Latest posts

Musse Solomon
1 Oct, 17:56
ነገ ከረፋዱ 4:00 ሠዓት ጀምሮ መንገዶች ይዘጋሉ።የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ መስከረም 23 ቀን 2019 ዓ/ም በአዲስ አበባ ከተማ በሚከበረውን የኢሬቻ ሆራ ፊንፊኔ በዓል ምክንያት መንገዶች ለተሽከርካሪዎች ዝግ እንደሚሆኑ አስታውቋል።ነገ መስከረም 22 ቀን 2019 ዓ/ም ከረፋዱ 4፡00 ሠዓት ጀምሮ እስከ መርሀ ግብሩ ፍፃሜ ድረስ ፡-- ከመገናኛ ወደ መስቀል አደባባይ (22 ወይም ጎላጎል አደባባይ ላይ እና ታች)- ከአድዋ ድልድይ ወደ ዘሪሁን ህንፃ እና ወደ ቅዱስ ዑራኤል አደባባይ (ዘሪሁን ህንፃ መስቀለኛ)- ከአትላስ መብራት ወደ ቅዱስ ዑራኤል አደባባይ (ፒኮክ መብራት)- ከቦሌ ሩዋንዳ ድልድይ ወደ መስቀል አደባባይ (ወሎ ሠፈር አደባባይ ላይ እና ታች)- ከጋዜቦ አደባባይ በደንበል ህንፃ ጀርባ ወደ ፊላሚንጎ እንዲሁም ከጋዜቦ አደባባይ በአዲሱ መንገድ ወደ ለገሃር መብራት (ጋዜቦ አደባባይ)- ከቅዱስ ቂርቆስ ታቦት ማደሪያ ወደ ለገሃር መብራት (ቅዱስ ቂርቆስ ታቦት ማደሪያ መብራት)- ከቀድሞው ብርሃን ኢትዮጵያ መስቀለኛ በአዲሱ መንገድ ወደ ቅዱስ ቂርቆስ ቤ/ክርስቲያን (ብርሃን ኢትዮጵያ መስቀለኛ)- ከአፍሪካ ህብረት ቅዱስ ሚካኤል መስቀለኛ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ (አፍሪካ ህብረት ቅዱስ ሚካኤል መስቀለኛ)- ከአፍሪካ ህብረት መብራት ወደ ሜክሲኮ አደባባይ (አፍሪካ ህብረት መብራት)- ከከፍተኛ ፍ/ቤት አደባባይ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ (ከፍተኛ ፍ/ቤት አደባባይ)- ከሜክሲኮ አረቁ ፋብሪካ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ (አረቄ ፋብሪካ መስቀለኛ)- ከሰንጋ ተራ 40/60 ቤቶች መገንጠያ ወደ ሠንጋ ተራ መብራት (ሠንጋ ተራ 40/60 መገንጠያ)- ከጎማ ቁጠባ መብራት ወደ ብሔራዊ ቴአትር (ጎማ ቁጠባ መብራት)- ከሜትሮሎጂ መታጠፊያ ወደ ፖስታ ቤት መብራት (ሜትዮሮሎጂ መታጠፊያ)- ከጥቁር አንበሳ ሼል ወደ ኤሚግሬሽን መብራት ( ጥቁር አንበሳ መስቀለኛ)- ከጎላ ቅዱስ ሚካኤል መስቀለኛ ወደ ኤሚግሬሽን መብራት (ጎላ ቅዱስ ሚካኤል መስቀለኛ)- ከቴዎድሮስ አደባባይ ወደ ኤሚግሬሽን መብራት (ቴዎድሮስ አደባባይ)
Related Channels
Other channels in the same section of the catalogue.
