍት ደራሲ ናት። በዚህ መድረክ ወጎችን እና ልብ ወለዶችን ታቀርባለች።

ProjectsENReligion

7,250subscribers

Open the Channel

Latest posts

  • የሕይወት እምሻው አጫጭር ታሪኮች/ Hiwot Emishaw

    22 Sept, 07:46

    ( ከላይ የቀጠለ)++++ በግነት ቃላት እያወደሰችኝ ከቆየች በኋላ አስተናጋጁ ተንቀልቅሎ ወደ እኛ መጣ።(ቀትረ ቢስ! ሳይጠራ ማን «ና» አለው…?)ቤቱ ወስዶ በነፃ እንደሚጋብዘው እንግዳ አጎንብሶ “ምን ጎደለ?” ሲል፣ «መንገጭላውን ባልኩት›› ስል “ሚክስድ ጁስ አለ ወይ?” ብላ ጠየቀችው።ቀና ብዬ አየሁት። በአንድ በኩል «በእርግጠኝነት ጁስ አይሰሩም» ብዬ አሰብኩ፤ ውድ ሬስቶራንት እንጂ የሰፈር ጁስ ቤት አይደል።በሌላ በኩል «ስለ ወንድ ልጅ አምላክ» የሚሉ ጭንቅ የተሞሉ ዓይኖቼን አይቶ «ቢኖርም የለም ይላታል» ብዬ ገመትኩ፡፡አምስት ዓይነት ጁስ እንዳላቸው ተናገረ።“በቃ ሚክስዱን አምጣልኝ” አለች ቀና ብላ እያየችው።ከውኃዬ የቀረውን እንጥፍጣፊ ጠጣሁ።
    984531231Open in Telegram
  • የሕይወት እምሻው አጫጭር ታሪኮች/ Hiwot Emishaw

    22 Sept, 07:45

    ምሳው (የ Somerset Maugham “The Luncheon” እንደልቤ ትርጉም)÷÷÷÷×ድግሱ ላይ ከሩቅ ሳያት «እሷ ናት፤ አይደለችም?» እስክል ድረስ ግር አለኝ።ካየኋት በጣም ቆይቶ ስለነበር፣ አፏ ስለጠበባቸው ከንፈሮቿን ገፍተውናብከፍተው ሁሌ ፈገግ ያለች የሚያስመስሏትን ትላልቅ ጥርሶቿን ባላይ እና አንድ ሰው በስሟ ሲጠራት ባልሰማ ኖሮ «እሷ አይደለችም» ብዬ ወደ ጨዋታዬ እመለስ ነበር።በዚህ ላይ ከማውቃት እጅግ ሰብታለች።የጋለ ሰላምታ አቀረበችልኝ።“ወይ ጉድ! ከተገናኘን ሦስት ወይም አራት ዓመት ይሆናል፤ አይደል? ጊዜው ግን እንዴት ይነጉዳል!” አለችኝ።ጭንቅላቴን በስምምነት ነቀነቅኩ።“ለመሆኑ የተገናኘንበትን ቀን ታስታውሳለህ? ምሳ ጋብዘኸኝ ነበር” አለችኝ።ያንን ምሳ እንዴት አላስታውሰውም?
    906179Open in Telegram
  • የሕይወት እምሻው አጫጭር ታሪኮች/ Hiwot Emishaw

    21 Sept, 16:50edited

    ድግሱ ላይ ከሩቅ ሳያት «እሷ ናት፤ አይደለችም?» እስክል ድረስ ግር አለኝ።ካየኋት በጣም ቆይቶ ስለነበር፣ አፏ ስለጠበባቸው ከንፈሮቿን ገፍተው ከፍተው ሁሌ ፈገግ ያለች የሚያስመስሏትን ትላልቅ ጥርሶቿን ባላይ እና አንድ ሰው በስሟ ሲጠራት ባልሰማ ኖሮ «እሷ አይደለችም» ብዬ ወደ ጨዋታዬ እመለስ ነበር።በዚህ ላይ ከማውቃት እጅግ ሰብታለች።የጋለ ሰላምታ አቀረበችልኝ።“ወይ ጉድ! ከተገናኘን ሦስት ወይም አራት ዓመት ይሆናል፤ አይደል? ጊዜው ግን እንዴት ይነጉዳል!” አለችኝ።ጭንቅላቴን በስምምነት ነቀነቅኩ።“ለመሆኑ የተገናኘንበትን ቀን ታስታውሳለህ? ምሳ ጋብዘኸኝ ነበር” አለችኝ።ያንን ምሳ እንዴት አላስታውሰውም? 🎁🎁🎁🎁 ሙሉውን ነገ ይጠብቁ፡፡
    1,370video276Open in Telegram
  • የሕይወት እምሻው አጫጭር ታሪኮች/ Hiwot Emishaw

    20 Sept, 14:31

    የተወደዳችሁ!ለእርቃን ሩብ ጉዳይ እና የቡና ቁርስ ለሶስተኛ ጊዜ ታትመው ጃፋር ገብተዋል።
    2,000video291272Open in Telegram
  • የሕይወት እምሻው አጫጭር ታሪኮች/ Hiwot Emishaw

    19 Sept, 12:19

    ‹‹ቢጫው ሹራብ››መቅደላ -----ቢጫውን ሹራብ ገዝቼላት ወደ ሜሎና ቤት ስደርስ፣ ዝናብ መጣሁ እያለ ማስፈራራት ጀመረ፡፡ሳሎን ከመግባታችን የቤቱን ጸጥታ ሳይ ብቻዋን መሆኗን፣ እና እናቷ አዲስ ዓለም ዘመድ ጥየቃ ስለሄዱ እስከ እሁድ እንደማይመለሱ ነገረችኝ።ባለ አንድ መቀመጫው ሶፋ ላይ ልቀመጥ ስሰናዳ፣ ሹራቡ ያለበትን ፌስታል ወዳስቀመጠችበት የመመገቢያ ጠረጴዛ ደጋግማ እያየች፣“ሻይ ላፍላ… ወይስ…?” አለችኝ። “አንቺን ደስ ያለሽን” አልኳት በተቀመጥኩበት እየተመቻቸሁ።“ሻዩን ማፍላት አፈላልሃለሁ” አለች እየተቅለሰሰለች። “ከዛ በፊት ግን አንድ ነገር ልንገርህ?” “ንገሪኝ።” “ይሄን ያመጣህልኝ ቢጫ ሹራብ ለመለካት ጓጓሁ… የእንቁጣጣሽ ዕለት ልብስ እንደተገዛላት ህጻን ልጅ ሰራኝ…” “ሃሃሃ…” “እንደ ልጅ አረገኝ አይደል…?” “እንደ ልጅ መሆን እኮ ችግር የለውም፡፡ ችግር ያለው የልጅ ስራ ካልሰራሁ ማለት ነው፡፡”
    1,9207016321Open in Telegram
  • የሕይወት እምሻው አጫጭር ታሪኮች/ Hiwot Emishaw

    16 Sept, 11:03

    ( ከላይ የቀጠለ)+++++ሜሎና እንደወትሮዋ ከመሸ ወደ ቤት ተመለሰች። ግድግዳውን ደገፍ ብሌ ጫማዋን በሩ ጋር አወለቀች። ቦርሳዋን በሩ አጠገብ ያለው ማንጠልጠያ ላይ ሰቀለች።ሶፋ ላይ በተቀመጥኩበት ጠጋ ብላና ጉንጬ ላይ እየሳመችኝ፣«ሄይ፣ እንዴት ነህ?» ብላኝ አሁን አሁን ደብል ሺፍት ሰርታ ስትመጣ እንደምትሆነው እየተንጠራወዘች ወደ መኝታ ቤት ገባች።ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ከሩቅ ስትጠራኝ ሰማሁ።«ሳሚ… ሳሚዬ?» «ወዬ?» «ሁዲዬን አይተኸዋል?»ገና በሩን ከፍታ ስትገባ፣ ገና ስማኝ ስታልፍ፣ ገና ወደ መኝታ ክፍላችን ስታቀና ይሄ ጥያቄ እንደሚመጣ ስላወቅኩ መልስና አኳሃኔን ለማስተካከል ብዙ ሳሰላስል ነበር፡፡ አይኖቼ ቴሌቪዥን ላይ፣ ሃሳቤ ግን እሷ ጋር ሆኖ፡፡
    2,84095115442Open in Telegram
  • የሕይወት እምሻው አጫጭር ታሪኮች/ Hiwot Emishaw

    16 Sept, 11:01edited

    ቢጫው ሹራብ---ሳሚ-----ሜሎና ወደ አሜሪካ ስትመጣ፣ ከኢትዮጵያ ጠቅልሎ ወደ አሜሪካ እንደሚጓዝ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ሻንጣ ሙሉ ሽሮ እና በርበሬ፣ በረዶ ያዘለ የዶሮ ወጥ፣ የአጥሚት እህልና ድርቆሽ ይዞ ከመምጣት ይልቅ ብዙ መጻሕፍትና በአውሮፕላን አትላንቲክ ውቂያኖስን መሻገር ያልነበረባቸው እዚህ ግቡ የማይባሉ ኮተተችን ተሸክማ ነበር የመጣችው።እንቅልፏን አስተካክላ ሻንጣዋን መፍታት ስንጀምር ይሄንኑ ነገርኳት።«እኔ የምለው ሜሉ… ይሄን ሁሉ መጽሐፍ ለምን ተሸክመሽ መጣሽ?» አልኳት፡፡ ወለሉ ላይ ዝርፍጥ ብላ ከሻንጣው ዕቃ ማውጣቷን ተወችና ቀና ብላ አይታኝ፣ «የትኞቹን?»አለችኝ፡፡ «ሁሉንም» አልኩና መጽሐፍቱን ተራ በተራ ከሻንጣዋ አወጣሁ፡፡ከአድማስ ባሻገር። ኦሮማይ። ፍቅር እስከ መቃብር። ግራጫ ቃጭሎች። ዶክተር አሸብር። ልጅነት። ማታ ማታ።
    2,250442Open in Telegram
  • የሕይወት እምሻው አጫጭር ታሪኮች/ Hiwot Emishaw

    16 Sept, 06:24

    የተወደዳችሁ!የ2018 መገባደጃ ላይ ብቸኛዋ እህቴ ጋር ተመልሼ ብዙ ተጫወትን።እኔ አዲሳባ እሷ ቶሮንቶ ሆነን በዳር እስከዳር ሚዲያ ብዙ አውግተናል።ሙሉውን ማየት ብትፈልጉ ክፍል አንድ እዚህ ይገኛል።https://youtu.be/ShMsvLSaEV0?si=ehpAtVhH5wQ0LXld
    2,009video1274Open in Telegram
  • የሕይወት እምሻው አጫጭር ታሪኮች/ Hiwot Emishaw

    15 Sept, 18:42

    ቢጫው ሹራብ---ሳሚ-----"...እንቅልፏን አስተካክላ ሻንጣዋን መፍታት ስንጀምር ይሄንኑ ነገርኳት።«እኔ የምለው ሜሉ… ይሄን ሁሉ መጽሐፍ ለምን ተሸክመሽ መጣሽ?» አልኳት፡፡ ወለሉ ላይ ዝርፍጥ ብላ ከሻንጣው ዕቃ ማውጣቷን ተወችና ቀና ብላ አይታኝ፣ «የትኞቹን?»አለችኝ፡፡ «ሁሉንም» አልኩና መጽሐፍቱን ተራ በተራ ከሻንጣዋ አወጣሁ፡፡ከአድማስ ባሻገር። ቀጥሎ ኦሮማይ። ፍቅር እስከ መቃብር። ግራጫ ቃጭሎች። ዶክተር አሸብር። ልጅነት። ማታ ማታ።ሁሉንም እያነሳሁ አልጋው ላይ ደራርቤ ሳስቀምጣቸው ዝም ብላ በኩርፊያ አየችኝ።
    2,470361011Open in Telegram
  • የሕይወት እምሻው አጫጭር ታሪኮች/ Hiwot Emishaw

    13 Sept, 08:22

    ‹‹ቢጫው ሹራብ›› ÷÷÷÷÷÷÷÷ሌላ ልታገባ ከታጨች በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ቤቷ ሲሄድ፣ በእጁ ትልቅ ውኃ ሰማያዊ የፕላስቲክ ምሳ ዕቃ ይዞ ነበር።ከወር ከአስራ አምስት ቀን በፊት ቀዶ ሕክምና ተደርጎለት በተኛበት አዲስ ሕይወት ሆስፒታል ልትጠይቀው ስትመጣ ያመጣችው ነው። ምን ይዤለት ልሂድ ብላ ስትጨነቅ ውላ እና አድራ ምግብ ይዛለት መጥታ፡፡ዕቃውን በማግስቱ በእህቱ በኩል ሊመልስላት ይችል ነበር። በዚህ ፈንታ የመኪናው የኋላ ወንበር ላይ አስቀምጦት ከረመ።አንድ ቅዳሜ ከሰዓት በኋላ ደወለላት።“ስሚማ፣ ንብረትሽ እኮ አሁንም እኔ ጋ ነው” ብሎ ጀመረ፡፡ “ምን? የምን ንብረት?” ብላ ጠየቀችው፡፡ “ዕቃሽ” “የቱ ዕቃ?” “ሆስፒታል ምግብ ያመጣሽበት ዕቃ ነዋ” “ኦ… እሱን ነው ንብረትሽ ምናምን የምትለው?” “በተወደደ ኑሮ ይሄን ያህል ንብረት መናቅ እንዴት ነው…? ይልቅ ቤት ድረስ ላመጣልሽ እችላለሁ።” “ኧረ በእማማ ሞት። አትደከም።”
    3,3001081371Open in Telegram
  • የሕይወት እምሻው አጫጭር ታሪኮች/ Hiwot Emishaw

    12 Sept, 16:35

    «...የሹራቡን ሰፋፊና ዘርፋፋ እጆች ግራና ቀኝ ይዛ ወደ ሰውነቷ አስጠግታ አየችው።ኪሱ አጠገብ ነጭ ነጠብጣቦች አየች።“አንተ፣ ይሄ ምንድነው…? አግማምተኸው የለ እንዴ…? አበላሸህብኝ እኮ ” አለች ጮክ ብላ። “ኧረ ባክሽ ተይ…እኔ አንቺ ትተሸው ከሄድሽ ንክች አላደረግኩትም…ራስሽ ነሽ ሁዲዬን ያበላሸሽው… ” ብሎ መለሰላት፡፡ ‹‹አሁን ይሄ እኔ ያበላሸሁት ይመስላል ?…›› ብላ ወደ ነጠበጣቦቹ እያየችና እየጠቆመች በረጅሙ ሳቀች፡፡እሱም ሳቀ።.....»
    3,300video1584Open in Telegram
  • የሕይወት እምሻው አጫጭር ታሪኮች/ Hiwot Emishaw

    10 Sept, 12:01edited

    እንኳን ለአዲሱ ዓመት አዳረሰን! (ትንሽ ይቀረናል ብዬ ነው) 🏵🏵🏵🏵🏵🏵🏵🏵🏵🏵
    Image from a post by የሕይወት እምሻው አጫጭር ታሪኮች/ Hiwot EmishawImage from a post by የሕይወት እምሻው አጫጭር ታሪኮች/ Hiwot Emishaw
    3,760691641Open in Telegram
  • የሕይወት እምሻው አጫጭር ታሪኮች/ Hiwot Emishaw

    2 Sept, 07:02

    «መዝሙረ ሄላም» (እንዲህም አረገኝ እንዲህም አረገኝ)(ማስጠንቀቂያ፦ ይህ ጽሑፍ መጽሐፉን ላላነበቡ አንዳንድ የታሪክ ጭብጦችን ቀድሞ ያሳውቃል /ሰፖይለር አለው/።)ለወትሮስ የጣመኝን መጽሐፍ ካገኘሁ ፈጣን አንባቢ ነኝ፡፡የአዳም ረታን «መዝሙረ ሄላም» 999 ገጾች አንብቦ ለመጨረስ ግን ወደ ሦስት ሳምንታት ገደማ ወስዶብኝ ባለፈው ሳምንት አጠናቀቅሁት።አሁን ሳስበው ግን መጽሐፉን ረጋ ብዬ ለማንበብ ይህንን ያህል ጊዜ መውሰዴ ተገቢ ነበር።የአዳም ረታ የቀደሙ ሥራዎች ቀንደኛ አድናቂ በመሆኔ «መዝሙረ ሄላም»ን የጀመርኩት እጅግ ትልቅ ግምት ይዤ፣ በጉጉት ተወጥሬ ነው።በእኔ እምነት 12ኛ መጽሐፉን ያበረከተልን አዳም በአማርኛ ሥነ-ጽሑፍ ውስጥ የሚይዘው ቦታ አቻ የሌለው ነው። ስለዚህ መጽሐፉን ድርሰትን የሚያፈቅር ሰው ገምጋሚ መነጽሬን አድርጌ መጀመሩ ትንሽ ከብዶኝ ነበር።ለዚህ መሰለኝ…መጽሐፉ እጄ ሲገባ የተሰማኝ ደስታ እና ፍርሃት ተቀላቀሉ። 999 ገጽ ያለው መጽሐፍ፣ በዚያ ላይ አዳም ረታ የጻፈው መሆኑን እያሰቡ መጀመሩ በራሱ ግዙፍ ጉዳይ ነው። በዓል ነው፡፡ብዙዎቻችን እንደምንስማማው የአዳም አጻጻፍ ሁልጊዜም «ማክሲማሊስት» ነው—ሁሉንም ነገር ያያል፤ ነገሮችን በጥልቅ ዝርዝር ያብራራል፤ አንዳንዴ በተለያዩ ዓይኖችና አንደበቶች ይደግማል፤ ማብራሪያ፣ ማስረጃ፣ ማስታወሻና ማሳበቂያ ሳይቀር ይሰጥሃል።
    5,32067721Open in Telegram
  • የሕይወት እምሻው አጫጭር ታሪኮች/ Hiwot Emishaw

    1 Sept, 15:43

    ‹‹እንዲህም አረገኝ…እንዲህም አረገኝ››የ አዳም ረታን ‹‹መዝሙረ ሄላም›› እንዴት አገኘሁት?📏📏📏📏✨✨✨✨ነገ✨✨✨✨
    Image from a post by የሕይወት እምሻው አጫጭር ታሪኮች/ Hiwot EmishawImage from a post by የሕይወት እምሻው አጫጭር ታሪኮች/ Hiwot Emishaw
    4,640234Open in Telegram
  • የሕይወት እምሻው አጫጭር ታሪኮች/ Hiwot Emishaw

    17 Aug, 15:18

    የተወደዳችሁ!በዚህ ዓመት እንደ ጉድ ፃፍኩ። እንደ ጉድ አነበባችሁኝ።እስከ አዲሱ ዓመት መጀመሪያ እረፍት ልወጣ ነው።የዚያ ሰው ይበለንና በአዲስ ጉልበት፣ በአዳዲስ ታሪኮች እና በሰባተኛ መጽሐፌ እንገናኛለን።እስከዚያ ያመለጧችሁን አንብቡልኝ። ቲክቶክ ካላችሁ ደግሞ እዚያ እዩኝ።ቸር ይግጠመን። 😘😘😘
    Image from a post by የሕይወት እምሻው አጫጭር ታሪኮች/ Hiwot EmishawImage from a post by የሕይወት እምሻው አጫጭር ታሪኮች/ Hiwot Emishaw
    6,6302023025541Open in Telegram
  • የሕይወት እምሻው አጫጭር ታሪኮች/ Hiwot Emishaw

    15 Aug, 10:21

    " ስጠብቅህ ነበር" በትረካ ( ከቲክቶኬ)
    6,080video171232Open in Telegram
  • የሕይወት እምሻው አጫጭር ታሪኮች/ Hiwot Emishaw

    14 Aug, 12:22

    ይህንን ዝግጅት ደስ ካላችሁና ከተመቻችሁ ኑ !መግቢያው ነፃ ነው ብለዋል የጋበዙኝ ወጣቶች።
    Image from a post by የሕይወት እምሻው አጫጭር ታሪኮች/ Hiwot EmishawImage from a post by የሕይወት እምሻው አጫጭር ታሪኮች/ Hiwot Emishaw
    7,750384Open in Telegram
  • የሕይወት እምሻው አጫጭር ታሪኮች/ Hiwot Emishaw

    13 Aug, 07:08

    ‹‹ስለ እንትን አትጻፍ››---ወዳጄ ሰለሞን ሳህሌ ትላንት ልብ ሰባሪ የፌስቡክ መልእክት ለጥፎ ነበር፡፡"ፍቅር እኮ ነው" የተሰኘውን መጽሐፉን ለአንባቢዎች ለማቅረብ ዝግጅቱን ጨርሶ ዛሬ ሊያስመርቅ ደፋ ቀና ሲል «ቁጥጥር ከሚያደርጉ» አካላት "መጽሐፉ አይመረቅም" የሚል የእገዳ መርዶ እንደደረሰው ነገረን።ውጥኑ፣ ገንዘቡ እና ህልሙ በአንዲት ውሳኔ እጁ ላይ ሟሙ።ይህ ምን ማለት እንደሆነ አውቃለሁና ማምሻውን በሶል ጉዳይ ተነስቼ ልል ስለምፈልገው ተለቅ ያለ ነገር እየተብሰለሰልኩ ሰሞኑን ሁለንተናዬን ወደተቆጣጠረው ድንቅ መጽሐፍ ንባቤ ተመለስኩ፡፡በረጅም ታሪኩ ውስጥ ካሉት መአት ሰዎች አንዱ ደራሲ በመሆን ዋዜማ ላይ ያለ ወጣት ገጸባህርይ ነው፡፡ የእሱን አንደኛ መደብ ትረካ ተመስጩ እያነበብኩ ነበር፡፡ የታሪኩ ‹‹መቼ›› በ1967 ዓ.ም መሆኑን ልብ በሉ፡፡ስለሶል ማሰቤን ሳላቆም እያነበብኩ እጩው ደራሲ የፓለቲካው መጋጋል ካሳሰባቸው እናቱ ጋር ያደረጋት ቁራጭ የስልክ ውይይት ፊት ለፊቴ መጣች፡፡‹‹ትጽፋለህ አሁን ድርሰት ምናምን?›› ይላሉ እናቱ፡፡ ‹‹አንዳንዴ›› ይመልሳል፡፡ እናቱ ያኔ ምን አሉ…?
    7,21040362063Open in Telegram
  • የሕይወት እምሻው አጫጭር ታሪኮች/ Hiwot Emishaw

    12 Aug, 07:11

    ተቃርኖ+++++ሰዓቱ ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ቢልም ካፌው አሁንም በሰው ተሞልቷል።የሚያረገርግ ገላቸው እና ደክሞም የሚያምር ፊታቸው የሚጣራ ሴት አስተናጋጆች የተጠጣ እና የተበላባቸውን ዕቃዎች፣ ሊበሉ የተሰናዱ ምግቦችንና በተስተናጋጆች ፊት የሚከፈቱ መጠጦችን የተሸከሙ መለስተኛ ጠረጴዛ የሚያህሉ ትሪዎችን አየር ላይ በሰቀሏቸው እጆቻቸው ሚዛን አስይዘው፤ በተፋፈጉ ጠረጴዛዎች እና እየተንፏቀቁ በተጠጋጉ ወንበሮች መሃከል ሲሆንላቸው እየተሽሎከለኩ፣ ሲያቅታቸው ከገጠማቸው ጋር እየታከኩና እየተላተሙ ውር ውር ይላሉ፡፡ዳሌና ደረታቸው ላይ የሚያንዣብቡና በዐይን የሚዳሯቸው ተባዕት ዓይኖች እንዲሁም ገላማጭና ፈራጅ እንስት ፊቶች እንቅስቃሴቸውን ያጅባሉ፡፡በመሃል አንደኛዋ አስተናጋጅ እንደ አለቃ ተጀንኖ ወደ ቆመው ቦርጫም ሰውዬ ሄደችና - ‹‹ለይኩን መሄዴ ነው›› አለችው፡፡እቃ ሊያመጡና ሊመልሱ የሄዱ ሁለት ሌሎች አስተናጋጆች-‹‹ሆ›› በሚል ተያዩና ከባልኮኒው ጀርባ ባለው ግማሽ በር ሾልከው ወደ ኪችኑ ገቡ፡፡‹‹ጭራሽ ለይስሙላ እንኳን አቶ ማለቱን ተወችው ማለት ነው?…እውነትም ማፈር ትተዋል›› አለች አንደኛዋ ቀድሟት ያመለጣትን ሳቅ ስቃ ስታበቃ፡፡‹‹እኛም የምንሰጠውን ሰጥተን በአራት ሰዓት ሺፍት…ለዛውም እያለመጥን ሙሉ ደሞዝ ባገኘን›› አለች ሌላኛዋ በስጨት ብላ፡፡
    5,470641774Open in Telegram
  • የሕይወት እምሻው አጫጭር ታሪኮች/ Hiwot Emishaw

    11 Aug, 18:17

    አዲስ ታሪክ/ ነገ 🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋
    4,370video194Open in Telegram