gram news
ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ channel avatar

ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ

@orthodox_doctrine1

Link https://telega.io/c/Orthodox_Doctrine1 Information Buy ads: https://telega.io/c/Orthodox_Doctrine1

ProjectsENReligion

7,180subscribers

Open the Channel

Latest posts

  • ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ

    22 Sept, 14:39

    ኃጢአት ላለማድረግ በግልጽም በስውርም ስትጋደል ያየህም ያላየህም ሰው አይቶ ሰምቶ ሲፈርድብህ፣ ”አልቀረብህም” ሲልህ…ግልጽና ስውር ትግልህን አይቶ ለመተው መሞከርህን ተመልክቶ ስለትግልህ ዋጋ ኃጢአቱን የሚያስተውህ እግዚአብሔር ነው!ዲ/ን ዘለዓለም ታዬ
    621358Open in Telegram
  • ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ

    22 Sept, 11:41

    forwarded from @deacon_gosa_tola12

    📖✨ ልዩ የመጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ ትምህርት ✨📖➥ከዛሬ ጀምሮ ለ3 ቀናት መሠረታዊ ሐሳቦችን እንመለከታለን።🔹 መጽሐፍ ቅዱስ ምንድነው? 🔹 እንዴት ማንበብና ማጥናት ይገባል? 🔹 ከመጽሐፍ ቅዱስ ምን እንማራለን? 🔹 ቃሉን እንዴት ወደ ሕይወት እናወርደዋለን?📅 ቀን 12 — ቀን 13 — ቀን 14➢ ቃሉን እንስማ፤ ➢ እንረዳ፤ ➢ እንኑረው!🍞እገሌኮ መማር አይፈልግም ለምትሉት ሰው ላኩለት፣ ምናልባት በእናንተ ምክንያት ይሄንን ሰው ወደ ቅዱስ መጽሐፍ ማዕድ ትጋብዙታላችሁ፣ ሰማያዊውን ክብር ታገኙበታላችሁ። በሉ ዝም ብላችሁ ላኩላቸው እስኪ የምር። ብቻዬን ከምመገብ ና አብረን እንመገብ በሉት አትፍሩ፣ ካህንም ቢሆን፣ ዲያቆንም ቢሆን፣ መምህርም ቢሆን የትኛውም ሰው ይሆን እናንተ ዝም ብላችሁ ብቻ ላኩላቸው። ማን ያውቃል ለመዳናቸው ምክንያት ትሆናላችሁ።📲 ይህንን Link ላኩላቸው፦ 👇👇👇 https://t.me/Deacon_Gosa_Tola12
  • ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ

    22 Sept, 04:05edited

    📚ርዕስ:- መድሎተ ፅድቅ ቅፅ 2 📝ደራሲ:- ዲ/ን ያረጋል አበጋዝ 📜ዘውግ፦ ሃይማኖታዊ 📖የገፅ ብዛት:- 533ለወዳጅ ዘመዶ ያጋሩ! ══════════════════ SHARE and JOIN🙏 https://t.me/hinokhailes_spiritual_teachings https://t.me/hinokhailes_spiritual_teachings 👆👆👆JOIN👆👆👆 ══════════════════
    1,160file14Open in Telegram
  • ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ

    19 Sept, 07:05

    forwarded from @deacon_gosa_tola12

    📖 ልዩ የመጋበዣ ማሳሰቢያ!!! 📖የቃሉን ምግብ በራሳችን ብቻ አንመገብ!✝️ይህንን ተከታታይ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ለመከታተል የተዘጋጀውን የቻናሉን Link እስከ ትምህርቱ መጀመሪያ ድረስ ለወዳጆቻችሁ፣ ለወንድሞቻችሁና ለእኅቶቻችሁ እያጋራችሁ ቆዩ። አንድ ሰው በቃሉ ሲጠማ፣ የተማራችሁትን ብቻችሁ ለራሳችሁ አትያዙ፤ ለሌላውም የመማር ዕድል ክፈቱ።➥ዛሬ የምትጋሩት አንድ Link ነገ ለአንድ ሰው የቃሉ መንገድ ሊሆን ይችላል። 📢 ስለዚህ ብቻችሁን አትመገቡ! የቃሉን ማዕድ አብረን እንብላ! እያጋራችሁ ጠብቁ፤ ትምህርቱም ሲጀምር አብረን እንጓዝ! 📖✝️📅 መስከረም 18፤ የትምህርቱ ጉዞ ይጀምራል።የቻናሉ Link 👇👇👇 https://t.me/Deacon_Gosa_Tola12 https://t.me/Deacon_Gosa_Tola12 https://t.me/Deacon_Gosa_Tola12
    1,660821Open in Telegram
  • ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ

    18 Sept, 19:23

    forwarded from @hinokhailes_spiritual_teachings

    <<የተፀፀቱ ሰዎችን ዕንባ የምትቀበል ጌታ ሆይ 🙏 አንተ የተቀበልከውን ፅኑ ለቅሶ እንዳለቀሰ እንደ ጴጥሮስ ያለ ዕንባን ሥጠኝ 🌊 አቤቱ እንደ ባህር በምትፈስስ ዕንባ እጠበኝ 🕊️ የማያቋርጥ የዕንባን ጎርፉ አፍስስልኝ 💧 >>ህማማት መፅሐፍ 📖 https://t.me/hinokhailes_spiritual_teachings https://t.me/hinokhailes_spiritual_teachings
    Image from a post by ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮImage from a post by ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ
    1,270127Open in Telegram
  • ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ

    18 Sept, 19:05

    📖 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት!!!📖✅ከኦሪት ዘፍጥረትእስከ ዮሐንስ ራእራ!!!🔔መስከረም 18 ይጀምራል! ➥በየቀኑ በተመጣጣኝ ምዕራፍ📖 እናነባለን! 💡 እንረዳለን! ✝️ በቤተ ክርስቲያን እምነትና ሥርዓት እንማራለን!📖ይህ ትምህርት ምን ያካትታል? ➤የእያንዳንዱ መጽሐፍ ታሪክና ይዘት ➤ዋና መልእክቱና የትምህርት ዓላማው ➤የትንቢት፣ የምሳሌና የምስጢር ገጽታዎች ➤ከሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ጋር ያለው ግንኙነት ➤ለክርስቲያናዊ ሕይወት የሚሰጠው ትምህርት📜ከዘፍጥረት → እስከ ራእይ ➥አንድ መጽሐፍ፣ አንድ ምዕራፍ፣ አንድ ትምህርት፣ በተከታታይ!
    Image from a post by ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮImage from a post by ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ
  • ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ

    17 Sept, 18:32

    forwarded from @dn_gosa_tola1224

    + አንቺ የሕይወት መድኃኒት መጀመሪያ ነሽ!!! +✍️【በዲያቆን ጐሥዓ ቶላ!!!】ድንግል ሆይ! በኃጢአትና በሞት ቁስል ለደቀቀው የሰው ልጅ ሕይወት፣ አንቺ የታላቁ ሕክምናና መድኃኒት መጀመሪያ ነሽ፤ በአዳም መተላለፍ ምክንያት በፍጥረት ሁሉ ላይ የሰለጠነው የሞት በሽታ ሊወገድ የቻለው፣ የአምላክ ፈውስ በአንቺ ማኅፀን ሰማያዊ መካነ-ሕክምናን በመሥራቱ ነው። አንቺ ከሕመም ሁሉ የምታድኚ፣ ነፍሳችንን ከኃጢአት ድዌ የምትፈውሺ እውነተኛዋ የድኅነት በርና የመለኮት ማደሪያ ነሽ። በገነት ውስጥ በተደረገው የመጀመሪያው ሽረት ምክንያት የሰው ልጅ ከተስፋው ተለይቶ በሐዘን ቁስል ሲሰቃይ፣ አንቺ የጽድቅ ተስፋና የመፈወስ ፋና ሆነሽ ወጣሽ፤ መድኃኔዓለም ክርስቶስን ያለ ወንድ ዘር በንጽሕና አዝለሽ ያስገኘሽ የተቀደሰች እርሻ ነሽ። ያ ከአንቺ የወጣው የሕይወት ፍሬ ለዓለም ሁሉ ፈውስ ሆነ፣ የመርገምንም እሾህ ከመሬት ላይ ጠረገ።እንደ ተጠበበ የሕክምና ሊቅ የማይመረመረውን ምስጢር እንዳዘጋጀ፣ አምላክም ለአዳም ልጅ ፈውስን ይሰጥ ዘንድ አንቺን ከፍጥረት ሁሉ ለይቶ ቀደሰሽ፤ አንቺ የሕይወት መና ያለብሽ የወርቅ መሶብ ነሽ። ያንቺ ንጽሕናና ትሕትና መድኃኒቱ የሚጠበቅበት ንጹሕ ማደሪያ ሆነ፤ በአንቺ አማካኝነት ከሰማይ የወረደው መድኃኒት የዓለምን ቁስል ፈወሰ። የሕይወታችን መነሻ፣ የድኅነታችንም መሠረት፣ አንቺን የያዘች ነፍስ ከቆሰለ ሕሊናና ከተስፋ መቁረጥ ድቅድቅ ጨለማ ትድናለች፤ በኃጢአት የተጎዳው አእምሯችን ያንቺን ስም ሲጠራ ዕረፍትን ያገኛል፣ በምልጃሽም ጥላ ሥር ሆኖ የመንፈስ ቅዱስን ፈውስ ይለማመዳል። አንቺ የታመሙት
  • ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ

    17 Sept, 18:27

    forwarded from @dn_gosa_tola1224

    + አንቺ የሕይወት መድኃኒት መጀመሪያ ነሽ!!! +✍️【በዲያቆን ጐሥዓ ቶላ!!!】➥በኋላ ይለቀቃል ይጠብቁ.........እስኪ ቻናሉንም ለጓደኞቻችሁ Share አድርጉ ቤተሰብ! 👇👇👇 https://t.me/Dn_Gosa_Tola1224 https://t.me/Dn_Gosa_Tola1224 https://t.me/Dn_Gosa_Tola1224
    Image from a post by ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮImage from a post by ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ
  • ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ

    17 Sept, 18:01edited

    "ለእናንተ የማሰባትን አሳብ እኔ አውቃታለሁ ፣ ፋፃሜና ተስፋ እሰጣችሁ ዘንድ የሠላም አሳብ ነው እንጂ የክፉ ነገር አይደለም ። " ትንቢተ ኤርሚያስ 29፥11
    Image from a post by ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮImage from a post by ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ
    1,450141Open in Telegram
  • ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ

    12 Sept, 04:58

    forwarded from @dn_gosa_tola1224

    በእግዚአብሔር ፍርሃት የተሞላ መንገድ ነው። ይህ መንገድ በዓለም ፊት መከራን፣ እስራትንና የሰው ጥላቻን ያተርፍ ይሆናል፤ መጨረሻው ግን ዘላለማዊ ክብርና የማይጠፋ አክሊል ነው።ስለዚህ እኛ ክርስቲያኖች በሕይወታችን ውስጥ ለጊዜያዊ ጥቅም፣ ለሰው ውዳሴ ወይም ሥልጣንን በመፍራት እውነትን ልንለውጥ አይገባም። እንደ መጥምቁ ዮሐንስ በእውነት ላይ መቆም፣ ኃጢአትንና ዓመፃን በገዛ ሕይወታችንና በዙሪያችን መታገል ይኖርብናል። በዓላቶቻችንና የልደት ቀኖቻችን እንደ ሄሮድስ በስካር፣ በዘፈንና በኃጢአት የሚከበሩ ሳይሆን፣ እንደ እውነተኛ ክርስቲያን ለእግዚአብሔር ምስጋና በማቅረብ፣ ድሆችን በመመገብና በጸሎት የሚከበሩ ሊሆኑ ይገባል። ​የካህኑ ዘካርያስና የቅድስት ኤልሳቤጥ ልጅ፣ የጽድቅና የእውነት ሰማዕት፣ የመድኃኔዓለም ክርስቶስ አያትና መጥምቅ የሆነው የቅዱስ ዮሐንስ በረከትና ጸሎት ከ ሁላችን ጋር ይሁን።​✍️ ዲያቆን ጐሥዓ ቶላ ወርኀ መስከረም 02, 2018 ዓ.ም ናዝሬት (አዳማ)፡ ኢትዮጵያhttp://t.me/Be_Gosa1224 http://t.me/Be_Gosa1224 http://t.me/Be_Gosa1224
  • ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ

    12 Sept, 04:58

    forwarded from @dn_gosa_tola1224

    + በሄሮድስ የልደት ድግስ የተሠዋው የእውነት ድምፅ +✍️ በዲያቆን ጐሥዓ ቶላ!!!ወዳጄ ሆይ፤ ቅዱሳት መጻሕፍትን ስንመረምርና የቅዱሳንን ሕይወት ስናስተውል፣ ከሰው ልጅ ተፈጥሮ ሁሉ መካከል ከሴቶች ከተወለዱት እንደ እርሱ ያለ ታላቅ ያልተነሣለት የመጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ ታሪክ የሃይማኖታችን የጽናትና የእውነት መሥዋዕትነት ትልቅ ማማ ነው። የዚህን ታላቅ ጻድቅ ሕይወት ከስር ከመሠረቱ አንሥተን ስንመለከት፣ እግዚአብሔር ለዓለም ያዘጋጀውን የድንቅ አሠራር ምሥጢርና የሰዎች ዓመፃ ምን ያህል እውነትን ለማፈን እንደሚታገል በግልጽ እንረዳለን።የመጥምቁ ዮሐንስ ታሪክ የሚጀምረው ከእምነትና ከጽድቅ ቤት ነው። አባቱ ካህኑ ዘካርያስ እና እናቱ ቅድስት ኤልሳቤጥ በጌታ ትእዛዝና ሕግ ሁሉ ያለ ነቀፋ እየሄዱ በእግዚአብሔር ፊት ጻድቃን ነበሩ (ሉቃ. 1፡6)። ይሁን እንጂ ሁለቱም አርጅተው ነበር፣ ኤልሳቤጥም መካን ነበረች። በሰው ዘንድ ተስፋ በተቆረጠበት፣ የእርጅና ዘመን በጫነባቸው ወቅት፣ ካህኑ ዘካርያስ በቤተ መቅደስ ሲያገለግል መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ተገለጠለት። መልአኩም "ጸሎትህ ተሰምቶልሃልና ሚስትህ ኤልሳቤጥ ወንድ ልጅ ትወልድልሃለች፣ ስሙንም ዮሐንስ ትለዋለህ" አለው። ይህ ልጅ ገና በእናት ማኅፀን ሳለ በመንፈስ ቅዱስ የሚሞላ፣ የብዙዎችን ልብ ወደ አምላካቸው የሚያመልስ፣ በኤልያስ መንፈስና ኃይል የሚመጣ ታላቅ ነቢይ እንደሚሆን ተበሠረ።ቅዱስ ዮሐንስ ከተወለደ በኋላ ያደገው በዓለም ቅንጦትና በቤተ መንግሥት ድሎት ውስጥ አልነበረም። ገና በልጅነቱ ወደ በረሃ ወጥቶ፣ የግመል ጠጉር ልብስ ለብሶ፣ የቆዳ
  • ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ

    10 Sept, 20:04

    forwarded from @dn_gosa_tola1224

    + 2019 ዓ.ም እንዴት እንቀበለው? +✍️【በዲያቆን ጐሥዓ ቶላ!!!】እነሆ 2019 ዓመተ ምሕረትን በደጃችን ላይ አግኝተናል። ታዲያ ይህንን የተባረከ አዲስ ዘመን እንዴት እንቀበለው? በምንስ ዓይነት መንገድ ወደ ሕይወታችንና ወደ ነፍሳችን እናስግባው? ​በዓለማውያን ዘንድ እንደሚደረገው በሥጋ መሻት፣ በመብልና በመጠጥ ስካር፣ በከንቱ ሆታና ፈጣሪን በማይከብር ውጫዊ ሽልማት ብቻ አይደለም! ይልቁንስ በንስሐ፣ በጸሎት፣ ልባችንን ለፈጣሪ በመስጠት፣ በይቅርታና ለተቸገሩት የርኅራኄ እጃችንን በመዘርጋት ሊሆን ይገባዋል። አዲስ ዓመትን መቀበል ማለት አዲስ ልብስ መልበስ ብቻ ሳይሆን፣ አዲስና ንጹሕ ልብን ተጎናጽፎ በእግዚአብሔር ፊት መቆም ማለት ነው።አስተውሉ! ዘንድሮ አዲሱ ዓመት በዕለተ ዓርብ ላይ መዋሉ ተራ የቀናት መለዋወጥና ተራ የታሪክ አጋጣሚ እንዳይመስላችሁ፤ እጅግ ታላቅና ጥልቅ የመንፈስ ምሥጢር አለው! ዓርብ ማለት የእኛ የታሪክ መታጠፊያ፣ የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ታላቅ ፍቅር በጎልጎታ መስቀል ላይ የተገለጠበት፣ የሞታችን ደብዳቤ የተቀደደበትና የሰው ልጅ ከኃጢአት ባርነት ነፃ የወጣበት ቅዱስ ዕለት ነው። አዲሱን 2019 ዓመተ ምሕረት በዕለተ ዓርብ መጀመራችን የሚያስተምረን ታላቅ ምሥጢር አለው።ዓርብ የፍቅርና የመስዋዕትነት ቀን ነው። አዲሱን ዘመን ስንጀምር፣ ክርስቶስ በመስቀል ላይ የገለጠልንን ያንን ወሰን የሌለው ፍቅር በልባችን ይዘን፣ እርስ በርሳችን በመዋደድና በመከባበር እንድንኖር ጥሪ ያደርግልናል። አሮጌውን ምቀኝነት፣ ቂም፣ ቁጣ፣ ሐሜትና የኃጢአት ልማድ ከክርስቶስ
    1,560191Open in Telegram
  • ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ

    10 Sept, 18:51

    forwarded from @dn_gosa_tola1224

    + 2018 ዓ.ም አመስግንን እንደ ተቀበልን አመስግነን እንሸኘው +✍️ በዲያቆን ጐሥዓ ቶላ!!!ወንድሞቼና እኅቶቼ ሆይ! የዘመናት ጌታ እግዚአብሔር በጥበቡ ሊመራን፣ በፍቅሩ ሊጎበኘንና በምሕረቱ ሊጠብቀን የሰጠንን የ2018 ዓመተ ምሕረት የሕይወት ጉዞ ልንፈጽም በደጁ ቆመናል። በዚህ ባለፈው ዘመን ውስጥ ብዙ አየን፤ ብዙ ተማርን፤ በደስታው ማዕበል ውስጥ ተደሰትን፤ በሐዘኑና በፈተናው እሳት ውስጥ ደግሞ አልፍን። ነገር ግን አስተውሉ! በዚያ ሁሉ ማዕበልና ፈተና ውስጥ ሳለን፣ ሳያጠፋን በሕይወት አቁሞ ለዚህች ሰዓት ያደረሰን እግዚአብሔር ምንኛ ድንቅና መሐሪ አምላክ ነው!ጻድቁ ኢዮብ በመከራውና በፈተናው ቀን "እግዚአብሔር ሰጠ፤ እግዚአብሔር ነሣ፤ የእግዚአብሔር ስም የተባረከ ይሁን" እንዳለ ሁሉ፣ እኛም የ2018 ዓመተ ምሕረትን ደጉን ብቻ ሳይሆን ክፉውንና መከራውንም ጭምር በልባችን አጽናንተን በእግዚአብሔር ምስጋና ልንሸኘው ይገባናል። ምክንያቱም እውነተኛ የአምላክ ልጅ በደስታው ጊዜ ብቻ ሳይሆን፣ በመከራውና በፈተናውም ቀን ለፈጣሪው ምስጋና ማቅረብን ያውቃል። መከራችን ነፍሳችንን የምታጠራ፣ ትዕቢታችንን የምትሰብር፣ ወደ አምላካችንም አቅፎ እንድንመለስ የምታደርግ ወርቃማ ትምህርት ቤት ናትና።በደስታና በተስፋ የተቀበልነውን ያንን አዲስ ዘመን፣ እነሆ አሁንም በታላቅ ምስጋናና በንስሐ አክብረን እንሸኘዋለን። ምክንያቱም ይህች 2018 ዓመተ ምሕረት ከአምላካችን የተሰጠችን ወርቃማ የታሪክ ገጽ ነበረች፤ ከእንግዲህ በኋላ ግን በዓይናችን አናያትም፣ በወርቅና በብልጽግና ተክሰን ዳግመኛ ልንመልሳት አትችልም።
    1,8601521Open in Telegram
  • ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ

    10 Sept, 16:37edited

    አንተ ብቻ ታመንለት 🙏እግዚአብሔር ለአባቶች የሰጠውን ቃል ኪዳን አላጠፋም። አንተም አትጠራጠረው፡: ረስቶኛልም አትበል። ሀይማኖቴም ስህተት ነው እያልክ አትናገር። ✨እሱ ማንንም አይዘነጋም፣ ታማኝ ነው። በምድራዊ ዘመንህ ባይፈፅመው እንደ ሙሴ ከብሄረ ሙታን አምጥቶህ የገባልህን ቃል ይፈፅማል። አንተ ብቻ ታመንለት። 🕊️min2 https://t.me/Orthodox_Doctrine1 https://t.me/Orthodox_Doctrine1
    1,7002542Open in Telegram
  • ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ

    9 Sept, 17:48edited

    እንሆናለን ያልነው ሌላ ሆነን የተገኘነው ሌላ😔በህይወታችን ውስጥ የተመኘ ነው እንደርስበታለን ብለን እንደ አርዕያ ( success ) ያየነው ማንነት ነበርን🎯።ግብረገብ ያለው ከዝሙት ፣ ከመጠጥ ፣ ከስርቆት ፣ ከሀጢአት የነፃ የሆነ የምንመኘው ማንነት ነበረን🕊️።እለት እለት < እኔ እንዲህ ነው የምሆነው እያልን > ለራሳችንም ለሌሎችም ያወራንለት ማንነት ነበረን📝።ዛሬ ግን ይሃ ማንነት በተቃራኒው ሆኖ ውስጣች ፣ ቤታችን ፣ ማንነታችን እንደቀልድ ተዋሀደን🎭።እንደ ቀልድ ጠጪ ሆንን እንደቀልድ አመንዝራ ሆንን🎭።ትላንት < ሰው እንዴት እንዲህ ያደርግል?🤔 > ብለን እንዳል ነበረዛሬ በዚያ Uጢያት በዚያ ቦታ እኛ ተተክተን ተገኘን።አልተከፋንም ይበልጥ ይሃንን ሃጢያት ለማሻሻል ጠንክረን ተነሳን💪።የጎደሉን የሀጢያት ስራዎች ለማከናውን ከወዳጅ እቅድ አወጣን ከጓደኛ ተማከረን ለነብስ ከሚጠቅመን ይልቅ ለስጋ ፈላጐት የሚበጀን ነድፍ ሀሳብ አዋቀርን📊።
    1,9802241Open in Telegram
  • ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ

    9 Sept, 09:37

    forwarded from @dn_gosa_tola1224

    ┼ በኃጢአት አለመሸነፍ!!! ┼✍️ዲያቆን ጐሥዓ ቶላ!!!ወዳጆቼ! በዚህ አላፊና ፈተና በበዛበት ዓለም ውስጥ ስትኖሩ፣ የነፍሳችሁን ሰላም የሚያደፈርሰውና ከፈጣሪያችሁ የሚለያችሁ ትልቁ ጠላት ውድቀት ሳይሆን በኃጢአት ተሸንፎ መቅረት ነው። መውደቅ የሰው ልጅ ድካም ነው፤ ወድቆ መቅረት ግን የጠላት ዲያብሎስ ፈቃድ ነው። ተነሥቶ መታገልና መመከት ግን የመንፈስ ቅዱስ አሠራርና የሰማያውያን ነፍሳት ታላቅ ግብራቸው ነው። ኃጢአት በሰው ልጅ ተፈጥሮ ውስጥ ያለ አካል ሳይሆን፣ በፈቃድ ድካም ምክንያት የሚመጣ ጊዜያዊ ጨለማ ነው።ኃጢአት ሲቀርብ እንደ ማር ይጣፍጣል፤ ሲፈጸም ግን እንደ እባብ በመርዝ ነፍስን ይገድላል። ከመፈጸሙ በፊት "አምላክ መሐሪ ነው፤ በኋላ ንስሐ ትገባለህ" እያለ ያታልልሃል፤ ከተፈጸመ በኋላ ደግሞ "ኃጢአትህ እጅግ ከብዷል፤ እግዚአብሔር አይምርህም" እያለ ወደ ተስፋ መቁረጥ ገደል ይገፋሃል። ​ነገር ግን! በእግዚአብሔር የምሕረት ባሕር ፊት የሰው ልጅ ኃጢአት ሁሉ ወደ ውቅያኖስ እንደወደቀች ትንሽ የእሳት ፍም ናት። ውቅያኖሱ ፍሟን አጥፍቶ ያጥላላታል እንጂ ፍሟ ውቅያኖሱን ልታቃጥለው አትችልም። ስለዚህ የኃጢአትህ ታላቅነት ሳይሆን የእግዚአብሔር የምሕረቱ ስፋት ይበልጣልና ተስፋ አትቁረጥ።ወዳጄ! ሰው የማያየኝ ቦታ ነው ብለህ የምትሠራው ኃጢአት ነፍስህን በስውር ያቆስላታል። ሰው ባያይህም፣ ፍጥረታትን ሁሉ በክንዱ የያዘ አምላክ ያይሃል። በሰው ፊት ከመፈርደስ ይልቅ በእግዚአብሔር ፊት በሚደረግ ንጹሕ ንስሐ ቁስልህን ታከም። የወጣትነት ደምና ምኞት እንደ ማዕበል በሚናወጥበት ጊዜ፣ ፈቃደ
    2,060163Open in Telegram
  • ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ

    7 Sept, 20:28

    forwarded from @dn_gosa_tola1224

    + ከሩፋኤል አሳድገኝ እስከ ሩፋኤል ይቅር በለኝ +✍️በዲያቆን ጐሥዓ ቶላ የተጻፈ!!!በጳጉሜን ማለዳ የደመናው ድምፅ ሰማዩን ሲያናውጠውና የዝናቡ አንጠብጣቢ በቆርቆሮው ላይ የተለየ ዜማ ሲደረድር፣ የልጅነት የዋህ ልባችን በፍስሐ ይሞላል። እግራችን በጭቃ እየተንሸራተተ፣ የብርድ ወጋግራ ሳይበግረን፣ በየመንደሩ ሰንደቅ ዓላማ መስለን ራቁታችንን እየሮጥን የሰማዩን በረከት በሰውነታችን ላይ ለመቀበል እጆቻችንን ወደ ሰማይ እንዘረጋለን። ከሰማይ የሚወርደውን እያንዳንዱን የዝናብ ጠብታ እንደ ሰማያዊ መና፣ እንደ ሰሊሆም ጠበል እየቆጠርን በሕፃንነት አፋችን የምንጮኸው ያ ቀጭን ድምፅ ዛሬም ድረስ በሰማያት ያስበተናል፦ “ሩፋኤል አሳድገኝ! እንደ ታላቆቼ አድርገኝ!” እያልን ከዝናቡ ጋር የተጫወትነው ያ ዘመን፣ ምንም ዓይነት የኃጢአት ዕድፍ ያልነካው የንጹሐን መንደር ነበር። የውኃውን ጣዕም እንደ መና እየቀመስን፣ በጭቃው ላይ እየተንከባለልን፣ የቅዱሳን መላእክትን ጥበቃ ያለ ምንም መጠራጠር የተቀበልንበት ያ የልጅነት ዘመን የትኛውንም ድንጋይ ልብ በትዝታ የማንበርከክ ታላቅ ኃይል አለው።ያን ጊዜ በየዋህነትና ባለማወቅ የፈጸምናቸው መንፈሳዊ ልማዶች፣ አድገን የመጻሕፍትን ምስጢር ስንመረምር፣ የእግዚአብሔርን ታላቅነትና የመላእክቱን አገልጋይነት ስንረዳ ድንቅ በሆነ የዕውቀት ብርሃን አበቡ። “ሩፋኤል” ማለት “እግዚአብሔር ፈዋሽ ነው” ማለት እንደሆነ፣ የዓይነ ሥውሩን የጦቢትን ዓይን ያበራ፣ በውቅያኖስ ደሴት ላይ የተሠራችውን ቤተ ክርስቲያን ከጋኔን ወከባ ያዳነ፣ የቤተ ሳይዳን ውኃ እያናወጸ ሕሙማንን የፈወሰ
    1,7401242Open in Telegram
  • ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ

    7 Sept, 11:48

    forwarded from @dn_gosa_tola1224

    📜ቅዱስ ሩፋኤል እና ነገረ ጳጕሜን ፫!!!📜✍️【በዲያቆን ጐሥዓ ቶላ የተጻፈ】ዓለም ሳይፈጠር፣ ጊዜያት ሳይቈጠሩ፣ ብርሃን ከብርሃን ሳይለይ አምላካችን እግዚአብሔር በአምላካዊ ፈቃዱ ሰማያትንና በውስጣቸው የሚኖሩ የብርሃን ሠራዊትን ፈጠረ። ከእነዚህም የብርሃን ዓለማት መካከል ሰማየ ሰማያት በሆነችው ቅድስት መንበሩ ዙሪያ፣ አእላፋት መላእክት በፍርሃትና በወዛደር እየተንቀጠቀጡ የእግዚአብሔርን ታላቅነትና ቅድስና ያመሰግናሉ። በእነዚህ ሁሉ ሰማያውያን ሠራዊት መካከል እግዚአብሔር በጸጋው አክብሮ፣ በቅድስናው አስጌጦ፣ በከፍተኛው የመላእክት ማዕረግ ላይ ከሾማቸው ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት አንዱና ሦስተኛው ገናናው መልአክ ቅዱስ ሩፋኤል ነው።ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሩፋኤል "መናብርት" (ዙፋናት) በሚባሉት የከበሩ ሰማያውያን መላእክት ነገዶች ላይ አለቃና መሪ ሆኖ የተሾመ ታላቅ አባት ነው። መናብርት የተባሉት መላእክት፣ የእግዚአብሔር የእግዚአብሔርነቱ ግርማና ክብር የሚያርፍባቸው፣ የመለኮት ምሥጢር የሚገለጥባቸው ሰማያውያን የክብር መንበሮች ናቸው። ቅዱስ ሩፋኤል በእነዚህ የብርሃን ሠራዊት ላይ በመሾም፣ በፍቅሩና በየዋህነቱ እየመራቸው፣ ወደ ፈጣሪ መንበር አብሮአቸው የሚቆም ሰማያዊ መኰንን ነው። መጽሐፍ "ከሰባቱ የከበሩ መላእክት አንዱ እኔ ሩፋኤል ነኝ" ብሎ እንደተናገረ፣ በእግዚአብሔር ፊት ዘወትር የመቆምና የመቅረብ ልዩ ባለመብትነት የተሰጠው ሊቀ መላእክት ነው።ሙሉውን ለማንበብ..........
    Image from a post by ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮImage from a post by ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮImage from a post by ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ
    2,0001732Open in Telegram
  • ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ

    7 Sept, 09:31

    "አዲስ ዓመት የተባለው ቀን መቁጠሪያ አዲስ ስላለው ነው ወይስ በእርግጥ በሕይወታችሁ ውስጥ አዲስ ዓመት ስለሆነ ነው? ከተመሳሳይ ልማዶች፣ ከተመሳሳይ ጠባይና ከተመሳሳይ ስህተቶች ጋር የምትገቡበት ከሆነና በውስጣችሁ ያለውን ነገር ሳትቀይሩ የምትቀበሉት ከሆነ እንዴት አዲስ ዓመት ሊሆን ይችላል? ስብእናችሁ በእነዚህ የተለዩ መንገዶች እንዲደነዝዝ አታደርጉትምን!?በዚህ አዲስ ዓመት ለተሻለ ኑሮ አንድ ተግባራዊ እርምጃ እንኳ መራመድ አለብኝ ብለህ ብትንቀሳቀስ ....በአዲሱ ዓመት ለእግዚአብሔር ስእለቶችህን፣ ቃል ኪዳኖችህንና መሀላዎችህን ብቻ አትደርድርለት፤ እነዚህ ሁሉ ከአንተ ፈቃድና ጥንካሬ በላይ ናቸውና፡፡ ይልቁንም ድካምህን ሳትዘነጋ ፍላጎቶችህን ሁሉ ሰብስበህ ለእግዚአብሔር በጸሎትህ ውስጥ አቅርብለት፡፡ በራስህ ችሎታ ላይ በመደገፍም እነዚህን ቃል ኪዳኖች አትግባ!ራስህን ለተሻለ ሕይወት እንደምትቀይር አድርገህ ለእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ከምትገባለት ይልቅ እርሱ ለተሻለ ሕይወት ይለውጥህ ዘንድ ከእርሱ ቃል ኪዳን ተቀበል።"(አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ- የሕይወት ልምድ ገጽ 29 በአያሌው ዘኢየሱስ የተተረጎመ)
    1,860117Open in Telegram
  • ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ

    6 Sept, 08:45edited

    አበባን_በሜዳአበባን በሜዳ የሚያፈካ ዘመንን በዘመን የሚተካ የሚለውጥ በጋ ክረምትን እግዚአብሔር ይምስገን/2/ወራትን በክረምት አሰናድቶ አሮጌውን ዘመን አሰናብቶ ፀሃይን በግዚያቱ ድንቅ ነው እግዚአብሔር ለፍጥረቱ/2/ሰማይን በደመና ታልብሶ ምድርን በነጠብጣብ አለስልሶ ልምላሜን የሰራው በግዚያቱ መጋቢ ነው አምላክ ለፍጥረቱ/2/አበቦች በተራራ ሲያበሩ አእዋፍ ለክብሩ ዘመሩ ፀሐይም በሰማይ ስተወጣ
    2,730file11Open in Telegram