gram news
Nolawi ኖላዊ channel avatar

Nolawi ኖላዊ

@nolawii

ይህ ቻናል ኦርቶዶክሳዊ መንፈሳዊ ትምህርቶች የሚተላለፉበት ነው። እግዚአብሔር አገልግሎቱን ያስፋ! 0911699907 ዲያቆን አሸናፊ መኰንን

ProjectsENReligion

9,260subscribers

Open the Channel

Latest posts

  • Nolawi ኖላዊ

    21 Sept, 07:10

    እግዚአብሔር ፍቅር ነውእግዚአብሔር ምሉዕ አካል አለው ፣ ፍቅርም ስሜት አይደለም ። እግዚአብሔር ዘላለማዊ ነው ፣ ፍቅርም ከሁኔታ በላይ ነው ። እግዚአብሔር የቦታ ዳርቻ የለበትም ፣ ፍቅርም ሁሉን ይወዳል ። እግዚአብሔር ብርሃን ነው ፣ ፍቅርም በእውነት ላይ ይመሠረታል ። ዓለም “ፍቅር ዕውር ነው” ይላል ፣ ይህ ቃል ለእውነተኛው ፍቅር ገላጭ አይደለም ፣ ለስሜት ስካር የሚነገር ነው ። እግዚአብሔር ትሑት ነው ፣ ፍቅርም ዋጋ ይከፍላል ። የሰው ፍቅር ተወዳጁ ባለው ነገር ላይ ይመሠረታል ። በመልኩ ቅላትና ጠይምነት ፣ በቁመቱ መርዘምና ማጠር ፣ በገንዘቡ ብዛትና በአነጋገሩ ማራኪነት ላይ ይመሠረታል ። ከእነዚህ ነገሮች አንዱ ሲጎድል የወደድነውን መጥላት እንጀምራለን ። እግዚአብሔር ግን የሚወደው እኛነታችንን ነው ። እርሱ የነፍሳችን ወዳጅ ነው ። እነዚህ ሁሉ መስፈርቶች የፍቅር መሠረት መሆን አይችሉም ። የእግዚአብሔር ፍቅር በራሱ በእግዚአብሔር ላይ ይመሠረታል ። የሚወደድ ሰው ቀርቶ የሚወደድ ማንነት የለንም ። ሰውንም ራሳችንንም የምንቀበለው በእግዚአብሔር ነው ። እግዚአብሔር በራሱ የፍቅር ባሕርይ ላይ ተመሥርቶ ያለ መስፈርት ይወደናል ። ይህ ፍቅር በማግኘት በማጣት አይለወጥም ።እግዚአብሔር እንዲወደን ብለን የምናደርገው ጥረት የለም ። እግዚአብሔር ፍቅር ስለሆነ ይወደናል ። የወደደን ስለወደድነው አይደለም ፣ እንኳን እግዚአብሔር ወላጆቻችን እንኳ የወደዱን ስለወደድናቸው አይደለም ። እግዚአብሔር ስለ ወደደን እንወደዋለን ። እኛ ጠላቶች ሳለን አፍቅሮናል ። የፍቅር መነሻው ፣ በመውደድ ቀዳሚው
    747251Open in Telegram
  • Nolawi ኖላዊ

    21 Sept, 04:18

    forwarded from @nolawii

    በዲያቆን አሸናፊ መኰንን የተጻፉትን ና በገበያ ላይ ያሉትን እነዚህን መጻሕፍት በሙሉ ለሚገዙ አዲስ አበባ ላይ ላሉ ወዳጆች ያሉበት ድረስ እናደርሳለን!1- የእግዚአብሔር ትዕግሥት 400 2- ብርቱ ድምፅ 250 3- ተንሥኡ ለጸሎት 60 4- ረጅሙ ፈትል 170 5- የጊዜው ቃል 200 6- ቅዱስ ጋብቻ 200 7- እንደ እኔ ከተሰማችሁ 150 8- የሕይወት መክብብ 150 9- አካላዊ ቃል 250 10- ቃና ዘገሊላ 250 11- ኒቆዲሞስ 170 12- ሳምራዊቷ ሴት 250 13-መጻጉዕ 250 14- እርስ በርሳችሁ180 15- ኅብስተ ሕይወት 250 16- የሕይወት ውኃ 250 17- ኦሪት ዘፍጥረት ትርጓሜ 300 18- ምዕራፈ ቅዱሳን 200
  • Nolawi ኖላዊ

    20 Sept, 08:06edited

    ይዋጉሃል አያሸንፉህምየድል ድምፅ#ዲያቆን #አሸናፊ #መኰ
    939file19111Open in Telegram
  • Live stream finished (1 hour)

    20 Sept, 08:04

  • Live stream started

    20 Sept, 06:53

  • Live stream finished (5 minutes)

    20 Sept, 06:53

  • Live stream started

    20 Sept, 06:47

  • Nolawi ኖላዊ

    20 Sept, 05:43

    ዛሬ እሑድ መስከረም 10 ቀን 2019 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ላይ ትምህርታችን ይጀምራል ::የትምህርታችን ርእስ "ይዋጉሃል አያሸንፉህምኤር. 15:20ማስታወሻ ብትይዙ ይመከራል።ሌሎች ወገኖቻችንንም ጋብዙhttps://t.me/Nolawii
    TelegramNolawi ኖላዊይህ ቻናል ኦርቶዶክሳዊ መንፈሳዊ ትምህርቶች የሚተላለፉበት ነው። እግዚአብሔር አገልግሎቱን ያስፋ! 0911699907 ዲያቆን አሸናፊ መኰንን
  • Nolawi ኖላዊ

    18 Sept, 15:45

    የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ዛሬ ዓርብ መስከረም 8 ቀን 2019 ዓ.ም የቀጥታ መርሐ ግብር አይኖረንም!የእግዚአብሔር ጸጋና በረከት ከእናንተ ጋር ይሁን !
    1,320115Open in Telegram
  • Nolawi ኖላዊ

    17 Sept, 13:30edited

    ምድር በ0ሥር ነገሮች ትጨነቃለች :-1. አላዋቂ ዝነኛ በሆነ ጊዜ ፣2. ባለጌ በተሾመ ጊዜ ፣3. ምሁር በዋሽ ጊዜ ፣4. ስስታም ባለጠጋ በሆነ ጊዜ ፣5. ያልሰለጠነ አቅም ባገኘ ጊዜ ፣6. ቄስ ጉበኛ በሆነ ጊዜ ፣7. ራስ ወዳድ ባገባ ጊዜ ፣8. ልጆች ቤትን በመሩ ጊዜ ፣9. ገላ ሸቀጥ በሆነ ጊዜ ፣
    Image from a post by Nolawi ኖላዊImage from a post by Nolawi ኖላዊ
    1,790691222Open in Telegram
  • Nolawi ኖላዊ

    17 Sept, 07:08

    የፍቅር ትርጉምማፍቀር ማለት መኖር ማለት ነው ። ፍቅር የሌለው ሕይወት የተዘጋ ቤት ነው ፣ የተዘጋ ቤት ይሸታል ፣ ያዘምማል ። ፍቅር የሌለው ቤት ምንም ቢያምር የተዋበ የመቃብር ስፍራ ነው ። ፍቅር የሌለው ተቋም ምንም ቢደራጅ ፈራሽ ነው ። ብዙ ሰው ሌላውን ማፍቀሩን እንደ ውለታ ይቆጥረዋል ፣ ፍቅር ከሌለው ግን መኖር እያቃተው እንደሚመጣ አይገነዘብም ። የምንወደው ለራሳችን ብለን ነው ። ፍቅራችንን የምንገልጥለት ስምንት ቢሊየን ሕዝብ አለ ። ፍቅር እንደ ዕቁብ ጣልና ልጣል የሚባል አይደለም ። ፍቅር እንደ ጅብ ጉዞ መጠባበቅ ያለበት አይደለም ። ፍቅር ሲያዘን መታዘዝ ተገቢ ነው ። መልካም መዓዛ ባለበት ንቦች ይታያሉ ። ፍቅር ሲኖረን መንፈሰ እግዚአብሔር ይቀርበናል ። መላእክት ሊያዩን ይጓጓሉ ። ምነው የእርሱ ጠባቂ ባደረገኝ ይላሉ ። ሕይወት ያለ ፍቅር ትርጉም የላትም ። ብዙ ሰዎች ገንዘብን ብቻ ሲያሳድዱ ፍቅርን ያጡታል ። ከልጆቻቸው ጋር ያላሳለፉ ወላጆች በመጨረሻ የማጣት ስሜት ያሰቃያቸዋል ። ልጆቹም የወላጅን ፍቅር ስላላገኙ ቢሳካላቸው እንኳ ትልቅ ጉድለት ይሰማቸዋል ። የሰው ልጅ ትልቅ ማንነቱ ረቂቅ ነው ። ሥጋው ማደሪያ ፣ ሳጥን ፣ ቤት ነው ፣ አዳሪው ግን ነፍሱ ናት ። ስለ አዳሪው ማኅደሩን ማክበር ይገባል ፣ ስለ ነፍስ ሥጋ የተከበረች ናት ። የሰው ልጅ ግን የሚበዛው ማንነቱ መንፈሳዊ ወይም ረቂቅ ነው ። ለመንፈሳዊ ማንነቱ ፍቅር አስፈላጊው ነው ።ብዙ ፍለጋዎች ይሳካሉ ፣ የሚወደንን ሰው ብንፈልግ ግን አይሳካልንም ። ምክንያቱም ካልወደድነው በቀር የሚወደን ማንም የለም ። መወደድ ዕዳ
    1,63034611Open in Telegram
  • Nolawi ኖላዊ

    15 Sept, 06:35edited

    የፍቅር ዓመትስለ ፍቅር ሦስት አስደናቂ ገለጻዎች አሉ ፤ እነርሱም፡- እግዚአብሔር ፍቅር ነው ፣ ፍቅር ለዘወትር አይወድቅም ፣ ፍቅር የነፍስ ጨው ነው የሚሉት ናቸው (1ዮሐ. 4፡8 ፣ ቁ. 16 ፤ 1ቆሮ. 13፡8 ፤ ማር. 9፡50)። እግዚአብሔር ፍቅር ነው ስንል እግዚአብሔር ፍቅርን አልተለማመደም ፣ ለዘላለም ፍቅር ነው ። እገዚአብሔር ፍቅር አለው አይልም ፣ ፍቅር የእግዚአብሔር አንዱ መገለጫ ሳይሆን ሌሎች ጠባያቱ ሁሉ የሚወጡት ከፍቅሩ መሆኑን የሚገልጥ ነው ። እግዚአብሔር ፍቅር ነው ተብሎ የተገለጠበት “አጋፔ” የሚለው ቃል ያለ ምክንያት ፣ ጥቅምን ታሳቢ ባለማድረግ የሚወድ ፍቅር መሆኑን የሚያሳይ ነው ። የእግዚአብሔር ፍቅር በመስቀል ላይ በዋለው ልጁ የተገለጠ ሲሆን ፍቅሩ ቃላት ሳይሆን ተግባርና መሥዋዕትነት ያለው መሆኑን ያስረዳል ። ብዙ ሥልጣኔዎች ተነሥተዋል ፣ እንደ ሰናዖር ግንብ መልሰው ፈርሰዋል ። ብዙ ግዛቶች ተመሥርተዋል ፣ እንደ እስክንድር ዘመናቸው ጥቂት ሆኗል ። ብዙ ባለጠጎች ከፍ ብለዋል ፣ ሲወድቁ ቁራሽ አጥተው ሞተዋል ። ለዘወትር የማይወድቅ ነገር በምድር ላይ ማግኘት ከባድ ነው ። ፍቅር ግን ለዘወትር አይወድቅም ተብሎ ተጽፎአል ። (1ቆሮ. 13፡8)። አፍቃሪም ዋጋው አይወድቅም ። ላለመውደቅ ብለን ሀብትን እንሰበስባለን ፣ ሥልጣንን እናደላድላለን ፣ ሠራዊት እናደራጃለን ፣ የትምህርት ወረቀቶችን እናበዛለን ። የነጋው ቀን ለመምሸቱ እርግጠኛ ባልሆነ በዚህ ዓለም ላይ የማይወድቅ ነገር አንድ ብቻ ነው ። እርሱም ፍቅር ነው ።ምግብን የሚያጣፍጠው ቅመም ነው ። ቅመሞች ከማጣፈጥ ባሻገር
    1,8203751Open in Telegram
  • Nolawi ኖላዊ

    15 Sept, 05:26

    forwarded from @nolawii

    በዲያቆን አሸናፊ መኰንን የተጻፉትን ና በገበያ ላይ ያሉትን እነዚህን መጻሕፍት በሙሉ ለሚገዙ አዲስ አበባ ላይ ላሉ ወዳጆች ያሉበት ድረስ እናደርሳለን!1- የእግዚአብሔር ትዕግሥት 400 2- ብርቱ ድምፅ 250 3- ተንሥኡ ለጸሎት 60 4- ረጅሙ ፈትል 170 5- የጊዜው ቃል 200 6- ቅዱስ ጋብቻ 200 7- እንደ እኔ ከተሰማችሁ 150 8- የሕይወት መክብብ 150 9- አካላዊ ቃል 250 10- ቃና ዘገሊላ 250 11- ኒቆዲሞስ 170 12- ሳምራዊቷ ሴት 250 13-መጻጉዕ 250 14- እርስ በርሳችሁ180 15- ኅብስተ ሕይወት 250 16- የሕይወት ውኃ 250 17- ኦሪት ዘፍጥረት ትርጓሜ 300 18- ምዕራፈ ቅዱሳን 200
  • Nolawi ኖላዊ

    13 Sept, 08:08edited

    የትምህርቱ ርእስ ቅዱስ ዮሐንስእንኳን ከ 2018 ዓ.ም ዘመነ ማርቆስ ወደ 2019 ዓ.ም ዘመን ሉቃስ በሰላምና በጤና አሸጋገራችሁ !ዲያቆን አሸናፊ መኰንን የአዲስ ዓመት ትምህርት
    2,110file23102Open in Telegram
  • Live stream finished (1 hour)

    13 Sept, 08:07

  • Live stream started

    13 Sept, 06:49

  • Nolawi ኖላዊ

    13 Sept, 05:28edited

    ዛሬ እሑድ መስከረም 3 ቀን 2019 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ላይ ትምህርታችን ይጀምራል ::የትምህርታችን ርእስ "ቅዱስ ዮሐንስማር. 1 ፥ 1-4ማስታወሻ ብትይዙ ይመከራል።ሌሎች ወገኖቻችንንም ጋብዙhttps://t.me/Nolawii
    TelegramNolawi ኖላዊይህ ቻናል ኦርቶዶክሳዊ መንፈሳዊ ትምህርቶች የሚተላለፉበት ነው። እግዚአብሔር አገልግሎቱን ያስፋ! 0911699907 ዲያቆን አሸናፊ መኰንን
  • Nolawi ኖላዊ

    12 Sept, 18:05

    https://vt.tiktok.com/ZSqm7hNcB/
  • Nolawi ኖላዊ

    12 Sept, 07:09edited

    እዘንለትከእውቀትም ከዕድሜም ድሀ ለሆነው ፣ ለአገርህ ዝመት እንጂ ከአገርህ ብላ ለማይባለው ፣ መኖር ርቆት ለጥቂቶች አኗኗሪ ለሆነው ፣ እንኳን ለነገ ለዛሬ እርግጠኛ መሆን ላቃተው ፣ ያልተማረ አስተማሪ ሰይፍ ይዞ ለሚነዳው ለዚያ ምስኪን እዘንለት ። የተባረከ ቀንን ለናፈቀው ፣ ፈልጎ ፈልጎ ላጣው ፣ አዲስ ዘመንን መጠበቅ ለደከመው ፣ ዛሬ እንደ ትላንቱ ለሆነበት ፣ የሚለው ጠፍቶት አፍ እያለው ዱዳ ለሆነው ፣ ከአገሩ ሲርቅ የዘመድ ፍቅር ላከሳው ፣ ወደ አገሩ ሲያስብ የተዘጋው በር ለሚመልሰው ለዚያ ጎበዝ እባክህ እዘንለት ። መንኩሶ ጋብቻ ፣ አግብቶ ምንኵስና ለሚያምረው ፣ የያዘው ነገር በእጁ ላይ ቶሎ ለሚያረጅበት ለዚያ ላንተ ሥራ እባክህ እዘንለት ።ከራሱም ፣ ከሰውም ፣ ከዘመንም ፣ ካንተም ተጣልቶ ላኮረፈው ፣ ሁለት ተስፋ ይዞ ፍርሃት ለሚንጠው ፣ ሁለት ዓለም ከጅሎ ሁሉም ባዶ ለሆነበት ፣ ራሱን ሸቀጥ አድርጎ ገበያ ላወጣው ፣ በሚፈርስ አካሉ ለሚመካው ለዚያ ወጣት እባክህ እዘንለት ። ውርስን ሲጠብቅ ሞት ለገጠመው ፣ ሽማግሌን እቀብራለሁ ሲል ለራሱ ቶሎ ለመሸበት ፣ መሰሉን ለሚገፋው ፣ ባዕድ ቢዘገይ እርስ በርሱ ለሚተላለቀው ፣ ድል በሌለው በወንድማማች እልቂት ለሚውለው ለዚያ ፈርሶ አፍራሽ እባክህ እዘንለት ።ተስፋ ቆርጦ ስለ መብል ብቻ ለሚያስበው ፣ በልቼ ልሙት ብሎ ለጨከነው ፣ መጽሐፍ ንቆ ጌጥ ለሚገዛው ፣ አሳብ አጥቶ መሣሪያ ለሚያነሣው ፣ ዓይን እያለው ማንበብ ለፈራው ፣ አእምሮ እያለው ማወቅን ለጠላው ፣ እረኛ ተኝቶበት አውሬ ለበላው ፣ ላልኖረላት ቤተ ክርስቲያን መሞት ለሚያምረው ፣
    2,4504474Open in Telegram
  • Nolawi ኖላዊ

    12 Sept, 03:44

    2,110video20102Open in Telegram