gram news
Injibara University channel avatar

Injibara University

@injiuniversity

You can view and join @injiuniversity right away.

ProjectsENEducation

21,546subscribers

Open the Channel

Latest posts

  • Injibara University

    22 Sept, 05:22

    ማስታወቂያ ለትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ፦ ==================
  • Injibara University

    21 Sept, 17:24

  • Injibara University

    21 Sept, 17:24

    የኢትዮጵያ ብሔራዊ ትያትር ልዑካን እንጅባራ ዩኒቨርሲቲን ጎበኙ ============= መስከረም 11/2019 ዓ.ም፤ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ትያትር ሥራ አስፈፃሚ ከተወሰኑ የአርቲስት አባላት ጋር በጋራ በመሆን የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲን የባህል ሙዝየም፣ የግቢውን አረንጓዴ ውበት፣ የአዳራሽ ግንባታ ሂደትንና የመሳሰሉትን ከዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች ጋር ጎብኝተዋል፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቲያትር ዋና ሥራ አስፈፃሚ አርቲስት አሊ ከማል ዩኒቨርሲቲውን ከጎበኙ በኋላ በሰጡት አስተያየት ዩኒቨርሲቲው ከተመሰረተ ጥቂት ዓመታት ቢሆንም ትምህርት ክፍሎችን በማስፋፋትም ሆነ በአጠቃላይ በግቢው ውስጥ የተከናወነው ተግባር የአመራሩን ተግባብቶ መሥራትና ቁርጠኝነት ልምድ ሊወሰድበት የሚገባ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ አርስት ከማል የግቢውን ውበትና መሰረተ-ልማት ሲገልጹም 30 ዓመት የተለፋበት ይመስላል በማለት አድንቀው አረንጓዴ ልማት ከተሠራበት በጥቂት ዓመታት ማልማት እንደሚቻል ዩኒቨርሲቲው ማሳያ መሆኑን ጨምረው ገልፀዋል፡፡ የጉብኝት ፕሮግራሙ የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ፣የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር አመራሮች እንዲሁም የዩኒቨርሲቲው የተለያዩ የሥራ ሂደት ኃላፊዎችና አስተባባሪዎች ከልዑክ አባላቱ ጋር በተገኙበት ተካሂዷል።ያለህን እምቅ አቅም ለይተህ ተጠቀም!
  • Injibara University

    19 Sept, 14:05

  • Injibara University

    19 Sept, 14:05

    እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ከአስተዳደርና ከአውትሶርስ ዘርፍ ሰራተኞች ጋር የ2018 ዓ.ም እቅድ አፈፃፀም ግምገማና የ2019 ዓ.ም እቅድ ትውውቅ አደረገ። =============================== መስከረም 9/2019 ዓ.ም፤ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲበዩኒቨርሲቲው የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም በአስተዳደርና በአውትሶርስ ዘርፍ ላይ የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራትን በመለየት በትኩረት ተገምግሟል።የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ሀላፊ ክንዴ ብርሃን (ዶ/ር) በግምገማ መድረኩ ላይ ተገኝተው እንደተናገሩት የአስተዳደርና አውትሶርስ ዘርፎች ለዩኒቨርሲቲው የመማር ማስተማር ሂደት መሳለጥና ዉጤታማ ክንውን ጉልህ ሚና ያላቸው የስራ ክፍሎች መሆናቸውን ጠቅሰው መድረኩ በዩኒቨርሲቲ በ2018 በጀት ዓመት የተከናወኑ አበይት የሥራ ክንውኖችን በመገምገም በቀጣይ ለ2019 በጀት ዓመት ግብዓት የሚሆኑ ገንቢ ሀሳቦች የሚንፀባረቁበት ከመሆኑ በተጨማሪ ለወደፊት ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች ላይ የመፍትሔ አቅጣጫ ለማስቀመጥ የሚረዳ ወሳኝ የውይይት ፕሮግራም መሆኑን ጨምረው ገልፀዋል።የዩኒቨርሲቲው የ2018 እቅድ አፈፃፀም ሪፖርትና የ2019 በጀት ዓመት እቅድ በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ስትራቴጂክ ጉዳዮች ሥራ አስፈጻሚ አቶ ልንገረው አትንኩት የቀረበ ሲሆን በሪፖርቱ በዩኒቨርሲቲው የተከናወኑ ዋና ዋና የስራ ክንውኖች፣ በዕቅድ አፈጻጸሙ ላይ የታዩ ጠንካራ እና ደካማ ጎኖች እንዲሁም በቀጣይ ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይቶች ተደርገውበታል።ትምህርት ሚኒስቴር በሀገር አቀፍ ዩኒቨርሲቲዎች ባካሄደው የተማሪዎች የእርካታ
  • Injibara University

    18 Sept, 17:10

  • Injibara University

    18 Sept, 17:07edited

    በተፈጥሮ እና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ በሚገኙ የቅድመ እና ድህረ ምረቃ ፕሮግራሞች ውጫዊ ሥርዓተ ትምህርት ማረጋገጫ ወርክሾፕ (External curriculum validation workshop) ተካሄደ፡፡ ============================ መስከረም 8/2019 ዓ.ም፤ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲበእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ተፈጥሮ እና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ በሚገኙ የቅድመ እና ድህረ ምረቃ ፕሮግራሞች ውጫዊ የሥርዓተ ትምህርት ማረጋገጫ ወርክሾፕ (External curriculum validation workshop) ተካሂዷል፡፡የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የትምህርት ጥራት ማጎልበቻ፣ ማረጋገጫ እና ኦዲቲንግ ዳይሬክተር ዓለም አምሳሉ (ዶ/ር) እንደተናገሩት ትምህርት ሚኒስቴር ከ2017 ዓ.ም ጀምሮ በርካታ ሪፎርሞች ማድረጉን ጠቅሰው ዩኒቨርሲቲው በእነዚህ ሪፎሞች መሰረት ቫሊዴሽንና አካዳሚክ አክረዲቴሽን እያደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡ዳይሬክተሩ አያይዘውም የስርዓተ ትምህርት ግምገማው ሲካሄድ ከዩኒቨርሲቲው ርዕይ ፣ ተልዕኮ እና የትኩረት ዘርፍ እንዲሁም ሀገር በቀል ዕውቀት እና ቴክኖሎጅን ጭምር በማካተት መሆን እንደሚገባቸው ገልፀዋልየእንጅባራ ዪኒቨርሲቲ ተፈጥሮ እና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ ዲን ታደለ ሽፈራው (ረ/ፕ) በበኩላቸው ኮሌጁ በ8 የቅድመ ምረቃ እና በ7 ድህረ ምቃ ፕግራሞች ላይ የተግባር ትምህርት፣ ቴክኖሎጅን እና ሀገር በቀል ዕውቀትን በማካተት በውጤት ላይ የተመሰረተ ስርዓተ ትምህርት ማረጋገጫ (outcome Based Curriculum validation) መደረጉን ተናግረዋል፡፡የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ድህር
  • Injibara University

    17 Sept, 15:24

Download the series as CSV
A feedback bot for your channel — free

Followers write to the bot, you answer by reply, your account stays hidden. Created in one tap.

How it works →
Create the bot