Latest posts

ከፍልስፍና ዓለም
23 Sept, 18:08
ጦርነትን በራሱ ለምን ማሸነፍ አልቻልንም ?አንዲት ሀገር ወደ ጦርነት ስትገባ ማን ጀመረዉ እንዴት ተጀመረ ብሎ ጠይቆ መልስ ማግኘት ቀላል ሊሆን ይችላል ነገር ግን እንዴት ያን ጦርነት ልንደጋግመዉ ቻልን ? ለሚለዉ ጥያቄ ግን መልስ ማግኘት እጅግ አስቸጋሪ ነዉ ።ምናልባትም ከዚህ በፊት አንዳንድ ሰዎች ታስታዉሱ ይሆናል ትዉልድ በሆነ ያክል ጋፕ ( ቆም ) ማለት አለበት ህፃናትን ወደዚህ ምድር ለማምጣት አትጣደፉ በሚለዉ ሀሳቤ ታዉቁኝ ይሆናል ። ለምን እንደዚህ እንዳልኩ ትንሽ ላብራራላችሁ ፦ በመጀመሪያ እንደ ኢትዮጵያ ዓይነት መሰረታዊ ፍላጎቶች ባልተሟሉባት ሀገር ህፃናትን ማምጣት ግሃነም ስለመኖሩ እርግጠኛ አደለሁም ነገር ግን በቅዱሳን መፅሐፍቶች እንደተፃፈዉ ከሆነ ግን ሀገሪቱ ያለችበት ሁኔታ ከግሃነም ብትበልጥ እንጂ አታንስም ስለዚህ አምጥተህ አታሰቃየዉ ለማለት ነዉ ። በመቀጠል ምናልባትም ተሳክቶልህ እና ፍላጎቶችን አሟልቼ አሳድጋለሁ ብትል ሀገሪቱ ያለችበት የዘር ፖለቲካ እና አድሏዊነት ወይም የእኔ ጊዜ ነዉ እያለ ሲያምቧርቅበት ሲሰማ ቂምና በቀልን እየተመገበ ያድግልህና ከዛስ ምን ሊሆን እንደሚችል መልሱን ለራስህ እተዉልሃለሁ ...አየህ ጎበዜ ከዚህ በፊት የተበድለናል የተጨቁነናል ታሪክ እየተነገረዉ ያደገ ልጅ ነዉ ስልጣን ሲይዝ በቀሉን ለመወጣት እየተሯሯጠ ያለዉ ስለዚህም ህፃኑን ከማምጣትህ ከማምጣትሽ በፊት ቆም ብለህ ቆም ብለሽ ማሰብ አለባችሁ የምላችሁ ትንሹ ምክንያቴ ይሄ ነዉ ።አሁን ላይ በሀገሪቱ ዉስጥ ያለዉ ጦርነት የቂም እና የበላይ ልሁን ግጭት ነዉ ይሄን ጦርነት መፍታት ደግሞ እጅግ አስቸጋሪ ነዉ ምክንያቱም አሁን ላይ የሀገር ሽማግሌዎች አይከበሩም የሃይማኖት አባቶች አቅማቸዉ ተዳክሟል ወይም ተሰሚነታቸዉ ቀርቷል ስለዚህም ማነዉ ከቂመኛ እና በቀለኛ የትዉልድ ጦርነት የሚያወጣን ?ምናልባትም መጀመሪያ ላይ የተጠቀምኩትን ጦርነትን ማሸነፍ ለምን አልቻልንም ለሚለዉ ዓረፍተ ነገር ወይም ጦርነትን ድል ልናደርግበት የምንችልባቸዉ መንገዶች ብዬ የማምንባቸዉን ሀሳቦች በጥቂቱ ላቀርብላችሁ እወዳለሁ!ማንኛዉም ሰዉ መብቱን በፍርድ ቤት ማግኘት እንደሚችል ሲያምን ፣ በልዩነት ተቻችሎ መኖር እንደሚቻል ማመን ሲችል ፣ መሬቱንም ሆነ ንብረቱ በህግ እንደሚጠበቅለት ሚመን ሲጀምር ፣ ድምፁን ያለምንም ማዋከብ በምርጫ ማሰማት እንደሚችል ሰያምን ፣ የኔ ዘር ከሌላዉ የተለየ አይደለም ብሎ ማመን ሲጀምር ፣ ከዚህ በፊት አዛዉንት ወላጆቹ ወይም የፖለቲካ ሊሂቃን ነኝ የሚል የተነገረዉን የተበድለናል ድሪቶ ታሪክ እርግፍ አድርጎ መተዉ ሲጀምር ፣ ከዚህ በተጨማሪ በመሪዎች ቦታ ያሉ ሰዎች ደግሞ የተበደለን ሰዉ መስማት እና ማዳመጥ ሲጀምሩ ፣ ከቦታዬ ተባርሪያለሁ ያሉ ግለሰቦችን ወደ ቦታቸዉ መመለስ ሲችሉ ፣ የተነጠቀዉን መብት በህግ መመለስ ሲችሉ ፣ የተጣላዉን ማህበረሰብ እንደገና ማነጋገር ሲችሉ ፣ ራሳቸዉ መሪዎች ከህግ በላይ እንዳላይደሉ መረዳት ሲችሉ እና ራሳቸዉ መሪዎች አስቸጋሪ እና ከአቅማቸዉ በላይ እንደሆነ በተረዱ ጊዜ ስልጣን ለህዝብ ማስረከብ እንደሚቻል ማመን ሲጀምሩ ምናልባትም ጦርነትን ልናሸንፈዉ እንችል ይሆናል በማለት ሀሳቤን እቋጫለሁ ።
ከፍልስፍና ዓለም
23 Sept, 12:12
ድንቁርና ሀገርን የሚያጠፋ እና ሕዝብን የሚያዋርድ ትልቅ ጠላት ነው።


ከፍልስፍና ዓለም
22 Sept, 06:10
በዋቄፈና እምነት መሰረት ዋቄፈና እንደሌሎቹ ሃይማኖቶች ለምን ቅዱስ መፅሀፍ እንደሌለዉ የሃይማኖቱ መሪዎች ሲያስረዱ እንዲህ የሚል አንድ አፈታሪክ ይናገራሉ።በድሮ ጊዜ እንደማነኛዉም ሃይማኖት ዋቃ(ፈጣሪ) ለዋቄፈታዎች የሚመሩበትን ህግ እና መንፈሳዊ መልዕክቱን የያዘ ቅዱስ መፅሀፍ ሰጧቸዉ ነበር።ነገር ግን ቅዱስ መፅሀፉን በአግባቡ ሳያስቀምጡት ይቀርና አንዲት ላም ቅርጥፍ አርጋ ትበላዋለች። በዚህም የተነሳ ዋቃ በመቆጣት ሌላ መፅሀፍ አልሰጣቹም ይላቸዋል፤ዋቄፈታዎችም ህግጋቱን በቃል ብቻ ሸምድዶ ለመያዝ እና ለትዉልድ ለማስተላለፍ ይገደዳሉ፤ ከዛ በተጨማሪም የመፅሀፉ መልዕክቶች በላሟ ሆድ ዉስጥ ይገኛሉ በሚል የላምን ሆድ እቃ እያዩ የመተንበይን ልምምድንም ያዳብራሉ።ይህም ልምምድ እስካሁን ድረስ በተለያዩ ልክ እንደ ኢሬቻ ባሉ የክበረ በዓል ጊዜያት ላይ ይከወናል።የዋቄፈናን ቅዱስ መፅሀፍ የበላቹ ላም በረከት በተቀሩት አብርሃማዊ ቅዱስ መፅሀፍቶች ላይም ይደር።🙏


ከፍልስፍና ዓለም
20 Sept, 20:54edited
በሀገራችን የተፈጠሩ የቅርብ ጊዜ ችግሮችአዉቃለሁ ይሄ ፍልስፍና ነክ ፅሑፎች እና ሀሳቦች የሚቀርቡበት ቦታ ነዉ ። ሆኖም ግን በእርጋታ እና በጥልቀት ለማሰብ ለመፈላሰፍ ዉጫዊ ሰላም አስፈላጊ ነዉ ። ይሄ ፅሑፍ ማነንም ለመቃወም ወይም ድጋፍ ለመስጠት አይደለም የግል አመለካከት ብቻ ነዉ ። እስኪ ስለ ሃይማኖት ስለ ዩንቨርስ ( ሁለንተና ) ስለ ስነ ፅሑፍ ስለ ፍልስፍና ከሞላ ጎደል የራሳችንም በአብዛኛዉ የታላላቅ አሲቢዎችን አመለካከት አስቀምጠናል ። እስኪ ደግሞ ስለ ሀገራችን በጥቂቱም ቢሆን እናዉጋ እንወያይ ....ብታምኑም ባታምኑም አሁን ላይ ኢትዮጵያ ብለን የምንጠራት ሀገር አዲስ አበባ እና ሌሎች አንዳንድ ትልልቅ ከተሞች ብቻ እየሆነች መጥታለች ። በአራቱም አቅጣጫ የራሡን ሀገር መንግስት ለመመስረት እየታገልኩ ነዉ የሚል ቡድን እና ማህበረሰብ ተፈጥሯል ።ከምንጊዜዉም በላይ በአስቸጋሪ ሁኔታ ዉስጥ ያለን ይመስለኛል ። ለምን እንደዚህ ብትንትናችን ሊወጣ ቻለ ? ለምን እርስ በርሳችን መተማመን እና መከባበር አልችል አልነ ? ምንድን ነዉ የሆነዉ ? ኢትዮጵያ ብለን የምንጠራት ሀገር 70 እና 80 ዓመት ወደ ኋላ የሚጎትታትን ችግር ለምን መፍጠር ቻልነ ? ወጣት ሁነን ሳለ ስለምን ሞትን ፈለጋ ወደ ጫካ ተጓዝነ ? በጣም ብዙ ጥያቄ ማንሳት ይቻላል ግን መልሶቻችን ልንከፍተዉ በማንችላቸዉ ቁልፎች ተቸንክረዉብናል ።ከዚህ በላይ እሮሮ ማቅረብ አሰልች ስለሚሆን ከላይ በርዕስ ለመግለፅ እንደሞከርኩት የቅርብ ጊዜ ስህተቶቻችን ወይም ችግሮቻችንን ወደ መዘርዘሩ እገባለሁ ፦1 አሁን ላለንበት ዉጥንቀጥ እንደ
ከፍልስፍና ዓለም
20 Sept, 18:46
አብዛኛዉን ጊዜ በሃይማኖት አፎሎጂስቶቻችን ዉይይቶች እና ሙግቶች ላይ የተለያዩ ህፀፆች ይሰራሉ፤ አልፎ ተርፎም ታዳሚ ካለዉ ታዳሚዎችን ለማሳመን የሚደረጉ manipulative አካሄዶች አሉ(በተለመዶ ይሄንን ፖለቲካ ይሉታል አሉ)። እና እሱን በደንብ የሚያጋልጥ ዉይይት እና ሙግቶችን እነዚህ ነገሮች ሲፈጠሩ figure out እንድናረግ የሚረዳን ቅልብጭ ያለች፣ረዘም ብላ አጠር ያለች፣አጠር ብላ ዉጥር ያለች፣ ዉጥር ብላ ጥርት ያለች booklet አዘጋጅቼላቹሃለዉ። 24 page ነች በደንብ ትነበብ። አሰልቺ እንዳትሆን በተቻለ መጠን ዋና ነጥብ ነጧቧ ተቀንድባ ነዉ የሰፈረችዉ 😁
ከፍልስፍና ዓለም
20 Sept, 04:57
ወሲብና ሲኖዶስሲኖዶስ ወሲብ እንደማታውቅ ትሆናለች። ግን በደንብ እንደምታውቀው እያሳየችን ነው። ሲኖዶስ ወሲብ ላይ ትሽኮረመማለች ። ውሸት ነው። ወሲብ በሲኖዶስ የተለመደ ነው።The Bible is full of sex story and pornography. And the Quran too1) ወሲብ አሪፍ ነው ባይ ዜ ዌ። ለወንድ ልጅ ደስታ ነው። ለሴት ልጅ ደግሞ አስፈላጊ ያደረገው አንዱ ምክንያት ወሲብ ነው። ተፈጥሮ (እግዜአብሔር/አላህ) ሴትን ልጅ የምትተካ (Substitute የምትደረግ) አድርጋ ነው የፈጠረቻት። ሴት ልጅ በሌላ ልትተካ (Substitute ልትደረግ) ትችላለች። ያን ያህል የግዴታ አስፈላጊ አይደለችም። አስፈላጊ ያደረጋት ወንድ ነው። ለምን ብሎ?! ለሴክስ። ታስፈልጋለች፣ አለ ወንድ ልጅ ስለሚፈልጋት ሴት ልጅ ትኖራለች። እግዜአብሔር አዳምን ከአፈር ከፈጠረ በኋላ ሊተዋት ነበር። አዳም ነው ታስፈልገኛለች ብሎ እንድትፈጠር ያደረጋት። ከዛ ከስጋው ፈጠራት። ፍላጎቱ (the recipe) የአዳም ነው። አዳም ፈለጋት፣ እንደፈለጋት እግዜር ፈጠራት። ያስፈለገችው ለወሲብ ነው። ወሲብ ወንድ የሚፈልገው፣ ሴትን አስፈላጊ ያደረገ ነገር ነው። ስለዚህ ጥሩ ነው። ያፈላልጋል። ይፈለጋል።2) Interms of ደስታ የወሲብ ደስታ ትልቅ ነው። ግሪኮቹ ለደስታ የተለያዬ ደረጃ አላቸው። ለምሳሌ ገንዘብ ማግኘት ከወሲብ እኩል አያስደስትም። ስለዚህ ትልቁ ደስታ የሚገኘው በወሲብ ነው። Lust is a greatest pleasure. የተሻለው ፍልስፍና ነው። ፍልስፍና ከሁሉም የበለጠ ደስታን ይሰጣል ተብሎ ይታመናል።
ከፍልስፍና ዓለም
19 Sept, 09:57edited
የሁለተኛዉ ክፍለዘመን ሮማዊዉ ፈላስፋ ሴልሰስ "True word" በተሰኘ መፅሀፉ ላይ ስለ ክርስትና ሲናገር እንዲህ ይላል።«የእነርሱ [የክርስቲያኖች] መመሪያና ትእዛዝ እንዲህ የሚል ነው፦ የተማረ፣ ጥበበኛ ወይም አስተዋይ የሆነ ማንም ሰው ወደ እኛ አይቅረብ፤ ምክንያቱም እነዚህ ችሎታዎች በእኛ ዘንድ እንደ ክፉ ይታያሉና። ነገር ግን ማንም ያልተማረ፣ ደንቆሮ፣ መሃይም ወይም ልጅ የሆነ ቢኖር በድፍረት ይምጣ። እነርሱ እንደነዚህ ያሉ ሰዎችን አምላካቸው የሚቀበላቸው አድርገው ማሰባቸው፣ መሳብ እና መማረክ የሚፈልጉት እንዲሁም ማሳመን የሚችሉት ሞኞችን፣ የተናቁትንና ደንቆሮዎችን፣ እንዲሁም ባሪያዎችን፣ ሴቶችንና ሕፃናትን ብቻ መሆኑን ያሳያል።»ምንም እንኳ የሴልሰስ መፅሀፍ በጊዜዉ በቤተክርስቲያን አማካኝነት ቢጠፋም ከሴልሰስ ሞት 70 አመታት ቡሃላ የመጣዉ የቤተክርስቲያን አባት ኦሪገን "Contra Celsum" በሚል ርዕስ መፅሀፉ ጠፍቶ ግን ተፅህኖዉ ላልጠፋዉ ፈላስፋ መልስ ፅፏል። ይህም ፅሁፍ ለእሱ መልስ ብሎ ከፃፈዉ መፅሀፍ ላይ የተወሰደ ነዉ።


ከፍልስፍና ዓለም
16 Sept, 16:43
የኢትዮጵያዊያን ተስፋ እና ምታህታዊ ለዉጥን መሻት ሳይ ሁሌም ያስደንቀኛል። አባይ ሊገነባ ነዉ የተባለ ሰሞን "በቃ አለፈልን" ያላለ አልነበርም። ከዉጭ ሆኖ ለታዘበዉ ግድቡ ኤሌትሪክ ሳይሆን በመቶ ቢሊየኖች የሚቆጠር ዶላር የሚያመነጭ ነበር የሚመስለዉ።በመቀጠል ደሞ ነዳጅ ተገኘ ሲባል "እግዚኦ እንደ አረቦቹ እግራችንን ሰቅለን እሩዝ በስጋ መብላታችን ነዉ በቃ፤ ድህነት አለቀለት" ተብሏል። ይህ ህዝብ እንደ ተስፋ አድራጊነቱ በተገላቢጦሽ አጭር ሜሞሪ ነዉ ያለዉ እና እሱም ተረሳ። አሁን ደሞ አንድ የከበረ ድንጋይ ተገኝቷል በጣም rare ስለሆነም በግራም የሚሸጥበት ዋጋ ተለቅ ያለ ነዉ የሚል ወሬ መናፈስ ከጀመረ ጀምሮ አብዛኛዉ ኢትዮጵያዊ እንቅልፍ አጧል፤ ብሎም የልንለወጥ ነዉ ዘፈኑ አሁንም ደርቷል። አንድ የተፈጥሮ ሀብት መገኘቱ ብቻ የአንድን ሀገር ኢኮኖሚ ወዲያዉኑ አይለዉጥም፤ የክምችቱ ብዛት፣ የማዕድኑ ጥራት ብሎም ቆፍሮ የማዉጣቱ አቅም ወሳኝነት አላቸዉ። ስለዚህ የሀገሬ ህዝብ ሆይ በአንድ ሌሊት መጦ ህይወትህን የሚቀይር ተዓምር የለም እና ተስፋህን በልኩ አርገህ ማህዲ እና እየሱስን ጠብቅ።


ከፍልስፍና ዓለም
14 Sept, 18:46
የማለዳ ድባብ ከተሰኘችዉ የበዕወቀቱ ስዩም የግጥም መድብል ዉስጥ አንዲት ወግ አገኘሁ እናም እጋብዛችሁ ዘንድ ወደደኩ ፦አንድ ገጠር ቀበሌ ዉስጥ አንዲት ስትፈጭ የምትኖር ሴት አለች ። ከጎደሎ ቀኖች ባንዱ ባሏ ታሞ ይተኛል ። ጎረቤቷ ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም አጥሯን ገፋ አድርጎ ቤት ይሰራል ። ጎረቤትየዉ ያዲሱን ቤት ግድግዳ ያቆመበት ( የገደገደበት ) ቦታ ሴትዮዋ ሽንቷን የምትሸናበት እንዲሁም ግብር ዉሃ የምትወጣበት ስፍረዋ ነበር ። የታመዉ ባሏ ሲሞት ቀብሩ ላይ እንዲህ አለቀሰች" እንኳን አንተ ሞተህ ፥ እያለህልኝ በሽንት መሽኛየ ላይ ፥ ገደገዱብኝ "ይህን ሲሰማ ለቀስተኛዉ ሁሉ ሳቀ ። ጥርሱ ይርገፍ ብለን ወደ ቀጣዩ ስንኝ እንድናልፍ በዕዉቄ ያሳስበናል ።


ከፍልስፍና ዓለም
14 Sept, 07:27edited
Alexamenos graffitoአሁን ላይ ከሞላ ጎደል በሁሉም የክርስትና ቤተ እምነቶች ላይ ሊባል በሚችል ሁኔታ portrait of Jesus's Crucifixion ይታያል። ይህንን ምስለ ስቅለቱን ለመጀመሪያ ጊዜ ማን ሳለዉ ብለን ስናይ በጊዜ ወደ ኋላ ወደ ሶስተኛው ክፍለ ዘመን እንድንጓዝ ታሪክ ያስገድደናል።የጥንት ክርስትያኖች በሥዕለ አድህኖዎች የሚያምኑ አልነበሩም። በብሉይ ኪዳንም ያለዉን "የተቀረፀ ምስልን አታርግ" የሚለዉን ትህዛዝ በጥብቅ የሚከተሉ በዛ መንገድ ስሎ መጠቀምንም ከአረማዊያን(ፓጋኖች) ተግባር ጋር የሚያያይዙ እና እንደ ጣኦት ማምለክም የሚቆጥሩ ናቸዉ።በጊዜያት ሂደት ግን ለክርስቲያኖች ሀሳብ ገባሪ በመሆን ለሃይማኖታቸዉ ብዙ አስተዋፅኦ ያረጉት አረማዊያን በዚህ ዘንድም ሌላ ሀሳብን እንካቹ አሏቸዉ። በ3ኛዉ ክፍለዘመን ላይ አንድ አረማዊ "Alexamenos" የሚባል ክርስትያን ላይ ለማላገጥ ሲል ለመጀመሪያ ጊዜ የክርስቶስን ምስለ ስቅለት በግርግዳ ላይ ሳለዉ።በጊዜዉም ስቅለት በሮማዎች ዘንድ በጣም የተዋረደ የአሟሟት መንገድ በመሆኑ በዛ መንገድ የሞተ ሰዉ የሚናቅ እና የሚኮነን ነበር።ከዛ የስላቅ ስህል በታችም "አሌክሲማኖስ አምላኩን ያመልካል" የሚል ቃላቶች ተፅፈዉ ነበር።ከጊዜያት ቡሃላም ቆስጠንጢንዮስ ሲነግስና ክርስትና መንግስታዊ ሃይማኖት ሲሆን ቀድሞ የነበረዉ የመስቀል ትርጉም ተቀየረ። መስቀልም ወንጀለኞች እና ቀማኞች የሚሰቀሉበት እና የዉርደትን ሞት የሚሞቱበት መሆኑ ቀርቶ የክርስቶስ ንፁህ ደም የፈሰሰበት ቅዱስ የሃይማኖት ምልክት መሆን ጀመረ።ከዛ ቡሃላም የተለያዩ ሥዕለ


ከፍልስፍና ዓለም
13 Sept, 17:51
የሹመት የመጀመሪያ አመት ላይማ ለአብይም ተጨብጭቧል አልቀጠለም እንጂ ውጣልኝ ከክለቤ


ከፍልስፍና ዓለም
12 Sept, 11:15
THE HUMANIST ROAD™
ከፍልስፍና ዓለም
12 Sept, 11:14
የሰዉ ልጅ ሥርዓታዊ እንስሳ ነዉ?አሁን ላይ በሁሉም የዓለም ማህበረሰብ በሚባል ደረጃ ሥርዓቶች አሉ።ባህላዊም ሆነ ሃይማኖታዊ እየተባሉ በማህበረሰቡ ህይወት ዉስጥ ትልቅ ቦታ ተሰጧቸዉ ሲተገበሩም ይኖራሉ። እና ይህ የሰዉ ልጅ ከሥርዓቶች(Rituals) ጋር ያለዉ ልዩ ቁርኝት ከምን የመጣ ነዉ ሲል ግሪካዊ-አሜሪካዊዉ የስነ ባህሪ እና ስነ-ሰብ ተመራማሪዉ ዲሜትሪስ ይጋላታስ አጥንቶ ባገኘዉ ዳሰሳ ላይ በፃፈዉ መፅሀፍ (Ritual:How seemingly senseless acts make life worth living) ተመስርተን እንቃኘዋለን።ሥርዓቶች ከቀን ተቀን ልማዶች የሚለዩት በኢ-ምክንያታዊነታቸዉ እና ከቁሳዊ ጥቅም ይልቅ ዉስጣዊ ተፅህኖ በማሳደራቸዉ ነዉ። ለምሳሌ ጥርስን መቦረሽ ጥርስ እንዲፀዳ ያደርጋል፣ ምግብን ማብሰል ርሀብን ይቀርፋል በተቃራኒዉ ዝናብን ለማስመጣት የሚደረግ ዳንስ ደመናን አይጠራም፣ለሟችም የሚደረግ ፍትሃት ሟችን ወደ ህይወት አይመልስም። እናም እነዚህ ቁሳዊ እና ተጨባጭ ዉጤት ብሎም ጥቅም የሌላቸዉን ነገሮች የሰዉ ልጆች ስለምን ለዘመናት ሲተገብሯቸዉ ኖሩ የሚለዉ ትልቅ ጥያቄን የሚያጭር ነዉ። ይህንንም ቅራኔ The Ritual paradox ስንል እንጠራዋለን።የሰዉ ልጆች ከሥርዓቶች ቁሳዊ እና ተጨባጭ ጥቅም የማያገኙ ከሆነ ታዲያ እንዴት ሥርዓቶችን ሊፈጥሩ ቻሉ ብለን ስንጠይቅ ጉዳዩ ወደ ሰዉ ልጆች ነገሮችን የመቆጣጠር መሻት እና ስነ ልቦናዊ መረጋጋት ፋይዳ ጋር ያመራል። ሰው ልጅ በህይወቱ ጉዞ ውስጥ ሊቆጣጠራቸው የማይችላቸውና ውጤታቸው ወዴት እንደሚያደላ በማያውቃቸው ጥልቅ



ከፍልስፍና ዓለም
11 Sept, 06:16
አዲሱን አመት ብዙ የምንፈላሰፍበት፤አዕምሮን ከሚያስሩ የሻገቱ አስተሳሰቦች የምንላቀቅበት እና የአስተሳሰብ አድማሳችንን የምናሰፋበት ያርግልን።መልካም አዲስ አመት


ከፍልስፍና ዓለም
10 Sept, 17:22
ምንድር ነዉ አዲስ አመት ?አዲስ ዓመት ለማክበር ከመሯሯጥ ይልቅ አዲስ አስተሳሰብ እና አመለካከት ይኖረን ዘንድ ብንተጋ ዓለምንም ሆነ እያንዳንዱን ቀናቶች እንለዉጣለን ።የራሳችንን ደስታ ለማክበር ሲባል የሌሎችን ህልዉና መስዋዕት የምናደርግ ከሆነ ቀናትን እንለዉጣለን እንጂ አዲስ አመለካከት አልፈጠርንም ።እኛ አዲስ አመት ለማክበር በደስታ ስንጮኽ ደሮዎች እና ሌሎች እንስሳቶች ደግሞ በሕይወታቸዉ የመጨራሻ ጮኽታቸዉን ያሰማሉ ።ብልህ ሰዉ እያንዳንዱን ቀን እንደ አዲስ ዓመት ይቆጥረዋል አዲስ አመለካከት ለመቀየር ዓመትም አይጠብቅም ። መንጋዊ ዕሳቤ ያለዉ ማህበረሰብ ደግሞ አመቱን ሙሉ ጠብቆም አስተሳሰቡንም አይቀይርም ። እናም አዲስ አመትን በጮኽትና በግርግር አክብሮ ወደ አሮጌዉ አስተሳሰብ ለመመልስ አትጣደፉ! እንደ ሀገር ብዙ አዲስ አመታቶችን አክብረናል ሆኖም ግን ለዉጥ አላመጣንም በኃይለኛ እንቅልፍ እና ማንኮራፋት ዉስጥ ነን እናም ከእንቅልፋችን ነቅተን አይናችን አሽተን እንግለጥና የብሩህ አስተሳሰብ ባለቤት እንሁን ።
ከፍልስፍና ዓለም
9 Sept, 16:31
ወቅቱ የበዓል ዋዜማ እንደመሆኑ መጠን የከተማዋ መንገዶች በበዓል ግብዓቶች ንግድ ጡፈዋል እና በመንገዶቼ እያዘገምኩ አንድ ትኩረቴን የሳበዉ እና ያስገረመኝን ነገር ላጫዉታቹ። እሱም በዶሮ ገቢያ ዉስጥ አንድ የዶሮ ነጋዴ ሞንታርቦ ይዞ በከፍተኛ ድምፅ መዝሙር ከፍቷል። የሚነግደዉ ዶሮ ነዉ እና መዝሙር ስለምን ይከፍታል ምንስ አገናኘዉ የሚል ይኖራል።ሰዉየዉ ግን በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ከፍተኛ ተፅህኖ ያለዉን የማርኬቲንግ ሳይኮሎጂ እየተጠቀመ ነበር። በዛን ቦታ ያን መዝሙር በመክፈቱ የዛ እምነት ተከታይ ሰዎችን ቅድመ ትኩረት ያገኛል፤ቀጥሎም ሰዎቹ ወደ ዋጋ ድርድር ሲገቡ ትርፍን ብቻ ትኩረት አርገዉ እንዳይደራደሩም ተፅህኖ ያረግባቸዋል።ሰዎች የሆነን ግብዓት ከእነሱ ተመሳሳይ እምነት ካለዉ ሰዉ እየገዙ መሆኑን ሲያዉቁ ሙሉ በሙሉ ትርፍን ያማካለ ድርድር አያረጉም ይልቁንም በ In-Group psychology መሰረት In Group favouritism ተፅህኖ ስር ይወድቃሉ።ይህም ማለት በእኔ ጎራ አለ የሚሉትን ሰዉ የበለጠ የማመን፣ለመርዳት የማሰብና በበጎ አይን የመመልከት ተፅህኖ ያድርባቸዋል።ይህ ደሞ ለነጋዴዉ ንግዱ እንዲሳለጥ ብሎም የተሻለ ትርፍን እንዲያገኝ የሚረዳዉ ዘዴ ነዉ። እናም ምርትን በመደበቅ እና Artificial inflation በመፍጠር ትርፍን ማግበስበስ ብቻ የሚያቀዉ የኢትዮጵያ ነጋዴ አዳዲስ ስልቶችን እየተማረ መምጣቱ ይበል የሚያሰኝ እና ለእኔም አግራሞትን ያጫረ ሆኖ አግኝቼዋለሁ።


ከፍልስፍና ዓለም
7 Sept, 18:57
በዓለም ላይ እጅግ ተደናቂ ሁለት ልቦለዶችን ፅፏል በመጨረሻ ዘመኑ ግን እነዚህን ልቦለዶች በመፃፉ አፍሯል ። ይህ እንደማንኛዉም The Arabian Nights ተረቶች የሚያስደንቅ የህይወት ታሪክ ነዉ ። ዉድ አንባቢ ሆይ ከዚህ በፊት የሊዮ ቶልስቶይን የመጨረሻ ዘመን የህወት ፍልስፍናዎች ወይም የህወትን ትርጉም ፍለጋ የባዘነበትን መፅሐፍ A Confession በተሰኘዉ ልክ እንደ ህይወት ታሪኩ በሚቆጠረዉ
ከፍልስፍና ዓለም
7 Sept, 15:10
በዓለም ላይ እጅግ ተደናቂ ሁለት ልቦለዶችን ፅፏል በመጨረሻ ዘመኑ ግን እነዚህን ልቦለዶች በመፃፉ አፍሯል ። ይህ እንደማንኛዉም The Arabian Nights ተረቶች የሚያስደንቅ የህይወት ታሪክ ነዉ ።ዉድ አንባቢ ሆይ ከዚህ በፊት የሊዮ ቶልስቶይን የመጨረሻ ዘመን የህወት ፍልስፍናዎች ወይም የህወትን ትርጉም ፍለጋ የባዘነበትን መፅሐፍ A Confession በተሰኘዉ ልክ እንደ ህይወት ታሪኩ በሚቆጠረዉ መፅሐፉ ቀንጨብ አድርጌ አቅርቤላችሁ ነበር ዛሬ ደግሞ ስለ ህይወቱ እና ስለመጨረሻዋ ህቅታ ድረስ የተጓዘበትን መንገድ ላቅርብላችሁ እናም በትዕግሥት ብታነቡት አሳዛኙን ህይወት እና በህወቱ ዉስጥ ያደረጋቸዉ ሁነቶች በሆነ ያክል ግንዛቤ እንደሚያስገኝላችሁ አልጠራጠርም ።በ20ኛዉ ክፍለ ዘመን መጀመሪያ በ1910 ስለሞተዉ ነብይ ነዉ ትረካችን የሚጀምረዉ ። ይኽ ሰዉ እጅግ በጣም የተከበረና ከመሞቱ ከሃያ አመት በፊት ጀምሮ አደናቂዎቹ እንደ ሐይማኖታዊ ጉዞ ያለማቋረጥና ማብቂያ በሌለዉ ሁኔታ ፊቱን በጨረፍታ ቢሆን ለማየት ድምፁን ለመስማት ወይም የልብሱን ቅምቅማት እንኳን ለመንካት ወደ ቤቱ እንደ ጅረት ጎርፈዋል ።ጓድኞቹም ቤቱ መጥተዉ ለዓመታት በመቀመጥ ከአንደበቱ የሚወጣዉን እያንዳንዱን ቃል ልዩ ምልክትና ምህፃረ ቃል በመጠቀም ከመፃፋቸዉ ሌላ በዕለት ተዕለት ህይወቱ ዉስጥ የሚያደርጋቸዉን ጥቃቅን ናቸዉ የተባሉ ነገሮች እንኳን ቢሆን ንቀዉ ሳያስቀሩ በዝርዝር በፅሁፍ አስፍረዋል ። እነዚህም ፅሑፎች በትላልቅ volume ለመታተም ችለዋል ።ሃያ ሶስት ሺህ የሚጠጋ መፅሐፍት_ልብ አድርጉ ሁለት ሺህ ሶስት መቶ
ከፍልስፍና ዓለም
7 Sept, 15:10



ከፍልስፍና ዓለም
6 Sept, 14:39
Why We Need a Writer Like Sebehat (እንደ ወረደ!!)Sebehat is the ultimate Ethiopian literary outlaw who gave zero fucks about society's delicate feelings. He wasn’t a typical, polished author; what made him outstanding was his unapologetic, raw authenticity. He brought the brothels (ውቤ በረሀ) directly onto the page with complete honesty. We can say he was a little sexist, but which classic writer wasn't? (በእርግጥ የስብሐት ጥቂት የሚባል አይደለም፤ የሰውን ትተን አህያ ስለመብዳት የጻፈ ብቸኛ ኢትዮጵያዊ ሳይሆን አይቀርም!)Why do we need a liberal writer like him, especially in a country like Ethiopia, where our culture is heavily shaped by religion, more specifically by Christianity? (ይህ በራሱ መጥፎ ነገር ነው እያልኩ አይደለም።) We have built a strong public image of ourselves as pristine, righteous, angelic people walking on earth. When a culture demands total spiritual perfection, the first thing forced into an invisible bag is human sexuality.
Related Channels
Other channels in the same section of the catalogue.
