Latest posts

ምስባከ ጳውሎስ (Paul's Pulpit)
21 Sept, 13:50
https://youtu.be/vPCNlfNURzAYouTubeሲኦል ምንድን ነው?በርካታ ሰዎችና አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ሲኦልንና ገሃነምን አንድ ያደርጓቸዋል። ስለ ገነትም ገራ መጋባት በስፋት ይስተዋላል። ለመሆኑ ሲኦል ምንድን ነው? ገሃነም እና ገነትስ? ይህ ቪዲዮ በጉዳዩ ላይ መለስተኛ ግንዛቤ ለመስጠት ይሞክራል።
ምስባከ ጳውሎስ (Paul's Pulpit)
20 Sept, 03:04
https://youtu.be/dZvXtc2kvCs?si=HHG4tHyWDe63_XVHYouTubeጳውሎስ ፈቃዱ - "ሐዋሪያው ጳውሎስ ደፍሮ ያልተናገረውን ደፍሬ አልናገርም፡፡" discussion with Paulos fekaduThis wasn’t just a conversation about theology. In this exclusive LiiPod interview, we go beyond the theologian and get to know Paulos Fekadu , the lessons he’s learned through marriage, parenting, life, and his own journey of faith. We talked about poetry…
ምስባከ ጳውሎስ (Paul's Pulpit)
17 Sept, 06:16edited
ከጥሩ እራትም፣ ከጥሩ አዳርም በኋላ አመስግኗት!https://www.tiktok.com/@paulosfekadu/video/7686234802944625942?is_from_webapp=1&sender_device=pc
ምስባከ ጳውሎስ (Paul's Pulpit)
16 Sept, 10:19edited
ስለ ሰይጣን አወዳደቅ - 3ስለ ሳጥናኤል አወዳደቅ ከዚህ በፊት ሁለት አሳቦችን አንሥቼ ነበር። የመጀመሪያው አሳቤ፣ ሳጥናኤል የወደቀው ከሰው መፈጠር በኋላ ስለ መሆኑ ለማስረዳት የሚሞክር ነበር። ሌላው አሳቤ ግን የሳጥናኤል ቀዳሚ ኀጢአት ዘፍጥረት 3 ላይ የተጠቀሰው ሊሆን እንደሚችል ጥርጣሬ እንዳለኝ የሚጠቁም ብቻ ነበር። ከዚያ ውጭ ሳጥናኤል አዳምንና ሔዋንን በኀጢአት ሊጥላቸው የተነሣው በምን ምክንያት ይሆን? የሚል ጥያቄ ሁሌም በአእምሮዬ ውስጥ አለ።እናላችሁ “ጻፈኝ ጻፈኝ” እያለ የሚፈታተነኝን “ነገረ ክርስቶሳዊ ነገረ ሰብ” ለማጥናት መጻሕፍትን ሳገላብጥ፣ ጠርጡለስ (Tertullian) በ202 ዓ.ም ገዳማ የጻፈውን ከሳጥናኤል ጋራ የሚገናኝ አንድ አሳብ አገኘሁ። እነሆ፦ጠርጠሉስ ስለ ትዕግሥት ማጣት ሲጽፍ ለዚህ ዐይነተኛ መነሻ አድርጎ ያቀረበው ሰይጣንን ነው። እግዚአብሔር የፈጠረውን አጽናፈ ዓለም እና ይህንም በአምሳሉ ለፈጠረው ሰው ሲያስገዛ ከዚህ የሚገኘው መልካም ውጤት ለሳጥናኤል ሊታየው አልቻለም፤ ወይም ያን ቆይቶ ለማየት ትዕግሥት አጣ። ስለዚህ ይህ አሠራር አልጥመው በማለቱ ሳጥናኤል በአዳም ላይ በቅናትና በምቀኝነት እንዲነሣበት አደረገው።በጠርጠሉስ አገላለጽ መሠረት ሳጥናኤል አዳምና ሔዋንን ሊፈትናቸው የተነሣው ቀንቶባቸው ነው። በእርሱ ዕይታ፣ የሳጥናኤል ውድቀት መነሻ ትዕግሥት የለሽነት ሲሆን፣ ትዕግሥት የለሽነትና ክፋት ይመጋገባሉ።I detect the nativity of impatience in the devil himself, at that very time when he impatientlyFacebookምስባከ ጳውሎስ - Paul's Pulpitስለ ሰይጣን አወዳደቅ - 3 ስለ ሳጥናኤል አወዳደቅ ከዚህ በፊት ሁለት አሳቦችን አንሥቼ ነበር። የመጀመሪያው አሳቤ፣ ሳጥናኤል የወደቀው ከሰው መፈጠር በኋላ ስለ መሆኑ ለማስረዳት የሚሞክር ነበር። ሌላው አሳቤ ግን የሳጥናኤል ቀዳሚ ኀጢአት ዘፍጥረት 3 ላይ የተጠቀሰው ሊሆን እንደሚችል ጥርጣሬ እንዳለኝ የሚጠቁም...
ምስባከ ጳውሎስ (Paul's Pulpit)
11 Sept, 16:14
https://youtu.be/3TX7ot7rqqU?is=EgUFcanS0Miup_KKYouTubeተልእኮው 'ሂዱ' ብቻ ሳይሆን 'አስተምሩ' የሚል ነው | ጳውሎስ ፈቃዱ | Melkam Podcast S01_E11የመልካም ፖድካስት የመጀመሪው ምዕራፍ፣ የመጨረሻው ክፍል እንግዳችን ጳውሎስ ፈቃዱ ነው። በጸሐፊነቱ፣ በአስተማሪነቱ እና በሞጋችነቱ በብዙዎች ዘንድ የሚታወቀው ጳውሎስ፣ አሁን ስለሚያገለግልባት ቤተ ክርስቲያን፣ በቅርቡ ለንባብ ስላቀረበው መጽሐፉ እና የግል ጕዳዮቹን በሚመለከት ቆይታ አድርገናል። የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ፤ ለሌሎችም ያጋሩ። https://youtube.com/@Melkam.Podcast?si=Q…
ምስባከ ጳውሎስ (Paul's Pulpit)
10 Sept, 08:48edited
ለሚቀጥለው ፕሮጀክቴ ጥናት ብጤ ልጀምር እያኮበኮብሁ ሆነና የአንዳንድ አባቶችን ጽሑፎች ገረፍ ገረፍ ሳደርግ፣ ሰሙናዊ ንትርካችንን የሚመለከት ነገር ከቄርሎስ ዘኢየሩሳሌም ጽሑፍ ውስጥ ተጠቅሶ አገኘሁ። እነሆ:-"… አምልኮህና መሰጠትህ እውነተኛ ከሆነ፣ መንፈስ ቅዱስ በአንተም ላይ ይወርዳል፤ የአብም ድምፅ በአንተ ላይ ይሰማል። ነገር ግን ድምፁ፣ 'ይህ ሰው ልጄ ነው' የሚል አይደለም፤ ይልቁንም 'ይህ ሰው አሁን ልጄ ሆኗል' የሚል እንጂ። አብ ስለ ኢየሱስ ሲናገር፣ 'ልጄ ነው' ይላል፤ ምክንያቱም 'በመጀመሪያ ቃል ነበረ፤ ቃሉም ከእግዚአብሔር ጋር ነበረ፤ ቃሉም እግዚአብሔር ነበረ' ተብሏልና (ዮሐ. 1፥1)። በእርሱ ላይ 'ልጄ ነው' የሚልበት ምክንያት እርሱ ሁልጊዜም የእግዚአብሔር ልጅ ስለ ነበረ ነው። ስለ አንተ ሲናገር ግን 'አሁን ልጄ ሆኗል' ነው የሚለው፤ ምክንያቱም በተፈጥሮ የልጅነት ማንነት አልነበረህምና። ነገር ግን የእግዚአብሔር ልጅነትን በጉዲፈቻ ተቀብለኸዋል። ኢየሱስ ዘላለማዊ ልጅ ነው፤ አንተ ግን ልጅነትን በጸጋ ተቀብለኸዋል።"ቅዱስ ቄርሎስ ከ313-386 የኖረ አባት ነው።… If your devotion is genuine, the Holy Spirit will descend on you too, and the Father’s voice will resound over you; but it will not say ‘this person is my Son’, but ‘this person has now become my son’. Over Jesus ‘is;, because ‘in the beginning was the Word, andFacebookምስባከ ጳውሎስ - Paul's Pulpitለሚቀጥለው ፕሮጀክቴ ጥናት ብጤ ልጀምር እያኮበኮብሁ ሆነና የአንዳንድ አባቶችን ጽሑፎች ገረፍ ገረፍ ሳደርግ፣ ሰሙናዊ ንትርካችንንን የሚመለከት ነገር ከቄርሎስ ዘኢየሩሳሌም ጽሑፍ ውስጥ ተጠቅሶ አገኘሁ፤ እነሆ። …. አምልኮህና መሰጠትህ እውነተኛ ከሆነ፣ መንፈስ ቅዱስ በአንተም ላይ ይወርዳል፤ የአብም ድምፅ በአንተ...
ምስባከ ጳውሎስ (Paul's Pulpit)
10 Sept, 08:26edited
እስከዚያው ሰብስክራይብ እያደረጋችሁ ቆዩማhttps://youtu.be/IuqAtop7Uus?si=0BsZwMGtHeooWIZuYouTubeቆይታ ከመምህር ጳውሎስ ፈቃዱ ጋር no topic was off the table. Coming soon🔥 COMING SOON… The guest you’ve been asking for. The conversation you didn’t expect. The questions we’ve never asked before. Controversial? Absolutely. Unfiltered? You already know. 👀 I sat down for what may be one of the most exclusive and thought-provoking…
ምስባከ ጳውሎስ (Paul's Pulpit)
7 Sept, 11:57edited
በክርስቲያን ወገኖች መካከል፣ "እኛ የእግዚአብሔር የጉዲፈቻ ልጆች ነን? ወይስ አይደለንም?" የሚል ሙግት ይደመጣል። ከዚህም የተነሣ በርእሰ ጉዳዩ ላይ አጠቃላይ የሆነ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ምልከታ ምን እንደ ሆነ ለማወቅ የሚሹ ብዙዎች ናቸው። ለመሆኑ እውነቱ የቱ ነንው? ይህ ቪዲዮ ለዚህ አንድ ምላሽ ነው።https://youtu.be/x3wdoIrFDIs?si=PCDVfodjrETkdvGhYouTubeየጉዲፈቻ ልጆች?በክርስቲያን ወገኖች መካከል፣ "እኛ የእግዚአብሔር የጉዲፈቻ ልጆች ነን? ወይስ አይደለንም?" የሚል ሙግት ይደመጣል። ከዚህም የተነሣ በርእሰ ጉዳዩ ላይ አጠቃላይ የሆነ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ምልከታ ምን እንደ ሆነ ለማወቅ የሚሹ ብዙዎች ናቸው። ይህም ቪዲዮ ለዚህ አንድ ምላሽ ነው።
ምስባከ ጳውሎስ (Paul's Pulpit)
1 Sept, 07:45
https://www.tiktok.com/@hanaadamu1/video/7680275379000495382?_r=1&u_code=eik5m59hg6gkh1&preview_pb=0&sharer_language=en&_d=eik60bclh4d1ek&share_item_id=7680275379000495382&source=h5_m
ምስባከ ጳውሎስ (Paul's Pulpit)
21 Aug, 15:29edited
Christological anthropology እንድጽፈው ያሽኮረምመኝ ጀምሯል ...
ምስባከ ጳውሎስ (Paul's Pulpit)
18 Aug, 15:14edited
ስለ ሰይጣን አወዳደቅ - 2ሳጥናኤል የወደቀው መቼ ነው?ስለ ሳጥናኤል አወዳደቅ ሲነሣ፣ ኢሳይያስ 14 እና ሕዝቅኤል 28 በአብዛኛው በማስረጃነት ይጠቀሳሉ። እነዚህ ክፍሎች እንደ ቅደም ተከተላቸው ስለ “የባቢሎን ንጉሥ” እና “የጢሮስ ንጉሥ” የሚናገሩ ናቸው። ነገር ግን ከጥንቷ ቤተ ክርስቲያን ጀምሮ ምንባቦቹ በአመስጥሮታዊ ትርጓሜ (allegorical interpretation) እየተወሰዱ ስለ ሰይጣን የሚናገሩ ተደርገው ይቀርባሉ። የዛሬው አሳባችን ከእነዚህ ምንባቦች ጋራ ግጭት የለውም፤ ከምንባቦቹ የምናገኘው እገዛም የለም።1) ሳጥናኤል የወደቀው ከዘፍጥረት 1፥1 በፊት ይሆን?የዚህ ጥያቄ ምላሽ ከባድ አይደለም። ቀድሞ ነገር ሳጥናኤል በዚያን ወቅት ተፈጥሮ ነበርን? የሚለው ጥያቄ ለዚህ ምላሽ ይሰጠናል። ከመፈጠሩ በፊት አይወድቅምና።በርግጥ መጽሐፍ ቅዱስ መንፈሳውያን ፍጥረታት መቼ እንደ ተፈጠሩ በግልጽ አይነግረንም። ነገር ግን “በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማያትንና ምድርን ፈጠረ” (አመት) በማለት የሚጀምር መጽሐፍ ቅዱስ ይዘን፣ እግዚአብሔር መላእክቱን “በመጀመሪያ” ከተባለው ጊዜ በፊት እንደ ፈጠረ ማመን የምንችል አይመስለኝም። “በመጀመሪያ” የሚለው በዚህ ስፍራ ያለው ቃል፣ ጊዜ (time) እንኳ የተፈጠረ መሆኑን የሚያስገነዝበን ነው።)እግዚአብሔር በመጀመሪያ የፈጠረው ሰማያትን ነው። የመንፈሳውያኑ ፍጥረታት መኖሪያም ሰማይ በመሆኑ እግዚአብሔር መኖሪያቸውን አስቀድሞ አዘጋጅቶ ይሆናል። ስለዚህ እግዚአብሔር ሰማያትን በሚፈጥርበት ጊዜ፣ መላእክትንም አብሮ እንደ ፈጠረ ብናስብ የተሻለ ነው። ከዚያም
ምስባከ ጳውሎስ (Paul's Pulpit)
15 Aug, 08:12edited
ስለ ሰይጣን አወዳደቅ - 1ለፍተሻ ....ሰይጣን የወደቀው ዘፍጥረት 3 ላይ ቢሆንስ? ማለትም፣ ቀዳሚ ኀጢአቱ አዳምንና ሔዋንን ለማሳት ማሰቡ፣ ማቀዱና መተግበሩ ቢሆንስ?https://www.facebook.com/share/p/1DbVDuJLxp/
ምስባከ ጳውሎስ (Paul's Pulpit)
8 Aug, 07:48edited
የወደድሁትና የተማርሁበት ውይይት።https://youtu.be/g0Jzf0Ijs-I?is=vmC1FaHw2-s65BvHYouTubeውጤታማው የወንጌል ሥርጭት ቤተ ክርስቲያን ተከላ ነው | አድማስ ጌታቸው (መጋቢ) | Melkam Podcast S01_E06የዚህ ሳምንት የመልካም ፖድካስት እንግዳ አድማስ ጌታቸው ይባላል። አድማስ በወጣትነት ዕድሜ ከሌሎች ወንድሞች ጋራ ሆኖ በተከላትና “ሕያው መንገድ ቤተ ክርስቲያን” በተሠኘች ቤተ ክርስቲያንን ውስጥ በመጋቢነት ያገለግላል። ስለ ቤተ ክርስቲያን ተከላ እና አመራር እንዲሁም ሌሎች ጕዳዮችን በተመለከተ ያደረግነውን ቆይታ ይከታተሉ። መልካም ቆይታ፣ ከመልካም ፓድካስት ጋራ! ይህ ፖድካስት ለብዙዎች እንዲደርስ…
ምስባከ ጳውሎስ (Paul's Pulpit)
2 Aug, 05:16edited
የአዲስ ኪዳን ምሁር በሆነችው ሶፋኒት ታመነ (ዶ/ር) የተቋቋመ የነገረ መለኮት በኣንላየን መቶ በመቶ ትምህርቱ በኣንላየን ነው። በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ!ለበለጠ መረጃ ቴሌግራሙን ይቀላቀሉ:- https://t.me/TyrannusCentreforTheology


ምስባከ ጳውሎስ (Paul's Pulpit)
28 Jul, 17:04edited
ካለፈው የቀጠለጌታ ኢየሱስ እንዴት የአዳም ኀጢአት ሳይተላለፍበት ቀረ?ጌታ ኢየሱስ ከእናቱ ከቅድስት ማርያም የሰውነትን ባሕርይ ተካፍሏል፤ የቱም ልጅ ከእናቱ የሚወስደውን ሁሉ እርሱም ከእናቱ ወስዷል። ከሰዎች ጋራ ሥጋና ደምን ተካፍሏል፤ በእናቱ በኩል ተዛምዶናል። ስለዚህም በሰውነቱ ከሰውነት ባሕርይ አንዳችም ያልጎደለው ምሉእ ሰው ነው። (ከመለኮትነት አንዳችም ያልጎደለው ምሉእ አምላክ መሆኑ እንደ ተጠበቀ ሆኖ።) በበርካታ ጥንታውያን ጽሑፎች ውስጥ ከድንግል ማርያም ሥጋና ነፍስ መንሣቱ የተጠቀሰው ይህንኑ ለማለት ነው።ከሥጋዋ ሥጋ ብቻ ሳይሆን፣ ከነፍሷ ነፍስ መንሣቱ የሚነገርበትን ዐውድ እዚህ ላይ ማንሣቱ ጠቃሚ ነው። የጥንቷ ቤተ ክርስቲያን ከተጋፈጠቻቸው ኑፋቄዎች መካከል አንዱ አቡሊናርዮሳስ (Applonarius) የተባለ ሰው ሲያቀነቅነው የነበረና ጌታ ኢየሱስ መለኮታዊ ነፍስ/መንፈስ እንጂ የሰው ነፍስ/መንፈስ እንደሌለው የሚናገር ነው። እንደ አቡሊናርዮሳዊነት ከሆነ፣ ጌታ አየሱስ የሰው hardware እና የአምላክ software ነው ያለው። የጥንቷ ቤተ ክርስቲያን፣ ጌታ ኢየሱስ በእናቱ በኩል የሰዎችን ሥጋና ደም ብቻ ሳይሆን ሁለንተናም መውሰዱን ለማስረገጥ ስትል፣ ሥጋና ነፍስ መንሣቱን ደጋግማ ታትት ነበር።ጌታ ኢየሱስ ከእናቱ ከማርያም ሥጋንና ነፍስን ነሥቷል የሚለውን አሳብ በቅጡ መረዳት ግን ያስፈልጋል። እርሱ የሰው ነፍስ ያለው መሆኑንን ማስረዳት ነው የተፈለገው። የቱም ፅንስ የእናቱን ሥጋም ሆነ ነፍስ ቆርሶ እንደማይወስድ ሁሉ የጌታ ኢየሱስም ጉዳይ ከዚህ ጋር ተመሳሳይ ነው። የቱም ሕፃን
ምስባከ ጳውሎስ (Paul's Pulpit)
27 Jul, 16:17edited
የቅዱሳት መጻሕፍት ግብ የቱ ነው?1) ኀጢአተኛ በእግዚአብሔር ፊት እንዴት እንደሚቆም ማስረዳት? ወይስ2) እግዚአብሔር በፍጥረቱ መካከል እንዴት እንደሚኖር ማስረዳት?https://www.facebook.com/PaulsPulpit/posts/pfbid0gukcWzsZrXXTdPPa3oScQaUAGBiCe6Wo87moLcZ87cvJU8kNgYLX5BBoFw2j9VdqlFacebookምስባከ ጳውሎስ - Paul's Pulpitየቅዱሳት መጻሕፍት ግብ የቱ ነው? 1) ኀጢአተኛ በእግዚአብሔር ፊት እንዴት እንደሚቆም ማስረዳት? ወይስ 2) እግዚአብሔር ከፍጥረቱ መካከል እንዴት እንደሚኖር ማስረዳት?
ምስባከ ጳውሎስ (Paul's Pulpit)
23 Jul, 15:06edited
ተሳስቼ አውቃለሁ።ጉዳዩ 20 ዓመታት ዐልፈዉታል።በMaxwell Whyte የተጻፈ “The Power of the Blood” የሚል መጽሐፍ ድሮ አንብቤ ነበር። የመጀመሪያው ምዕራፍ ጌታ ኢየሱስ ደሙን ከእናቱ እንዳላገኘው እና ከሰማይ ያመጣው መሆኑን የሚናገር እንደ ነበር አስታውሳለሁ። አዲስ ነገር ይማርካል አይደል? በዚህም ላይ ትምህርተ ድነትንም የተማርሁት ኢየሱስ ሥጋና ደም ከማርያም እንዳልነሣ በሚያስረዳ መልኩ ነበር። ስለዚህ ያን ምዕራፍ ወደ አማርኛ አመጣሁትና የአዲስ አበባ ሙሉ ወንጌል ልሳን በሆነው “ቀንዲል” የተሰኘ መጽሔት ላይ እንዲታተም ሰጠሁ። “ደም - የሕይወት ሕይወት” የሚል ርዕስ ተሰጥቶት ታተመ።ከብዙ ዓመታት በኋላ “ያልተንኳኩ በሮች”ን ላሳትም ስንቀሳቀስ በሰበስብኳቸው ጽሑፎች ውስጥ ያን ጽሑፍ አካትቼው ነበር። ረቂቁን አስቀድሜ ከሰጠኋቸው ሰዎች መካከል የቀንዲል መጽሔት አዘጋጅ የነበረው ወንድም አንዱ ነበር። በመካከል በነበሩት ዓመታት ውስጥ ጥቂት የነገረ መለኮት ትምህርት ቀስሞ ስለ ነበር ጽሑፉ ትክክል ላይሆን እንደሚችል ነገረኝ። መጋቢ በቀለ ወ/ኪዳን እና ዘማሪ ገዛኸኝ ሙሴም አስቀድመው ረቂቁን ሲያነብቡ ያንኑ አጸኑልኝ። ያን ጽሑፍ ነጥዬ አወጣሁና ለተስፋዬ ሮበሌ እና ለተስፋሁን ኀጢያ ሰጠኋቸው። የሁሉም አቋም አንድ ነበር። እናም ጽሑፉን በመጽሐፌ ሳላካትተው ሳላካትተው ቀረሁ። (የታተመው በ2000 ዓ.ም. ነው።)ከዚያማ እኔም የነገረ ክርስቶስ መጻሕፍት ንባብ ውስጥ ገባሁ። የነገረ መለኮት ሥልጠናም ጀመርሁ። የቤተ ክርስቲያንን ታሪክም አጠናሁ። እነዚህም ወደ ርቱዕ አስተምህሮFacebookምስባከ ጳውሎስ - Paul's Pulpitተሳስቼ አውቃለሁ! ጉዳዩ 20 ዓመታት ዐልፈውታል። በMaxwell Whyte የተጻፈ “The Power of the Blood” የሚል መጽሐፍ ድሮ አንብቤ ነበር። የመጀመሪያው ምዕራፍ ጌታ ኢየሱስ ደሙን ከእናቱ እንዳላገኘው እና ከሰማይ ያመጣው መሆኑን የሚናገር እንደ ነበር አስታውሳለሁ። አዲስ ነገር ይማርካል...
ምስባከ ጳውሎስ (Paul's Pulpit)
18 Jul, 11:52edited
አሁንም፤ ከባለፈው የቀጠለ ነው።የእግዚአብሔር ትልቁ ዓላማ ፍጥረቱን ሁሉ በመሲሑ በኩል መዋጀት ሲሆን፣ ለዚህ ክቡር ዓላማው የመረጣቸው ሰዎች አሉ። እነዚህ ሰዎች ምን ዐይነት ሰዎች እንደሚሆኑ ከመወለዳቸውም በፊት ያውቃል። የት ድረስ እንደሚጸኑ፣ የት ድረስ እንደሚወድቁ ያውቃል። እግዚአብሔር ሲመርጣቸው ቅድመ ዕውቀቱን ተጠቅሟል? ወይስ አልተጠቀመም ብሎ መሟገት ግን ይቻላል። (በዚህ ቦታ የምናነሣው ምርጫ ከድነት ጋራ የሚያያዝ አይደለም።)እግዚአብሔር ለዚህ ክቡርና ታላቅ ዓላማው ሰዎችን ሲመርጥ፣ ስለ ሰዎቹ ያለውን ዕውቀት ከግምት ሳያስገባ በዘፈቀደ እንደ መረጣቸው የሚያስቡ ሰዎች አሉ። በተቃራኒው ደግሞ፣ እግዚአብሔር ስለሚመርጣቸው ሰዎች ቅድመ ዕውቀቱን ተጠቅሟል የሚሉ አሉ። ክቡሩን ዓላማውን ለመሸከም ያልመረጣቸው ሰዎች አሉ፤ ዓላማውን እንዲሸከሙ የመረጣቸውም አሉ። ለመረጣቸው ግን ጸጋውን ይሰጣቸዋል። ያዕቆብና ኤሳው ለዚህ ምሳሌ መሆን ይችላሉ። እግዚአብሔር ሆን ብሎ አስቦና አቅዶ ነው የመረጣቸው። ውድቀታቸውንም፣ ብርታታቸውንም ለዓላማው ይጠቀምበታል በማለት ማሰብም ይቻላል። እኔም ይህን እያልሁ ነው።ስለ ምርጫ ሲነሣ፣ ብዙዎች ምርጫ ሁሉ ለድነት እንደሚመስላቸው እየታዘብሁ ነው። ይህን ያልተቀበለ ሰውም ከስም ልጠፋ (labling) አያመልጥም። ምን ማለት ይቻላል?እግዚአብሔር ለመሲሑ መምጣት መንገድ ሲያበጃጅ ከመረጣቸው ሰዎች አንዱ ቂሮስ ነበር።“እግዚአብሔር ለቀባሁት፥ አሕዛብንም በፊቱ አስገዛ ዘንድ የነገሥታትንም ወገብ እፈታ ዘንድ፥ በሮቹም እንዳይዘጉ መዝጊያዎቹን በፊቱ እከፍት ዘንድ፥ ቀኝFacebookምስባከ ጳውሎስ - Paul's Pulpitአሁንም፤ ከባለፈው የቀጠለ ነው። የእግዚአብሔር ትልቁ ዓላማ ፍጥረቱን ሁሉ በመሲሑ በኩል መዋጀት ሲሆን፣ ለዚህ ክቡር ዓላማው የመረጣቸው ሰዎች አሉ። እነዚህ ሰዎች ምን ዐይነት ሰዎች እንደሚሆኑ ከመወለዳቸውም በፊት ያውቃል። የት ድረስ እንደሚጸኑ፣ የት ድረስ እንደሚወድቁ ያውቃል። እግዚአብሔር ሲመርጣቸው ቅድመ...
ምስባከ ጳውሎስ (Paul's Pulpit)
16 Jul, 10:28edited
ካለፈው የቀጠለ ...እግዚአብሔር ሁሉን አዋቂ ነው። እያንዳንዳችን ምን ዐይነት ሰው እንደምንሆን ለማወቅ እስክንወለድና ሥራችንን እስክንከውን መቆየት አያስፈልገውም።እግዚአብሔር አብርሃምን፣ ይስሐቅን፣ ያዕቆብን ... መርጧል። እስማኤልንና ኤሳውን ግን አልመረጠም። በሁለቱም ጎራ ያሉ ሰዎች ምን ዐይነት ሰዎች እንደሚሆኑ ግን አስቀድሞም ያውቅ ነበር።እግዚአብሔር መሲሑን ልኮ ፍጥረቱን የመቤዠት ዓላማው ዓለም ሳይፈጠርም የነበረ ነው። ለአዳምና ለሔዋንም ይህን ቃል ገብቶላቸዋል። ስለዚህ መሲሑ ለእግዚአብሔር “2ኛ ዕቅድ” (Plan B) አይደለም። እስራኤል እንደማትወድቅ ገምቶ፣ ስትወድቅበት መሲሑን ወደ ማምጣት አልሄደም። እስራኤል የት ድረስ እንደምትጓዝ አስቀድሞም ያውቃል። አብርሃም፣ ይስሐቅ፣ ያዕቆብ ... በሚል የጀመረው ጉዞ እስራኤልን ቢያስገኝም እንኳ እስራኤል እንደምትወድቅ እግዚአብሔር አስቀድሞም ያውቃል።እግዚአብሔር መሲሁን የማምጣት ዕቅዱን እንዲሁ በዘፈቀደ ያካሄደው አይደለም። የተመረጡትም ሰዎች በአጋጣሚ የተገኙ አልነበሩም። ሆን ብሎ ነው የመረጣቸው። እግዚአብሔር አስቦ፣ አቅዶ፣ አውቆ ነው ሰዎችን ለዓላማውና ለክቡር ኀላፊነት የሚመርጠው። የሚመርጣቸው ሰዎች የት ድረስ ኀላፊነቱን እንደሚሸከሙና ዓላማውን እንደሚፈጽሙ፣ የቱጋ ደግሞ እንደሚደናቀፉና እንደሚወድቁ ያውቃል። ያንም ለዓላማው ይጠቀምበታል።ይህም ሆኖ ግን እግዚአብሔር በማንም ችሎታና ብቃት ላይ አይታመንም። ለመረጣቸው ሰዎች ሁሉ ጸጋውን ሰጥቷቸዋል፤ በጸጋው ደግፏቸዋል፤ በጸጋው አስችሏቸዋል።እንዲህም ሆኖ ግን የተመረጡቱ ሊወድቁFacebookምስባከ ጳውሎስ - Paul's Pulpitካለፈው የቀጠለ ... እግዚአብሔር ሁሉን አዋቂ ነው። እያንዳንዳችን ምን ዐይነት ሰው እንደምንሆን ለማወቅ እስክንወለድና ሥራችንን እስክንከውን መቆየት አያስፈልገውም። እግዚአብሔር አብርሃምን፣ ይስሐቅን፣ ያዕቆብን ... መርጧል። እስማኤልንና ኤሳውን ግን አልመረጠም። በሁለቱም ጎራ ያሉ ሰዎች ምን ዐይነት ሰዎች...
ምስባከ ጳውሎስ (Paul's Pulpit)
11 Jul, 10:11edited
ያዕቆብና ኤሳው ገና ሳይወለዱ፣ በጎ ወይም ክፉ ምንም ሳያደርጉ እግዚአብሔር ከሁለቱ አንዱን ለትልቅ ዓላማና ኀላፊነት መምረጡ ምን ይደንቃል? ያዕቆብ ወይም ዔሳው ምን ዐይነት ሰዎች እንደ ሆኑ፣ ለተመረጡበት ግብና ተልዕኮ ኀላፊነት ብቁ ይሁኑ አይሁኑ እግዚአብሔር ማወቅ የሚችለው ከተወለዱ በኋላ ነውን? ኀላፊነት ለመሸከም መቻላቸውን ለማወቅ በጎ ወይም ክፉ ሲያደርጉ ማየት ያስፈልገዋልን? ሰዎቹ ሲወለዱና ሲያድጉ ምን ምን ዐይነት ሰዎች እንደሚሆኑ እግዚአብሔር አስቀድሞም ያውቅ ነበር።ወገኖች፤ ይህ አሳብ ስለ ድነት አይደለምhttps://www.facebook.com/PaulsPulpit/posts/pfbid0DvmBMbSwrDha8ujD3WQ9nkTAyZKPbxT2WqZ7KSRjMc2WFMLsKLoBGryBZ7KaRQR4lFacebookምስባከ ጳውሎስ - Paul's Pulpitያዕቆብና ኤሳው ገና ሳይወለዱ፣ በጎ ወይም ክፉ ምንም ሳያደርጉ እግዚአብሔር ከሁለቱ አንዱን ለትልቅ ዓላማና ኀላፊነት መምረጡ ምን ይደንቃል? ያዕቆብ ወይም ዔሳው ምን ዐይነት ሰዎች እንደ ሆኑ፣ ለተመረጡበት ግብና ተልዕኮ ኀላፊነት ብቁ ይሁኑ አይሁኑ እግዚአብሔር ማወቅ የሚችለው ከተወለዱ በኋላ ነውን? ኀላፊነት...
Related Channels
Other channels in the same section of the catalogue.
