Latest posts

𝙞𝙗𝙧𝙖𝙝𝙞𝙢 𝙝𝙚𝙮𝙧𝙚𝙙𝙞𝙣 𝙘𝙝𝙖𝙣𝙣𝙚𝙡
21 Sept, 16:03
የቁርኣንህ ገጽ መለያ ክር የት ላይ ደረሰ?ቦታውን እየቀየረ ነው ወይስ ቁርኣንን በመተውህ ምክንያት በአንድ ቦታ ቆሞ ቀርቷል?ልክ እንደ ስልክህ ሁሉ የራስህ የሆነ የተለየ ቁርኣን አለህ?! t.me/ibrahim_furii
𝙞𝙗𝙧𝙖𝙝𝙞𝙢 𝙝𝙚𝙮𝙧𝙚𝙙𝙞𝙣 𝙘𝙝𝙖𝙣𝙣𝙚𝙡
19 Sept, 17:10
ያ ረብ! ከሃሳብ ክብደትና ከልብ ጭንቀት አቅልልልኝ፤ ነገሬን ሁሉ ላንተ አደራ ሰጥቻለሁ። ጌታዬ ሆይ! እኔ በሚታየኝ ሳይሆን አንተ ለኔ መልካም ነው ብለህ በምታየው ነገር ልቤን አረጋጋው። t.me/ibrahim_furii
𝙞𝙗𝙧𝙖𝙝𝙞𝙢 𝙝𝙚𝙮𝙧𝙚𝙙𝙞𝙣 𝙘𝙝𝙖𝙣𝙣𝙚𝙡
18 Sept, 16:11
«ምንም ነገር ቢዘገይ አትበሳጭ፤ ከጀርባው አንተ የማታየው፣ ነገር ግን ለአንተ የተሸሸገ ትልቅ መልካም ነገር አለና።»http://t.me/ibrahim_furii
𝙞𝙗𝙧𝙖𝙝𝙞𝙢 𝙝𝙚𝙮𝙧𝙚𝙙𝙞𝙣 𝙘𝙝𝙖𝙣𝙣𝙚𝙡
18 Sept, 03:35

𝙞𝙗𝙧𝙖𝙝𝙞𝙢 𝙝𝙚𝙮𝙧𝙚𝙙𝙞𝙣 𝙘𝙝𝙖𝙣𝙣𝙚𝙡
17 Sept, 18:03
ታሪኩ እዚህ ይጀምራል አያበቃምም......http://t.me/ibrahim_furii
𝙞𝙗𝙧𝙖𝙝𝙞𝙢 𝙝𝙚𝙮𝙧𝙚𝙙𝙞𝙣 𝙘𝙝𝙖𝙣𝙣𝙚𝙡
17 Sept, 03:09
«የጣፋጮችን ሁሉ ጣዕም ቀመስኩ፤ ከጤናና ከሰላም የሚበልጥ ጣዕም አላገኘሁም። የመራራዎችን ሁሉ መራርነት ቀመስኩ፤ ከሰው እጅ የመጠበቅን ያህል መራር አላገኘሁም። ድንጋይንና ብረትን ተሸከምኩ፤ ከዕዳና ከብድር የሚከብድ የከበደ ሸክም አላገኘሁም።»http://t.me/ibrahim_furii
𝙞𝙗𝙧𝙖𝙝𝙞𝙢 𝙝𝙚𝙮𝙧𝙚𝙙𝙞𝙣 𝙘𝙝𝙖𝙣𝙣𝙚𝙡
14 Sept, 03:59
የወላጆቹን ውለታ የሚረሳ ሰው ምስጢር አይታመንም፤ በችግር ቀን ከጎን አይቆምም፤ ከእርሱም ምንም በጎ ነገር አይጠበቅም። ለገዛ ቤተሰቦቹ ታማኝ ያልሆነ ሰው፣ ሌላውን ለማታለልና ለመክደት ወደኋላ አይልም። t.me/ibrahim_furii
𝙞𝙗𝙧𝙖𝙝𝙞𝙢 𝙝𝙚𝙮𝙧𝙚𝙙𝙞𝙣 𝙘𝙝𝙖𝙣𝙣𝙚𝙡
12 Sept, 03:07
«ጌታዬ ሆይ! የቁርኣንን በረካ፣ የቁርኣን መጅሊሶችን እና የቁርኣን ወዳጅነትን አትንሳን። » http://t.me/ibrahim_furii
𝙞𝙗𝙧𝙖𝙝𝙞𝙢 𝙝𝙚𝙮𝙧𝙚𝙙𝙞𝙣 𝙘𝙝𝙖𝙣𝙣𝙚𝙡
10 Sept, 10:52
አላህ ወዳጆቻችንን ያቆይልን፣ ጤናችንን ይጠብቅልን፣ ቀልባችንን የሠጠንን ፀጋ እንዳያጣጥም የሚዘናጋ አያድርግብን፣ያለንን በማሳነስ ያጣንን በማግዘፍ ከሚጠመዱት አያድርገን። t.me/ibrahim_furii
𝙞𝙗𝙧𝙖𝙝𝙞𝙢 𝙝𝙚𝙮𝙧𝙚𝙙𝙞𝙣 𝙘𝙝𝙖𝙣𝙣𝙚𝙡
8 Sept, 18:20
የሺሻ፣የጫት፣ የትምባሆ መሸጫ ሱቅ የከፈተውን ሰው ሁሉ አላህ ቅኑን መንገድ እንዲመራው እለምነዋለሁ፤ ልረግመው አልፈልግም፤ ይልቁንም መልካም ነገርንና የማስተዋል ልቦናን እመኝለታለሁ። ምክንያቱም የሠራው ሥራ ስንቱን ጤና አደቀቀው! የሚያቀርበው ምርት ስንቱን ቤተሰባዊ ግንኙነት አበላሸው! የማኅበረሰቡንም ገጽታ አበላሸ! ከሰዎች መካከል ለክፉ ነገር መክፈቻ፣ ለበጎ ነገር ደግሞ መዝጊያ የሆኑ አሉ። t.me/ibrahim_furii
𝙞𝙗𝙧𝙖𝙝𝙞𝙢 𝙝𝙚𝙮𝙧𝙚𝙙𝙞𝙣 𝙘𝙝𝙖𝙣𝙣𝙚𝙡
7 Sept, 13:29
የመርከዝ ኢብኑ አባስ የ2018 ተመራቂ ተማሪዎች የሽኝት ፕሮግራም http://t.me/ibrahim_furii
𝙞𝙗𝙧𝙖𝙝𝙞𝙢 𝙝𝙚𝙮𝙧𝙚𝙙𝙞𝙣 𝙘𝙝𝙖𝙣𝙣𝙚𝙡
6 Sept, 18:12edited
የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት🎓الحمد لله الذي بنعمته تتم الصالحاتየመርከዝ ኢብን አባስ የቁርአን ሂፍዝ ማዕከል ተመራቂ ተማሪዎቻችን፤ ይህንን ፅሁፍ የምጽፍላችሁ በእናንተና ባስመዘገባችሁት ውጤት ልቤ በኩራትና በደስታ ተሞልቶ ነው። ለሁለት ዓመታት ያህል በነበረው የቁርአንና የእውቀት ጉዞ ላይ ቆይታችሁን አጠናቃችሁ ለዚህ ታላቅ ማዕረግ የበቃችሁ 120 ተማሪዎቻችን፣ እንኳን ለዚህ አበቃችሁ! እንኳን ደስ አላችሁ! በዛሬው ዕለት የቁርአን ምርቃት ፕሮግራማችን በዚህ መልኩ ደምቆ፣ አምሮና ተውቦ በመጠናቀቁ እጅግ በጣም ደስ ብሎኛል። አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ በያላችሁበት ቦታ ሁሉ ይጠብቃችሁ፤ ዲኑንና ኡማውን በቅንነት የምታገለግሉ ያድርጋችሁ። በቀጣይ የሕይወት ዘመናችሁ ሁሉ በደረሳችሁበት ቦታ የሸሪዓን እውቀት በመቅሰም የምትተጉ፣ የሰለፎችን መልካም ጎዳናና መንገድ የምትከተሉ ያድርጋችሁ፤ ሁልጊዜም ዱዓችን ከእናንተው ጋር ነው። አብሮ በመኖር፣ አብሮ በመብላትና በመጠጣት ያሳለፍነውን የወንድማማችነት ጊዜ ስናስታውስ መለያየቱ ቢከብድም፣ ኢንሻ አላህ ወደፊትም በኸር ሥራዎች ላይ አብረን እንደምንቀጥል ሙሉ ተስፋ አለን። አላህ መልካሙን ሁሉ ይግጠማችሁ።ለአላህ ብዬ እጅግ አድርጌ እወዳችኋለሁ። t.me/ibrahim_furii
𝙞𝙗𝙧𝙖𝙝𝙞𝙢 𝙝𝙚𝙮𝙧𝙚𝙙𝙞𝙣 𝙘𝙝𝙖𝙣𝙣𝙚𝙡
5 Sept, 13:48
በተሸሁድ ጊዜ ወደ አመልካች ጣት መመልከት ከሱና ነው። የአላህ መልእክተኛ ﷺለተሸሁድ በሚቀመጡበት ጊዜ የግራ እጃቸውን በግራ ጭናቸው ላይ ያደርጉ ነበር። በአመልካች ጣታቸው ይጠቁሙ ነበር። እይታቸውም ከሚያመልከቱበት ጣታቸው አያልፍም ነበር። (ሶሒሕ አል-ነሳኢ)t.me/ibrahim_furii
𝙞𝙗𝙧𝙖𝙝𝙞𝙢 𝙝𝙚𝙮𝙧𝙚𝙙𝙞𝙣 𝙘𝙝𝙖𝙣𝙣𝙚𝙡
4 Sept, 16:07
ለደስተኛ ህይወት አምስት ወርቃማ ምክሮች ~ በራስህ ተማመን፦ በውስጥህ ላለው ማንነትና ችሎታ ቦታ ስጥ። መልካም ሰው ሁን፦ መልካም ማድረግ ለሌሎች ብቻ ሳይሆን ለራስህም ሰላም ይሰጣል። ሁልጊዜ ይቅር በል፦ ይቅርታ ማድረግ ከበደል ይልቅ ነፃነትን መምረጥ ነው። ቀና አስተሳሰብ ይኑርህ፦ በየትኛውም ሁኔታ ውስጥ በጎውን መንገድ ለመመልከት ሞክር። ማንንም አትጎዳ፦ በንግግርህም ሆነ በተግባርህ የሌሎችን ሰላም አታደፍርስ። t.me/ibrahim_furii
𝙞𝙗𝙧𝙖𝙝𝙞𝙢 𝙝𝙚𝙮𝙧𝙚𝙙𝙞𝙣 𝙘𝙝𝙖𝙣𝙣𝙚𝙡
4 Sept, 05:22
ለሰዎች ወሬ ጆሮ አትስጥ! ~ ነፍሳት ሁልጊዜ የሚከበቡትና ጥቃት የሚያደርሱት የሚያበሩትን መብራቶች ብቻ ነው። አንተም የምታበራና ስኬታማ ሰው ስለሆንክ የሰዎች ወሬ አይክበድህ፤ መንገደህን ቀጥል! t.me/ibrahim_furii
𝙞𝙗𝙧𝙖𝙝𝙞𝙢 𝙝𝙚𝙮𝙧𝙚𝙙𝙞𝙣 𝙘𝙝𝙖𝙣𝙣𝙚𝙡
2 Sept, 13:32
ሐራም የሆኑ ግንኙነቶች «ጊዜያዊ ደስታ…. ዘላቂ ጸጸት።»
𝙞𝙗𝙧𝙖𝙝𝙞𝙢 𝙝𝙚𝙮𝙧𝙚𝙙𝙞𝙣 𝙘𝙝𝙖𝙣𝙣𝙚𝙡
2 Sept, 09:32edited
አሰላሙ አለይኩም ወረህመቱላሂ ወበረካቱህ| [ مركز ابن عباس لتحفيظ القرآن الكريم والتربية والإسلامية ]|📣 ታላቅ የምረቃ ጥሪ 📢መርከዝ ኢብነ ዓባስ የቁርዓን ሂፍዝና ኢስላማዊ ተርቢያ ማእከል ለሁለት ዓመት ቁርዓን በመሀፈዝ እና መሰረታዊ የሆኑ ኢስላማዊ እውቀቶችን በመቅሰም የቆዩ ብርቅዬ ልጆቹን እሁድ ጳጉሜ 1/13/2018 ከጠዋቱ 2:00 ጀምሮ አየርጤና በሚገኘው አንተነህ አዳራሽ ውስጥ ያስመርቃ።📮ማሳሰቢያ:–ለሴቶች የተዘጋጀ ቦታ አለን።🗓በዕለቱ ከሚቀርቡ ፕሮግራሞች በጥቂቱ:–🌿በአይነቱ ለየት ያለና አምስተኛ ጊዜ ልዩ ሽልማት የሚያስገኝ የቁርኣን ውድድር 🌿በቁርዓን ላይ አስደናቂ ትዕይንቶች 🌿አስደማሚ የሆነ የድምፅ ውድድር 🌿ነድዋዎች እና ሌሎችም ውብ የሆኑ ምርጥ ምርጥ ፕሮግራሞች አሉን………
𝙞𝙗𝙧𝙖𝙝𝙞𝙢 𝙝𝙚𝙮𝙧𝙚𝙙𝙞𝙣 𝙘𝙝𝙖𝙣𝙣𝙚𝙡
2 Sept, 05:26edited
መወድሰ ቁጥብያ ~ የቀደሙት ሰለፎች ያስተላለፉትን ትምህርት እንዲሁም የሶሃባዎችን ታላቅ ክብርና ማዕረግ የሚሸረሽሩ የአስተሳሰብ አዝማሚያዎችን ማስፋፋት ለኡማው ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ያመዝናል፤ በመሆኑም ጥንቁቅና አርቆ አሳቢ የሆኑ የሱና ዑለማዎች ባሉበት ሁኔታ የዚህ አይነት የተሳሳቱ አመለካከቶችን ማስተዋወቅና መደገፍ ተገቢ አይደለም። t.me/ibrahim_furii
𝙞𝙗𝙧𝙖𝙝𝙞𝙢 𝙝𝙚𝙮𝙧𝙚𝙙𝙞𝙣 𝙘𝙝𝙖𝙣𝙣𝙚𝙡
1 Sept, 11:05
እንደሚታወቀው በትናንትናው እለት በመርከዛችን 22 ተማሪዎች ሙሉ በሙሉ ቁርአንን ሀፍዘው አጠናቀዋል።ከእነዚህ ውስጥ አንዱ ተማሪ ተራው ደርሶ የሱረቱል በቀራህን የመጨረሻ አንቀጽ እያነበበ ሂፍዙን ሲያጠናቅቅ፣ ሲገለገልበት የነበረው የቁርአን ሽፋን ላይ ይህችን የቁርኣን አንቀፅ አስተዋልኩ፦(إِنَّهُ مَن يَتَّقِ وَيَصْبِرْ فَإِنَّ اللَّهَ لَا يُضِيعُ أَجْرَ الْمُحْسِنِينَ)"እነሆ፤ አላህን የሚፈራና የሚታገስ፤ አላህ የበጎ አድራጊዎችን ምንዳ በፍጹም ውድቅ አያደርግም።"ቁርአን የመሐፈዝ ጉዞ በውጣ ውረድና በትግል የተሞላ ቢሆንም፣ ይህ ተማሪ ሽፋን ላይ ባሰፈራት በዚህች አንቀጽ ጥንካሬ እያገኘ ለዚህ ታላቅ ደረጃ በቅቷል።በማንኛውም የበጎ ስራ ጉዞ ላይ ሲደክመንና ተስፋ ልንቆርጥ ስንል ይህችን የአላህ ቃል እናስታውስ። በፅናትና በትዕግስት ከተጓዝን፣ አላህ ድካማችንን ከንቱ አያደርገውም።አላህ ለተማሪዎቻችን በቁርአን የመመራት፤ እኛንም በበጎ መንገድ ላይ ፅናቱን ይስጠን!🤲 http://t.me/ibrahim_furii
𝙞𝙗𝙧𝙖𝙝𝙞𝙢 𝙝𝙚𝙮𝙧𝙚𝙙𝙞𝙣 𝙘𝙝𝙖𝙣𝙣𝙚𝙡
31 Aug, 16:53
🎉 እንኳን ደስ አላችሁ! 🎉 الحمد لله رب العالمين 🤲ለአላህ ምስጋና ይገባውና፣ በዛሬው እለት በመርከዝ ኢብኑ አባስ በአንድ ቀን ሃያ ሁለት (22) ተማሪዎች የቁርአን ሂፍዛቸውን በአላህ እገዛ ሙሉ በሙሉ አጠናቀዋል።አላህ ቁርኣንን በልቦቻቸው ውስጥ እንዲያጸናላቸው፣ ወደፊትም በክለሳቸው (በሙራጃዓው) ላይ ጠንክረው የሚሰሩና የሚተጉ እንዲያደርጋቸው ዱዓችን ነው!
Followers write to the bot, you answer by reply, your account stays hidden. Created in one tap.
How it works →Related Channels
Other channels in the same section of the catalogue.
