gram news
✟ ኦርቶዶክሳዊ ሥነ-ጹህፎች ✟ channel avatar

✟ ኦርቶዶክሳዊ ሥነ-ጹህፎች ✟

@orthodoxawi_gtm

╭━─━─━─ ➻ በዚህ ቻናል የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ያን አስተምሮን እና ሥርዓትን የጠበቁ መንፈሳዊ ግጥሞችን፣ መነባንቦችን፣ ትረካዎችን፣ ዜናዎችን ፣ደብዳቤዎችን፣ ትምህርታዊ ጹሑፎችን፣ ብሂለ አበው፣ ከመጽሐፍት ዓለም እና ሌሎችም ''መንፍሳዊ ሥነ-ጹሑፎችን'' ያገኛሉ። . . . ለማስታወቂያና ሃሳብ አስተያየትን ወይም ቻናሉን በተለያዩ መንፈሳዊ ስነ-ጹሑፎች ለመደገፍ 👇 @YOHANNES_2421 ላይ አድርሱን።

ProjectsENReligion

33,600subscribers

Open the Channel

Latest posts

  • ✟ ኦርቶዶክሳዊ ሥነ-ጹህፎች ✟

    22 Sept, 06:04edited

    ቅዱስ ሚካኤል✍በክንፋህ ከልለኝ ከዓለሙ ጥፋትልቤን አያውረው ቅናት ና ክፋትኃጢያትን አላብዛ ከደጀህ እርቄበበደል አልኑር ሚካኤል አባቴአንተ ከፊት ምራኝ በጉዞዬ ሁሉወድቄ እንዳልቀር አደራ አባቴእጄን እንዳትለቀው ከጥፋቱ ስፍራእንድኖር አግዘኝ በመልካም ጎዳናከኔ እንዳትለይ በይተኛውም ስፍራ
    1,74019844Open in Telegram
  • ✟ ኦርቶዶክሳዊ ሥነ-ጹህፎች ✟

    22 Sept, 05:28edited

    ሚካኤል ❤️❤️❤️የአክናፋቱ መራገቢያ ከሀገር ምድሩ የሚሰፉ የፃድቃንን የዘውድ አክሊል በምስጋና የሚደፉ አካላቱ ማይዳሰስ ከንፋሳት የረቀቁ በምን ጥበብ ተመስጥረው ሰው ማቀፍን አፈለቁ ቸርነቱ ሰርክ እንዳዲስ ደሃ ለቅሶን የሚሰማ አቤት ፍቅሩ አቤት ደስታው በደጃፉ ላደኩማ ሲባርከኝ ሚካኤል ስል ሲያስተምረኝ ያምላኩን ቃል ስለምነው ሁሌም እኔን ከአምላኩ ጋር ያስታርቃል በፈተና የሚያፀናኝ በችግሬ የማላጣው በድዬ ሲያይ ሚንገበገብ ሚያስገመግም ሀይለ ቁጣው
    1,51011742Open in Telegram
  • ✟ ኦርቶዶክሳዊ ሥነ-ጹህፎች ✟

    22 Sept, 05:28edited

    አስቸገርኩክ አይደል🥹አስቸገርኩ አይደል ፍሬ አልባ ሆኜቀን በቀን ስበድል ኃጢያቴን አብዝቼከህግ ስወጣ ትዛዝህን ትቼአንተ በይቅርታ ስታልፈኝ እያየህአስቸገርኩ አይደል ፍቅርህን አርክሼአንተ ስትምረኝ አልመለስ ብዬየሞትክልኝ ሞት ዋጋህን አቅልዬእግሬን ስትከተል እንደ ቀልድ እያየሁልክ እንደ ይሁዳ እኔ እየበደልኩ
    1,400108321Open in Telegram
  • ✟ ኦርቶዶክሳዊ ሥነ-ጹህፎች ✟

    21 Sept, 03:37

    በማርያም ጣት✍ ገጣሚ ህሊና ደሳለኝ📢በየቀኑ ኦርቶዶክሳዊ ሥነ-ጹህፎች ለማግኘት ቻናላችንን ይ🀄️ላ🀄️ሉ 👇👇 💚 @orthodoxawi_gtm 💚 💛 @orthodoxawi_gtm 💛 ❤️ @orthodoxawi_gtm ❤️ ይ🀄️ላ🀄️ሉ👆👆🤍
    2,029file17773Open in Telegram
  • ✟ ኦርቶዶክሳዊ ሥነ-ጹህፎች ✟

    21 Sept, 03:37

    በማርያም ጣትእኔ ብናኝ ማረፊያ አልባ እውድቅት ምሽግ ያጣሁ ስለ ግፌ መማለጃ የማርያም ጣት ይዤ መጣሁ የእናትህ ስም የሽፈነው አንድ የቀረኝ ድንግል ስጋ አንድ የቀረኝ ታማኝ አካል ዛሬም ደጅህ ተጎናብሶ በእንባ ልውስ ምሕረት ያካል ስሜ ሀገር መልኬ ቅድስት ልጆቼ እሾህ ግብሬ አጋም ዛሬስ ችዬ እኒን እጆች ወደ ስምህ አልዘረጋም አላነሳም እጄን ችዬ ልለማመን አቅም የለኝም ለግፍ ነውሬ ምህረት እንጂ ካንተ ፍትህ አልመኝም ቀና እንዳልል ሀዘን ሰብቆኝ ከደጅህ ስር ተንበርክኬ መሬትህን በህንባ አጥባለው በማርያም ስም ምልጆ ልኬ ጨቅላዎቼን ቀብሪያለው የስስቴን ሳልጠግባቸው ጀግናዎቼን ሽኝቻለው ትኩስ ሀፈር ጭኜባቸው የሞት ክምር ያስቆጠረኝ የግፍ ድርድር የቃኘሁት እጆችህን እሚገፍ ምን ሀጢያት የሰራሁት መሀፀኔ ተባረከ ከበርኩኝ ስል በስፍራቸው በጥል ፍቅሬን አመከኑት ፍሬዎቼን ምንላርቸው
    1,90018555Open in Telegram
  • ✟ ኦርቶዶክሳዊ ሥነ-ጹህፎች ✟

    21 Sept, 03:28edited

    🔴"ከመስቀል ስር ያለች መስቀል "●በገጣሚ ህሊና ደሳለኝ♦️"ከመስቀል ስር ያለች መስሸል" ................................................. በአይሁድ ህሊና ያልታቀደ ህማም ያልታሰበ ስቃይ፣ ይኸው መስቀሉ ስር ይኸው እግሮቹ ላይ። ዮሀንስ አልቅሶ ሙሾ ያልደረተለትበልቡ ርህራሄ፣ ያልተደመጠ ሞት ያልተወጀ ቅጣት ያልተሰማ ኤሎሄ። አባሽ ያጣቁስል አይዞን ያጣ ወዮ፣ አዲስ ጎለጎታ አዲስ ቀራንዮ። በፅሞና ችንካራ ህማም ሲንቀለቀል፣ ይኸው መስቀሉ ስር የወደቀች መስቀል። የዚህ ሰው እናቱ.............................📢በየቀኑ ኦርቶዶክሳዊ ሥነ-ጹህፎች ለማግኘት ቻናላችንን ይ🀄️ላ🀄️ሉ 👇👇 💚 @orthodoxawi_gtm 💚 💛 @orthodoxawi_gtm 💛
    1,690file18421Open in Telegram
  • ✟ ኦርቶዶክሳዊ ሥነ-ጹህፎች ✟

    19 Sept, 13:15edited

    መስቀሉ በፊቴየቀራኒዮ አርማ የፍቅር ሰሌዳ የሰላም ብራና ቀለሙን የቀዳ የድህነት ማህደሯ ጠቋሚ መሪዋ እንቅፋት ነቃፊ አዳኝ ጠባቂዋ የሰማዩ ንጉስ ስጋው ቆርሶባት ደሙን አፍስሶ ላቡን ደቅኖባት የትውልድን አረም ሊነቅል ከስሩ ባሪያውን መስሎ ወረደ ከክብሩ። ኤሎሄ ብሎ ጮኸ አምላክ ሆኖ ሳለ የጠላትን መንግስት ንዶ እየጣለ ደብዳቤውን ደምስሶ በችንካሩ ፋቀው የዕዳው ፅሕፈት በደሙ ጠረገው። በመስቀል የዋለ ጎልጎታ ያደረ እባቡን ቀጥቅጦ አዳምን የማረ ሄዋንን ከጭንቀቷ ጎትቶ ያወጣት ልጆቿን ከሲኦል አትርፎ ከእሳት በመስቀሉ ገፅ በችንካሩ ጫፍ በእሾህ አክሊል ብሳት በከሳሾቹ አፍ
    2,330267641Open in Telegram
  • ✟ ኦርቶዶክሳዊ ሥነ-ጹህፎች ✟

    19 Sept, 13:15edited

    ✝የደመራው መስቀል✝ይሄ ደመራ ነው ደመራውም የእሳት ዘመኑ የጎረምሳ ያውም የትኩሳት አልፎ አልፎ አልፎ ሳስታውሰው መስቀልን እንደሰው እድሜ ይመስለኛል ቆሞ ሚለኮሰው ተስፋዬ እንደመሸ እድሜዬ እንደኮሰሰ ስንቴ ችቦ በርቶ መስቀል ተቶከሰ አልፎ አልፎ አልፎ ሳስታውሰው ስንት ዘመን መሽቶ ስንት ዘመን ነጋ ስንት ያስተናገድኩት የህይወትን በጋ ስንቱን ነገር ተውኩት ስንት ነገር ተወኝ ስንቱስ ተራምጄ ስንቱስ ተራመደኝ የህይወትን ክረምት እሰከምሻገረው እስከ ሚሻገረኝ ዘንድሮም ዘንድሮም በደመራው ምክንያት ቆሞ በሚነደው ስንቱን አስታወስኩት🤔 አላባራም ዝናብ ጭቃ ጉዌት ለኮ መስኩ አላበበም ጭቃው መቼ ደርቆ አልፈነዳም አደይ ሜዳው አላበበም የቱ ነው አዲስ አመት ገና ነው አልጠባም
    2,14014653Open in Telegram
  • ✟ ኦርቶዶክሳዊ ሥነ-ጹህፎች ✟

    18 Sept, 08:05

    አምላኬ መልሰኝ🥹አምላኬ መልሰኝ ወደ ልጅነቴያ የደጉ ዘመን ያ የፍቅሩ ጊዜተንኮል የሌለበት ንፁ ነው ልጅነትከኃጢያት የራቀ ክፋትን የናቀልቡ የተሞላ በመልካሙ ፍሬነበረ ልጅነት የደግነት ማያአምላኬ መልሰኝ አድጌ ቆሸሽኩኝያ አንተን ንፁ ፍቅር ትቼ በዓለም ተሸነፍኩኝበኃጢያት ጎዳና እግሬ ተረማምዶ
    2,88030221097Open in Telegram
  • ✟ ኦርቶዶክሳዊ ሥነ-ጹህፎች ✟

    17 Sept, 05:36edited

    መስከረም አቅጄ •••• በሞራል ሞልቼ ጥቅምትን አስቤ•••• ለመስራት ወጥቼ ህዳር ላይ ደርሼ•••• ልሰራ አሰብኩና ታህሳሰን መረጥኩኝ•••• መንገዴን ላቀና ጥምቀት ደርሷል ብዬ•••• ጥርን ትቼ አለፍኩ የካቲት ልዘጋጅ •••• ብዬ ራሴን ሸወድኩ መጋቢት ፀሀዩ•••• ከብዷል ልሻገር ሚያዚያ ደረሰ•••• ፋሲካን ላክብር ግንቦት ደብሮኛል •••• ቆይ ትንሽ ልፍታታ ሰኔ ዘነበብኝ •••• ልጠለል ለአንዳፍታ
    3,740661710853Open in Telegram
  • ✟ ኦርቶዶክሳዊ ሥነ-ጹህፎች ✟

    15 Sept, 04:25

    ✝️ መስቀል ነዉ ሀይላችን ✝️ምድር ሊያፀዳት፥ከሀጢያት ክምር በደል የሌለበት፥አንድ እግዚአብሔር ለሰዉ ልጆች ሁሉ፥በሰጣቸዉ ተስፋ በዘመን ፍፃሜ፥ሞትን ሊያጠፋእንደተናገረዉ፥ቃል ከሰማይ ወርዶ ንፅህይት ከሆነችዉ፥ከማርያም ተወልዶ ሰላሳ ሶስት አመት፥ተገልፆ በምድር ሀገር እየዞረ፥ወንጌልን ሲያስተምር ህሙማ'ነ ስጋን፥ሲፈዉስ በታምር ህሙማ'ነ ነፍስን፥ያድናቸዉ ነበር በእዉነተኛ ፍቅርእንዲህም እያረገ፥ሲያበራት ምድርን እሷ በምላሹ---ስታዘጋጅለት፥ስቃይ እና ሞቱን ደጋግማ ስትነክስ፥ያበላት እጁን እሱ ይፀልያል---እሱ ይፀልያል፥ስለሷ ሰላም ሁሉን ይቅር ይላል፥በእመብርሀን ስም፤
    4,0104011552Open in Telegram
  • ✟ ኦርቶዶክሳዊ ሥነ-ጹህፎች ✟

    13 Sept, 17:20

    የመስቀል በዓል ግጥም !( ርዕስ - ለሚፈሩህ ምልክትን ሰጠሃቸው )ከይሴ…….ተኩላ…….እባቡን ሊያንቀጠቅጡ የጥንቱን ጠላት የዘራውን ሊያሳጭዱት ………….በኃይለ መስቀል ወጥረው ሊቀጡ!ኃይልን ሰጠሃቸው…. የጨለመውን ሊያበሩ የጎበጠን ሊያቀኑ ጋኔንን ሊሰድዱ..….ህሙምን ሊያድኑ!ሥልጣን ሰጣሃቸው…… አንተ በሞትህበት..…..በተመሰቀለው እንጨትህ ልጆችህ ልጅ ልጆችህ… የኃይልህ መገለጫ ደም የፈሰሰበት ልዩ ፍቅርህ ሥልጣን ሆኗቸዋል…..ሰለጠኑበት…ዲያቢሎስን ኃይል ሆኗቸዋል ……አየሉበት……...ፀራቸውን መድኃኒት ሆኗቸዋል...ተፈወሱበት…ደዌያቸውን!
    6,880297531Open in Telegram
  • ✟ ኦርቶዶክሳዊ ሥነ-ጹህፎች ✟

    13 Sept, 08:40

    +የመስቀል ሥነጽሑፍ - የመስቀል ፍቅር ! !( የመስቀሉ ፍቅር )የመስቀሉ ፍቅር_ ላለ በልባቸው በባዕዳን ምድር_ ሆኖ መኖሪያቸው የእምዬ ኢትዮጵያ_ ሥርዓት ለራባቸው እነሆ ደስታ_ እዛው ሄደላቸው።የተዋሕዶ ፍሬ_ አበው ያስተማሩት ወንጌልን የሚሰብክ _ በረጋው አንደበት ዶግማና ቀኖናን _ ትውፊትን ሊያስተምር እነሆ ተገኘ_ በጣሊያን ምድር።የነጮቹ ዕርስት_ ሮማ ኢጣሊያ ጴጥሮስ ወ ጳውሎስ_ ያሉብሽ ሃሌ ሉያ የሐዋርያቱ ደም _ ጎርፉ የወሰደሽ መቼም አትረሺም_ በቀደመው ስራሽ።እንኳን ደረሳችሁ_ ለመስቀል በዓል
    4,280287541Open in Telegram
  • ✟ ኦርቶዶክሳዊ ሥነ-ጹህፎች ✟

    13 Sept, 08:40

    የመስቀል ሥነጽሑፍ !!( መስቀል ኃይላችን ነው )የነገር መስቀሉን መነሻ የታሪኩን መዳርሻ መርምራ ለማወቅ ብትሻ እመቆስጠንጢኖስ ንግስት እሌኒ ተደብቋት መቼ ቀረ ምስጢር ሆኖ እንደተቀበር፡፡ በባዕድ ሃገር በኢየሩሳሌም ሐይማኖቷን ደብቃ ለእውነት ተነስታ ፀንታ ታጥቃ ተራ ሰው መስላ ራሷን ንቃ መስቀሉን አስቀድማ ስታስፈልግ በገጠር በከተማ ኪራኮስ እስራኤላዊው በአምላክ ቃል እያፅናናት የመስቀሉን ቦታ እየመራት ደመራውን ደምራ
    3,160117621Open in Telegram
  • ✟ ኦርቶዶክሳዊ ሥነ-ጹህፎች ✟

    13 Sept, 08:39

    ሥነጽሑፍ - የደመራ ግጥም !( ርዕስ - የደመራ ዓመት )መስቀል የከበረው ትናንት መስሏቸው ያዩ ተገረሙ ክብሩ አስደንቋቸው ትናንትና አይደለም የበራው ደመራ ዘንድሮ ዓመት ፈጀ የመስቀሉ ሥራስንት አይሁድ ተነሥተው መስቀሉን ቀበሩ? ስንትስ እሌኒዎች ሊያወጡት ቆፈሩ? ጅጅጋ ሲዳማ ውጡ ተናገሩቤተ ክርስቲያን ልክ እንደ ደመራ በእሳት ተለኩሳ ደምቃ ስታበራ ካህናት ምእመናን እንደ ችቦ ነድደው ስንቴ አከበሩት ለመስቀሉ ታርደው?ስንት ጊዜ አፏጨ ዲያቢሎስ ተቆጣ ስንት ሟርት ተሰማ ስንት ቁጣ መጣ?
    3,920187551Open in Telegram
  • ✟ ኦርቶዶክሳዊ ሥነ-ጹህፎች ✟

    12 Sept, 06:20edited

    + አንገት ተቆርሶ የተከበረ ልደት +በመጽሐፍ ቅዱስ ልደት ያከበሩት የግብፁ ንጉሥ ፈርዖንና የይሁዳው ገዢ ሄሮድስ ናቸው:: እርግጥ ነው ልደትን ማክበር በአሕዛብ ነገሥታት ቢዘወተርም የሚነቀፍ ነገር አይደለም:: ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱስም የሚጀምረው የሰማይና የምድርን ልደት በሚተርከው "ኦሪት ዘልደት" ነው:: "እግዚአብሔር አምላክ፥ ሰማይንና ምድርን ባደረገ ቀን፥ በተፈጠሩ ጊዜ፥ የሰማይና የምድር ልደት ይህ ነው" (ዘፍ. 2:4)ትልቅዋ አፈር መሬት በሰባት ዓመት ማረፍዋን አይተን እኛም በሰባት ቀን እንደምናርፍ የምድርን ልደት መተረክ አይተን ልደታችንን ብናከብር ክፋት የለውም:: (Microcosm /ንዑስ ዓለም/ እንዲል ቴዎሎጂ) የመድኃኔዓለምን ልደት ከፍ አድርገን የብዙ ቅዱሳንን ልደት ደግሞ እንዲሁ በቤተ ክርስቲያን ማክበራችን ልደት አንዱ እግዚአብሔርን ማመስገኛ ቀን ስለሆነ ነው:: ከኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት አንዳንዶቹ ደግሞ የልደቴ ቀን ብለው የሚያከብሩት ለዳግም ልደት ክርስትና የተነሡበትን ቀን ነው::በዛሬው ዕለት ሔሮድስ ያከበረው ልደት ግን እጅግ የተረገመው ልደት ነበር:: ተጋባዦቹ የንጹሕን ሰው ደም የጠጡበት ልደት ሔሮድያዳ እንደ ታላቂቱ ባቢሎን "በሰማዕቱ ደም ሰክራ" የዋለችበት የልደት ግብዣ ቀን ነበር::በዚህ ልደት የተቆረሰው ኬክ አይደለም:: በዚህ ልደት እፍ ተብሎ የጠፋው ሻማ አይደለም:: በሰይፍ ተቆርሶ በሰሃን የቀረበው ከሴት ከተወለዱት ሁሉ የሚመስለው የሌለ ቅዱስ ሰው አንገት ነበር:: በሻማ ፈንታ የጠፋው ክርስቶስ "እርሱ የሚያበራ መብራት ነበር እናንተም ጥቂት ዘመን
    4,270308642Open in Telegram
  • ✟ ኦርቶዶክሳዊ ሥነ-ጹህፎች ✟

    12 Sept, 06:20

    Image from a post by ✟ ኦርቶዶክሳዊ ሥነ-ጹህፎች ✟Image from a post by ✟ ኦርቶዶክሳዊ ሥነ-ጹህፎች ✟
    3,580161153Open in Telegram
  • ✟ ኦርቶዶክሳዊ ሥነ-ጹህፎች ✟

    11 Sept, 07:30edited

    ቅዱስ ዮሐንስ፡ ርእሰ ዐውደ ዓመት መ/ር ጌታቸው በቀለ
    4,330138543Open in Telegram
  • ✟ ኦርቶዶክሳዊ ሥነ-ጹህፎች ✟

    11 Sept, 07:30

    ቅዱስ ዮሐንስ፡ ርእሰ ዐውደ ዓመት መ/ር ጌታቸው በቀለ ዘመን አልፎ ዘመን ሲተካ የመሸጋገሪያው ዕለት በየዓመቱ “ቅዱስ ዮሐንስ” እየተባለ ይጠራል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የዘመን መለወጫ፣ ዕንቁጣጣሽ፣ ርእሰ ዐውደ ዓመት ይባላል፡፡ ርእሰ ዐውደ ዓመት የበዓላት ሁሉ የበላይ፣ ራስ ማለት ነው፡፡ ይህ በዓል የዓመት መጀመሪያ እንደመኾኑ መጠን በየዓመቱ ወሮች በመጀመሪያ ቀን ይከበራል፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ ለምን ተባለ? ቅዱስ ዮሐንስ ተብሎ የተሰየመው በነቢዩ ዘካርያስ ልጅ በመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ እንጂ በሐዋርያው (ወንጌላዊው) ቅዱስ ዮሐንስ አለመሆኑን ልብ ማለት ይገባል፡፡ ነገሩ እንዲህ ነው፡- ቅዱስ ማርቆስ ወንጌሉን ሲጽፍ “የእግዚአብሔር ልጅ የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል መጀመሪያ እነሆ መንገድህን የሚጠርግ መልእክተኛዬን በፊትህ እልካለሁ፡፡ የጌታን መንገድ አዘጋጁ፡፡ ጥርጊያውን አቅኑ” እያለ “በምድረ በዳ የሚጮኸ ሰው ድምፅ” ተብሎ በኢሳይያስ እንደተነገረ የነቢዩ ዘካርያስ ልጅ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ በዘመነ ብሉይ መጨረሻና በዘመነ ሐዲስ መጀመሪያ ላይ ተነስቶ “መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ!” እያለ ስለ ክርስቶስ አዳኝነት እየመሰከረ በምድረ በዳ የንስሐን ጥምቀት እያጠመቀ መጣ ብሎ ለዘመነ ወንጌል የመጀመሪያ ምዕራፍ ትምህርትና ተግሳጽ እንዳደረገው ቅዱስ ማርቆስ በወንጌሉ ይነግረናል፡፡ /ማር. ፩1፥፲፬፤ ኢሳ. ፵፥፫-፬/፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ በመጨረሻም በሄሮድስ ትዕዛዝ ራሱን የተቆረጠ ታላቅ ሰማዕት ነው፡፡የመጥምቁ ዮሐንስ ተግባር ለዘመነ ወንጌል በር ወይም መነሻ ሆኖ መገኘቱን በመረዳት የቤተ
    3,31013544Open in Telegram
  • ✟ ኦርቶዶክሳዊ ሥነ-ጹህፎች ✟

    11 Sept, 04:22edited

    ስንቶች ወተው ቀርተዋል ስንቶች የአልጋ ቊራኛ ሆነዋል እኛ ግን በቸርነቱ እዚህ ደርሰናልን ! 2018ትን አሰጀምሮ ላሰጨረሰን ለልዑል እግዚአብሔር ክብርና ምሰጋና ለእርሱ ይሁን አሜን።🙏❤✟ ኦርቶዶክሳዊ ሥነ-ጹህፎች ✟
    Image from a post by ✟ ኦርቶዶክሳዊ ሥነ-ጹህፎች ✟Image from a post by ✟ ኦርቶዶክሳዊ ሥነ-ጹህፎች ✟
    2,9302615943Open in Telegram