gram news
INSA - የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር - INSA channel avatar

INSA - የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር - INSA

@insagovet

Official INSA Telegram Channel በእዚህ የቴሌግራም ቻናል የሳይበርና የኢንፎርሜሽን መረጃዎች፤ የስራና ጨረታ ማስታወቂያዎች ያገኛሉ፡፡ ይከተሉን/Join Us On: YouTube: https://www.youtube.com/@cyberigna1003/fe Facebook: https://www.facebook.com/INSA.ETHIOPIA Twitter ፡ https://x.com/INSAEthio

ProjectsENMilitary

13,400subscribers

Open the Channel

Latest posts

  • INSA - የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር - INSA

    22 Sept, 14:38

    የትምህርት ተቋሞቻችን ከሳይበር ጥቃት ምን ያህል የተጠበቁ ናቸው?የትምህርት እና የምርምር ዘርፍ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለሳይበር ጥቃት በከፍተኛ ሁኔታ ከተጋለጡት የሥራ ዘርፎች መካከል አንዱ ነው። በቅርቡ የወጣው የ "Check Point" የ2025 ጥናት እንደሚያሳየው፣ የትምህርት ተቋማት በዓለም አቀፍ ደረጃ በሳምንት በአማካይ 4,356 የሳይበር ጥቃቶችን ያስተናግዳሉ።ለመሆኑ ትምህርት ቤቶች ለምን የጥቃት ዒላማ ይሆናሉ? የትምህርት ተቋማት፣ ኮሌጆችና ዩኒቨርሲቲዎች ሰፊና ክፍት የሆኑ የዲጂታል መረቦችን (networks) መጠቀማቸው፣ እንዲሁም ለሳይበር ደህንነት የሚመድቡት በጀት አነስተኛ መሆን ለጥቃት ተጋላጭ አድርጓቸዋል።የጥቃቱ ስፋት ሲታይ በመደበኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች፡ የትምህርት ቤቶች አገልግሎት መቋረጥ ሊያጋጥም የሚችል ሲሆን፤ የተማሪዎች ውጤት፣ የጤና መረጃዎች፣ እንዲሁም የመምህራን ግላዊ መረጃዎች የጥቃት ኢላማ ይሆናሉ። በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት፡ ፕሮፌሰሮችና ተመራማሪዎች ለዓመታት የደከሙባቸው አእምሯዊ ንብረቶች (Intellectual Property) እና ወሳኝ የጥናትና ምርምር መረጃዎች የመሰረቅ ከፍተኛ ስጋት ይደቀንባቸዋል። ተጨማሪውን ለማንበብ፡- https://web.facebook.com/INSA.ETHIOPIA
    Image from a post by INSA - የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር - INSAImage from a post by INSA - የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር - INSA
    89331Open in Telegram
  • INSA - የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር - INSA

    22 Sept, 09:02

    የሀገራት የመረጃ ልውውጥ ወሳኝነት - ለሳይበር ደህንነትየአውሮፓ ኦዲተሮች ፍርድ ቤት (The European ‌Court of Auditors - ECA) ባሳለፍነው ሰኞ እንዳስታወቀው፤ የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት በሳይበር ጥቃቶች ዙሪያ በቂ መረጃ አለመለዋወጣቸው የህብረቱን የሳይበር ደህንነት የጋራ መከላከያ ጥረቶች እያዳከመው ይገኛል።27ቱ የአውሮፓ ህብረት ሀገራት ስብስብ ለሳይበር ደህንነት ዘርፍ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት በተያዘው የፈረንጆቹ 2026 በጀት አመት 1.4 ቢሊዮን ዩሮ (1.61 ቢሊዮን ዶላር) የመደበ ሲሆን፣ ትብብርን ለማሻሻል ጥረት እያደረገ ቢሆንም በሚፈለገው ልክ ውጤታማ መሆን እንዳልቻለ ገልጿል። የሪፖርቱ አዘጋጆች "ደካማ የመረጃ ልውውጥ የመላው የደህንነት ስርዓቱ ዋነኛ ደካማ ጎን (Achilles heel) ሆኗል" ብለዋል።አደገኛ የሳይበር ጥቃት በሚያጋጥምበት ጊዜ ፈጣን እና ተግባራዊ ሊደረግ የሚችል መረጃ መለዋወጥ ወሳኝ ነው፤ ይህ ካልሆነ ኔትወርኮች እና የደህንነት ስርዓቶች እሴታቸውን ያጣሉ ሲል ሪፖርቱ አክሎ ገልጿል። ለአብነትም በመስከረም 2025 በለንደን፣ ብራስልስ፣ በርሊን እና ደብሊን አውሮፕላን ማረፊያዎች ላይ የተፈጠረውን የራንሰምዌር (Ransomware) ጥቃት ጠቅሶ፣ የትኛውም ጥቃቱ የደረሰበት ሀገር ለአውሮፓ የሳይበር ደህንነት ኤጀንሲ ሪፖርት አለማድረጉን ገልጿል።ባለፈው ሐምሌ ወር፣ የአውሮፓ ኮሚሽን የሳይበር ደህንነት መረጃ ልውውጥን በተመለከተ የህብረቱን ህጎች ከራሳቸው ብሄራዊ ህግ ጋር ባለማጣጣማቸው ፈረንሳይ፣ አየርላንድ፣ ኔዘርላንድስ እና ስፔንን በአውሮፓ
    Image from a post by INSA - የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር - INSAImage from a post by INSA - የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር - INSA
  • INSA - የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር - INSA

    21 Sept, 14:01

    ከክፍል ውስጥ እስከ ሳይበር ምህዳር፡ የዘመኑ መምህር የዲጂታል ክህሎት እና የሳይበር ደህንነት🎓 ለመላው የሀገራችን አንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እንዲሁም የኮሌጅ እና ዩኒቨርሲቲ መምህራን በሙሉ፤ እንኳን ለአዲሱ የትምህርት ዘመን በሰላም አደረሳችሁ!አዲሱን የትምህርት ዘመን ሲጀምሩ የዲጂታል ክህሎትዎን ማሳደግ እና የሳይበር ደህንነትዎን (Cyber Hygiene) መጠበቅ የዕቅድዎ ዋነኛ አካል ሊሆን ይገባል፡፡ አሁን ባለንበት የዲጂታል ሽግግር እና አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ዘመን፣ ቴክኖሎጂን ከማስተማር ስራ ጋር ማስተሳሰር ጊዜን ለመቆጠብ፣ ተማሪዎችን በንቃት ለማሳተፍ እና ትምህርትን ይበልጥ ማራኪ ለማድረግ እጅግ ወሳኝ ነው፡፡ይሁንና ኢንተርኔት ለትምህርት የሚያስገኘው ጥቅም የጎላ እንደሆነ ሁሉ፣ ተቋማዊ እና የግል መረጃዎችን ለሳይበር ጥቃት የመጋለጥ እድልንም ይዞ ይመጣል። ስለዚህ ስኬታማ፣ ዲጂታል ክህሎት ያለው እና የሳይበር ደህንነቱ የተጠበቀ መምህር ለመሆን ምን ማድረግ አለብዎት?📌 የኤአይ (AI) ቴክኖሎጂን በአግባቡ መጠቀም፦ የ AI መሳሪያዎችን በመጠቀም የወረቀት ስራዎችን ማቃለል እና የትምህርት አሰጣጡን ማዘመን ይችላሉ። ነገር ግን ተማሪዎች በራሳቸው የማሰብ አቅማቸውን እንዳይዘነጉ ቴክኖሎጂውን በሃላፊነት እንዲጠቀሙበት አቅጣጫ ማሳየት እና መምራት ይገባዎታል። ተጨማሪውን ለማንበብ፡- https://web.facebook.com/INSA.ETHIOPIA
    Image from a post by INSA - የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር - INSAImage from a post by INSA - የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር - INSA
    1,77083Open in Telegram
  • INSA - የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር - INSA

    21 Sept, 09:04

    የሳምንቱ የሳይበር ደህንነት መረጃዎች (ከመስከረም 4 እስከ 10/2019 ዓ.ም)ሰላም! በየሳምንቱ ሰኞ ይዘንላችሁ የምንቀርበውን “ሳምንቱ በሳይበር” ሳምንታዊ የሳይበር ደህንነት መረጃዎች፤ በዲጂታሉ ዓለም የተመዘገቡ አበይት ዜናዎችን፣ አዳዲስ የቴክኖሎጂ ስጋቶችን እና የመፍትሔ ሃሳቦችን እንዲሁም ሳምንታዊ የመጽሐፍ እና ዘጋቢ ፊልም ጥቆማ አካተን እነሆ ብለናል::1. ሀገራዊ የሳይበር ደህንነት መረጃ የቁልፍ መሠረተ ልማት ተቋማት የ1 ዓመት የዝግጅት ጊዜ መቆጠር ጀምሯል—አስፈላጊውን ዝግጅት ያጠናቁ! በቅርቡ በነጋሪት ጋዜጣ የታወጀውን የቁልፍ መሠረተ ልማቶች የሳይበር ደህንነት ጥበቃ አዋጅ (ቁጥር 1426/2018) ተከትሎ፣ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) አዋጁን ወደ ሙሉ ትግበራ ለማስገባት የሚያስችሉ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን እየሰራ ይገኛል። በአዋጁ መሠረት የተለዩ 12 የቁልፍ መሰረተ ልማት ዘርፎች (የፋይናንስ፣ የቴሌኮም፣ የጤና፣ የትራንስፖርት፣ የኃይል አቅርቦት እና ሌሎችም) ውስጥ የሚመደቡ የቁልፍ መሠረተ ልማት ባለቤቶችና ኦፕሬተሮች አዋጁ በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የ1 ዓመት የዝግጅት ጊዜ ተሰጥቷቸዋል። ይህ የተሰጠው የ1 ዓመት ጊዜ ተቋማት በአዋጁ ላይ የተዘረዘሩትን 18 ዋና ዋና የሳይበር ደህንነት ግዴታዎች ለማሟላት የሚዘጋጁበት ወሳኝ ምዕራፍ ነው።በመሆኑም ሁሉም የቁልፍ መሠረተ ልማት ተቋማት ይህ የጊዜ ገደብ ከማብቃቱ በፊት የውስጥ የሳይበር ደህንነት ፖሊሲዎቻቸውን እንዲቀርጹ፣ የሰው ኃይልና የቴክኖሎጂ አቅማቸውን እንዲገነቡ፣ እንዲሁም አስተዳደራችን
    Image from a post by INSA - የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር - INSAImage from a post by INSA - የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር - INSA
    1,86021Open in Telegram
  • INSA - የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር - INSA

    18 Sept, 11:37

    ተቋምዎ የሲስኮ (Cisco) ሲስተምን ይጠቀማል? እንግዲያውስ ይህ የሳይበር ደህንነት መረጃ እርስዎን ይመለከታል!የሲስኮ (Cisco) ኩባንያ በ “Cisco Identity Services Engine (ISE)” ምርቱ ላይ እጅግ አደገኛ የሆነ እና ከፍተኛ ጉዳት ሊያደርስ የሚችል የደህንነት ክፍተት (Vulnerability) መገኘቱን አስታውቋል።ይህ የደህንነት ክፍተት (CVE-2026-76460) በቴክኖሎጂው አለም ከፍተኛው የሆነውን (CVSS 10.0) ደረጃ የተሰጠው ነው። የሳይበር ጥቃት አድራሾች ምንም አይነት የይለፍ ቃል ወይም ህጋዊ ፈቃድ ሳያስፈልጋቸው የተበላሸውን የ “API endpoint” ክፍተት በመጠቀም ወደ ተቋማት ሲስተም ሰብረው በመግባት ሙሉ ቁጥጥር (Root Privilege) እንዲያገኙ ያስችላቸዋል። የሲስኮ ISE ሲስተም በተቋማት ውስጥ የኔትወርክ (Wired, Wireless እና VPN) መዳረሻዎችን የሚቆጣጠር ማዕከላዊ የደህንነት መድረክ በመሆኑ ክፍተቱ አደጋውን የከፋ ያደርገዋል።ተቋማት ምን ማድረግ አለባቸው? ሶፍትዌሩን ማዘመን (Update)፡ ሲስኮ ለችግሩ መፍትሄ የሚሆን የሶፍትዌር ማሻሻያ አውጥቷል። በመሆኑም 'Cisco ISE' እና 'Cisco ISE-PIC' የምትጠቀሙ ተቋማት ያለምንም መዘግየት ሲስተማችሁን አፕዴት (Update) እንድታደርጉ ይመከራል። ተጨማሪውን ለማንበብ፡- https://web.facebook.com/INSA.ETHIOPIA
    Image from a post by INSA - የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር - INSAImage from a post by INSA - የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር - INSA
    2,9901254Open in Telegram
  • INSA - የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር - INSA

    17 Sept, 09:01

    አዳዲስ የሳይበር ታለንቶችን ፍለጋ በጅማ… 🔍💻ወጣቶች ያላቸውን የቴክኖሎጂ ፍላጎት፣ እውቀት እና ልዩ ተሰጥኦ ለማሳደግ ብዙ ርቀቶችን ቢሄዱም ህልማቸውን እውን ማድረግ ቀላል አልነበረም፡፡ በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር #INSA "ኢትዮ ሳይበር ታለንት" የተለኮሰው የእውቀት ፋኖስ አድማሱን በማስፋት፣ በአዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የሰመር ካምፕ ፕሮግራሙን አንድ ብሎ ካስጀመረበት 2013 ዓ.ም ጀምሮ በርካታ የቴክኖሎጂ ተሰጥኦ ያላቸውን ወጣቶች ማስተማር እና ማብቃት ችሏል፡፡ ይህንን ወርቃማ እድል ተሰጥኦ ላላቸው ወጣቶች በሙሉ ከደጃፋቸው ለማድረስ ፕሮግራሙ በ 2018 ዓ/ም በሀገራችን በሚገኙ 6 ዩኒቨርሲቲዎች የተካሄደ ሲሆን፣ ከእነዚህም መካከል ጅማ ዩኒቨርሲቲ አንዱ ነበር፡፡ በጅማ ዩኒቨርሲቲ የተካሄደውን የ5ኛውን ዙር የሳይበር ታለንት ሰመር ካምፕ ስልጠና፣ የተማሪዎቹን የውድድር መንፈስ እና የቆይታ ሁኔታ "ሳይበርኛ" የቴሌቪዥን ፕሮግራም በልዩ ዝግጅት ዳስሶታል። 👇 ሙሉ ፕሮግራሙን ለማየት ከታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ፡ 🔗 https://youtu.be/U6a1u4I0Y4E?si=Kv0356M63ORaCLKr #INSA #EthioCyberTalent #Cyberigna #JimmaUniversity #CyberSecurity #DigitalEthiopia2030
    YouTubeአዲስ ታለንት ፍለጋ በጅማ! 5th Summer Camp in JimmaUnlocking Future Tech Leaders: 5th Summer Camp in Jimma! Welcome to the 5th Summer Camp in Jimma, dedicated to discovering and nurturing the next generation of tech innovators and cybersecurity talent! In this video, watch brilliant young minds pitch innovative…
    3,32043Open in Telegram
  • INSA - የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር - INSA

    15 Sept, 10:46

    አሁን ያለው ዝግጅታችን በቂ አይደለም! — ግዙፍ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ለአስቸኳይ የሳይበር መከላከል ጥሪ አቀረቡበዓለም አቀፍ ደረጃ ግዙፍ የሆኑ የቴክኖሎጂ ተቋማት የሳይበር ጥቃቶችን፤ በተለይም ደግሞ በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) የታገዙ የሳይበር ጥቃቶችን ለመመከት የተቀናጀና የጋራ የሳይበር መከላከል እርምጃ (Defensive Surge) መወሰድ እንዳለበት አሳሰቡ።ማይክሮሶፍት (Microsoft)፣ ኦፕንኤአይ (OpenAI)፣ አልፋቤት (Alphabet)፣ አንትሮፒክ (Anthropic) እና አማዞን (Amazon) ግዙፍ የቴክኖሎጂ ተቋማት በጋራ ባወጡት መግለጫ፤ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተፈጸሙ የሚገኙ የሳይበር ጥቃቶች ስፋትና ረቂቅነት እየጨመረ እንደሚሄድ በማስጠንቀቅ ጥቃቶቹን በጋራ ለመመከት የሚያስችሉ ሦስት ምክረ ሃሳቦችን አቅርበዋል፦ አሁን ያለው አደረጃጀትና ዝግጅት በቂ አለመሆኑን መገንዘብ፦ ነባሩ የደህንነት አሰራር እየተወሳሰቡ የሚመጡ የሳይበር ጥቃቶችን ለመመከት በቂ አለመሆኑን አምኖ መቀበል። የመከላከል አቅምን በ-AI ቴክኖሎጂ ማብቃት፦ የሳይበር ደህንነት ጠባቂዎችንና ተቋማትን በዘመናዊ የ-AI የመከላከል አቅም ማስታጠቅ። የተቀናጀና የጋራ ምላሽ መስጠት፦ በሁሉም እርከኖች የተቀናጀ የመከላከል ምላሽ መፍጠር።ኩባንያዎቹ ወደፊት ሊወሰዱ ይገባል ያሏቸውን 4 ዋና ዋና እርምጃዎችም ጠቁመዋል፦ ተጨማሪውን ለማንበብ፡- https://web.facebook.com/INSA.ETHIOPIA
    Image from a post by INSA - የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር - INSAImage from a post by INSA - የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር - INSA
    3,660102Open in Telegram
  • INSA - የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር - INSA

    14 Sept, 08:28

    በአዲስ መንፈስ ወደ ትምህርት ቤት፡ የዲጂታል ዘመን ተማሪዎች ማወቅ ያለባቸው 5 የሳይበር ጥንቃቄዎችለውድ የኢትዮጵያ ታዳጊ ወጣት ተማሪዎች፤ እንኳን ለ2019 የትምህርት ዘመን በሰላም አደረሳችሁ! አዲሱ ዓመት አዲስ እቅድ የምናወጣበት፣ አሮጌ ልማዶቻችንን ትተን በታደሰ መንፈስ ወደ ትምህርታችን የምንመለስበት ውብ ወቅት ነው። ዛሬ ትምህርታችን ከቴክኖሎጂ እና ከኢንተርኔት ጋር እጅግ የተቆራኘ ነው። የትምህርት መረጃዎችን ለማግኘት፣ የምርምር ስራዎችን ለመስራት እና አዳዲስ ክህሎቶችን ለመቅሰም ኢንተርኔት የማይተካ ሚና አለው። ይሁን እንጂ የዲጂታል ዓለም ከጥቅሙ ጎን ለጎን የተለያዩ የሳይበር አደጋዎችን ይዞ እንደሚመጣ ልብ ማለት ይገባል።በሀገራችን የኢንተርኔት ተደራሽነት እየሰፋ በሄደ ቁጥር፣ ህጻናት እና ወጣቶች (ተማሪዎች) የሳይበር አጥቂዎች ቀዳሚ ዒላማ እየሆኑ መጥተዋል። ስለዚህ የ2019 የትምህርት ዓመት ስንጀምር የሚከተሉትን የሳይበር ደህንነት እና የዲጂታል ንቃት እቅዶች በማውጣት ራሳችንን እንጠብቅ፡ኢንተርኔትን ለዕውቀት ብቻ ተጠቀሙ: አዲሱን ዓመት ዲጂታል አሻራችንን ለትምህርት ብቻ እንድናውለው እናቅድ። ማህበራዊ ሚዲያዎችን ለጥናት እና ለአእምሮ ማበልጸጊያ እንጂ ትምህርታችንን እንዲያዘናጋን አንፍቀድ። ተጨማሪተጨማሪውን ለማንበብ፡- https://web.facebook.com/INSA.ETHIOPIA
    Image from a post by INSA - የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር - INSAImage from a post by INSA - የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር - INSA
    3,710161Open in Telegram
  • INSA - የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር - INSA

    11 Sept, 12:15

    Image from a post by INSA - የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር - INSAImage from a post by INSA - የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር - INSAImage from a post by INSA - የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር - INSAImage from a post by INSA - የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር - INSA
    4,530261381Open in Telegram
  • INSA - የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር - INSA

    11 Sept, 12:15

    ከ3,000 በላይ ድሮኖች፣ አንድ ደማቅ ሰማይ! ​የ2019 አዲስ ዓመት አቀባበል በታሪካዊ የድሮን ሾው ደምቆ አምሽቷል። በቴክኖሎጂ እና በብርሃን የተሸለመው ሰማያችን የአዲሱ ዘመን ተስፋችን ማብሪያ ሆኗል። #droneshow #INSA #Newyear #2019E.C
    Image from a post by INSA - የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር - INSAImage from a post by INSA - የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር - INSAImage from a post by INSA - የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር - INSAImage from a post by INSA - የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር - INSA
    4,2601372Open in Telegram
  • INSA - የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር - INSA

    10 Sept, 09:16

    የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር የ2019 አዲስ ዓመት የመልካም ምኞት መልዕክት አስተላለፉየኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ ለመላው የሀገራችን ህዝቦች እንዲሁም ለተቋሙ አመራሮችና አባላት የእንኳን አደረሳችሁ መልካም ምኞታቸውን አስተላልፈዋል።አዲሱ ዓመት የሰላም፣ የጤና ፣ ሀገራዊ አንድነታችን የሚጠናከርበት፣ የተጀመሩት የልማትና የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ስራዎቻችን ወደ ላቀ ደረጃ የሚሸጋገሩበት የስኬት ዓመት እንዲሆን ዋና ዳይሬክተሯ ምኞታቸውን ገልጸዋል።ወ/ሮ ትዕግስት በመልዕክታቸው ፣ ባሳለፍነው የበጀት ዓመት የተቋሙ አመራር እና አባላት ሌት ተቀን ሳይታክቱ የሀገራችንን የሳይበር ምህዳር ደህንነቱን በመጠበቅና ሀገራዊ የዲጂታል ሉዓላዊነትን በማረጋገጥ ለተመዘገበዉ ስኬት እና ውጤት የላቀ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።በ2019 አዲስ ዓመትም አዳዲስ የቴክኖሎጂ ዕድሎችን በመጠቀምና ሊያጋጥሙ የሚችሉ የሳይበር ስጋቶችን አስቀድሞ በመከላከል ረገድ የተጀመሩትን ሀገራዊ የሳይበር አቅም ግንባታዎች አስተዳደሩ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ዋና ዳይሬክተሯ አረጋግጠዋል።በመጨረሻም ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ ወቅቱ የበዓል ወቅት እንደመሆኑ በኦንላይን ገበያዎች፣ በማህበራዊ ሚዲያ እና በዲጂታል የክፍያ ስርዓቶች ላይ የሚፈጸሙ የሳይበር ማጭበርበሮችና የመረጃ ስርቆቶች የመጨመር ዝንባሌ ያላቸው በመሆኑ ህብረተሰቡና ተቋማት አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። በተለይም በኤስኤምኤስ (SMS)፣ በዋትስ አፕ፣ በቴሌግራም እና በኢሜይል የሚላኩ
    Image from a post by INSA - የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር - INSAImage from a post by INSA - የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር - INSA
    2,630175311Open in Telegram
  • INSA - የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር - INSA

    10 Sept, 08:08

    ​"የዲጂታል ሽግግር ምርጫ ሳይሆን የልማታችን ዋና ማዕከል ነው!" - የተከበሩ አቶ ታገሰ ጫፎ​ጳጉሜን 5/2018 ዓ/ም፤ አዲስ አበባ:- "ነገን ዛሬ መገንባት፣ ዲጂታል ሽግግር፣ ሰው ሰራሽ አስተውሎት፣ የምግብ ሉዓላዊነትና ሀገራዊ የአደጋ ስጋት አስተዳደር ለኢትዮጵያ ማንሰራራት" በሚል ሀገራዊ ፋይዳው የጎላ መሪ ሃሳብ "የነገ ቀን" (ጳጉሜን 5) በሳይንስ ሙዚየም በድምቀት እየተከበረ ይገኛል።​የዕለቱ ዋና ዓላማ የነገዋን ብሩህ ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ ዛሬ ላይ ጽኑ መሠረት መጣልን ማሳሰብ ሲሆን፣ በዚህም የዲጂታል ሽግግር እና የሳይበር ደህንነት ወሳኝ ሚና እንዳላቸው በስፋት ተመላክቷል።​በፕሮግራሙ ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢፌዲሪ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ ታገሰ ጫፎ፣ ኢትዮጵያ የዲጂታል ሽግግሯን በብቃት ለመምራት የሚያስችላትን ግልጽ ስትራቴጂ ነድፋ ወደ ተግባር መግባቷን ገልጸዋል። ይህንኑ ስትራቴጂ ስኬታማ ለማድረግ የሰው ሃይል ልማት፣ ሀገር በቀል የቴክኖሎጂ ፈጠራዎችና የሳይበር ደህንነት በከፍተኛ ትኩረት እየተሰራባቸው መሆኑን አብራርተዋል። ተጨማሪተጨማሪውን ለማንበብ፡- https://web.facebook.com/INSA.ETHIOPIA
    Image from a post by INSA - የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር - INSAImage from a post by INSA - የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር - INSAImage from a post by INSA - የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር - INSAImage from a post by INSA - የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር - INSA
    2,02951Open in Telegram
  • INSA - የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር - INSA

    10 Sept, 04:45

    🇪🇹 ጳጉሜን 5 - "የነገ ቀን" 🇪🇹​የሳይበር ደህንነቷ የተረጋገጠች ዲጂታል ኢትዮጵያን ለትውልድ!​ጳጉሜን 5/2018 ዓ.ም "የነገ ቀን" በሀገር አቀፍ ደረጃ በድምቀት ሲከበር፣ ነገን ዛሬ ላይ ሆነን የምንቀርጽበት፣ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ግስጋሴያችንን እና በቴክኖሎጂ በራስ አቅም የምትቆም አዲሲቷን ኢትዮጵያን ዕውን የምናደርግበትን ብሩህ ራዕይ የምናስብበት ዕለት ነው።​ይህ ቀን ሀገራችን በዲጂታሉ ዘርፍ ያስመዘገበቻቸውን ጉልህ ስኬቶች — የዜጎችን ህይወት ያቀለለውን የአንድ ሞሰብ አገልግሎት፣ የነገዋን ሀገር የሚረከቡ አዳዲስ ፈጣሪ ወጣቶችን አቅም የሚገነባውን የ5 ሚሊዮን ኮደርስ ኢኒሼቲቭ፣ እንዲሁም ዘላቂ የሳይበር ደህንነትና ሉዓላዊነትን በማረጋገጥ በኩል የተጓዝንበትን ስኬታማ መንገድ የምናከብርበት ልዩ ቀን ነው።​በተለይም የኢትዮጵያ ልጆች እና ወጣቶች ነገ የሚቀበሏት ሀገር በዲጂታሉ ዓለም ምን እንደምትመስል በስፋት የምንወያይበት ዕለት ነው።የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ​አስተዳደር (ኢመደአ) የሳይበር ደህንነቷ የተረጋገጠ ዲጂታል ኢትዮጵያን ዕውን በማድረግ ሂደት፤ ሀገራችን በጀመረችው የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ ላይ ሊያጋጥሙ የሚችሉ የሳይበር ስጋቶችን አስቀድሞ በመከላከልና በመቀልበስ የሀገሪቱን የሳይበር ሉዓላዊነት ለማስጠበቅ የኢትዮጵያ የሳይበር ጋሻ ሆኖ ቆሟል።​🌼 ​እንኳን ለ "የነገ ቀን" እንዲሁም ለብሩህ ተስፋ ለተሞላው ለ2019 ዓ.ም አዲሱ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ!​ 🌼#INSA ​#የነገ_ቀን #ጳጉሜን5 #DigitalEthiopia2030
    Image from a post by INSA - የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር - INSAImage from a post by INSA - የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር - INSA
    2,05082Open in Telegram
  • INSA - የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር - INSA

    9 Sept, 17:33

    "የኅብር ቀን"ን በማስመልከት ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር የተደረገ የበዓል መዋያ ድጋፍ! 🇪🇹አዲስ አበባ፤ ጳጉሜን 4​/2018 ዓ/ም:- በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተከበረ የሚገኘውን ጳጉሜን 4 "የኅብር ቀን" በማስመልከት፤ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 ነዋሪ ለሆኑና የኢኮኖሚ አቅማቸው ዝቅተኛ ለሆኑ የሕብረተሰብ ክፍሎች የማዕድ ማጋራት መርሃ ግብር አካሄደ።​በዚህ የድጋፍ አሰጣጥ መርሃ ግብር ላይ የኢመደአ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ አስቴር ዳዊት ተገኝተው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል። በመልዕክታቸውም፤ በዓሉን ስናከብር አቅም የሌላቸውን ወገኖቻችንን በማሰብ፣ ማዕድ በማጋራት እና አብሮነትን በሚያጎለብት መልኩ ሊሆን ይገባል ብለዋል።ተጨማሪ የሳይበር ደህንነት መረጃዎችን ለማግኘት፡- • ድረ ገጽ፦ https://www.insa.gov.et • ፌስቡክ፡- https://web.facebook.com/INSA.ETHIOPIA • ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@insa_et?_t=8qBKkyp092r&_r=1 • ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/@cyberigna1003/featured • ትዊተር (X) ፦ https://twitter.com/INSAEthio • ሊንክድኢን:- https://www.linkedin.com/.../information-network.../ • የሳይበር ጥቃት ጥቆማ ለመስጠት፡- ነጻ የስልክ መስመር 933