Latest posts

Hawassa University
25 Sept, 11:54
የትምህርትና ስነ-ባህሪ ሳይንስ ኮሌጅ ከሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ት/መምሪያ ጋር በትብብር ለመስራት የሚያስችላቸዉን መግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ // መስከረም 15/2019 በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የትምህርትና ስነ-ባህሪ ሳይንስ ኮሌጅ እና የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ት/መምሪያ በትምህርት ልማት ዘርፍ ትርጉም ያለዉ ለዉጥ ያመጣል ተብሎ የታመነበት መግባቢያ ሰነድ የሁለቱም ተቋማት አመራሮችና የሚመለከታቸዉ ባለ ድርሻ አካላት በተገኙበት በዩኒቨርሲቲዉ አፍሪካ ህብረት አደራሽ የፊርማ ማኖር ሥነ-ስርዓት ተከናዉኗል:: በስነስርዓቱ ሀዋሳ ዩኒቨረሲቲን በመወከል የዩኒቨርሲቲዉ አካዳሚ ጉዳዮች ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር እንጂነር ፍሰሃ ጌታቸዉ በሰነዱ ላይ የፈረሙ ሲሆን፣ መግባቢያ ሰነዱ በሁለቱ አጋር አካላት መካከል ከዚህ ቀደም ሲሰሩ የነበሩ ስራዎችን ወደ ላቀ ደረጃ ያሸጋግራል ብለዋል:: ዶ/ር ፍስሃ አያይዘዉም ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ እንደ ሀገር በትምህርት ልህቀት ማዕከልነት ከተመረጡ ጥቂት አንጋፋ ዩኒቸርሲቲዎች አንዱ እንደመሆኑ በሀዋሳ ከተማ የትምህርት ጥራት ችግሮችን ለመቅረፍ በሚደረገዉ ርብርብ ጉልህ ሚና ለመጫወት ከምን ጊዜዉም በላይ ቁርጠኛ መሆኑን አሳዉቀዋል:: የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ት/መምሪያ ኃላፊ ዶ/ር ብርሃኑ ደሳለኝ በበኩላቸዉ መምሪያዉ ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ጋር በከተማዉ ትምህርት ልማት ጉዳይ ላይ በትብብር መስራትን እንደ መልካም አጋጣሚ እንደሚቆጥሩት ገልጸዉ በትምህርት አመራር፣ መምህራን ልማት እና የስርዓተ-ትምህርት አተገባበርና ቤተሙከራዎች አጠቃቀም ላይ በጋራ ቢሰራ ከተማ አስተዳድሩ ፍላጎት እንዳለዉ አሳዉቀዋል:: የመግባያ ሰነዱን ይዘትና ዓላማ በተመለከተ የኮሌጁ ዲን ዶ/ር ሳሙኤል አሰፋ ገለጻ ያደረጉ ሲሆን መልካም ተሞክሮዎችን መለዋወጥና የዕዉቀት ሽግግር ማድረግ፣ ምርምችን በትብብር መስራት፣ የመምህራን ስልጠና፣ የትምህርት ግብeብች ድጋፍ፣ የትምምርት ፕሮግራሞችና ፕሮጀክቶች አተገባበር ድጋፍና ክትትል ማድረግ ላይ ያተኮረ መሆኑን ተናግረዋል:: በስነ-ስርዓቱ ላይ ከዩኒቨርሲቲዉና ከተማ አስተዳድሩ ት/መምሪያ የተለያዩ ስራ ክፍሎች የተወጣጡ አካላት ተገኝተዋል::ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሁሌም ለልህቀት!2,110Open in Telegram
Hawassa University
25 Sept, 11:11
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ምስረታ የወርቅ ኢዮቤልዩ ክብረ-በዓል አስተባባሪ ዐቢይ ኮሚቴ ስራ እንቅስቃሴ ተገመገመ // መስከረም 15/2019 ዓ/ም 50ኛ ዓመት የምስረታ ክብረ በዓሉን የወርቅ ኢዮቤልዩ ዝግጅት በበላይነት እንዲያስተባብር ተልዕኮ የተሰጠዉ ዐቢይ ኮሚቴ የስራ እንቅስቃሴዉን እና መሪ ዕቅዱን በተመለከተ ለዩኒቨርሲቲዉ ማኔጅመንት ካዉንስል አቅርቦ ግብረ-መልስ ተሰጥቶታል የዉይይት መድረኩን የዩኒቨርሲቲዉ ፕሬዝዳንት የመሩት ሲሆን የዐቢይ ኮሚቴዉን ስራ እንቅስቃሴና ዕቅድ በተመለከተ የኮሚቴዉ ሰብሳቢ ዶ/ር መልሰዉ ደጀኔ አጠር ያለ ሪፓርት ማብራሪያ አቅርበዉ ትኩረት ያሻል የተባሉ ጉዳዮችን በተመለከተ ገለጻ አድረገዋል:: የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ችሮታዉ አየለ የኮሚቴ አባላቱንና አስተባባሪዎቹን እስካሁን ለተከናወኑ ሰፊ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች በራሳቸዉና በዩኒቨርሲቲዉ ስም ምስጋና አቅርበዋል:: ፕሬዝዳንቱ እና የማኔጅመንት ካዉንስል አባላቱ በዐቢይ ኪሚቴዉ የቀረበዉን ዝርዝር እቅድ ካደመጡ በኋላ ማብብሪያ በሚፈልጉ ጉዳዮች ላይ ጥያቄዎችን እንዲሁም ቢሻሻልና ትኩረት ቢደረግበት ባሏቸዉ ጉዳዮች ላይ ደግሞ ሀሳብና አስተያየት ሰጥተዋል:: የዐቢይ ኮሚቴዉ ሰብሳቢ፣ ጸሐፊና አባላቱ ደግሞ ለተነሱት ጥያቄዎችና አስተያየቶች አስፈላጊዉ ምላሽ እና ማብራሪያ ሰጥተዋል:: የቀረበዉ ዕቅድ ተሸሽሎ ለማኔጅመንት ዉሳኔ ሲቀርብ የሚወሰንና ተግባራዊ የሚደረግ ስለመሆኑ አቅጣጫ ተቀምጧል:: በዉይይት መድረኩ በዐቢይ ኮሚቴዉ ተዘጋጅተዉ የቀረቡት የክብረ በዓሉ ሎጎ እና መሪ ጥቅስ ቀርቦ ሰፊ ዉይይት ከተደረገ በኋላ ጸድቋል:: በተጨማሪም የበዓሉ አከባበር የጊዜ ሠሌዳ የዩኒቨርሲቲዉን አካዳሚክ ካሌንደር እና ሀገራዊ ኹነቶችን ከግምት ዉስጥ ባስገባ መልኩ በ3 ምዕራፎች ተከፍሎ፣ ሰፋፊ ዝግጅቶችን በማካተት ሁሉንም የዩኒቨርሲቲዉን ማህበረሰብ፣ ባለ ድርሻና አጋር አካላትን በንቃት ባሳተፈ መልኩ ዓመቱን በሙሉ በደማቅ ሁኔታ እንደሚከበር ከተያዘዉ ዕቅድ ለማወቅ ተችለሏል:: የክብረ በዓሉ የመጀመርያዉ ምዕራፍ የሆነዉ መርሃ-ግብሩን ይፋ ማድረጊያ መድረክ በቅርቡ እንደሚካሄድ ይጠበቃል::ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሁሌም ለልህቀት2,620Open in Telegram
Hawassa University
25 Sept, 08:34
የፕሮግራም ጥቆማ Ø የሀገር ዕድገትና ሁለንተናዊ ለዉጥ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ከሳይንስ፣ ምርምርና ፈጠራ ጋር እጅጉን የተቆራኘ ነዉ:: Ø ለእነዚህ ጉዳዮች የሚሰጥ ትኩረትና ዋጋ መክፈል በሀገራት መካከል በግልጽ የሚታይ ለዉጥ አምጥቶ እናያለን:: Ø የሀገራት በኢኮኖሚ ማደግ፣ በቴክኖሎጂ መራቀቅ፣ የሰለጠነ ማህበረሰብ መፍጠር፣ ጠንካራ ተቋማትን መገንባት፣ ለዜጎች የተቀላጠፈ አገልግሎቶች መስጠት፣ ሰላምና ጸጥታን ማረጋገጥና ወዘተ በሳይንሳዊ ምርምር ዉጤቶችና ልዩ ልዩ ፈጠራዎች የተደገፈ ስለመሆኑ የገሃድ እዉነት በመሆኑ ብዙ መረጃ መዘርዘር የሚያሻዉ ጉዳይ አይደለም:: Ø በእነዚህ ጉዳዮች እኛስ የት ነን? ወዴትስ እየሄድን ነዉ? Ø ሀገራችንም ሆነች ተቋሞቻችን ለምርምር እና ፈጠራ ምን ያክል በጀት፣ የሰዉ ኃይልና ጊዜ እንንድባለን? Ø ዓመታዊ በጀታችን ምን ያክል ደርሷል? ስንት ተመራማሪዎች አሉን? Ø ምን ያህል የምርምር ፕሮጀክቶች ይከናወናሉ? ምን ያክሉስ ይታተማሉ ወይስ ወደ ተግባር ይሸጋገራሉ? Ø በሀገር አቀፍ እና ክልል ደረጃ ያሉ ፓሊሲዎቻችን ስለ ምርምርና ፈጠራ ምን ይላሉ? Ø እስካሁን የተከናወኑ የምርምርና ፈጠራ ስራዎ እደ ሀገር ምን አበርክቶ ነበራቸዉ? Ø በቀጣይ እንደ ሀገር የምርምርና ትብብር ስራዎችን በተመለከተ ለተመራማሪዎች፣ ድህረ-ምረቃ ተማሪዎች፣ ለአካባቢዉ ማህበረሰቦችና ተቋማት፣ ፓሊሲ አዉጪዎች ምን አቅጣጫ ተይዟል? ምን አዲ ነገር አለ? ከማን ምን ይጠበቃል? በሚሉ ጉዳዮች ላይ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ምርምርና ትብብር ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ታፈሰ ማቴዎስ እና ዶ/ር ምህረተአብ አብርሃም በ«ከምርምር ዓለም» ሬድዮ ፕሮግራም ኤፍ ኤም 100.9 ላይ ዓርብ መስከረም 15/2019 ዓ/ም እንዲያደምጡ እንጋብዝዎታለን:: ለእርስዎ የተዘጋጀ ፕሮግራም! ያድምጡ ይሳተፉ፣ ያካፍሉ! ከምርምር ዓለምሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሁሌም ለልህቀት!3,760Open in Telegram
Hawassa University
24 Sept, 17:48edited
የሃዘን መግለጫ // መስከረም 14/2019 ዓ/ምበሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የአራተኛ ዓመት የህግ ትምህርት ቤት ተማሪ የነበረችው ቤተሰላም ተስፋዬ በደረሰባት ድንገተኛ ህልፈተ ሕይወት የተሰማንን መሪር ሃዘን እየገለፅን፣ ለመላው ጓደኞቿ፣ ቤተሰቦቿ፣ ወዳጅ ዘመዶቿ እና ለሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ በሙሉ ልባዊ መፅናናትን እንመኛለን!ነብስ ይማር! 😭ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ
5,310Open in Telegram
Hawassa University
22 Sept, 14:11


5,150Open in Telegram
Hawassa University
21 Sept, 17:32

7,160Open in Telegram
Hawassa University
19 Sept, 21:57
በተሻሻለው የመረጃ አደረጃጀት እና አስተዳደር ላይ ለዩኒቨርሲቲዉ የስራ ኃላፊዎች ስልጠና ተሰጠ። \\ መስከረም 09/2019 ዓ/ም በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የ2019 የትምህርት ዘመን መረጃን ወደ ከፍተኛ ትምህርት መረጃ አስተዳደር ስርዓት (HEMIS) በማስገባት ሂደት ላይ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ እና ወቅታዊ፣ ተዓማኒ እና ጥራቱን የጠበቀ የመረጃ አያያዝ ለመዘርጋት የሚያስችል ስልጠና ለዩኒቨርሲቲዉ ዲኖች፣ ዳይሬክተሮች፣ የሰው ሀብት ስራ አስፈጻሚዎች እና የዳታ ማኔጅመንት አስተባሪዎች በትምህርት ሚኒስቴር ባልደረቦች አማካኝነት ከ08-09/01/2019 ዓ/ም ተሰጥቷል። በስልጠናው ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ላይ የተገኙት የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዚደንት ዶ/ር ኢ/ር ፍሰሐ ጌታቸው መረጃ የአንድ ተቋም ትልቁ ሀብት እንደመሆኑ የመረጃን ወቅታዊነትና ጥራት መጠበቅ አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመው ትክክለኛ መረጃን በጥንቃቄ ከመሰብሰብና ከማደራጀት ጀምሮ ወደ ተጨባጭ ውጤት ለመቀየር በሚሰራው ስራ ሁሉም የዩኒቨርሲቲው ሰራተኞች ተፈላጊውን እውቀት አግኝተው በትብብር ሊሰሩ እንደሚገባ አሳስበዋል። የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስትራቴጂክ ጉዳዮች ስራ አስፈጻሚ አቶ ሙሉጌታ ቡርቃ በበኩላቸው የHEMIS (Higher education management information system) መረጃ አስተዳደር ስርዓት በከፍተኛ ትምህር ተቋማት ውስጥ ያለውን የመረጃ ስርዓት ወጥ በሆነና ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ለማስተዳደር እንደ ዋነኛ መሳሪያ ሆኖ እያገለገለ እንደሚገኝ ገልጸዋል። በተጠናቀቀው የ2018 በጀት አመት ይህንኑ የመረጃ8,560Open in Telegram
Hawassa University
19 Sept, 21:52



7,430Open in Telegram
Hawassa University
19 Sept, 21:15
የእንሰሳት ህክምና ፋካሊቲ መምህራንን የማማከርና አሰልጣኝነት አቅም የሚያሳድግ የስልጠና መድረክ ተካሄደ። \\ መስከረም 09/2019 ዓ/ም ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ከብሩክ ኢትዮጵያ (Brooke Ethiopia) ጋር በመተባበር የእንስሳት ህክምና ተማሪዎችን የክሊኒካል እውቀትና ተግባራዊ ክህሎት ለማዳበር የሚያስችል "Animal Health Mentoring Framework" (የእንስሳት ጤና የአማካሪነትና ስልጠና ማዕቀፍ) የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ለእንሰሳት ህክምና ፋካሊቲ መምህራን ከመስከረም 7 እስከ 9 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ ተሰጥቷል፡፡ የእንስሳት ህክምና ፋካሊቲ ዲን ዶ/ር ይፋት ደምባርጋ አዲሱ የትምህርት ዘመን መጀመሩን ተከትሎ የተዘጋጀው ይህ ስልጠና መምህራን የተሻለ የማማከርና የማብቃት(Mentorship) አቅም እንዲገነቡ የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል። ዶ/ር ይፋት አክለውም የእንስሳት ህክምና ትምህርት በንድፈ ሀሳብ፣ በክሊኒካል እና ቤተሙከራ በሚከናወኑ ተግባራዊ ስልጠናዎች የሚተገበር በመሆኑ ትምህርቱን የሚሰጡት መምህራን ብቁ የሆነ ግንዛቤ ሲጨብጡ ተማሪዎች በተግባራዊ የእንስሳት ህክምና ክህሎት የዳበሩ፣ ብቁና ተወዳዳሪ ሆነው እንዲወጡ ማስቻል እንደሚቻል አብራርተዋል። ይህ የማማከርና የስልጠና ማዕቀፍ በተለይም ከ4ኛ እና 5ኛ ዓመት የእንስሳት ህክምና ተማሪዎች ክሊኒካል ትምህርት ጋር በቀጥታ ተቀናጅቶ የሚሰጥ መሆኑን የገለጹት በተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ የምርምርና ትብብር ተ/ዲን ዶ/ር ከድር ወልየ ስልጠናው ተማሪዎች በክሊኒክ፣ በላቦራቶሪና በመስክ የህክምና ስራዎች ወቅት የሚያጋጥሟቸውን ችግሮች7,270Open in Telegram
Hawassa University
19 Sept, 21:15



6,080Open in Telegram
Hawassa University
19 Sept, 06:04
College of Agriculture Organizes Technical Meeting with Nestlé Foundation at College of Agriculture // September 17, 2026The School of Nutrition, Food Science and Technology (SNFST) at Hawassa University’s College of Agriculture (CoA) held a technical meeting with the Nestlé Foundation under the theme, “Building a Sustainable Institutional Partnership to Advance Maternal, Child and Adolescent Nutrition and Food Systems” on September 17-18, 2026 at Geremew Haile Hall, CoA.Delivering the welcoming and opening remarks, Dr. Zerihun Demirew, Dean of the College of Agriculture, highlighted Ethiopia’s significance as one of the major centers of origin and diversity for several domesticated and nutritionally dense food crops, as well as their wild relatives.Dr. Zerihun noted that the meeting provides an important platform for establishing meaningful collaboration in research, capacity7,880Open in Telegram
Hawassa University
19 Sept, 06:03



7,040Open in Telegram
Hawassa University
18 Sept, 05:44
የትምህርትና ስነ-ባህሪ ሳይንስ ኮሌጅ ከሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ለተወጣጡ ርዕሳነ መምህራን፣ ሱፐርቫይዘሮችና ደጋፊ የትምህርት ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና መርሃ-ግብር አስጀመረበሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የትምህርትና ስነ-ባህሪ ሳይንስ ኮሌጅ ከሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ለተወጣጡ ርዕሳነ መምህራን፣ ሱፐርቫይዘሮችና ደጋፊ የትምህርት ባለሙያዎች የሚሰጥ ለ3 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ የአቅም ግንባታ ስልጠና በቀን 07/01/2019 ዓ/ም በዩኒቨርሲቲዉ ዋና ግቢ አስጀምሯል፡፡ የዩኒቨርሲቲዉ አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር እንጂነር ፍሰሃ ገታቸዉ በስልጠናዉ መክፈቻ ስነ-ስርዓት ላይ ተገኝተዉ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ እና ከተማ አስተዳድሩ በብዙ ጉዳዮች ላይ ለረጅም ዘመናት አብረዉ ሲሰሩ መቆየታቸዉን አስታዉሰዉ፣ የትምህርት ጉዳይ ትልቅ እና ቅድሚያ የሚሰጠዉ ጉዳይ መሆኑን ተናግረዋል:: ም/ፕሬዝዳንቱ ስለ ትምህርት አይተኬ ሚና ሲናገሩ ጠንካራ ህገራት የተመሰርቱት በጠንካራ የትምህርት ስርዓት በመገንባት ነዉ ብልዋል:: ዶ/ር እንጅነር ፍስሃ አክለዉም ትምህርት የህይወት ዘመን ጉዳይ በመሆኑ በስራ ላይ ያሉ ባለሙያዎችም ሆኑ መሪዎች ራሳቸዉን ዘወትር ለትምህርትና ስልጠና ክፍት ማድረግ አለባቸዉ ብለዋል:: የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ት/መምሪያ ኃላፊ ዶ/ር ብርሃኑ ደሳለኝ በበኩላቸዉ መምሪያዉ ክሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ጋር ብዙ ስራዎችን እየሰራ እንዳለ ጠቅስዉ፣ አጠገባችን ላይ በሀገር አቀፍ ደረጃ የትምህርት ልህቀት ማዕክል የሆነዉ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ መኖሩ ለከተማዉ የትምህርት ማህበረሰብ ልዩ ዕድል መሆኑን8,260Open in Telegram
Hawassa University
18 Sept, 05:44



7,090Open in Telegram
Hawassa University
17 Sept, 19:04edited
Wondo Genet College of Forestry and Natural Resources Successfully Hosts an International Dialogue ,"African Fire Dialogue" // September 17, 2026 The second day of "African Fire Dialogue: From Balem to Addis Ababa — Building an African Agenda for Fire-Resilient Landscapes," was conducted at Wondo Genet College of Forestry and Natural Resources (WGCFNR) on 16 September, 2026. This high-level multi-sectorial dialogue, which was officially began a day before this event continued today with important and engaging activities. The first activity of the event included visit to the forest and areas of wild fire-prone sites in WGCFNR compound. The trip aimed at looking at the infrastructures available on the ground in line with fire management, including the forest roads that serve to access the forests, the fire breaks that are used to suppress the transmission of fire, and the towers that are8,380Open in Telegram
Hawassa University
17 Sept, 19:04



7,840Open in Telegram
Hawassa University
17 Sept, 14:31
የሐዘን መግለጫ // መስከረም 07/2019 ዓ/ምበሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የሜዲካል ላቦራቶሪ ክፍል ባልደረባ በነበሩት ወ/ሮ ጽዮን ማቴዎስ ድንገተኛ ሕልፈት የተሰማንን ጥልቅ ሐዘን እየገለፅን ለቤተሰቦቻቸው: ለወዳጅ ዘመዶቻቸውና የሥራ ባልደረቦቻቸው ልባዊ መጽናናትን እንመኛለን። ነብስ ይማር!ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ
9,450Open in Telegram
Hawassa University
17 Sept, 14:16


10,000Open in Telegram
Related Channels
Other channels in the same section of the catalogue.
