Latest posts

Law School Media
10 Sept, 15:32
ክርስቲያን ታደለን ጨምሮ ከ600 በላይ እስረኞች በይቅርታና ክሳቸው ተቋርጦ ከእስር ተለቀቁህገ መንግስታዊ ስርዓቱን በሀይል ለመናድ ሞክረዋል በሚል ታስረው የነበሩ ግለሰቦች እንዲፈቱ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ከመንግስት ጋር ላለፉት 5 ወራት ጥረት ሲያደርግ መቆየቱን አስታውቋል።በፍርድ ቤት ውሳኔ ታሰረው የነበሩት በይቅርታ፣ በክስ ሂደት ላይ የነበሩት ደግሞ ክሱ እንዲቋረጥ ተደርጎ ከ6 መቶ በላይ እስረኞች በዛሬው እለት እንዲፈቱ መደረጉን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽነር ብርሃኑ አዴሎ ገልጸዋል።ይህ ቁጥር ክልሎች በየራሳቸው ከሚፈቷቸው ውጭ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፣ የተፈቱት እስረኞች ከአማራና ከኦሮሚያ በፌደራል ደረጃ የታሰሩ እንደነበሩም ተነግሯል።በይቅርታ ከመፍታትና ክስ ከማቋረጥ በተጨማሪም በህግ የታገዱ መብቶቻቸው እንዲመለሱ መደረጉ ተገልጿል።በተመሳሳይ መዝገብ የሚገኙ 28 የሚሆኑ እስረኞች የይቅርታ ጥያቄ ባለማቅረባቸው ከእስር አለመፈታታቸውን ኢሰመኮ አስታውቋል።Via: TIKVAETHIOPIAJoin Us Your Trusted Legal Info Centre @Law_School_Media @Law_School_Media @Law_School_Media



Law School Media
10 Sept, 08:42
⚖️ ክቡራን የ Law School Media ቤተሰቦች፣ በመጀመሪያ ይህን ቡድን በፍቅር ተቀላቅላችሁ፣ በንቃት እየተሳተፋችሁ እና ከቀን ወደ ቀን እያሳደጋችሁት ስለሆነ ከልብ እናመሰግናለን። የእናንተ ድጋፍና ተሳትፎ ይህን Group በፍጥነት እያሳደገው ይገኛል። Law School Media ዓላማው ለህግ ተማሪዎች እና ለህግ ባለሙያዎች ትክክለኛ፣ ጠቃሚ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ማድረስ፣ የትምህርት ልምዶችን ማጋራት እና የሙያ እድሎችን ማቅረብ ነው።እንዲሁም የተሻሉ የህግ ትምህርት ማስታወሻዎች፣ የፍርድ ቤት ውሳኔዎች፣ የስኮላርሺፕና ኢንተርንሺፕ እድሎች፣ የስራ ማስታወቂያዎች እና ሌሎችም ጠቃሚ ይዘቶችን በተከታታይ እናጋራለን። 📢 አንድ ትንሽ ጥያቄ አለን። ይህ ቡድን ለብዙ የህግ ተማሪዎች እንዲደርስ እያንዳንዳችሁ የምታውቋቸውን የህግ ተማሪዎች፣ ምሩቃን እና ፍላጎት ያላቸውን ሰዎች Invite በማድረግ የቤተሰባችን አካል እንዲሆኑ እንጋብዛቸው። የእያንዳንዳችሁ ትንሽ ተሳትፎ ይህን group የበለጠ ጠንካራ ያደርገዋል። 🎉 በተጨማሪም... ዛሬ የጷግሜ ወር መጨረሻ ሲሆን፣ ነገ አዲሱን የኢትዮጵያ ዓመት እንቀበላለን። 🌼 እንኳን ለ2019 ዓ.ም. አዲስ ዓመት በሰላም፣ በጤና እና በደስታ አደረሳችሁ! 🌼 አዲሱ ዓመት ለሁላችሁም የትምህርት ስኬት፣ የሙያ እድገት፣ ጤና፣ ሰላም፣ ፍቅር እና ብዙ መልካም እድሎችን ይዞላችሁ ይምጣ። ህልማችሁ የሚሳካበት፣ ጥረታችሁ ፍሬ የሚያፈራበት እና የተሻለ ስኬት የምታስመዘግቡበት ዓመት ይሁንላችሁ። 🙏 እናመሰግናለን! ⚖️ Law School Media "Knowledge Shared,
Law School Media
10 Sept, 07:24edited
☎️ እስካሁን የጠሩ ዩኒቨርሲቲዎች ዝርዘር!🪛 Debra Birhan University -Health Students --መስከረም 5 -ነባር ተማሪዎች ---መስከረም 7-8🪛 Mekelle University ---መስከረም 9-10🪛 Odabultum University -- መስከረም 7-8🪛 Werabe University--- መስከረም 8-9🪛 Mettu University ---መስከረም 7-8🪛 Selale University ---መስከረም 7-8🪛 Mekdela Amba University --- መስከረም 7-8🪛 Bonga University -- መስከረም 7-8
Law School Media
9 Sept, 17:00
ማስታወቂያለዓቃቤ ሕግ ደረጃ ሦስት ተወዳዳሪዎች የፈተና ቀን ስለማሳወቅየኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር ሐምሌ 18 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣው ክፍት የሥራ ቅጥር ማስታወቂያ መሰረት በዐቃቤ ሕግ ደረጃ ሦስት (በዜሮ ዓመት ልምድ) የተመዘገባችሁ እና መስፈርቱን የምታሟሉ ተመዝጋቢዎች (ለፈተና የሚቀርቡ ተወዳዳሪዎች ዝርዝር ከሚፈተኑበት አዳራሽ አድራሻ ጋር ከዚህ ማስታወቂያ ስር ተያይዟል) የመጀመሪያ ዙር የጽሁፍ ፈተና መስከረም 09 ቀን 2019 ዓ.ም አዲስ አበባ መርካቶ አማኑኤል ሆስፒታል ፊት ለፊት በሚገኘው ኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር የአዲስ ከተማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከጠዋቱ 3፡00 ጀምሮ የሚሰጥ በመሆኑ ማንነታችሁን የሚገልፅ ዲጅታል መታወቂያ በመያዝ በሰአቱ በቦታው እንድትገኙ እያሳወቅን ወደ ፈተና አዳራሽ ምንም ዓይነት የኤሌክትሮኒክስ መገልገያ ፣ ማጣቀሻም ሆነ ሕግጋትን ይዞ መግባት በጥብቅ የተከለከለ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡Join Us Your Trusted Legal Info Centre @Law_School_Media @Law_School_Media @Law_School_Media




Law School Media
9 Sept, 15:16
#ArsiUniversityአርሲ ዩኒቨርሲቲ የነባር የቅድመ-ምረቃ እና የድኅረ-ምረቃ መደበኛ ተማሪዎች ምዝገባ መስከረም 09 እና 10/2019 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል።ትምህርት መስከረም 12/2019 ዓ.ም እንደሚጀመር ተገልጿል።በ2019 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር አርሲ ዩኒቨርሲቲ የምትመደቡ አዲስ ተማሪዎች (መደበኛ እና ሪሚዲያል) እንዲሁም በ2018 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያገኛችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ በቀጣይ ይገለጻል ተብሏል።በ2018 ዓ.ም በቦቆጂ ካምፓስ የነበራችሁ ተማሪዎች ወደ ዋናው ካምፓስ የምትሔዱ ሲሆን፣ ሌሎች ተማሪዎች በሙሉ ባለፈው ዓመት ስትማሩ ወደነበረበት ካምፓስ የምትገቡ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል። Join us Your Trusted Legal Info Center @Law_School_Media @Law_School_Media @Law_School_Media


Law School Media
9 Sept, 13:06
#WolkiteUniversityወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የሁሉም ነባር የቅድመ-ምረቃ እና የድኅረ-ምረቃ መደበኛ እና ተከታታይ መርሐግብር ተማሪዎች የመመዝገቢያ ቀናት መስከረም 04 እና 05/2019 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል፡፡በሀትምህርት ሚኒስቴር የምትመደቡ አዲስ ገቢ መደበኛ እንዲሁም በ2018 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርታችሁን በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የተከታተላችሁና የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች መግቢያ መስከረም 07 እና 08/2019 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡Join Us Your Trusted Legal Info Centre @Law_School_Media @Law_School_Media @Law_School_Media


Law School Media
9 Sept, 06:48
ለወሎ ዩኒቨርሲቲ 2ኛ ዓመት እና በላይ ነባር መደበኛ ተማሪዎች በሙሉየወሎ ዩኒቨርሲቲ 2ኛ ዓመት እና በላይ ነባር የቅድመ ምረቃ እና ድህረ ምረቃ መደበኛ ተማሪዎች የ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የመግቢያ ጊዜ መስከረም 11 እና 12/2019 ዓ.ም ሲሆን በተጠቀሱት ቀናት በግቢዎቻችሁ (በደሴ ግቢ፣ በኮምቦልቻ ግቢ፣ እና በልዕልት ህክምና ግቢ) ሪፖርት ማድረግ ያለባችሁ መሆኑን እንገልፃለን።ማሳሰቢያ፡-የምዝገባ ጊዜ ከመስከረም 11 እና 12፤ መስከረም 13/2019 ዓ.ም በቅጣት ምዝገባ ሲሆን ትምህርት መስከረም 13/2019 ዓ.ም ይጀመራል።በ2019 ዓ.ም አዲስ ለሚመደቡ የ1ኛ ዓመት ተማሪዎች፣ የሪሜዲያል ተማሪዎች እና በ2018 ዓ.ም የሪሜዲያል ትምህርት ተምራችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች ጥሪ ወደፊት በማስታወቂያ የምንገልፅ ይሆናል።ለሁሉም ተማሪዎች የመታወቂያ የሚሆን 3x4 የሆነ ሁለት ጉርድ ፎቶግራፍ መያዝ ይኖርባችኋል።ከተጠቀሱት ቀናት ቀድሞም ሆነ ዘግይቶ ለሚመጣ ተማሪ ዩኒቨርሲቲው የማያስተናግድ መሆኑን እንገልፃለን።Join Us Your Trusted Legal Info Centre @Law_School_Media @Law_School_Media @Law_School_Media


Law School Media
8 Sept, 16:30edited
#WerabeUniversity #ጥሪማስታወቂያወራቤ ዩኒቨርሲቲ የሁሉም ነባር የቅድመ እና ድኅረ-ምረቃ መደበኛ መርሐግብር ተማሪዎች የ2019 ትምህርት ዘመን ምዝገባ መስከረም 08 እና 09/2019 ዓ.ም የሚከናወን መሆኑን ገልጿል፡፡👉 በቅጣት ምዝገባ የሚደረገው እና ትምህርት የሚጀምርበት ቀን መስከረም 11/2019 ዓ.ም መሆኑ ተገልጿል።በ2019 ዓ.ም ከትምህርት ሚኒስቴር የምትመደቡ የአንደኛ ዓመት እና የሪሚዲያል ተማሪዎች እንዲሁም በ2018 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም በወራቤ ዩኒቨርሲቲ ያጠናቀቃችሁና የማለፊያ ነጥብ ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ቀናት ወደፊት የሚገለፅ መሆኑን ተቋሙ አሳውቋል።Join Us Your Trusted Legal Info Centre @Law_School_Media @Law_School_Media @Law_School_Media


Law School Media
8 Sept, 16:18edited
#OdaBultumUniversityኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ የነባር መደበኛ ተማሪዎች የ2019 ትምህርት ዘመን ምዝገባ የሚካሔደው መስከረም 07 እና 08/2019 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል፡፡ትምህርት መስከረም 11/2019 ዓ.ም ይጀመራል ተብሏል።በ2018 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርታችሁን በኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ ተከታትላችሁ ማለፍያ ነጥብ ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች፤ ለ2019 ዓ.ም አዲስ ገቢ (ፍሬሽማን) ተማሪዎች ምደባ በትምህርት ሚኒስቴር ይፋ ሲደረግ ወደፊት በሌላ ማስታወቂያ ጥሪ እንደሚደረግላችሁ ተገልጿል፡፡Join Us Your Trusted Legal Info Centre @Law_School_Media @Law_School_Media @Law_School_Media


Law School Media
8 Sept, 15:59
የተማሪዎች ጥሪ ማስታወቂያ💥 ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ ሁሉም ነባር ተማሪዎች በመስከረም 7 እና 8 ቀን 2019 ዓ.ም. ወደ ግቢ እንዲገቡ በይፋ አስታውቋል።ለነባር (2ኛ ዓመት እና ከዚያ በላይ) የሰላሌ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በሙሉ እንኳን ለ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን አደራሳችሁ እያልን ምዝገባ የሚካሄደው መስከረም 7-8/2019 ዓ.ም መሆኑን እናሳውቃለን፡፡መልካምና ሰላማዊ ጉዞ! ወደ ግቢያችሁ በደህና እንድትመለሱ እንመኛለን!ማሳሰቢያ👇 1. ማንኛውም ተማሪ “National ID” ይዞ መምጣት ያለበት መሆኑን፣፤ 2. ተማሪዎች በተወሰነው የጥሪ መርሃ ግብር መሠረት በወቅቱ እንዲገኙ እናሳውቅዎታለን። ከተጠቀሱት ቀናት በፊትም ሆነ በኋላ ወደ ግቢ መግባት አይፈቀድም። @Law_School_Media @Law_School_Media @Law_School_Media
Law School Media
8 Sept, 15:41



Law School Media
8 Sept, 13:18
ለጤናቸው አደገኛ ካልሆነ በስተቀር ባልና ሚስት ከጋብቻ የሚጠበቀውን መደበኛውን የሩካቤ ስጋ ግንኙነት መፈፀም አለባቸው። ይህንንም የሚቃረን ማንኛውንም አይነት ስምምነት ውጤት አይኖረውም።የኢፌድሪ የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አንቀፅ 53(2) እና (3)Join Us Your Trusted Legal Info Centre @Law_School_Media @Law_School_Media @Law_School_Media
Law School Media
8 Sept, 05:25edited
📣የምዝገባ ጥሪ ማስታወቂያ ‼️ 📢ለባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ነባር ቅድመ ምረቃ እና ድህረ ምረቃ መደበኛ ተማሪዎች በሙሉ 1) የቅድመ ምረቃ 3ኛ ዓመትና ከዚያ በላይ እንዲሁም የነባር የድህረ ምረቃ ተማሪዎች ፤ 2) የትምህርት ክፍል ምደባቸውን ያወቁ 2ኛ አመት ተማሪዎች(Anesthesia, Comprehensive Nursing, , Law, Midwifery, Pharmacy, Pre-medicine and Veterinary Medicine) የ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የመጀመሪያው ወሰነ ትምህርት ምዝገባ የሚካሄደው ከመስከረም 07-08/2019 ዓ.ም መሆኑን እየገለጽን ምዝገባ የሚካሄደው ፕሮግራሙ በሚገኝበት ካምፓሶች መሆኑን እንገልጻለን።⚠️ ማሳሰቢያ⚠️ ከተጠቀሰው የምዝገባ ጊዜ በፊትም ሆነ ዘግይቶ የሚመጣን ተማሪ የማንቀበል መሆኑን እናሳውቃለን፡፡የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራርና አልሙናይ ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬትJoin Us Your Trusted Legal Info Centre @Law_School_Media @Law_School_Media @Law_School_Media


Law School Media
7 Sept, 14:34edited
#MekelleUniversityመቐለ ዩኒቨርሲቲ የነባር የቅድመ-ምረቃ መደበኛ ተማሪዎች የ2019 ትምህርት ዘመን ሪፖርት ማድረጊያ ቀናት መስከረም 09 እና 10/2019 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል።በመሆኑም ነባር ተማሪዎች በተጠቀሱት ቀናት ሪፖርት እንዲያደርጉ ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል።Join Us Your Trusted Legal Info Centre @Law_School_Media @Law_School_Media @Law_School_Media


Law School Media
7 Sept, 10:11edited
ዩንቨርስቲዎች ከማንኛውም ወታደራዊ እና የትጥቅ እንቅስቃሴ ነፃ መሆን እንዳለባቸው በማስመልከት ከትምህርት ሚንስተር የተላለፈ ጥብቅ ማሳሰቢያ:Join Us Your Trusted Legal Info Centre @Law_School_Media @Law_School_Media @Law_School_Media


Law School Media
7 Sept, 09:05
ዳግም ዳኝነት!ዳግም ዳኝነት ማለት በፍትሐብሔር ክርክር የተሰጡ ፍርዶች በሥነ ሥርአት ሕጉ የተቀመጡ ሁኔታዎች ሲሟሉ ጉዳዩን መጀመሪያ ባየው ፍርድ ቤት ዳግም ሚታዩበት ሥነ-ሥርዓት ነው። • ዳግም ዳኝነት የሚታይባቸው ሁኔታዎች ዳግም ዳኝነትን የተመለከቱ ሥነ-ሥርዓቶች በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 6 ስር የተሸፈኑ ሲሆን ማንኛውም ሰው ይግባኝ ሊቀርብበት በሚችል ፍርድ ወይም ውሳኔ ወይም ትዕዛዝ ላይ ቅሬታውን አቅርቦ ከመሰማቱ በፊት ወይም ይግባኙን ለማቅረብ ያልተፈቀደበት ፍርድ ወይም ውሳኔ ወይም ትዕዛዝ ቢሰጥበት ቀጥሎ በተዘረዘሩት ምክንያቶች ብቻ ፍርዱን ለፈረደው ወይም ትዕዛዙን ወይም ውሳኔውን ለሰጠው ፍርድ ቤት የተወሰነውን የዳኝነት ክፍያ በመክፈል አቤቱታ ለማቅረብ ይቻላል። ምክንያቶቹ የሚከተሉት ናቸው፡- የመጨረሻ ፍርድ ወይም ውሳኔ ወይም ትዕዛዝ የተሰጠው በሐሰት ተዘጋጅቶ የቀረበውን ሰነድ ወይም ሐሰተኛ የምስክርነት ቃልን ወይም መደለያን ወይም ወንጀል ጠቀስ የሆነ ተግባርን መሠረት በማድረግ ሲሆንና አቤት ባዩም ፍርድ ከመሰጠቱ በፊት አስፈላጊውን ትጋት አድርጎ ለማወቅ ያለመቻሉን ለማስረዳት የቻለ እንደሆነ፣ ከላይ የተዘረዘሩት ተግባሮች መፈፀማቸው ቢገለፅ ኖሮ ለፍርዱ መለወጥ ወይም መሻሻል በቂ ምክንያት ሊሆኑ ይችሉ እንደ ነበረ ለማስረዳት የቻለ እንደሆነ ነው፡፡ ከላይ የተጠቀሱትን ምክንያቶች በመግለፅ በደል ደርሶብኛል ሲባል ዳኝነት እንዲታይ የሚቀርበው አቤቱታ ይግባኝ በሚቀርብበት አይነት እንደሚቀርብ የፍትሐብሔር ሥነ ሥርአት ሕግ ቁጥር 6(2) የሚደነግግ ሲሆን የይግባኝ ማመልከቻ የሚቀርበው
Law School Media
6 Sept, 17:07
🔴25 የሙስና ወንጀሎች🔴 (አዋጅ ቁጥር 881/2007 )1. በሥልጣን ያለአግባብ መገልገል (አንቀፅ 9) 2. ጉቦ መቀበል (አንቀፅ 10) 3. የማይገባ ጥቅም መቀበል (አንቀፅ 11) 4. አስታራቂ ሽማግሌዎችና ሌሎች ሰዎች የሚፈፅሙት ጉቦ የመቀበል ወንጀል (አንቀጽ 12) 5. የመንግስት ወይም የሕዝባዊ ድርጅት ስራን በማያመች አኳኋን መምራት (አንቀጽ 13) 6. አደራ በተሠጠው ዕቃ ያለአግባብ ማዘዝ (አንቀፅ 14) 7. በሥራ ተግባር የሚፈፀም የመውሰድና የመሰወር ወንጀል (አንቀፅ 15) 8. በሥልጣን ወይም በኃላፊነት መነገድ (አንቀፅ 16) 9. በህገወጥ መንገድ መሰብሳብ ወይም ማስረከብ (አንቀፅ 17) 10. ያለአግባብ ጉዳይን ማጓተት (አንቀፅ 18) 11. ዋጋ ያለውን ነገር ያለክፍያ ወይም ያለበቂ ክፍያ ማግኘት (አንቀፅ 19) 12. ያለአግባብ ፍቃድ መስጠት ወይም ማፅደቅ (አንቀፅ 20) 13. ምንጩ ያልታወቀ ንብረትና ገንዘብ (አንቀፅ 21) 14. የሥራ ሚስጥርን መግለፅ (አንቀፅ 22) 15. መንግሥታዊ ወይም የህዝባዊ ሰነዶችን አስመስሎ ማዘጋጀት፣ ወደ ሐሰት መለወጥ ወይም በሐሰተኛ ሰነድ መገልገል (አንቀፅ 23) 16. መንግስታዊ ወይም የህዝባዊ ድርጅት ስነዶችን ማጥፋት ወይም ጉዳት ማድረስ (አንቀ8 24) 17. ጉቦ ወይም ተገቢ ያልሆነ ጥቅም መስጠት (አንቀፅ 25)
Law School Media
5 Sept, 19:44
⚖️ የአዲሱ የወንጀል ሥነ-ሥርዓት እና ማስረጃ ሕግ መሠረታዊ መርሖች1️⃣ ሕጋዊነት እና የሕግ የበላይነት (አንቀጽ 4 እና 16) 📌የሕግ የበላይነት፦ ማንኛውም ሥልጣን ያለው አካል አሠራሩን በሕግ የበላይነት መርሕ ላይ ብቻ ይመሠርታል። 📌ሕገ-መንግሥታዊ መቃኘት፦ የሕጉ አፈጻጸም ከሕገ-መንግሥቱ፣ ኢትዮጵያ ካጸደቀቻቸው ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ስምምነቶች ጋር በተጣጣመ መልኩ ይተረጎማል። 📌የሥልጣን ወሰን፦ የወንጀል ምርመራ እና የክስ ሒደት በሕግ ሥልጣን በተሰጣቸው አካላት እና ፍርድ ቤቶች ብቻ ይከናወናል።2️⃣ እንደ ጥፋተኛ ያለመቆጠር መብት /Presumption of Innocence/ (አንቀጽ 5) 📌የነፃነት ግምት፦ ማንኛውም ሰው በሕግ በተቋቋመ ፍርድ ቤት ጥፋተኛነቱ በሕግ አሰራር መሠረት እስካልተረጋገጠ ድረስ ነፃ ሆኖ የመገመት መብት አለው። 📌የማስረዳት ኃላፊነት፦ የወንጀሉን ጥፋተኛነት የማስረዳት ሙሉ ሸክም የዐቃቤ ሕግ እንጂ የተከሳሽ አይደለም። 📌ክስን አለመክሰስ፦ ማንኛውም ሰው በራሱ ላይ እንዲመሰክር ወይም እውነቱን እንዲያምን አይገደድም። 3️⃣ በአንድ ወንጀል ድጋሚ አለመከሰስ እና አለመቀጣት /Double Jeopardy/ (አንቀጽ 6) 📌አንድ ሰው በሕግ መሠረት የመጨረሻ በሆነ ውሳኔ በተቀጣበት፣ በነፃ በተለቀቀበት ወይም በአማራጭ መፍትሔ (Alternative Dispute Resolution) ዕልባት ባገኘበት ጉዳይ ላይ እንደገና አይከሰስም፤ አይቀጣምም። 4️⃣ በሕግ ፊት እኩልነት እና የተከራካሪዎች እኩል መብት (አንቀጽ 7 እና 13) 📌ለልዩነት እኩል መሆን፦ ተጠርጣሪዎችና
Law School Media
5 Sept, 09:57edited
በይርጋ የማይታገዱ ጉዳዮች 1)እናት የምታቀርበዉ የመካድ ክስ ሰመቁ 167286 መጋቢት 27 ቀን 2011 ዓ.ም 2)የድምፅ ብክለት (nuisance civil code 1225) ቅፅ 11, 42824 3)መመሪያወች ከህግ ዉጭ መዉጣት አዋጅ ቁጥር 1183/2020 አንቀፅ 53 እና ተከታዮቹ 4)የመፋለም መብት(petitory action) ቅፅ 10,43600 & HOF 67/2011 5) በህጉ በተቀመጠዉ ጊዜ ዉርሱን ያጣራ ወራሽ የዉርስ ሀብት ክፍፍል ክስ ቅፅ 10,38533 6)በአደራ የተሠጠን ዕቃ በዉሉ ላይ ገደብ ከሌለዉ ከአደራ ተቀባዩ ለማስመለስ(Contract of bailment) ቅፅ 10,48048 7)ቀጣይነት ያለዉ የዉል መጣስ(continous breach of contract) ቅፅ 6,28686 8) ህገወጥ ዉል(unlawful contract) ቅፅ 12,43226 9)የዉርስ ሀብቱን ስመሀብት በጋራ ያስመዘገበ ወራሽ ሠመቁ 151868 ያልታተመ 10)የወራሽነት የምስክር ወረቀት ይሰጠኝ አቤቱታ ሠመቁ 236246 ያልታተመ 11)የዉርስ ሀብትን በጋራ ይዞ እየተጠቀመ ባለ ሠዉ ላይ የሚቀርብ ክስ 216383 ያልታተመ 12)ሟች በህይወት እያለ ንብረቱን በያዘዉ ሰዉ ላይ ማች ከሞተ በኋላ በወራሾች የሚቀርብ ክስ 213601 ያልታተመ 13)በወለድ አግድ (antichresis) የማይንቀሳቀሰዉን ንብረት በመያዣ የሠጠ ሰዉ እዳዉን በማንኛዉም ጊዜ ከፍሎ ንብረቱን ማስመለስ ይችላል ቅፅ 13 72463 14)የመያዣ ዉል(mortgage) ቀሪ የሚሆን(character of lapse)እንጅ የይርጋ ጉዳይ(period of limitation) አያስነሣም
Law School Media
5 Sept, 09:04edited
#NGATResultነሐሴ 20 እና 21/2018 ዓ.ም የተሰጠው የ2018 ዓ.ም የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ውጤት ተለቋል።ውጤትዎን ለማየት 👇 https://result.ethernet.edu.etሊንኩን ከተጫኑ በኋላ 'NGAT Results' ላይ 'View Results' የሚለውን በመጫንና Username በማስገባት ውጤትዎን ይመልከቱ።#Share To Your FriendsJoin Us Your Trusted Legal Info Centre @Law_School_Media @Law_School_Media @Law_School_Media


Related Channels
Other channels in the same section of the catalogue.
