Latest posts

ማን ዩናይትድ ኢትዮ ፋንስ
7 Oct, 17:04
ለጆሽ 35 ሚሊዮን ?ክለባችን ማንችስተር ዩናይትድ ኔዘርላንዳዊውን አጥቂ ጆሹዋ ዚርክዜን በጥር የዝውውር መስኮት ለመሸጥ 35 ሚሊዮን ዩሮ ገደማ እንደሚፈልግ ተገልጿል ።[ ስፖርት ዊትነስ ]@man_united_ethio_fan @man_united_ethio_fan
ማን ዩናይትድ ኢትዮ ፋንስ
7 Oct, 16:43edited
"በካሪንግተን አጣብቂኝ ውስጥ የሚገኘው ማንችስተር ዩናይትድ !!ከቶተንሃም ጋር ለሚያደርገው ወሳኝ ጨዋታ በጉዳት አበሳውን እያየ ነው" !!ማንችስተር ዩናይትድ ቅዳሜ ከቶተንሃም ሆትስፐር ጋር ከሚያደርገው ትልቅ ጨዋታ በፊት በበርካታ ቁልፍ ተጫዋቾች ጉዳት ስጋት ውስጥ ወድቋል ።ማርከስ ራሽፎርድ እና ኮቢ ማይኑ ሁለቱም ከእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ስብስብ ውጭ መሆናቸው ይታወሳል ።ቤንጃሚን ሼሽኮ ተደጋጋሚ የእግር ሺን ጉዳት ስጋት ምክንያት ከስሎቬኒያ ስብስብ መውጣቱ ይታወሳል ።አማድ ዲያሎ ቁርጭምጭሚት ላይ በደረሰበት ጉዳት ምክንያት አሁንም ከክለቡ ልምምድ ፎቶዎች ውጪ ሆኗል ።ዶርጉ እና ማዝራዊ ሁለቱም ከዓለም አቀፍ ግዴታቸው ቀደም ብለው መመለሳቸው ይታወሳል ።ማቲያስ ዲ ሊክት በዝግ ስታዲየም በተደረገ የወዳጅነት ጨዋታ ቢሳተፍም ለቅዳሜ የመድረሱ ነገር እርግጥ አይደለም።ውድድሩን ቀዝቃዛ ጅምር ካደረገ በኋላ አሰልጣኝ ማይክል ካሪክ ከባድ የጨዋታ መርሃ ግብር ከመጀመሩ በፊት አማራጮችን አጥብቆ እንደሚፈልግ ተዘግቧል ።መረጃው የሳይመን ስቶን ፣ ቢቢሲ ነው !!@man_united_ethio_fan @man_united_ethio_fan
ማን ዩናይትድ ኢትዮ ፋንስ
7 Oct, 16:17
የካርሎስ ባሌባ አስደናቂ ተጽዕኖ በክለቡ ውስጥ !!የክረምቱ ፈራሚ ካርሎስ ባሌባ በክለቡ ውስጥ በጣም ጥሩ ስሜት መፍጠሩ ተገልጿል። እሱ በጣም በጥሩ ሁኔታ መሰልጠን ብቻ ሳይሆን ተጫዋቾቹም በጣም በፍጥነት ተቀብለውታል ።ሰራተኞቹ የእሱን ስብዕና ይወዱታል። በተጨማሪም በየቀኑ አዎንታዊ ሃይልን ያመጣል። በሁሉም ግምገማዎች መሰረት ቀድሞውኑ በቡድኑ ውስጥ ካሉ በጣም አስቂኝ ሰዎች አንዱ መሆኑም ተገልጿል ።[ Sully ]@man_united_ethio_fan @man_united_ethio_fan
ማን ዩናይትድ ኢትዮ ፋንስ
7 Oct, 15:54
“ልምምድ ላይ መጥፎ ነበር።”ዌይን ሩኒ ስለ ካርሎስ ቴቬዝ፦“ቴቬዝ ልምምድ ላይ በጣም መጥፎ ነበር፤ ጨዋታ ላይ ግን ሙሉ ጉልበቱን እንደሚሰጥ ስለምናውቅ እንቀበለው ነበር።”“እንግሊዝኛም ብዙም መናገር አይችልም ነበር። ለቻምፒየንስ ሊግ ጨዋታዎች ወደ ኤርፖርት ስንሄድ ከቤቱ እወስደው ነበር::”“እንዴት እንደሆነ ባላውቅም መንገድ ላይ እንግባባ ነበር። እንግዳ ነገር ነው!”@man_united_ethio_fan @man_united_ethio_fan
ማን ዩናይትድ ኢትዮ ፋንስ
7 Oct, 15:44
ስለ ጉዳቱ የተሰጠ ምላሽ የለም !የቤንያሚን ሼሽኮ የእግር አጥንት ጉዳት በድጋሚ ካገረሸ በኋላ ስለ ሁኔታው ከማንችስተር ዩናይትድም ሆነ ከስሎቬኒያ ብሔራዊ ቡድን እስካሁን ምንም ይፋዊ መረጃ አልተሰጠም።[Simon Stone]@man_united_ethio_fan @man_united_ethio_fan
ማን ዩናይትድ ኢትዮ ፋንስ
7 Oct, 15:34
“ይህ ቀን እንዳይደርስ እንመኝ ነበር።”የክለባችን ተጫዋች ሊሳንድሮ ማርቲኔዝ ሊዮኔል ሜሲ ለአርጀንቲና የመጨረሻ ጨዋታውን ስለማድረጉ፦“ይህ ቀን እንዳይደርስ እየተመኘን በብዙ ጭንቀት ነበር የጠበቅነው፤ የማይደርስ ይመስል ነበር ዛሬ ግን ደረሰ።"“ከዚህ በኋላ ለቀጣዩ የብሔራዊ ቡድን ጨዋታ ከእኛ ጋር እንደማይኖር ማሰብ አሁንም ከባድ ነው።"“እነዚህ ጊዜያት በፍጥነት ያልፋሉ፤ ስለዚህ በተቻለን መጠን እያንዳንዱን ቅጽበት ሙሉ በሙሉ እንዲያጣጥም እንፈልጋለን።”@man_united_ethio_fan @man_united_ethio_fan
ማን ዩናይትድ ኢትዮ ፋንስ
7 Oct, 15:22
በዘንድሮዉ የኔሽንስ ሊግ ውድድር እስካሁን በነበረው ጨዋታ የWHO SCORED ምርጥ 11 ተጫዋቾች !!ሴኔ ላመንስ ተካትቷል ።@man_united_ethio_fan @man_united_ethio_fan
ማን ዩናይትድ ኢትዮ ፋንስ
7 Oct, 15:15
አንድሬይ ሳንቶስ እድሉን ቢያገኝ አብሮት ልምምድ ማድረግ የሚፈልገውን አርአያውን ሲጠየቅ፦“ክርስቲያኖ ሮናልዶ።”@man_united_ethio_fan @man_united_ethio_fan
Related Channels
Other channels in the same section of the catalogue.
