Latest posts

M.O.R. Medium Tax Payers No 1 Branch Office
26 Sept, 08:36
ለኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት አመራርና ሠራተኞች ሲሰጥ የነበረው የሞጁላር ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡መስከረም 16/2019 ዓ/ምበገቢዎች ሚኒስቴር የመካከለኛ ቁጥር-1 ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የታክስ ከፋዮች ትምህርትና መረጃ አቅርቦት የስራ ሂደት አመራር እና ባለሙያዎች አማካኝነት ለኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት አመራርና ሠራተኞች ከመስከረም 11/2019 ጀምሮ ሲሰጥ የነበረው የሞጁላር ስልጠና ተጠናቋል።ስልጠናው በክፍል አንድ ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ እና የወጪ መጋራት፣ ከቤት ኪራይ እና ከንግድ ስራ ከሚገኝ ገቢ፣ ከተከፋይ ሂሳቦች ላይ ታክስ ቀንሶ ማስቀረት፣ በክፍል ሁለት ቀጥተኛ ባልሆኑ ታክሶች በአዲሱ የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር 1341/2016፣ ኤክሳይዝ ታክስ፣ የቴምብር ቀረጥ እና በሱር ታክስ አስተዳደር ሥርዓት እንዲሁም በክፍል ሶስት ታክስ ባልሆኑ ገቢዎች የታክስ ከፋይ ምዝገባ፣ ስረዛ እና ክሊራንስ አሰጣጥ፣ የታክስ ማስታወቂያዎች እና ቅጾች፣ ታክስንና ሌሎች ክፍያዎችን ስለመሰብሰብና ማስከፈል እንዲሁም የታክስ አስተዳደራዊ እና የወንጀል ቅጣቶች እና ተያያዥ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ ተሰጥቷል፡፡በመጨረሻም የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት የሥልጠና ክፍል ኃላፊ የሆኑት ዶ/ር እንዳልካቸው አበበ ተገኝተው ከስልጠናው በርካታ የታክስ ህግ እውቀቶችንና አሰራሮችን እንዳገኙ ስልጠናውን ለሰጡ የመካከለኛ ቁጥር-1 ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የታክስ ከፋዮች ትምህርትና መረጃ አቅርቦት የስራ ሂደት አመራርና ባለሙያዎች ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

1,440Open in Telegram
M.O.R. Medium Tax Payers No 1 Branch Office
26 Sept, 08:29
በማኅበራዊ አካታችነትና በኤች አይቪ ኤዲስ ዙሪያ ለቅ/ጽ/ቤቱ ሠራተኞችና አመራሮች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሠጠ፡፡መስከረም 16/2019 ዓ.ምበገቢዎች ሚኒስቴር የመካከለኛ ቁ.1 ግብር ከፋዮች ቅ/ቤት ለቅ/ጽ/ቤቱ ሠራተኞችና አመራሮች በማኅበራዊ አካታችነትና በኤች አይቪ ኤዲስ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሠጥቷል፡፡ሥልጠናውን በይፋ ያስጀመሩት የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የተቋማዊ አቅምና ድጋፍ ም/ስራ አስኪያጅ አቶ አቡ ብርኪ ቅ/ጽ/ቤታችን ማህበራዊ ጉዳዮችን አካቶ በመተግበር ኃላፊነቱን በተግባር እየተወጣ ነው ያሉ ሲሆን እንደማሳያም ቅ/ጽ/ቤቱ ለማህበራዊ ችግር የተጋለጡ ህጻናትን ድጋፍ እንደሚያደርግ ጠቅሰው በገንዘብ ድጋፍ ከማድረግ ባለፈ ያሉበትን የትምህርትና ሌሎች ሁኔታዎችን የመከታተል የመምከርና ብቁ ዜጋ እንዲሆኑ እንዲሆኑ ቅ/ጽ/ቤታችን የበኩሉን ማህበራዊ ኃላፊነት እየተወጣ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል፡፡አቶ አቡ አያይዘውም ይህንንም ይበልጥ አጠናክሮ ለማስቀጠል የተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠናዎችን በመስጠት ለሰራተኞቻችን በየጊዜው ግንዛቤ መፍጠር አስፈላጊ እንደሆነ አስገንዝበዋል፡፡ በዚህም መነሻነት ይህ ዛሬ በኤች አይቪ ኤዲስና ተያያዥ ማህበራዊ ጉዳዮች አካታችነት ዙሪያ የተዘጋጀው የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና አንዱ ማሳይ ነው ያሉ ሲሆን ተሳታፊዎችም በትኩረት እንዲከታተሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቡድን አስተባበባሪ ወ/ሮ አለምፀሀይ ረዳ እንደ ቅ/ጽ/ቤት ሴቶችና ወጣቶችን ለማብቃት መሰል የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠናዎችን እንዲያገኙ ማድረግ የቡድኑ አንዱ ኃላፊነት እንደሆነ ገልጸው በቀጣይም ከበላይ አመራሩና ሌሎች የስራ ክፍሎች ጋር በጋራ በመሆን ሴቶችና ወጣቶች ወደ አመራርነት እንዲመጡ ለማስቻል በአመራር ክህሎት (Leadership Skills) ፣ ራስን የማብቃት (Personal Empowerment) እንዲሁም የወጣቶች ስብዕና ግንባታ (Youth Personality Development) እና መሰል ጉዳዮች ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠናዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል፡፡ስልጠናው በእጩ ዶ/ር ኃይለማሪያም አማካኝነት ከሁሉም የቅ/ጽ/ቤቱ የስራ ክፍሎች ለተውጣጡ አመራርና ሠራኞች ተሰጥቷል፡፡በመጨረሻም የቅ/ጽ/ቤቱ የሰው ኃብት ሥራ አመራርና ልማት የሥራ ሂደት አስተባባሪ አቶ ሳምሶን መንግስቱ በየትኛውም ሁኔታ በሁሉም ዘርፍ በገጠርም በከተማም ያሉ ሴቶችን ማብቃት ጥቅሙ ለሴቶች ብቻ ሳይሆን ለሀገር ዕድገት እንደሆነ ገልፀው ከዚህ ስልጠና ያገኘነውን ግንዛቤ ወደ ተግባር መቀየር እንደሚገባ አሳስበዋል።1,270Open in Telegram
M.O.R. Medium Tax Payers No 1 Branch Office
24 Sept, 12:11edited
በተሻሻለው የታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1434/2018 ላይ ስልጠና ተሰጠ፡፡መስከረም 14/2019 ዓ/ምበገቢዎች ሚኒስቴር የመካከለኛ ቁ-1 ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለፋይናንስ ኃላፊዎችና የሂሳብ ባለሙያዎች በተሻሻለው የታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1434/2018 ላይ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡ሥልጠናው በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የታክስ ከፋዮች ትምህርት ዋና መሪ ባለሙያ በሆኑት አቶ ታምራት ጅግሳ አማካኝነት ተሰጥቷል፡፡በሌላ በኩል በስልጠና መርሃግብሩ ላይ የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የታክስ ማስታወቅ የስራ ሂደት-2 የስራ ሂደት አስተባባሪ የሆኑት ወ/ሮ ደስታ አባዲ ተገኝተው በአዲሱ የገቢ ግብር አዋጅ 1395/2017 አንቀፅ 33 መሰረት በሰንጠረዥ 'ሐ' መክፈል ያለበት ግብር ከፋይ ከአንድ በላይ የስራ መስክ /ንግድ ፍቃድ ገቢ ያገኘ ከሆነ ገቢያቸዉን ነጣጥለው በኢ-ታክስ ሲስተም ላይ እንዴት ማሳወቅ እንዳለባቸው ማብራሪያ እና ስልጠና ሰጥተዋል፡፡


3,730Open in Telegram
M.O.R. Medium Tax Payers No 1 Branch Office
24 Sept, 11:08
የመመዘኛ ፈተና ተሰጠ፡፡መስከረም 14/2019 ዓ/ምበገቢዎች ሚኒስቴር የመካከለኛ ቁ-1 ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ምዕራፍ አንድ ላጠናቀቁ 26ኛ ዙር የሞጁላር ስልጠና ተከታታዮች በዛሬው ዕለት የመመዘኛ ፈተና ተሰጥቷል፡፡


3,530Open in Telegram
M.O.R. Medium Tax Payers No 1 Branch Office
22 Sept, 13:19
ምዕራፍ አንድ የሞጁላር ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡መስከረም 12/2019 ዓ/ምበገቢዎች ሚኒስቴር በመካከለኛ ቁጥር-1 ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ግብር ከፋዮችን በመሰረታዊ የታክስ ህጎችና አሠራሮች እንዲሁም አዋጆች ላይ ያላቸውን ግንዛቤ ለማሳደግ ታስቦ መስከረም 06 /2019 ዓ/ም ጀምሮ ለ26ኛ ዙር የሞጁላር ስልጠና ተከታታዮች በምዕራፍ አንድ ቀጥተኛ በሆኑ ታክሶች ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ እና የወጪ መጋራት፣ የቤት ኪራይ ገቢ ግብር፣ ከንግድ ስራ ገቢ ግብር እና ከተከፋይ ሂሳቦች ላይ ግብርን ቀንሶ ማስቀረት ዙሪያ ሲሰጥ የነበረው ስልጠና በዛሬው ዕለት ተጠናቋል፡፡ስልጠናውን የሰጡት የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የታክስ ከፋዮች ትምህርት ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑት ወ/ሮ ዚነት አሕመድ ናቸው።


1,970Open in Telegram
M.O.R. Medium Tax Payers No 1 Branch Office
22 Sept, 12:44

2,300Open in Telegram
M.O.R. Medium Tax Payers No 1 Branch Office
22 Sept, 11:31

M.O.R. Medium Tax Payers No 1 Branch Office
22 Sept, 11:31

2,720Open in Telegram
M.O.R. Medium Tax Payers No 1 Branch Office
22 Sept, 08:26edited
ለኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት አመራርና ሠራተኞች የሞጁላር ስልጠና መስጠት ተጀመረ፡፡መስከረም 12 /2019 ዓ/ምበገቢዎች ሚኒስቴር የመካከለኛ ቁጥር-1 ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የታክስ ከፋዮች ትምህርትና መረጃ አቅርቦት የስራ ሂደት ባለሙያዎች ለኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት አመራርና ሠራተኞች የመጀመሪያውን ምዕራፍ የሞጁላር ስልጠና መስጠት ጀምረዋል፡፡በስልጠና መርሃግብሩ ላይ የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት የሥልጠና ክፍል ኃላፊ ደ/ር እንዳልካቸው አበበ ተገኝተው የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈው ስልጠናው በታክስ ህግ አሰራር ያለባቸውን የእውቀት ክፍተት ሊሞላ የሚችል ወሳኝ ስልጠና በመሆኑ ሠልጣኞቹ ትኩረት ሰጥተው እንዲከታተሉ አሳስበዋል፡፡የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የታክስ ከፋዮች ትምህርትና መረጃ አቅርቦት የስራ ሂደት አስተባባሪ የሆኑት አቶ ተግባሩ ታምሩ እንዳሉት ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ግብር ከፋዮች በመሰረታዊ የታክስ ህጎችና አሰራሮች ያላቸውን ግንዛቤ በማሳደግ ግብርን በፍቃደኝነት የመክፈል ባህላቸውን እንዲያሳድጉ እንዲሁም ባለማወቅ እንዳይቀጡ ለማድረግ በማሰብ በተለያዩ የስልጠና አማራጮች ስልጠመናውን እየሰጠ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡ስልጠናው በመጀመሪያው ምዕራፍ ቀጥተኛ ከሆኑ ታክሶች ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ እና የወጪ መጋራት ዙሪያ ተሰጥቷል፡፡


3,170Open in Telegram
M.O.R. Medium Tax Payers No 1 Branch Office
22 Sept, 07:56
የታክስ ደረሰኝ ያለመስጠት ተጠያቂነትመስከረም 12/2019 ዓ.ምበተሻሻለው የፌዴራል ታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1434/2018 መሰረት የታክስ ደረሰኝ ያለመስጠት የሚያስከትለውን ተጠያቂነት በተመለከተ የሚከተለውን ይላል፡- 👉የታክስ ደረሰኝ ሊሰጥ ሲገባ ያልሰጠ ማንኛውም ታክስ ከፋይ ለገዢ ባልሰጠው በእያንዳንዱ ደረሰኝ ብዛት ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) ቅጣት ይቀጣል። 👉ይሕ ቅጣት በባለሥልጣኑ ሊነሳ አይችልም። 👉ለአንድ ግብይት በተሰጠ ተመሳሳይ ደረሰኝ ላይ የተለያዩ ዋጋዎችን በመመዝገብ የሽያጭ ዋጋን ያሳነሰ ወይም የሽያጭ ዋጋን በማሳነስ ደረሰኝ የሰጠ ማንኛውም ሰው ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) የገንዘብ መቀጫ እና ከአምስት እስከ ሰባት ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት ይቀጣል።
3,000Open in Telegram
M.O.R. Medium Tax Payers No 1 Branch Office
21 Sept, 17:40

M.O.R. Medium Tax Payers No 1 Branch Office
21 Sept, 17:40

3,560Open in Telegram
M.O.R. Medium Tax Payers No 1 Branch Office
21 Sept, 14:01
ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በነሐሴ ወር ብቻ ከ9.17 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን አስታወቀ፡፡መስከረም 11/2019 ዓ/ምበገቢዎች ሚኒስቴር የመካከለኛ ቁ.1 ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት በነሐሴ ወር ቀጥተኛ ከሆኑ ታክሶች፣ ቀጥተኛ ካልሆኑ ታክሶችና ታክስ ካልሆኑ ገቢዎች 8,608,034,721.03 ብር ለመሰብሰብ አቅዶ 9,172,401,636.96 ብር በመሰብሰብ የእቅዱን 106.56% በመቶ ማሳካት መቻሉን የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የዕቅድና በጀት አፈፃፀም ክትትል ቡድን አስተባባሪ የሆኑት አቶ ሙሉጌታ አበባው የቅ/ጽ/ቤቱ የማኔጅመንት አባላት ባካሄዱት የነሐሴ ወር ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ ወቅት ባቀረቡት ሪፖርት ላይ አመላክተዋል፡፡አፈፃፀሙ ከባለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወር ክንውን ጋር ሲነፃፀር የብር 2.51 ቢሊዮን ወይም የ37.7 በመቶ ብልጫ እንዳለው ተገልጿል፡፡በቀረበው ሪፖርት ላይ የሁሉም የስራ ክፍሎች የሥራ ሂደትና ቡድን አስተባባሪዎች እንዲሁም የየዘርፉ ምክትል ሥራ አስኪያጆች በነሐሴ ወር በየስራ ክፍሉ በነበሩ ጠንካራ ጎኖችና በቀጣይ ወራቶች ቢሰሩ የገቢ አፈፃፀሙን ሊያሳድጉ በሚችሉ አንኳር ነጥቦች ላይ ሠፋ ያለ ውይይት አድርገዋል፡፡የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ስራ አስኪያጅ ተወካይ እና የታክስ ስርዓት ም/ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ እቴነሽ ደሱ ዓመት በ2019 በጀት ዓመት በነሐሴ ወር በገቢ አሰባሰብ ስራችን አመርቂ ውጤት ያስመዘገብንበት ወቅት በመሆኑ ለዚህ ውጤት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ በየደረጃው ለሚገኙ አመራርና ሠራተኞች እንዲሁም ግብራቸውን በወቅቱ አስታዉቀው ለሚከፍሉ ታማኝ3,910Open in Telegram
M.O.R. Medium Tax Payers No 1 Branch Office
21 Sept, 14:01



3,490Open in Telegram
M.O.R. Medium Tax Payers No 1 Branch Office
21 Sept, 12:37

3,960Open in Telegram
M.O.R. Medium Tax Payers No 1 Branch Office
21 Sept, 09:15

M.O.R. Medium Tax Payers No 1 Branch Office
21 Sept, 09:15

M.O.R. Medium Tax Payers No 1 Branch Office
21 Sept, 09:15

M.O.R. Medium Tax Payers No 1 Branch Office
21 Sept, 09:15

M.O.R. Medium Tax Payers No 1 Branch Office
21 Sept, 08:48
Related Channels
Other channels in the same section of the catalogue.
