Latest posts

Ministry of Health ET
25 Sept, 05:41
ከክትባት በኋላ በህጻናት ላይ የሚከሰቱ እንደ ትኩሳት፣ መቅላት ወይም እብጠት ያሉ ቀላል ምልክቶች ክትባቱ እየሰራ መሆኑን የሚያሳዩ ናቸው።#ChildImmunization #VaccinesSavesLivesWebsite: moh.gov.et Facebook: Ministry of Health,Ethiopia Twitter: x.com/fmohealth YouTube: youtube.com/@FMoHealthEthiopia Tiktok: tiktok.com/@mohethiopia Telegram: t.me/M0H_EThiopia Linkedin: lnkd.in/ewFJ6V


Ministry of Health ET
23 Sept, 05:14
በወሊድ ምክንያት የሚከሰትን የደም መፍሰስ እንዳይከስት መከላከል የሚያስችል እና የእናቶችና ህጻናት ጤናን የሚያሻሽሉ መመሪያዎች የማስተዋወቂያ መድረክ ተካሄደ ___________በማስተዋወቂያው መድረኩ ላይ ተገኝተው መልዕክታቸውን ያስተላለፉት የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጀ ድጉማ በመልዕክታቸው መመሪያዎቹ በወሊድ ምክንያት የሚከሰትን የደም መፍሰስ እንዳይከሰት መከላከል የሚያስችል እና የእናቶችና ህጻናት ጤናን የሚያሻሽሉ መሆናቸውን ገልጸዋል።ሀገራችን ኢትዮጵያ በ2030 ለማሳካት ለያዘችው የእናቶችና ህጻናት ሞት ቅነሳ ጉልህ ሚና የሚጫወቱ ሲሆን ለተፈጻሚነታቸው የሁሉም ባለድርሻ አካላት እና አጋር አካላት ርብርብና ትብብር ይጠይቃል ብለዋል...MoreWebsite: moh.gov.et Facebook: Ministry of Health,Ethiopia Twitter: x.com/fmohealth YouTube: youtube.com/@FMoHealthEthiopia Tiktok: tiktok.com/@mohethiopia Telegram: t.me/M0H_EThiopia Linkedin: lnkd.in/ewFJ6V




Ministry of Health ET
23 Sept, 05:11
ኢትዮጵያ የቲቢና ሌሎች የሰንባ በሽታዎች ስርጭትን ለመግታትና ዓለማቀፍ ግቦችን ለማሳካት በቁርጠኝት እየሰራች ትገኛለች ________የቲቢ፣ ስጋ ደዌ እና ሌሎች የሰንባ በሽታዎችን አስመልክቶ ጤና ሚኒስቴር የሚመለከታቸውን አካላት በማቀናጀት የምርመራና የህክምና ተቋማትን የማስፋፋት፣ አዳዲስ መመርመሪያ መሳሪያዎችንና መድኃኒቶችን የማስገባት ስራዎች እያከናወነ እንደሚገኝ በጤና ሚኒስቴር የበሽታዎች መከላከል እና መቆጣጠር መሪ ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ህይወት ሰለሞን ገልጸዋል።በቲቢ፣ ስጋ ደዌ እና ሌሎች የሰንባ በሽታዎችን ላይ ትርጉም ያለው ለውጥ ለማምጣት የማህበረሰብ አቀፍ መከላከል ስራዎችን ማጠናከር፣ የህክምና ጥራት ማረጋገጥ ስራዎች፣ የአለም ጤና ድርጅት ምክረ ሃሳቦችን መተግበር እና የመረጃ ጥራትን ከመጠበቅ አንፃር በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ ዶ/ር ህይወት አክለው ገልጸዋል...MoreWebsite: moh.gov.et Facebook: Ministry of Health,Ethiopia Twitter: x.com/fmohealth YouTube: youtube.com/@FMoHealthEthiopia Tiktok: tiktok.com/@mohethiopia Telegram: t.me/M0H_EThiopia Linkedin: lnkd.in/ewFJ6V




Ministry of Health ET
19 Sept, 18:34
28th Annual Health Sector Review Meeting (ARM)CALL FOR EXPRESSION OF INTEREST (EOI)The Federal Ministry of Health (MOH) invites health-sector stakeholders to express their interest in exhibiting at the 28th Annual Health Sector Review Meeting (ARM), to be held in Hossana from October 21–23, 2026.Theme: “Transformative Reform for a Sovereign and Resilient Health System”The exhibition will provide a platform to showcase achievements, innovations, evidence, testimonies, lessons learned, ongoing initiatives, and transformative reforms contributing to the strengthening of Ethiopia’s health system...MoreWebsite: moh.gov.et Facebook: Ministry of Health,Ethiopia Twitter: x.com/fmohealth YouTube: youtube.com/@FMoHealthEthiopia Tiktok: tiktok.com/@mohethiopia Telegram: t.me/M0H_EThiopia Linkedin: lnkd.in/ewFJ6V


Ministry of Health ET
18 Sept, 19:15
"ዲጂታል ሳይኪያትሪ በአፍሪካ፡ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስን (AI) ለተደራሽ እና ጥራት ያለው የአእምሮ ጤና ክብካቤ!" በሚል መሪ ሃሳብ የኢትዮጵያ ሳይኪያትሪስትስ ማህበር እና የአፍሪካ ሳይኪያትሪስትስ ማህበር የጋራ ጉባኤ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ ________የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ በጉባኤው የመክፈቻ ንግግራቸው AI እና ዲጂታል ሳይኪያትሪ ታካሚዎች ዘንድ ለመድረስና ለአእምሮ ጤና ህክምና ያለውን ከፍተኛ ፍላጎት ለማሟላት ቁልፍ ናቸው ብለዋል።በሳይኪያትሪ ዘርፍ ቴክኖሎጂን በሉአላዊነት ስሜት መጠቀም አስፈላጊነትን አጽንኦት የሰጡት ዶ/ር መቅደስ፤ ከሁኔታዎች ጋር እንድንላመድ የሚያስችሉንን ቴክኖሎጂዎች መተግበር ያስፈልጋል ብለዋል።በአፍሪካ የጤና እንክብካቤን ለማሻሻል ፈጠራ የታከለባቸውን ቴክኖሎጂዎች የምንጠቀምበት ጊዜ አሁን መሆኑንም ተናግረዋል...MoreWebsite: moh.gov.et Facebook: Ministry of Health,Ethiopia Twitter: x.com/fmohealth YouTube: youtube.com/@FMoHealthEthiopia Tiktok: tiktok.com/@mohethiopia Telegram: t.me/M0H_EThiopia Linkedin: lnkd.in/ewFJ6V




Ministry of Health ET
18 Sept, 14:43
የጉበት በሸታን ለመከላከል መንግስት ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን እየሰራበት ይገኛል _________ዘጠነኛው የአፍሪካ የጉበት በሽታዎች ኮንፈረንስ/COLDA 2026/ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል።ጤና ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ የጨጓራና የአንጀት ህክምና ማህበር እና ከጉበት በሽታዎች ማህበር ጋር በመተባበር ባዘጋጀው በዚህ አህጉራዊ ጉባኤ ላይ ንግግር ያደረጉት የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ የጉበት በሸታን ለመከላከል የኢትዮጵያ መንግስት በቁርጠኝነት እየሰራበት እንደሆነ፥ መድኃኒቱ ከመንግስት መደበኛ በጀት ተገዝቶ በነፃ ለታካሚዎች እየተሰጠ እንደሆነ እና ህፃናት እንደተወለዱ የሄፓታይቲስ ቢ ክትባት በማስጀመር ከ90 በመቶ በላይ ህፃናትን ተደራሽ ማድረግ እንደተቻለ ገልጸዋል...MoreWebsite: moh.gov.et Facebook: Ministry of Health,Ethiopia Twitter: x.com/fmohealth YouTube: youtube.com/@FMoHealthEthiopia Tiktok: tiktok.com/@mohethiopia Telegram: t.me/M0H_EThiopia Linkedin: lnkd.in/ewFJ6V




Ministry of Health ET
18 Sept, 05:44
የጤና ሚኒስቴር እና የልማት አጋሮች የጋራ የምክክር መድረክ ተካሄደ __________የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ በመድረኩ የመክፈቻ ንግግራቸው ባለፈው ዓመት በጤናው ዘርፍ ያጋጠሙ ተግዳሮቶች እና የተመዘገቡ ስኬቶችን አንስተዋል።በቀጣይም ዘላቂ የጤና ሥርዓት ለመገንባትና የጤና መዋቅርን ለማጠናከር በቅንጅትና በትብብር መስራት አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል...MoreWebsite: moh.gov.et Facebook: Ministry of Health,Ethiopia Twitter: x.com/fmohealth YouTube: youtube.com/@FMoHealthEthiopia Tiktok: tiktok.com/@mohethiopia Telegram: t.me/M0H_EThiopia Linkedin: lnkd.in/ewFJ6V




Ministry of Health ET
17 Sept, 17:35
ዓለም ዓቀፍ የህሙማን ደኅንነት በቀን! World Patient Safety Day!#PatientSafetyWebsite: moh.gov.et Facebook: Ministry of Health,Ethiopia Twitter: x.com/fmohealth YouTube: youtube.com/@FMoHealthEthiopia Tiktok: tiktok.com/@mohethiopia Telegram: t.me/M0H_EThiopia Linkedin: lnkd.in/ewFJ6V


Ministry of Health ET
16 Sept, 17:26
የተግባር ሙያ ፈቃድ ፈተና ለወሰዳችሁ የአንስቴዥያ ተመዛኞች በሙሉ ___________በጳጉሜ 3/2018 ዓ.ም የተሰጠውን የተግባር ሙያ ፈቃድ ፈተና የወሰዳችሁ የአንስቴዥያ ተመዛኞች ከመስከረም 6/2019 ዓ.ም ጀምሮ https://hple.moh.gov.et ላይ በመግባት የብሄራዊ መለያ ቁጥር(FAN) እና Password በማስገባት የፈተና ውጤታችሁን መመልከት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን በውጤታችሁ ላይ ቅሬታ ያላችሁ ተመዛኞች ውጤት ከተገለጸበት ዕለት አንስቶ ባሉት 5(አምስት) ተከታታይ የስራ ቀናት በስልክ ቁጥር 952 በመደወል ጥያቄዎቻችሁን ማቅረብ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡ፈተናውን ያለፋችሁ ተመዛኞች ከሃሙስ መስከረም 7/2019 ዓ.ም ጀምሮ ስም ዝርዝራችሁ ወደ ክልል የሚላክ ስለሆነ የሙያ ፈቃዳችሁን 12ተኛ ክፍል በጨረሳችሁበት ክልል ማውጣት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡Website: moh.gov.et Facebook: Ministry of Health,Ethiopia Twitter: x.com/fmohealth YouTube: youtube.com/@FMoHealthEthiopia Tiktok: tiktok.com/@mohethiopia Telegram: t.me/M0H_EThiopia Linkedin: lnkd.in/ewFJ6V


Ministry of Health ET
16 Sept, 11:41
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ድንገተኛ የማህበረሰብ ጤና ሕክምና ቡድን (EMT) ከዓለም ጤና ድርጅት እውቅና አገኘ __________የማህበረሰብ ድንገተኛ የጤና ስጋት ሲከሰት ዜጎቻችንን ቀድሞ ለመጠበቅና ሲከሰትም በበቂ ሁኔታ ለመቆጣጠር የሚያስችል አቅም እየተፈጠረ መምጣቱን እና ውጤታማ መሆኑን የሚያረጋግጥ እውቅና ነው፤ ለኢትዮዽያ የህክምና ዘርፍ ልዩ የኩራትና የደስታ ቀንም መሆኑን የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ገልጸዋል።የተገኘው ስኬት በጤና ሚኒስቴር፣ በኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት (EPHI) እና በባለድርሻና አጋር አካላት የጋራ ቅንጅትና ትብብር አማካኝነት ለዓመታት በተከናወነ አመራርነት፣ ኢንቨስትመንት፣ ሥልጠናና እና ድጋፍ የተገኘ በመሆኑ እንደ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ሁሉንም አካላት ላበረከቱት አስተዋጽኦ ሚኒስትሯ አመስግነዋል፡፡ በቀጣይም የተገኘውን ውጤት በማላቅ እና ትጋታችንን በመጨመር ለሌሎች የጤና ግቦች መሳካት ትብብራችን ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል...MoreWebsite: moh.gov.et Facebook: Ministry of Health,Ethiopia Twitter: x.com/fmohealth YouTube: youtube.com/@FMoHealthEthiopia Tiktok: tiktok.com/@mohethiopia Telegram: t.me/M0H_EThiopia Linkedin: lnkd.in/ewFJ6V




Ministry of Health ET
14 Sept, 12:44
ከመጠን በላይ ስኳር፣ ጨው እና ስብ የያዙ ምግቦችን በመቀነስ ፍራፍሬ፣ አትክልት፣ ጥራጥሬ እና በፕሮቲን የበለፀጉ ምግቦችን እንዲሁም በቂ ውሃ በየቀኑ በመውሰድ ጤናማ አመጋገብን ይከተሉ!#healthylifestyle #eathealthy #unhealthydietWebsite: moh.gov.et Facebook: Ministry of Health,Ethiopia Twitter: x.com/fmohealth YouTube: youtube.com/@FMoHealthEthiopia Tiktok: tiktok.com/@mohethiopia Telegram: t.me/M0H_EThiopia Linkedin: lnkd.in/ewFJ6V


Ministry of Health ET
10 Sept, 12:13
መልካም አዲስ አመት #HappyNewYear Website: moh.gov.et Facebook: Ministry of Health,Ethiopia Twitter: x.com/fmohealth YouTube: youtube.com/@FMoHealthEthiopia Tiktok: tiktok.com/@mohethiopia Telegram: t.me/M0H_EThiopia Linkedin: lnkd.in/ewFJ6V


Ministry of Health ET
10 Sept, 08:01
ጳጉሜን 5 የነገ ቀንWebsite: moh.gov.et Facebook: Ministry of Health,Ethiopia Twitter: x.com/fmohealth YouTube: youtube.com/@FMoHealthEthiopia Tiktok: tiktok.com/@mohethiopia Telegram: t.me/M0H_EThiopia Linkedin: lnkd.in/ewFJ6V


Ministry of Health ET
9 Sept, 17:58
በአዲስ አበባ መስተዳደርና በ አፋር ክልሎች የህብር ቀንን ምክንያት በማድረግ የድጋፍ እና የጤና ተቐማት ጉብኝት መርሐ ግብር ተካሄደ _________የበአዲስ አበባ መስተዳደር ጤና ቢሮ ሃላፊዎች እና የማኔጅመንት አባላት በራስ ደስታ ዳምጠዉ መታሰቢያ ሆስፒታል በመገኘት የወለዱ እናቶችን በመጎብኘት እና እንኳን አደረሳችሁ በማለት ስጦታ ማበርከት ችለዋል።እንዲሁም በአፋር ክልል፥ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በዱብቲ ሆስፒታል በመገኘት ተቋሙ ለማኅበረሰቡ የሚሰጠውን የሕክምና አገልግሎት የጎበኙ ሲሆን፣ በሕክምና ላይ ለሚገኙ ከ 300 በላይ ታካሚዎችም የማእድ ማጋራት መርሃ ግብር አድርገዋል።Website: moh.gov.et Facebook: Ministry of Health,Ethiopia Twitter: x.com/fmohealth YouTube: youtube.com/@FMoHealthEthiopia Tiktok: tiktok.com/@mohethiopia Telegram: t.me/M0H_EThiopia Linkedin: lnkd.in/ewFJ6V




Ministry of Health ET
9 Sept, 17:57
በደቡብ ኢትዮጵያ፣ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ እና ሲዳማ ክልሎች ጷግሜን 4 የህብር ቀን በተለያዩ ዝግጅቶች ተከብሯል _______ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጷግሜን 4 የህብር ቀን በማስመልከት የስራ ሃላፊዎች በጂንካ ጠቅላላ ሆስፒታል በህክምና ላይ ያሉ ህሙማንን በመጎብኘት ማዕድ አጋርተዋል።በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ጤና ዘርፍ አመራሮች በወራቤ ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ተኝቶ ታካሚ ህሙማ በመዘዋወር ጠይቀዋል፡፡በጉብኝቱ የተለያዩ የህክምና ግብዓቶች ድጋፍ የተደረገ ሲሆን፣ በበጎ ፈቃድ የደም ልገሳ መርሃ ግብርም ተካሂዷል።በተጨማሪም በሲዳማ ክልል የዘመን መለወጫ በዓልን በማድረግ ምክንያት የክልሉ ጤና ቢሮ ሃላፊና አመራሮች በአዳሬ አጠቃላይ ሆስፒታል እና በአላሙራ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን የማእድ ማጋራት መርሀ ግብርም ተካሂዷል።Website: moh.gov.et Facebook: Ministry of Health,Ethiopia Twitter: x.com/fmohealth YouTube: youtube.com/@FMoHealthEthiopia Tiktok: tiktok.com/@mohethiopia Telegram: t.me/M0H_EThiopia Linkedin: lnkd.in/ewFJ6V




Ministry of Health ET
9 Sept, 17:56
የሐረሪ ክልል እና የድሬደዋ አስተዳደር ጳጉሜ 4፣ የህብር ቀንን ምክንያት በማድረግ የድጋፍ እና የጤና ተቐማት ጉብኝት መርሐ ግብር አካሄዱ _____________የጳጉሜ 4፣ የህብር ቀንን ምክንያት በማድረግ በድሬደዋ አስተዳደር በሳቢያን ጠቅላላ ሆስፒታል ከአንገት በላይ የቀዶ ህክምና ወረፋ የሚጠብቁ ታካሚዎችን ችግር ለመፍታት የተዘጋጀ የበጎ ፍቃድ ህክምና ማስጀመሪያ መርሃ-ግብር ተካሂዷል።በመርሃ-ግብሩ ላይ ከፍተኛ አመራሮች የተገኙ ሲሆን የቀዶ ህክምና አገልግሎት ያገኙ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።እንዲሁም በሐረሪ ክልል በሕይወት ፋና ስፔሻላይዝድ ሁሉን አቀፍ ሆስፒታል ጉብኝት የተካሄደ ሲሆን ለሕሙማን የምግብ እና የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁስ ድጋፍ ተደርጓል። በተጨማሪ የአብረሃ ባሕታ ሰው ሰራሽ አካል ድጋፍ እና ፌስቱላ ማዕከል ተጎብኝቷል።Website: moh.gov.et Facebook: Ministry of Health,Ethiopia Twitter: x.com/fmohealth YouTube: youtube.com/@FMoHealthEthiopia Tiktok: tiktok.com/@mohethiopia Telegram: t.me/M0H_EThiopia Linkedin: lnkd.in/ewFJ6V




Ministry of Health ET
9 Sept, 13:37
የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታልን በመጎብኘት ባለሙያዎችን አበረታቱ ——— ጳጉሜ 4 የኅብር ቀንን አስመልክቶ በተካሄደ የሆስፒታል ጉብኝት የተሳተፉት የጤና ሚኒስቴር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ፣ ሚኒስትር ዴአታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ እና ሌሎች የስራ ኃላፊዎች በዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል እየተሰጠ የሚገኘውን አገልግሎት ጎብኝተዋል።በሆስፒታሉ የሕክምና አገልግሎት በማግኘት ላይ የሚገኙ ታካሚዎችን የጎበኙት የስራ ኃላፊዎች፤ በሆስፒታሉ ለወለዱ እናቶች ስጦታዎችን አበርክተዋል።ቀኑ ኅብረ ብሔራዊነታችንን የምናስብበት ዕለት ነው ያሉት ዶ/ር መቅደስ፤ ዕለቱን በዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል በማሳለፋቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል።ኅብረተሰቡን በትጋት እያገለገሉ የሚገኙ የሆስፒታሉ ሠራተኞችን ያመሰገኑት ሚኒስትሯ፤ የመልካም አዲስ ዓመት መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።በመድረኩ የተሻለ ውጤት ላስመዘገቡ የሆስፒታሉ ባለሙያዎች ማበረታቻ ተሰጥቷል።Website: moh.gov.et Facebook: Ministry of Health,Ethiopia Twitter: x.com/fmohealth YouTube: youtube.com/@FMoHealthEthiopia Tiktok: tiktok.com/@mohethiopia Telegram: t.me/M0H_EThiopia Linkedin: lnkd.in/ewFJ6V




Ministry of Health ET
9 Sept, 13:35
ጳጉሜ 4 የኅብር ቀንን አስመልክቶ ሃገር አቀፍ ነፃ ሕክምና እና የምርመራ አገልግሎት መርሐ ግብር በመካሄድ ላይ ይገኛል ________ጳጉሜ 4 የህብር ቀንን አስመልክቶ በመስቀል አደባባይ በተዘጋጀ መርሃግብር የመንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና፣ ሰራተኞች እና የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በተሳተፉበት የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ተካሂዷል።በመርሃግብሩ ንግግር ያደረጉት የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ጳጉሜ 4 የኅብር ቀንን በጋራ በተለያዩ ፕሮግራሞች ስናከብር ህብረብሄራዊ አንድነታችንን በማስጠበቅ ኢትዮጵያን ወደ ከፍታ ለማሻጋገር ሁላችንም በጋራ ልንቆም ይገባል ብለዋል። መርሃግብሩ በመንግስት ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት አስተባባሪነት እና በጤና ሚኒስቴር አዘጋጅነት የተካሄደ ሲሆን፤ ስምንት የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች (ሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ፣ ሰላም፣ ባህልና ስፖርት፣ ትምህርት፣ ውጭ ጉዳይ እና ፍትሕ ሚኒስቴር ናቸው) በመርሀግብሩ መሳተፋቸውን ዶ/ር መቅደስ ገልጸዋል...MoreWebsite: moh.gov.et Facebook: Ministry of Health,Ethiopia Twitter: x.com/fmohealth YouTube: youtube.com/@FMoHealthEthiopia Tiktok: tiktok.com/@mohethiopia Telegram: t.me/M0H_EThiopia Linkedin: lnkd.in/ewFJ6V



Related Channels
Other channels in the same section of the catalogue.
