gram news
ጋብቻ እና ልባም ሴት channel avatar

ጋብቻ እና ልባም ሴት

@httpstme8rjldnzsnim4yme02015

"ሚስት ያገኘ ፥ በረከትን አገኘ ፥ ከእግዚአብሄር ዘንድ ፥ ሞገስን ይቀበላል ። ምሳ 18:22

ProjectsENReligion

6,990subscribers

Open the Channel

Latest posts

  • ጋብቻ እና ልባም ሴት

    10 Sept, 09:48

    በቸርነትህ ዓመትን ታቀዳጃለህ፥ ምድረ በዳውም ስብን ይጠግባል። መዝሙረ ዳዊት 65:11
    Image from a post by ጋብቻ እና ልባም ሴትImage from a post by ጋብቻ እና ልባም ሴት
    2096321Open in Telegram
  • ጋብቻ እና ልባም ሴት

    10 Sept, 05:55

    👉 አንዲት ታዋቂ ሴት በገንዘብ አጠቃቀም ጉዳይ ስለ ትዳሯ የተናገረችው ነው ። አንብባችሁ እንደ እግዚአብሔር ቃል አስተያየት ስጡ።በትዳር ላይ የእኔ ገንዘብ የእኔ ነው የእሱ ገንዘብ ግን የጋራ ገንዘብ ነው። እኔ ሰርቼ ያመጣሁትን ገንዘብ ለራሴ እጠቀማለሁ እሱ ሰርቶ ያመጣውን ግን ለቤታችን፣ ለልጆቻችን ት/ቤት ክፍያ፣ ለህክምና እና ለሌሎችም እንጠቀምበታለን ወንድ ወጥቶ ወርዶ ቤተሰብን ማስተዳደር አለበት ወንድ ፕሮቫይደር ነው ። እኔ ሰርቼ ብዙ ገንዘብ እንኳን ባገኝ የእኔ ገንዘብ እሱን አይመለከተውም ።📢 አስተያየት ስጡበት።❓ ❓
    317111Open in Telegram
  • ጋብቻ እና ልባም ሴት

    9 Sept, 16:07edited

    💍 ወድ ለንጉሱ ሴት ልጆች (ላላገባችሁ)እግዚአብሔርን ለማይወድ ፥ አምልኮ ፀሎት ለማይወድ ሰው ልብሽን አትስጭ።ጥያቄ ?አሁን በጀመርሽው relationship ፀሎትሽ አምልኮ መንፈሳዊ ህይወትሽ ጨመረ ቀነሰ ?የቀረብሽው ሰው እምነትሽን ያከብራል ? ወደ አምልኮ ፀሎት ይገፋፋሻል? በስራሽ በትምህርትሽ ያበራታታሻል? ራዕይሽን ለመሆን ያሰብሽውን ይደግፋል ?ሰላምሽ ጨመረ ወይስ ጠፋ? #የኔ_እህት ሰላምሽን ከሚነሳ relationship ብቻሽን በሰላም ብትሆኝ ይሻላል ። ጎመን በጤና😂 ብቸኝነትን አትፍሪ።የእግዚአብሔር ፈቃድ ያለበት relation የመጀመሪያው መታወቂያው "ሰላም " ነው። የአዕምሮ እና የልብ ሰላም ። ምክንያቱም ኢየሱስ የሰላም አምላክ ነው። "ሰላምን እተውላችኋለሁ፥ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ " የዮሐንስ ወንጌል 14:27 ሰላም ከሌለ ኢየሱስ የለም። የእርሱም መልካም ፈቃድ የለም።
    Telegramጋብቻ እና ልባም ሴት"ሚስት ያገኘ ፥ በረከትን አገኘ ፥ ከእግዚአብሄር ዘንድ ፥ ሞገስን ይቀበላል ። ምሳ 18:22
    522105111Open in Telegram
  • ጋብቻ እና ልባም ሴት

    9 Sept, 04:50

    ⁉️ወድ የእግዚአብሔር ልጆች ማግባት የለብኝም የምትሉት ምን አይነት ሰው ነው?💎 ለእናንተ የማይሆን የተሳሳተ የትዳር ጓደኛ ስታገቡ ለበዛ ትዳር ውስጥ ችግሮች ይገጥማቸዋል።‼️ አንዳንዶች ተቃራኒያቸውን ነው የሚያገቡት ። ካገቡ ጀምሮ ህይወታቸው ያሰቡት አይነት አልሆነም።🌀 አንዳንዶች መልካቸውን ፥ ሰውነታቸውን ፥ ሀብታቸውን ፥ ጤናቸውን ፥ ፋይናንሳቸውን ፥ ንግድ ፥ ስራቸውን ፥ መንፈሳዊ ህይወታቸውን አንዳንዶች ደግሞ በሚያሳዝን ሁኔታ ህይወታቸውን አጥተዋል ። ስለዚህ የሚበጃችሁን ለማግባት እግዚአብሔር በዚህ አቅጣጫ እንዲረዳችሁ ፀልዩ ። ይህንን የምታደርጉ ከሆነ በጋብቻ ውስጥ የሚገጥማቸውን ችግሮች ትቀንሳላችሁ።⁉️ ታዲያ የማይበጅ ሰው ምን አይነት ነው ?1. የማይወድሽን አታግቢ ፦ የማይወድሽ ለስሜት ስለማይጠነቀቅ ብሎም ትኩረት ስለማይሰጥ ይሳደባል ፥ ያናድዳል ፥ ይደበድባል።2.በተለያዩ የህይወት ዘርፍ ከአንቺ ጋር የማይስማማ ከሆነ ጥሩ የትዳር ሰው ሊሆን አይችልም።በእምነት(ሀይማኖት )፥ በአላማ ፥ በባህሪ ፥በስብዕና ፥በአስተሳሰብ ፥ በህልም የማይስማማ ሰው ማግባት የለብሽም።“በውኑ ሁለት ሰዎች ሳይስማሙ በአንድነት ይሄዳሉን?” — አሞጽ 3፥3
    Telegramጋብቻ እና ልባም ሴት"ሚስት ያገኘ ፥ በረከትን አገኘ ፥ ከእግዚአብሄር ዘንድ ፥ ሞገስን ይቀበላል ። ምሳ 18:22
    6071511Open in Telegram
  • ጋብቻ እና ልባም ሴት

    9 Sept, 04:50

    👇👇👇
    Image from a post by ጋብቻ እና ልባም ሴትImage from a post by ጋብቻ እና ልባም ሴት
  • ጋብቻ እና ልባም ሴት

    8 Sept, 17:13

    እግዚአብሔር አምላክም ከአዳም የወሰዳትን አጥንት ሴት አድርጎ ሠራት፤ ወደ አዳምም አመጣት። — ኦሪት ዘፍጥረት 2:22 (አማርኛ 1954)
    Image from a post by ጋብቻ እና ልባም ሴትImage from a post by ጋብቻ እና ልባም ሴት
    63411Open in Telegram
  • ጋብቻ እና ልባም ሴት

    8 Sept, 06:37

    📖“አቤቱ፥ ለአፌ ጠባቂ አኑር፥ የከንፈሮቼንም መዝጊያ ጠብቅ።” — መዝሙር 141፥3
    740142111Open in Telegram
  • ጋብቻ እና ልባም ሴት

    6 Sept, 13:43edited

    ⁉️ ለ" ነፃነት " ትዳር ይፈርሳል ?📢 "ለነፃነት" ብላችሁ ትዳራችሁን ለመተው ያሰባችሁ ለእናንተ ነው።💢 "ነፃነቴን እፈልጋለሁ " በሚል ሀሳብ ትዳርን መተው ሰላም ደስታ ያመጣል?💢 እውነታው ግን ትዳርን መተው ባል የሰጠሽን ፍቅርና ሰላም አውጥቶ መጣል ከባድ ዋጋ ያስከፍላል ።#ወድ_ሴቶች "ነፃነት " ብቸኛ ነው የሚያደርግሽ ። ትዳር "እስር ቤት ፥ አሰልቺ ነው ፥ የባል ፍቅር እንደ ቁጥጥር ፥ እንክብካቤው ደረቅ ልማድ ነው ብለሽ ጥለሽ መውጣት ውጤቱ ለብቻ መመገብ ፥ ለብቻ መኖር ፥ ሀሳብሽን እንኳ ልታካፍይ ሰው አጥተሽ ድብርት ህይወት እንድትገፊ ያደርጋል።😭 ልጆችሽ ያለ አባት ፍቅር እንዲያድጉ እና እንዲሰቃዩ ምክንያት ትሆኛለሽ ። የአባት ፍቅር የማያውቁ ያልተረጋጉ በጥያቄ ውስጥ የሚኖሩ ልጆች ይሆናሉ።😭 "አባት ግዢልኝ" ለሚል ህፃን መልስሽ ምንድነው ? "አባቴ ጋ ውሰጂኝ " መች ነው የሚመጣው ጓደኞቼ አባት አላቸው የኔ አባትስ ? ለሚሉ መቆሚያ የሌለው ጥያቄዎች ምን ይሆን መልስሽ ?🌀 አንቺስ "በኔ ስህተት ልጆቼን ያለ አባት አሳጣው " እንዲህ ቢሆን እንዲህ ይሆን ነበር እያልሽ የህሊና ወቀሳ ፥ ሙግት ፀፀት ይገጥምሻል።🌀 Online ላይ በየዕለቱ እንቅልፍ አጥተሽ የምትከታተያቸው single mam ነን "ነፃ ሰው ነኝ " የሚሉ ተረቶች ከፀፀት አያስጥሉም። ላንቺ ፀፀት ግድ የላቸውም። Tik tok ላይ ለሊቱን ሙሉ ፀረ ወንድ(ትዳር) ጥላቻ የሚነዙ ፥ ፍቺ ነፃነት ነው የሚሉ ፌሚኒስት ሴቶች ከብቸኝነት አያድኑሽም።
    Telegramጋብቻ እና ልባም ሴት"ሚስት ያገኘ ፥ በረከትን አገኘ ፥ ከእግዚአብሄር ዘንድ ፥ ሞገስን ይቀበላል ። ምሳ 18:22
    1,09010221Open in Telegram
  • ጋብቻ እና ልባም ሴት

    6 Sept, 04:58

    ክፉ ነገር ወደ አንተ አይቀርብም፥ መቅሠፍትም ወደ ቤትህ አይገባም። — መዝሙረ ዳዊት 91:10
    1,02016111Open in Telegram
  • ጋብቻ እና ልባም ሴት

    5 Sept, 13:36

    Image from a post by ጋብቻ እና ልባም ሴትImage from a post by ጋብቻ እና ልባም ሴት
    1,28064211Open in Telegram
  • ጋብቻ እና ልባም ሴት

    5 Sept, 07:53

    ♨️ ሴተኛ አዳሪ ሴት ማግባት ምን ችግሮች አሉት? መፅሐፍ ቅዱሳዊ ዕይታ እነሆ፦✍️ የሴተኛ አዳሪነትን ሕይወት የኖረችን ሴት ማግባት በመጽሐፍ ቅዱስ እይታ እና በሰዋዊው የኑሮ እውነታ ውስጥ የራሱ የሆኑ ፈተናዎችና ጥልቅ መንፈሳዊ ትምህርቶች አሉት። ይህንን ርዕስ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መርሆችን እና ሊያጋጥሙ የሚችሉ ተግባራዊ ችግሮችን መሠረት በዚህ መልክ ተቀምጧል ።1. መጽሐፍ ቅዱሳዊው እይታ (The Biblical Perspective)መጽሐፍ ቅዱስ የሰውን ልጅ ያለፈ ታሪክ ሳይሆን የአሁኑን የልብ ንስሐና ለውጥ ላይ ያተኩራል። በዚህ ረገድ ሁለት ታላላቅ ምሳሌዎችን ማንሳት ይቻላል፡የነቢዩ ሆሴዕ እና የጎሜር ታሪክ (ሆሴዕ 1)፦እግዚአብሔር ነቢዩ ሆሴዕን አመንዝራይቱን ጎሜርን እንዲያገባ አዞታል። ይህ የሆነው እግዚአብሔር ለእስራኤል ሕዝብ ያለውን ጥልቅ፣ ይቅር ባይና የማይለወጥ ፍቅር ለማሳየት ነው። ታሪኩ የሚያስተምረው እግዚአብሔር ሰዎችን ከኃጢአት ጭቃ ውስጥ አንስቶ የማደስ ኃይል እንዳለው ነው።የጋለሞታይቱ ረዓብ ታሪክ (ኢያሱ 2)፦ረዓብ የኢያሪኮ ሴተኛ አዳሪ ነበረች። ነገር ግን በእግዚአብሔር አምና የእስራኤልን ሰላዮች በመደበቋ ሕይወቷ ተረፈ። በኃላም የናሆም ሚስት ሆና፣ በቤተልሔም ክብርን አግኝታ፣ የታላቁ ንጉሥ የዳዊትና የኢየሱስ ክርስቶስ የትውልድ ሐረግ (ማቴዎስ 1:5) ውስጥ ለመካተት በቅታለች። ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፤ አሮጌው ነገር አልፎአል፤ እነሆ፣ አዲስ ሆኖአል። 2 ቆሮንቶስ 5:172. ሊያጋጥሙ የሚችሉ ማኅበራዊና ሥነ-ልቦናዊ ችግሮች
    Telegramጋብቻ እና ልባም ሴት"ሚስት ያገኘ ፥ በረከትን አገኘ ፥ ከእግዚአብሄር ዘንድ ፥ ሞገስን ይቀበላል ። ምሳ 18:22
    1,250811Open in Telegram
  • ጋብቻ እና ልባም ሴት

    5 Sept, 07:47

    🕊 የጐመን ወጥ በፍቅር መብላት የሰባ ፍሪዳን ጥል ባለበት ዘንድ ከመብላት ይሻላል። — መጽሐፈ ምሳሌ 15:17
    961311Open in Telegram
  • ጋብቻ እና ልባም ሴት

    4 Sept, 16:43edited

    📌 የሞቱ ሰዎች በህይወት ካሉ ሰዎች ጋር መነጋገር ይችላሉ ?ሙታን ከሕያዋን ጋር መገናኘት ይችላሉ? በዚህ ጉዳይ መፅሐፍ ቅዱስ ምን ይላል ?🏮 መፅሀፍ ቅዱስ አማኞች ከሙታን ጋር ተገናኝተው መልዕክት ወይንም መንፈሳዊ ትምህርት እንዳይቀበሉ ያስጠነቅቃል ።1. እግዚአብሔር ሙታንን መጠየቅን ይከለክላል።"አስማተኛም፥ መተተኛም፥ በድግምት የሚጠነቍልም፥ መናፍስትንም የሚጠራ፥ ጠንቋይም፥ ሙታን ሳቢም በአንተ ዘንድ አይገኝ። ዘዳግም 18:11❌ መሪ ጌታ ፥ ደብተራ መናፍስት ጠሪ ፥ ደጋሚዎች መተተኞች የባህል መድኃኒት አዋቂ ነን የሚሉ ደጋሚዎች ስራቸው በእግዚአብሔር አምላክ ፊት አስፀያፊ ነው። ቃሉ፦ "ይህንም የሚያደርግ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት የተጠላ ነው፤ ዘዳግም 18:122. ሙታን ወደ ዚህ ዓለም ተመልሰው ከህያዋን ጋር አይገናኙም ። 💤“ሙታን ምንም አያውቁም።” መክብብ 9:5
    Telegramጋብቻ እና ልባም ሴት"ሚስት ያገኘ ፥ በረከትን አገኘ ፥ ከእግዚአብሄር ዘንድ ፥ ሞገስን ይቀበላል ። ምሳ 18:22
    1,20052111Open in Telegram
  • ጋብቻ እና ልባም ሴት

    4 Sept, 15:29

    👇👇👇
    Image from a post by ጋብቻ እና ልባም ሴትImage from a post by ጋብቻ እና ልባም ሴት
  • ጋብቻ እና ልባም ሴት

    4 Sept, 07:38edited

    ጥያቄ ❓❓ከፍቺ በኋላ ክርስቲያን ዳግመኛ ማግባት ይችላል ?መልሱን በዝርዝር እመልስበታለው ✈️
    1,21021Open in Telegram
  • ጋብቻ እና ልባም ሴት

    4 Sept, 01:18

    ባሎች ሆይ፥ ክርስቶስ ደግሞ ቤተ ክርስቲያንን እንደ ወደዳት ሚስቶቻችሁን ውደዱ፤ በውኃ መታጠብና ከቃሉ ጋር አንጽቶ እንዲቀድሳት ስለ እርስዋ ራሱን አሳልፎ ሰጠ፤ — ወደ ኤፌሶን ሰዎች 5:25
    1,140521Open in Telegram
  • ጋብቻ እና ልባም ሴት

    3 Sept, 16:43

    forwarded from @httpstme8rjldnzsnim4yme02015

    የስልክ ጥሪ ነው ተጠቀሙት እኔ የምጠቀመው ሞገስ ያለው ጥሪ ነው።
    1,290file1631Open in Telegram
  • ጋብቻ እና ልባም ሴት

    3 Sept, 16:40

    forwarded from @asterabebechannel

    1,220file71Open in Telegram
  • ጋብቻ እና ልባም ሴት

    3 Sept, 16:39

    forwarded from @asterabebechannel

    1,170file43Open in Telegram
  • ጋብቻ እና ልባም ሴት

    3 Sept, 10:31

    1,320poll21Open in Telegram