gram news
ኩራዝ channel avatar

ኩራዝ

@kuraz2016

እንኳን ደህና መጣችሁ"Welcome! ፨የዚህ ቻናል ዋና አላማ አንባቢ ትውልድ ለመፍጠር ታስቦ የተከፈተ ነው "ሳትማሩና መጻሕፍት ሳታነቡ የምታገኙት ዕውቀት አይኖርም" መጽሐፈ ቀሌምንጦስ ከዚህ ቻናል ውጭ ሌላ ምንም አይነት ቻናልም ሆነ ተወካይ የለኝም ። "ሰው ለሰው ጥሩም ነው ጠሩም ነው" ለሀሳብ አስተያየት @Whibeslase

ProjectsENReligion

19,600subscribers

Open the Channel

Latest posts

  • ኩራዝ

    14 Sept, 08:02

    መልክአ 📚ቅዱስ ዮሐንስ ፍቁረ እግዚእሰላም ለአፈከ ዋዕዩ (ግለቱ) ሣያቃጥለው የመለኮት አፍ ለሣመው ለአፍህ ሰላምታ ይገባል ፍጥሞ የምትባል ደሴት ምስጢርን ያየህ ቅዱስ ሆይ የራዕይህን ትርጓሜ ማንበብ መተርጎም እችል ዘንድ የአንደበትህ ማህተም ለእኔ ፍታልኝ(ግለፅልኝ)ሰላም ለአስናኒከ የአባቶች ትራፊ ሞት ፍሬን ላልቀመሱ (ላላኘኩ) እንደ ወተት ነጫጭ ለሆኑ ጥርሶችህ ሰላምታ ይገባል የተላከ ሐዋርያ እና ነብይ ቅዱስ ዮሐንስ ሆይ ንግግሬ የጣፈጠ እና ያማረ ይሆን ዘንድ ጨው ንግግርህ አልጫው አንደበቱን ያጣፍጠው ::ሰላም ለልሳንከ ሁለት መንገዶች ለሚናገር አንደበትህ ሰላምታ ይገባል እንደዚሁም አንዲቷ የሕይወት አንዲቷ የሞት ናቸው የዕውቀትን ባህር የምትዋኝ የቋንቋዎች አባት ቅዱስ ዮሐንስ ሆይ ከእነዚህ ከሁለቱ ሕይወት በተሰኘችው መንገድ ውሰደኝ ከአንተ ዘንድ የመምሐኛት ይህች ናትናሰላም ለቃልከ የተመሰገነ ወንጌልን ካስተማሩ ከሦስቱ ወንጌላውያን ይልቅ ነገሩ ልዑል (ከፍ) ያለ ለሆነው ለቃልህ ሰላምታ ይገባል የእግዚአብሔር ወዳጅ ብፁዕ ዮሐንስ ሆይ በእኔ ላይ ክፈ የመከሩ ጠላቶቼን በቃልህ ትዕዛዝ ትበትንልኝ ዘንድ ልመናዬን በፊትህ አደርሳለሁ::በረከቱ ረድኤቱ አማላጅነቱ አይለየን አሜን።🙏🙏🙏
    Image from a post by ኩራዝImage from a post by ኩራዝ
  • ኩራዝ

    14 Sept, 05:11

    🌼 "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። 🌼🌼 #መስከረም ፬ (4) ቀን።🌼 እንኳን #ከግብጽ_ለኢትዮጵያ_ሊቀ_ጳጳስ ተሾመው ለመጡ በመላው ዓለም እና በኢትዮጵያ ብዙ የዋሻ እና የሕንጻ ቤተ ክርስቲያንን ላነጹ #ለብፁዓዊ_አቡነ_ሙሴ ዘድባ ለዕረፍት በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።✝ ✝ ✝ 🌼 #ብፁዕ_አቡነ_ሙሴ_ዘድባ፦ በአባታቸው የእቤታችን ጠባቂ የአረጋዊ ቅዱስ ዮሴፍ የልጅ ልጅ ሲሆኑ፤ በእናቸው በኩል ድንግል ማርያም ከልጇ ጋር በቃና ዘገሊላ ሰርግ የተገኘችበት የዶኪማስ የልጅ ልጅ ናቸው። የአባታቸው ስም ቅዱስ ዮስጦስ ሲባል፤ የእናታቸው ስም ቅድስት ጵስርስቅላ (ሶልያና፡ማርያም) ይባላል።🌼 በሊቀ መላእክት በቅዱስ ገብርኤል አብሳሪነት ታኅሣሥ 8 ቀን ተወለዱ። በዚህች ቀን ከእናታቸው እቅፍ በመውረድ "ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ምስጋና ይሁን፤ ከጨለማ ወደ ብርርሃን ላወጣኸኝ" ብለው ፈጣርያቸውን አመስግነዋል። በ40 ኛው ቀን የጌታ ሐዋርያት ቅዱሳን ጴጥሮስ፣ ያዕቆብ፣ ፊሊጶስና እንድርያስ ሆነው ጥር 18 ክርስትናን አቡነ ሙሴን አነሱዎቸው።🌼 በ3 ዓመታቸው ወላጆቻቸው ለቤተ ክርስቲያን ሰጧቸው። ቅዱስ ፋኑኤልና ቅዱስ ዮናኤል ሕብስት ሰማያዊ እያመጡ ይመግቧቸው ነበር። ከዚህ በኋላ መምህራቸው ዝክረ ጻድቅ ብሉያትንና ሐዲሳትን አስተማራቸው። በወንጌላዊው በቅዱስ ማርቆስ እጅ ዲቁና ተሾሙ። እመቤታችን ማርያምም ለብፁዓዊ ሙሴ ልፋፈ ጽድቅ፣ ሰኔ ጎልጎታን፣ ባርቶስና ራዕየ ማርያምን ሰታቸዋለች። ወገባቸውን ከጠጉር በተሰራ መታጠቂያ ይታጠቁ ነበር። አቡነ ዘበሰማያትም በጀመሩ ጊዜ ሰባቱ ሰማያት ተከፍተውላቸው ከአጋዕዝተ ዓለም ሥላሴ ጀምሮ ሁሉንም ቅዱሳን በግልጥ ያያሉ። ሲሰግዱ እንባቸው ደረታቸውና እግራቸውን እያራሰ በመሬት ይፈሳል። በዓለም ብዙ የዋሻ ቤተ ክርስቲን አንጸዋል።🌼 የህንፃ ሥራ ከመደመራቸው በፊት 40 ቀን ይጾማሉ። ሁለቱ መላእክት ቅዱስ ፍርክኤልና ቅዱስ ፍናኤል እየረዷቸው መቅደስን ያንጻሉ። የዋሻ ቤተ መቅደስ ሥራ ጎን ለጎን መስቀልና ሌሎች ንዋየ ቅዱሳት ይሠራሉ። የሚሠሯቸው መቅደሶች ከፊሉ የሚታዩ ምዕመናን የሚገለገሉባቸው ሲሆን የቀሩት የማይታዩ ስውራን የሚገለገሉበት ነው። አቡነ ሙሴ ጵጵስና የተሾሙት በ 12ቱ ሐዋርያት በአንድነት ነው። ዘመናቸውን ሁሉ ከ24ቱ ካህናተ ሰማይ ጋር በመሆን የአብ የወልድ የመንፈስ ቅዱስን መንበር አጥነዋል። በድንግልናቸው በንጽሕናቸው የከበሩ 12 ክንፍ የተጎናጸፉ ናቸው። ጥቂቶች ለማየት የታደሉትን ብሔረ ብፁዓን ሄደው አይተዋል።🌼 አቡነ ሙሴ በግብፅና በእስራኤል መካከል ሲካር በሚባል ቦታ ካገለገሉ በኋላ ጣዖታትን ለማሳፈር ወደ መቄዶንያ ሄደው ጣዖት አምላኪውን ንጉሥ ገሰጹት። ንጉሥ ተቆጥቶ አጥንታቸው እስኪሰበር ድረስ በብረት አስደብድቦ በብረት አልጋ ላይ አስተኝቶ እሳት አነደደባቸው። ቅዱስ ሚካኤልና ቅዱስ ገብርኤል ግን ዳሰው ፈወሷቸው። በማግስቱ ወደ ፍርድ አደባባይ ቢወስዷቸው ምንም እንዳልሆኑ ንጉሡ በማየቱ በንዴት ሰውነታቸውን በሰይፍ አስቆራረጠ። ከሰውነታቸው ደም፣ ውሃ፣ ወተትና መዓር ወጣ። ጌታችንም አድኗቸው "በስምህ የተማፀነውን መልካም ነገር አደርግታለሁ" ብሎ ቃል ኪዳን ገባላቸው።🌼 በግብጽ አንስጣስዮስ ቴዎዶስዮስ ተብለው ሢነግሡ መላእክት የአባቱ የዳዊት መንግሥት ቅባት ቀቧቸው፤ የመንግሥት ልብስ አለበሷቸው፤ የመንግሥት ሥርዓት ሁሉ ሰጧቸው። የጣዖታትን ቤት አፍርሱ "ቤተ ክርስቲያንን ሥሩ" በማለት ኅዳር 12 ቀን አዋጅ ነጋሪን ላኩ። ጌታችን በግብፅ ተሶዶ ሳለ ለአረጋዊ ቅዱስ ዮሴፍ የተናገረው ትንቢት ተፈፀመ "ከልጅህ የሚወለድ በግብፅ ያሉትን ጣዖቶች አፍርሶ ሃይማኖትን ያጸናል" ብሎ ነበር። እዲሁም ቅድስት አርሴማ ሳትወለድ በስሟ የተሰየመውን ታቦት በግብፅ ያገኙና ያከበሩ ናቸው (ገድለ አርሴማ 7ኛ ተአምር)።🌼 በግብፅ ደብረ ምጥማቅ ማርያም በመጀመሪያ ሰርተው የቀደሱት አቡነ ሙሴ ናቸው። በተጨማሪ ብዙ የሕንጻ ቤተ ክርስቲያንና የዋሻ ቤተ ክርስቲያን አንጸዋል። እንደ ቅዱሳን ብዙ ድንቅ ተአምር አድርገዋል። ለምሳሌ አውሬ ገድሏቸው ተጠራቅሞ የነበረ አፅም ላይ ጸልየው አራት ሺህ የሞቱ ሰዎችን ከሞት አስነስዋል። 40 ዓመት በንግሥና ከቆዩ በኋላ ከብዙ ተከታዮቻቸው ጋር ወደ አስቄጥስ ገዳም ለምነና ስጓዙ በበረሃው ተርበው ለወደቁት ወደ እግዚአብሔር ሲጸልዩ መና ወርዶላቸው መግበዋል አስቄጥስ ገዳም ሲደርሶ አቡነ መቃርስ ነበሩ የተቀበሏቸው፡፡🌼 በአስቄጥስ በአቡነ እንጦንስ ስም የመጀመሪያውን ቤተ ክርስቲያን ሠርተው ከፈፀሙ በኋላ አቡነ እንጦንስንና አቡነ መቃርስ በምንኵስና ልብስ፣ በመላእክት አስኬማ፣ በቅንዓት፣ በቀሚስና በቆብዕ ላይ ለ40 ቀን ጸልየው ጥር 22 ቀንተክለ ማርያም ብለው ሰይመው አመነኰሷቸው። በዚያውም አቡነ መቃርስ ከበታቻቸው ሾሙ። በአስቄጥስ ብዙ ተከታዮቻቸውን አመንኵሰው ቀድሞ ወደ፡ሠሯቸው ቤተ መቅደሶች ይልኳቸው ነበር። የቀሩት ደግሞ በኋላ ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ አብረዋቸው መጥተዋል።🌼 የኢትዮጵያ የመጀመርያው ጳጳስ አቡነ ሰላማ በማረፋቸው ነገሥታት አብርሃ ወአጽብሃ ጳጳስ እንዲልኩላቸው ከእጅ መንሻ ጋር ወደ ግብፅ ላኩ። አቡነ አትናቴዎስ ፈቃደ እግዚአብሔር ጠይቀው አቡነ ሙሴ ከአስቄጥስ ገዳም ለኢትዮጵያውያን አባት እዲሆኑ አቡነ ሚናስ ብለው ሾሙ። ከሦስት ሺህ ልጆቻቸው ጋር ሆነው ብዙ ቅርስ ይዘው አባታችን ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ ሕዝቡ በደስታ ተቀበሏቸው። ብዙ መጽሐፍትን ከአረብኛ ወደ ግእዝ ቋንቋ ተርጉመው ጽፈዋል። ይጽፉበት የነበረው ብዕር አድሮ በማግስቱ ለምልሞ አብቦ ይገኛል። ቀለም ይበጠብጡበት የነበረው የቀንድ ዋንጫም ከመሬት ተጣብቆ ያገኙት ነበር። በእጃቸው ሲያላቅቁት ከመሬት ጠበል ይፈልቃል፣ በጠበሉም ህሙማንን ፈውሰውበታል።🌼 በኢትዮጵያ 5መቶ የዋሻ ቤተ ክስቲያን ያነጹ ሲሆን በአጠቃላይ በመላው ዓለም ከ10 ሺህ በላይ ቤተ ክርስቲያ ሰርተዋል፣ አንጸዋል (መለከት መጽሔት 2007 ዓ.ም)። በእንቁና በእብነ በረድ ከሠራቸው ቤተ ክርስቲያኖች መካከል በአራራት ደብር (ከምድር ጥፋት በኋላ የኖኅ መርከብ መጀመርያ ያረፈችበት) በጻድቁ ኖኅ ስም፣ አብርሃም ሥላሴን በድንኳኑ ባስተናገደበት ስፍራ በቅድስት ሥላሴ ስም፣ በሕንድ (በሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ መቃብር ቦታ) በቅዱስ ቶማስ ስም፣ በአርማንያና በፋርስ (በሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ስጋውን ባሳረፉበት ቦታ) በቅዱስ ጊዮርጊስ ስም።🌼 በኢትዮጵያ በአቡነ ሙሴ ከታነጹት ቤተ ክርስቲያ ውስጥ የተወሰኑት፦1.የድባ መቅደሰ ማርያም አቡነ ሙሴ አንድነት ገዳም (ባለ ሰባት መቅደስ ፎቅ)፣ የረፍታቸው ቦታ፣ በትረ ሙሴያቸውና የእጅ መስቀላቸው ያለበት (ሰሜን ወሎ ዳውንት)2.አእማድ ቅድስት ሥላሴ ገዳም (መቄት) እንደ አቡነ አሮን መንክራዊ ጣራው ክፍት ሆኖ ዝናብ የማይገባው፣🌼 በመጨረሻ ብፁዕ አቡነ ሙሴ በቤተ ሚናስ ቤተመቅደስ የድባ መቅደሰ ማርያም አቡነ ሙሴ ገዳም መሰከረም 4 በዕለተ እሁድ ዐረፋ። ወርሃዊ በዓላቸው ወር በገባ በ4 ነው። በተለይ ጋብቻን የሚቀድሱ፣ ክህነት የሚባርኩ፣ መናንያንን የሚያጸኑ አረጋዊን አባት ናቸው። ከአባታችን ከብፁዕ አቡነ ሙሴ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትንና በረከትን ያሳትፈን በጸሎታቸውም ይማረን!። ምንጭ፦ የድባ መቅደሰ ማርያም አቡነ ሙሴ አንድነት ያሳተመው መጽሔት ላይ የተወሰደ።
  • ኩራዝ

    14 Sept, 04:05

    https://youtube.com/shorts/S2YwcQJoaPM?si=WGJdzvBao5uD2r4v
    YouTube#ኢትዮጵያ_ኦርቶዶክስEnjoy the videos and music you love, upload original content, and share it all with friends, family, and the world on YouTube.
  • ኩራዝ

    14 Sept, 04:00edited

    የዕለቱ ስንቅ"የሆነ በጎ ነገር አድርጎ (ከሰው) ዋጋ የሚጠብቅ የራሱን ፈቃድ እንጂ እግዚአብሔርን አላገለገለም"አባ ማርቆስ ተሐራሚሰናይ ዕለተ ሰኑይኩራዝ የዕውቀት አድማስመስከረም 4/1/2019 ዓ/ም
  • ኩራዝ

    14 Sept, 03:55

    forwarded from @nolawii27

    ቆላስይስ 3 ²³ ለሰው ሳይሆን ለጌታ እንደምታደርጉ፥ የምታደርጉትን ሁሉ በትጋት አድርጉት፥ ²⁴ ከጌታ የርስትን ብድራት እንድትቀበሉ ታውቃላችሁና፤ የምታገለግሉት ጌታ ክርስቶስ ነውና። ²⁵ የሚበድልም የበደለውን በብድራት ይቀበላል፥ ለሰው ፊትም አድልዎ የለም።
  • ኩራዝ

    14 Sept, 03:43

    https://youtube.com/shorts/Qf8VtcAXw8c?si=mLDYWLQNYMghWDfa
    YouTubeእንኳን አደረሳችሁ #ኢትዮጵያ_ኦርቶዶክስEnjoy the videos and music you love, upload original content, and share it all with friends, family, and the world on YouTube.
  • ኩራዝ

    14 Sept, 02:50

    forwarded from @http_orthodox_news

    ❤️‍🩹 ለስልክ መጥሪያ መዝሙሮች የምትፈልጉ እንሆ ❤️‍🩹🥰 💠የንስሐ💠
  • ኩራዝ

    13 Sept, 20:26

    📜ይህቺን ዓመት ደግሞ ተወኝ!!!📜 ​ በወይኑ ቦታ ላይ፣ በምሕረት ተተክዬ፣ ዓመታት ነጎዱ ፍሬ ሳላሳይህ፣ በዓለም ተታልዬ። በስም ሕያው ሆኜ በግብሬ ግን፣ ደርቄ ሞቻለሁ፣ ይህቺን ዓመት ተወኝ! እያልኩ እለምናለሁ።ከከፍታው ወንበር እስከ ዝቅታው ደጅ፣ የወደቅኩኝ ልጅህ ነኝ፣ በሰው ፊት አበብኩኝ በውስጤ ግን፣ ባዶ ቅጠል ብቻ ያለኝ፣ የምሳርህ ስለት፣ ከመሬቱ ስሬን ቆርጦ ሳይጥለኝ፣ በድንግል ማርያም ብዬ ልማጸንህ፣እባክህ ይህቺን ዓመት ተወኝ።እንደ አዳም ተሸሸግኩ ከፊትህ ርቄ በበለስ ቅጠሎች፣ የኃጢአቴን ዕርቃን ልሸፍን ሞከርኩኝ በከንቱ ምስሎች፣ አንተ ግን ታውቃለህ የልቤን ምሥጢር ሁሉንም አይተኸኝ፣ የምሕረትህን በር ዛሬስ እንዳትዘጋ ይህቺን ዓመት ተወኝ።በመቅደስህ ቆሜ ቃልህን ሳስተምር በአበው አንደበት፣ በሕይወት አልኖርኩት ከበደኝ ተራራው የትሕትናው እውነት፣ ያስተማርኩት ሁሉ ሌላውን ሲፈውስ እኔ ግን ታመምኩኝ፣ መድኃኒዓለም አባቴ ሆይ እባክህ ይህቺን ዓመት ደግሞ ተወኝ።በቅዳሴው ድምፅ በሰዓታቱ ዜማ በቅኔው ማኅሌት፣ ካባውን ደርቤ በመቅደስህ ቆሜ ስናገር በድፍረት፣ አንተ ግን የውስጤን ድርቀት እያወክ ዐይተህ ዝም አልከኝ፣ ዛሬስ ደጅህ ቆሜ አስመሳይ ነው ብለህ መች ቆረጥከኝ? አሁንም እላለሁ ይህቺን ዓመት ደግሞ ታግሠህ ተወኝ።ከሊባኖስ ዝግባ ከዘንባባው ጽድ ከጻድቃን ተጋድሎ፣ የእኔ ሕይወት ባዶ ነው በእሾህና በአሜኬላ ከጽድቅ ጎድሎ። የድንግል ምልጃ በወርቅ ጽና ላይ ዕጣኑን ሲያጥንልኝ፣ ስለ እናትህ ጸሎት ብለህ አምላኬ ሆይ ይህቺን ዓመት ተወኝ።መጽሐፍ ቅዱሱ ስንክሳሩ የቅዱሳን ታሪክ ሲወሳ፣ የጻድቃን ተጋድሎ የወርቅ ጽና ሆኖ በሰማይ ሲበራ፣ እኔ ግን ከንቱ ነኝ የቃልህን ማዳበሪያ አፍስሰህብኝም፣ በኃጢአት በእሾህ አሜኬላ ታስሬ ፍሬ አላፈራሁም።አውቃለሁ አምላኬ ዕድሜዬ አብቅቷል ፍሬን ሳላሳይህ፣ በቃላት ታጀብኩኝ በምግባር ግን ባዶ ሆኜ ስጠብቅህ፣
  • ኩራዝ

    28 Jan, 16:38

    forwarded from @enzira_mezmur

    ​​ጥር ፳፩ የእመቤታችን በዓለ ዕረፍት (አስተርእዮ ማርያም)”አስተርእዮ ማርያም“አስተርእዮ ማለት መታየት፣ መገለጥ ማለት ነው። ቃሉ አስተርአየ ታየ፣ ተገለጠ ከሚለው የግዕዝ ግሥ የተገኘ ነው። ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በገባው ቃል ኪዳን መሠረት በሥጋ የተገለጠበት(የታየበት) ፣ አንድነት ሦስትነቱም የተገለጠበት ወቅት በመሆኑ ከልደት በዓል እስከ ጥር መጨረሻ በሙሉ ዘመነ አስተርእዮ በመባል ይታወቃል። የእመቤታችን በዓለ ዕረፍት በዘመነ አስተርእዮ ውስጥ ስለሚከበር “አስተርእዮ ማርያም” ተብሏል።ልቡናዋ በይኩነኒ የጸና ንጽሐ ሥጋ ፣ ንጽሐ ነፍስ፣ ንጽሐ ልቡና አስተባብራ የያዘች ወላዲተ አምላክ ምንም እንኳን የአምላክ እናት ብትሆንም ሞተ ሥጋ ለሁሉም ዕጣ ፈንታ በመሆኑ በቃል መነገሩ በልብ መታሰቡ ከፍ ከፍ ይበልና ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “ተንሥኢ ወንዒ” የነፍሴ ደስታ የኾንሽ ውድ እናቴ ሆይ ተነሥተሽ ወደ እኔ ነዪ (መኃ ፪፥፲) ብሏታል።ሞታ ለማርያም የዐጽብ ለኲሉቅዱስ ዳዊት “ነኪር ነገሩ በእንቲአኪ ሀገረ እግዚአብሔር “ መዝ.፹፮፥፫ እግዚአብሔር ማህጸንሽን ከተማ አድርጎ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን የኖረብሽ ሆይ ስለ አንቺ የተነገረው የተደረገው ነገር ዕጹብ ድንቅ ነው እንዳለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የአምላክ እናት ሆና ማረፏ ይደንቃል። ታላቁ የቤተክርስቲያናችን አባት ቅዱስ ያሬድ ሞቷ የሚያስደንቅ መሆኑን «ሞትሰ ለመዋቲ ይደሉ ሞታ ለማርያም የዐጽብ ለኲሉ፤ ሞት ለማናቸውም ሰው ሁሉ የተገባ ነው የማርያም ሞት ግን ሁሉን ያስደንቃል» በማለት ገልጾታል።በቀሲስ
    Image from a post by ኩራዝImage from a post by ኩራዝ
    57521Open in Telegram
  • ኩራዝ

    28 Jan, 16:22

    ማንም ሀዘንህን አይወስድም ስለዚህ🤨 ማንም ደስታህን እንዲወስድ አትፍቀድ
  • ኩራዝ

    28 Jan, 10:58

    #መጣላት አለና: ሚስጥር አትናገር። #መታረቅ አለና፡ ክፉም አትናገር። በዚህ አለም ኑሮ የሚሻለው ነገር ብዙ ማዳመጥ ነው!! ብዙ ከመናገር 🤫
    736102Open in Telegram
  • ኩራዝ

    28 Jan, 10:10

    አስተርዮ ማርያም➯በዘመነ አስተርዮ የጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መገለጥ የሆነበትና የአምላካችን አንድነትና ሦስትነት የተገለጠበት ብቻም ሳይሆን በጥር ፳፩ የከበረች እናቱ ቅድስት ድንግል ማርያም የዕረፍት ቀን በመሆኑ “አስተርዮ ማርያም” በማለት በዓልን አናደርጋለን፡፡➯የአምላክ እናት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዚህ ምድር ላይ ፷፬ ዓመታትን ከኖረች በኋላ መንፈስ ቅዱስ ባስገነዘባት መሠረት በክብር ዐርፋለች፡፡ የዚህን ዓለም መከራና ሥቃይ ለሰዎች ድኅነት የተቀበለችው ክብርት እናታችን በሥጋ ብትሞትም እንደ ልጇ ደግሞ በትንሣኤዋ ተነሥታለች፤ ይህም የሆነው በተቀደሰች ዕለት ነሐሴ ፲፮ ነው፡፡➯እመ ብርሃን ከእናትና ከአባቷ ጋር ሦስት ዓመት፣ በቤተ መቅደስ ፲፪ ዓመት፣ ከተወዳጁ ልጅዋ ጋር ፴፫ ዓመት ከሦስት ወር፣ ከጌታችን ዕርገት በኋላ ከወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ ጋር ፲፭ ዓመት፣ በድምሩ ፷፬ ዓመት በዚህ በኃላፊው ዓለም ኖራ ጥር ፳፩ ቀን በ፵፱ ዓመተ ምሕረት በክብር ዐርፋለች፡፡➯ክርስቲያኖች በሙሉ ይህንን በዓል ልናከብር ይገባልና ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ሥርዓትን ሠርታልናለች፡፡ “አስተርዮ ማርያም” በሕዝበ ክርስቲያን ዘንድ የሚከበር በዓል በመሆኑ በሀገራችን ኢትዮጵያ እና በመላው የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ማኅበረሰብ ዘንድ በድምቀት ይከበራል፡፡ በዓሉን የምናከብረውም የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ከዚህ ዓለም ድካም ማረፍ በማዘከር ብቻ ሳይሆን አማላጅነቷና ተረዳኢነቷን በማሰብና ተስፋ በማድረግ ነው፡፡➯ስለዚህም እመ ብዙኃን እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
  • ኩራዝ

    28 Jan, 09:38

    😇 ዛሬ የቅዱስ አባታችን አባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት 84ኛ ዓመት የልደት በዓላቸው ነው።ሰው በጠፋበት ሰዓት አጽናኝ አባት ሆነው የተገኙ ስጦታችን ነዎት!ቅዱስነቶ እድሜና ጤና ይስጥዎት 🙏መልካም ልደት!!
    Image from a post by ኩራዝImage from a post by ኩራዝ
    684154Open in Telegram
  • ኩራዝ

    28 Jan, 08:57edited

    ብዙ መከራ የተቀበለ ሰው ብዙ ትምህርት ይማራል። መጽሐፈ ሲራክ 31:11ብርና ወርቅ አገር ያጸናሉ ከሁለቱ ይልቅ በጎ ምክር ደስ ታሰኛለች። መጽሐፈ ሲራክ 40:25
  • ኩራዝ

    28 Jan, 08:54edited

    መሳ 16፥ 19 "በጉልበትዋም ላይ አስተኛችው ፤ አንድ ሰውም ጠርታ የራስ ጠጉሩን ሰባት ጉንጉን አስላጨችው..."​ፍትወት (Lust) የራሱ ድርሻ ቢኖረውም ፣ የሳምሶን ዋነኛ እና ጥልቅ ችግር የማይመጥኑትን እና ዋጋ የማይሰጡትን ሰዎች መምረጡና አብዝቶ እንዲቀርቡት መፍቀዱ ነበር። ለምሳሌ ያህል ፦👇📍​የቲምናዋ ሚስቱ እንቆቅልሹን ከነገራት በኋላ አታለለችው ፣ አሳልፋም ሰጠችው።📍​ደሊላ ሦስት ጊዜ አሳልፋ ሰጠችው ፤ እሱ ግን ወደ እርስዋ መመለሱን ቀጠለ።ወገኖቼ በዛ ​ወሳኝ ሰዓት እሷ ብቻዋን አልነበረችም ፀጉሩን እንዲቆርጥላት አንድ ሰው ጠራች። በተመረጡ ሰዎች ላይ የሚደረግ ሴራ ብዙ ጊዜ ለብቻ አይከናወንም። ብዙውን ጊዜ ለስልጣን ፣ ለሴራ እና ለሙስና በተንኮል አብረው የሚሰሩ ተባባሪዎች አሉ።የእኔ ተወዳጆች ​የሰዎችን ተፈጥሮ መረዳት ጠቢብን ፣ ሞኝን እና ክፉን ለመለየት ይረዳል። ቃላት የሰውን እውነተኛ ማንነት እና እሴት እምብዛም አይገልጡም ፤ ተግባር ግን ይናገራል።​ሳምሶን የማስጠንቀቂያ ምልክቶችን (Red flags) ችላ በማለቱ ፣ ተባብረው ሊያጠፉት የተዘጋጁ ጠላቶቹን ወደ ህይወቱ በጣም አስጠጋ።ወከዚህ ታሪክ በመማር ማን ወደ ህይወታችሁ እንደሚገባ በጥንቃቄ ምረጡ (Guard your access)። ክህደት ብዙውን ጊዜ የሚመጣው ከተባባሪዎች ጋር ነው።መጥራት እስኪችሉ ድረስ አታቅርባቸው።
    Image from a post by ኩራዝImage from a post by ኩራዝ
  • ኩራዝ

    28 Jan, 08:08

    Image from a post by ኩራዝImage from a post by ኩራዝ
  • ኩራዝ

    27 Jan, 17:37

    ለክብር አትጓጓ ለከንቱም ውዳሴ ፤ ‎በከንቱ ውዳሴ አይገኙም ሥላሴ ።ኩራዝ
    820143Open in Telegram
  • ኩራዝ

    27 Jan, 13:00

    ሰዎች ሳቅህን ያያሉ እግዚአብሔር ደግሞ በልብህ የያዝከውን ህመምህን ያያል🥺
  • ኩራዝ

    27 Jan, 12:04

    ማሸነፍ የምትችለዉ አእምሮህ ከስሜትህ ሲበልጥ ብቻ ነው
  • ኩራዝ

    27 Jan, 11:50

    የመማር ጥቅሙ ከመሳሳት መመለስ እንጂ መርካት አይደለምቅዱስ ጀሮም
    Image from a post by ኩራዝImage from a post by ኩራዝ