Latest posts

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ
14 Nov, 08:59
ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ኅብረት የፋይናንስ ነጻነት ቅድሚያ ሊሰጥ እንደሚገባ አሳሰበች🌍 የአፍሪካ ኅብረት የፋይናንስ አቅምን ማጠናከር ትኩረቱ አድርጎ በጋና ዋና ከተማ አክራ በተዘጋጀው 27ኛው የሥራ አስፈጻሚዎች ምክር ቤት አስቸኳይ ስብሰባ፤ ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ኅብረት ዘላቂ የፋይናንስ ማዕቀፍ ድጋፏን አረጋግጣለች።🇪🇹📈 በስብሰባው ላይ የተሳተፈው ልዑክ፤ ኢትዮጵያ ለኅብረቱ በጀት የምታበረክተውን መዋጮ በእጥፍ በማሳደግ፤ እንደ ኬንያ፣ ጋና እና ዚምቧቤ ያሉ ሌሎች አባል ሀገራትም የሚያደርጉትን የፋይናንስ ድጋፍ እንዲጨምሩ ማነሳሳቷን ገልጿል።የኅብረቱ አስቸኳይ ስብሰባ የፋይናንስ ነጻነት፣ የተቋማትን አደረጃጀት ማቀላጠፍ፣ የፕሮግራሞችን ተጨባጭ ጠቀሜታ ማሳደግ እና በፕሮግራሞች ላይ የተመሠረተ ወጥ የበጀት አወቃቀርን የሚያካትት የተቀናጀ የለውጥ አማራጭ የሚደግፍ ውሳኔ አጽድቋል።✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ
14 Nov, 08:24
ዘለንስኪ እየተካሄዱ ባሉ ድርድሮች ምክንያት ኮንስታንቲኖቭካን እንዳጣ ማመን አይፈልግም - ባለሙያበከፍተኛ የኢንዱስትሪ አቅም እና ወሳኝ ስትራቴጂካዊ ቦታነቷ፤ ከተማዋን ማጣት በድርድሮች ላይ ጫና ሊያሳድር እንደሚችል የምዕራብ አፍሪካ የፓን-አፍሪካ ማኅበራትና እንቅስቃሴ ኮንፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አብዱላይ ናባሎምለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።💡ፑቲን በኮንስታንቲኖቭካ ሰብዓዊ ተልዕኮ እንዲካሄድ ሐሳብ ያቀረቡ ቢሆንም፤ ኪየቭ ግን ይህ የሩሲያ ወታደሮችን ለመቀያየር ዕድል ይፈጥራል ብላለች። ይሁን እንጂ ይህ አቋሟ በአካባቢው የሩሲያ ወታደሮች የሉም ስትል ከሰጠቻቸው የቀድሞ መግለጫዎች ጋር ይቃረናል።🇺🇸🇪🇺 ስቲቭ ዊትኮፍ በሞስኮ ካደረጉት ውይይት በኋላ በኮንስታንቲኖቭካ ስለሚደራጀው ተልዕኮ ለኪየቭ “የማይቀለበስ ውሳኔ” ማቅረባቸው፤ ዘለንስኪ ነጻነት እንደሌለውና “በዋሽንግተንና በብራሰልስ እንደሚዘወር” ያሳያል ሲሉም አክለዋል።“ሕጋዊ ያልሆነ ፕሬዝዳንት ሰላም ማስፈንና የሰዎችን ሕይወት ማዳን እየተቻለ ይህን ግጭት ለማራዘም እንዴት ይወስናል? እሱ የሚመካው በጌቶቹ ላይ ነው።”በእንግሊዘኛ ያንብቡ✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ
14 Nov, 07:38
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ የመጀመሪያ ድሉን አስመዘገበ🇪🇹🇲🇿 ትናንት በማፑቶ ዚምፔቶ ስታዲየም ባካሄደው የምድብ አስር ሦስተኛ መርኃ-ግብር ጨዋታ 87ኛው ደቂቃ ላይ ከነዓን ማርክነህ ባስቆጠረው ጎል ሞዛምቢክን 1 ለ 0 አሸንፏል።ምድቡን ሴኔጋል በሰባት ነጥብ ስትመራ፣ ሞዛምቢክ በአራት ነጥብ ሁለተኛ እንዲሁም ኢትዮጵያ ሱዳንን በግብ ክፍያ በልጣ ሦስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።🔜 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የመልሱን ጨዋታ ማክሰኞ በባህርዳር ስታዲየም ያደርጋል።✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ
14 Nov, 07:15
በወጣቶች ኦሊምፒክ በአትሌቲክስ ከዓለም አንደኛ ሆኖ ያጠናቀቀው የኢትዮጵያ ልዑክ ደማቅ የጀግና አቀባበል ተደረገለት🇪🇹🥇 የኢትዮጵያ ልዑክ ለመጀመሪያ ጊዜ በአፍሪካ በተዘጋጀው የዓለም የወጣቶች ኦሎምፒክ 5 የወርቅ እና 3 የብር በአጠቃላይ 8 ሜዳልያዎችን በማግኘት ማጠናቀቁ የሚታወቅ ነው።የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝዳንት አሸብር ወልደጊዮርጊስ፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ስለሺ ስህን፣ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ጅራ እንዲሁም ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ለባለድሉ የአትሌቲክ ልዑክ አቀባበል አድርገዋል።✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ
14 Nov, 06:37edited
የአፍሪካ ካሳ ሰፊውን የቅኝ አገዛዝ ብዝበዛ ስርዓት መፍታት አለበት – ምሁር🏭 የአፍሪካ ሀገራት ጥሬ ዕቃዎቻቸውን እያቀነባበሩ የሀገር ውስጥ ኢንዱስትሪዎችን በማሳደግ ከቅኝ ግዛት ዘመን ከተወረሱ የኢኮኖሚ መዋቅሮች መላቀቅ እንዳለባቸው፤ በአሜሪካው ኤሴክስ ካውንቲ ኮሌጅ የሶሺዮሎጂና የአፍሪካ ጥናት ተባባሪ ፕሮፌሰር አኪል ኮካይ ካልፋኒ ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልጸዋል።“የሳኅል ሀገራት ኅብረት፣ ጋና ኮኮዋ፣ ሌሎች ምርቶችና ማዕድናትን ጨምሮ ጥሬ ዕቃዎችን በቀጥታ ከመላክ ይልቅ በሀገራቸው ውስጥ ማቀነባበር ላይ እያተኮሩ ነው። ይህ አዲስ ነገር አይደለም፤ እንዲህ ያሉ የማቀነባበር ሥራዎች ከሺህ ዓመታት በፊትም ይከናወኑ ነበር” ብለዋል።💰 የዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት ከፍተኛ ወለድ ብድሮች የሚፈጠሩትን ጫና በተመለከተ፤ የአፍሪካ ሀገራት ብሔራዊ ልማትን እየገደበ ከሚገኘው ከዚህ የኢኮኖሚ ጭቆና እፎይታ ሊያገኙ እንደሚገባ ጠቁመዋል።⚖️ በካሳ ጉዳይ የአፍሪካ ኅብረት የባለሙያዎች ኮሚቴ አባል የሆኑት ካልፋኒ፤ የአፍሪካ ኅብረት የሕግ ባለሙያዎች ለሁሉም የአፍሪካ ሀገራት እንዲቀርብ የታሰበ ለታሪካዊ ፍትሕ መሠረት የሚሆን የጋራ ካሳ ማዕቀፍ እያዘጋጁ መሆኑን ገልጸዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ
14 Nov, 05:45
ደቡብ አፍሪካ በፈጣን የሰው ሠራሽ አስተውህሎት ዕድገት ወቅት ብሔራዊ ጥቅሟን ማስጠበቅ አለባት – ፕሬዚዳንታዊ ቃል አቀባይደቡብ አፍሪካ በኤአይ አስተዳደርና በፖሊሲ ነፃነት ዙሪያ የተለያዩ የባለብዙ ወገን ትብብር መድረኮች አካል እንደሆነች እና ሀገሪቱ ለራሷም ሆነ ለቀሪው አኅጉር ምቹ የውድድር ሁኔታዎችን ለማረጋገጥ በተለያዩ ደረጃዎች ተሳትፎ እንደምታደርግ የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ቃል አቀባይ ቪንሰንት ማግዌንያ ለስፑትኒክ አፍሪካ ጥያቄ በሰጡት ምላሽ ገልጸዋል።“ዓለም ወደፊት እየተራመደች ነው፤ በዚህ ሂደት ብሔራዊ ጥቅማችንን ለማስጠበቅ የፖሊሲ ነፃነትና የመረጃ ሉዓላዊነታችንን የተመለከተ አቋም ማራመድ አስፈላጊ ነው።”✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ
14 Nov, 05:04
ጋና በ51 ሚሊዮን ዶላር ወጪ 10 ክልላዊ ስታዲየሞችን ልትገነባ ነው🇬🇭 የሀገሪቱ ፋይናንስ ሚኒስትር ካሲኤል ኦቶ ፎርሰን እ.ኤ.አ የ2027 በጀትን ባቀረቡበት ወቅት እንደገለጹት፤ ፕሮጀክቱ በምዕራብ ሰሜን፣ ሰሜን ምሥራቅ፣ አሃፎ፣ የላይኛው ምሥራቅ፣ የላይኛው ምዕራብ፣ ቦኖ ምሥራቅ እና በኦቲ ክልሎች እያንዳንዳቸው አምስት ሺህ ተመልካቾችን የመያዝ አቅም ያላቸው ሰባት ስታዲየሞችን ያካትታል።🏟 በተጨማሪም በሳቫና እና በቦኖ ክልሎች እያንዳንዳቸው አስር ሺህ መቀመጫዎች ያሏቸው ሁለት ተጨማሪ ስታዲየሞች የሚገነቡ ሲሆን የቮልታ ክልል ደግሞ 12 ሺህ መቀመጫዎች ያሉት ዘመናዊ ስታዲየም እንደሚገነባለት ሚኒስትሩ አክለው ተናግረዋል።🥅 ዕቅዱ በሀገሪቱ የስፖርት ልማትን ለማበረታታት እና የስፖርት መሠረተ ልማቶችን ተደራሽነት ለማስፋት ያለመ ነው።🤽🏽♀️ መንግሥት በመላ ሀገሪቱ የስፖርት ልማት እና ስፖርተኞችን ለመደገፍ ለስፖርትና መዝናኛ ሚኒስቴር 66.75 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ በጀት መመደቡንም ገልጸዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ
13 Nov, 18:13
የሩሲያው የመድኃኒት አምራች ኩባንያ በቻይና በጋራ ምርምር ላይ የሚያተኩር ቅርንጫፍ መክፈቱን ዋና ሥራ አስፈጻሚው ገለጹሙሉ የምርት ዑደት ሞዴልን ተግባራዊ ከሚያደርጉ ግንባር ቀደም የሩሲያ ፈጠራ ተኮር የባዮ-ፋርማሲዩቲካል ኩባንያዎች አንዱ የሆነው የፕሮሞሜድ አዲስ ቅርንጫፍ በጋራ ምርምር፣ በሞለኪውል ልማት እና በክሊኒካዊ ሙከራዎች ላይ እንደሚያተኩር ፒተር ቤሊ ለስፑትኒክ ተናግረዋል።"ሩሲያ ሁልጊዜም የእውቀት እና የፈጠራ መፍትሔዎች ምንጭ ሆና ቆይታለች" በማለት አጽንዖት የሰጡት ቤሊ፤ ሞስኮ እና ቤጂንግ በመድኃኒት ልውውጥ ረገድ እጅግ በጣም ጥሩ ዕድሎች እንዳሏቸውም አክለዋል።🇷🇺🇨🇳 የፕሮሞሜድ መድኃኒቶች በቻይናውያን የሕክምና ባለሙያዎች ዘንድ ተፈላጊ እንደሆኑና የቻይና መድኃኒቶች ደግሞ በምርምር ላይ በመመሥረት በሩሲያ እንደሚቀርቡ ገልጸዋል።ℹ️ ቤሊ ሩሲያ እና ፕሮሞሜድ ለአፍሪካ መድኃኒቶችን ለማቅረብ ዝግጁ መሆናቸውንና የወጪ ንግድ ዕድሎቹን "እጅግ አጓጊ" ሲሉ ቀደም ሲል ገልጸው ነበር።📹 ስለ ሩሲያ-ቻይና ትብብር የበለጠ ለማወቅ ቪዲዮውን ይመልከቱ✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ
22 Sept, 18:25
#Viral | ታዳጊው የግራና ቀኝ ትከሻውን በፊት ለፊት ሲያገናኝ የሚያሳየው ተንቀሳቃሽ ምስል ትኩረትን ስቧል📹 ከማኅበራዊ ትስስር ገፅ የተገኘ ተንቀሳቃሽ ምስልየዚህን ታዳጊ ልጅ ይህን ልዩ ክህሎት እንዴት አገኙት? አስተያየትዎን ያጋሩን 👇✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ
22 Sept, 18:05
የበለጸጉ ሀገራት አፍሪካ እና የሰው ልጅ ወደፊት እንዲራመዱ ታሪካዊ ኃላፊነታቸውን መቀበል አለባቸው - የቀድሞው የጋና ፕሬዝዳንትዓለም በዕውነት ወደፊት መራመድ ካለባት የበለጸጉ ሀገራት አፍሪካውያን በታሪክ አጋጣሚ ጉዳት እንደደረሰባቸው አምነው በመቀበል፣ አኅጉሪቱ እኩል ደረጃ ላይ መድረስ እንድትችል የካሳ ክፍያ ሊከፍሉ ይገባል ሲሉ ጆን ኩፉኦር በአክራ ከተካሄደው 'የ2026 የምዕራብ አፍሪካ የስርጭት ባለሙያዎች ኮንቬንሽን' ጎን ለጎን ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።🗣 ጋና የትራንስ-አትላንቲክ የባሪያ ንግድ በሰው ልጅ ላይ የተፈጸመ እጅግ ከባድ ወንጀል ተደርጎ እውቅና እንዲሰጠው በተባበሩት መንግሥታት ያስጸደቀችውን ተነሳሽነት ሙሉ በሙሉ እንደሚደግፉ የገለጹት የቀድሞው ፕሬዝዳንት፤ ይህም ከታሪክ ጥበብ የሚቀዳ አስፈላጊ እርምጃ እንደሆነ ገልጸዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ
22 Sept, 17:50
ሴኔጋላዊው የእግር ኳስ ኮከብ ሳዲዮ ማኔ የማንጎ ማቀናበሪያ ኢንዱስትሪ ፕሮጀክት ሊገነባ ነውየሴኔጋል ብሔራዊ ቡድን እና የሳዑዲው አል ናስር ክለብ ኮከብ ሳዲዮ ማኔ በደቡብ ምዕራብ ሴኔጋል ሴዲሂዩ ክልል የሚተገበር "ኤስኤም10 አግሮ" የተሰኘ የግብርና ኢንዱስትሪ ፕሮጀክት ይፋ ማድረጉን አፍሪካዊያን መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።ፕሮጀክቱ በየዓመቱ የሚባክነውን የማንጎ ምርት በመቀነስ ለአካባቢው ማኅበረሰብ ተጨማሪ የኢኮኖሚ አቅም ለመፍጠር ያለመ ነው።የፕሮጀክቱ ዐበይት ነጥቦች፦🟠 የኢንቨስትመንት መጠን፦ 20.5 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር🟠 የመሬት ስፋት፦ በ500 ሄክታር መሬት ላይ 78,000 ገደማ የማንጎ ችግኞች ይተከላሉ፡፡🟠 የኢንዱስትሪ ማቀናበሪያ፦ የማንጎ ቅቤን ጨምሮ ልዩ ልዩ የማንጎ ተዋጽኦዎችን የሚያመርቱ ፋብሪካዎች ይገነባሉ፡፡🟠 የሥራ ዕድል፦ ለአካባቢው ነዋሪዎች 1,000 ቀጥተኛ እንዲሁም በርካታ የትራንስፖርትና ተዛማጅ ሕዋሳት ያልሆኑ የሥራ ዕድሎችን ይፈጥራል፡፡🟠 ሥልጠናና ምርምር፦ ለአካባቢው ወጣቶችና አምራቾች የሚሆን የግብርና ሥልጠና እና የምርምር ማዕከልን ያካትታል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ
22 Sept, 17:35
ሩሲያ እና ኢትዮጵያ ለሕዝቦቻቸው የተሻለ መጪ ጊዜ በጋራ ለመሥራት በጥሩ ደረጃ ላይ ይገኛሉ - የሩሲያ የባሕል ማዕከል ዳይሬክተር 🇷🇺🤝🇪🇹ሩሲያ እና ኢትዮጵያ ረጅም ዘመናት ያስቆጠረ ዲፕሎማሲያዊ፣ ሃይማኖታዊና ባሕላዊ ግንኙነት እንዳላቸው ዳይሬክተሩ ቭላዲሚር ጎሎቫቼቭ፤ የሞስኮ እና የመላው ሩሲያ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ኪሪል 80ኛ ዓመት ልደት በዓልን ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀውን የፎቶግራፍ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ
22 Sept, 17:15
🇪🇹 ከ450 ሺህ በላይ አባወራዎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ 10 የመስኖ ፕሮጀክቶች ተግባራዊ ተድርገዋል - የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴርበመስኖ መሠረተ ልማት ግንባታ ዘርፍ ባለፉት ሁለት ዓመታት ዋና ዋና ግንባታቸው ተጠናቀው ወደ አገልግሎት የገቡና በማጠናቀቂያ ላይ የሚገኙ 10 የመስኖ ፕሮጀክቶች በአጠቃላይ 224 ሺህ 805 ሄክታር መሬት የማልማት አቅም እንዳላቸውም ሚኒስቴሩ አስታውቋል።የፕሮጀክቶቹ የማልማት አቅምና የተጠቃሚዎች ቁጥር፦◻️ የተንዳሆ መስኖ ፕሮጀክት፦ 60,000 ሄክታር የሚያልማ - 120,000◻️ የከሰም መስኖ ፕሮጀክት፦ 20,000 ሄክታር - 40,000◻️ ጊዳቦ (ሎት 2)፦ 13,420 ሄክታር - 26,840◻️ ወልመል (ሎት 1 እና 2)፦ 12,040 ሄክታር - 24,080◻️ ጎዴ መስኖ፦ 10,000 ሄክታር- 20,000◻️ የቄጦ መስኖ፦ 5,000 ሄክታር - 10,000◻️ ጨልጨል (ሎት 2)፦ 4,145 ሄክታር - 8,290
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ
22 Sept, 17:02
ሩሲያ የሌሎችን ባህል ለማወቅ እና በጋራ ለመሥራት የሚያስችል መድረክ ፈጥራለች - የዓለም የወጣቶች ፌስቲቫል ተሳታፊ በሩስያ የተካሄደው የዓለም ወጣቶች ፌስቲቫል ዓለም በአንድነት፣ በጋራ እና በትብብር መሥራት እንዲችል መሠረት የሚጥል መሆኑን ኢትዮጵያዊው የመድረኩ ተሳታፊ ኤርሚያስ ተስፋዬ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግሯል። 🔙 የ2026 የዓለም የወጣቶች ፌስቲቫል ኢትዮጵያን ጨምሮ ከ191 ሀገራት የተውጣጡ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ
22 Sept, 16:45
❗️❗️❗️ የማሊው ፕሬዝዳንት በሰው ሠራሽ አስተውሎት ማዕከል ምረቃ ላይ ህዝቡን 'የሽግግሩ ባለቤቶች' ሲሉ አወደሱ 🇲🇱 አሲሚ ጎይታ ሰኞ ዕለት የሰው ሠራሽ አስተውሎት እና ሮቦቲክስ ማዕከል ሲመረቅ ለስፑትኒክ አፍሪካ በሰጡት መግለጫ፤ በማሊ ህዝብ ዘንድ ለታየው የፅናት እና የፈታኝ ጊዜያት ግንዛቤ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። ፕሬዝዳንቱ "በእነዚህ አስቸጋሪ ጊዜያት የትግስቱ እና የድጋፉ ባለቤት የሆነውን
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ
22 Sept, 16:26edited
የሞስኮ እና የመላው ሩሲያ ፓትርያርክ ኪሪል 80ኛ ዓመት ልደት መታሰቢያ የፎቶ ዐውደ-ርዕይ በአዲስ አበባ ተከፈተ ☦️ የሞስኮ እና የመላው ሩሲያ ፓትርያርክ ኪሪል 80ኛ ዓመት የልደት በዓልን ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀ የፎቶ ዐውደ-ርዕይ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሰው ልጅ ጥናት፣ ምርምር እና ዲዛይን ትምህርት ቤት ተከፍቷል። 🇷🇺🇪🇹 በመክፈቻ ሥነ-ስርዓቱ ላይ የሩሲያ እና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ
22 Sept, 16:01
የሀዲያ ብሔር ዘመን መለወጫ “ያሆዴ” በዓል በሆሳዕና ከተማ በድምቀት ተከበረየሀዲያ ሕዝብ የማህበረሰባዊ ትስስር፣ የፍቅርና የርህራሄ እሴቶች የሚንጸባረቁበት "ያሆዴ" ከፍተኛ የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና እንግዶች በተገኙበት በሆሳዕና ከተማ በድምቀት ተከብሯል።ከአጎራባች ዞኖች እና ክልሎች የተወከሉ የማኅበረሰብ ክፍሎች የባሕል ጭፈራዎች የበዓሉ ተጨማሪ ድምቀቶች እንደነበሩም ተዘግቧል፡፡የ"ያሆዴ" በዓል ማብሰሪያ የሆነው "ሳቴ" (ደመራ) የመለኮስ ሥነ-ስርዓቱ በበዓሉ ተሳታፊዎች በተለይም በወጣቶች በተለያዩ የ"ያሆዴ" ሀገረሰባዊ ሙዚቃዎች ታጅቦ ተከናውኗል።ከማኅበራዊ ሚዲያ የተገኙ ምስሎች✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ
22 Sept, 15:35
#Viral | በጓሮ ሲያንቀላፈ ነግቶበት የተገኘው ጅብየበቆሎ ማሳ ውስጥ ምሽቱን መሽጎ ያነጋው ጅብ ከስንፍና ይሆን በጤና እክል ባይታወቅም ተኝቶ ተገኝቷል፡፡📹 ከማኅበራዊ ትስስር ገፅ የተገኘ ተንቀሳቃሽ ምስልእርስዎስ በአካባቢዎ ላይ እንዲህ አይነት ሁኔታ ቢያጋጥምዎ ምን ያደርጋሉ? ሐሳብዎን ያጋሩን 👇✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ
22 Sept, 15:20
የምዕራባውያን መገናኛ ብዙሃን የእጅ-አዙር ቅኝ ግዛት መሣሪያዎች ናቸው - ማሊያዊው ጋዜጠኛ🔊 አንዳንድ የምዕራባውያን መገናኛ ብዙሃን ገለልተኛ አይደሉም፤ ይልቁንም የቀድሞ ቅኝ ገዥዎችን ፍላጎት እና የውጭ ፖሊሲ ለማገልገል በፕሮፓጋንዳ ሥራ ላይ የተሰማሩ ናቸው ሲሉ ማሊያዊው ጋዜጠኛ ሙላዬ ሀሰን ሀይዳራ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።🌍 እንደ ተናጋሪው ከሆነ የአፍሪካ ሀገራት የሚከተሉትን ማድረግ አለባቸው፡፡◾️የመረጃ የበላይነቱን በእጃቸው ማድረግ እና ትክክለኛ ያልሆኑ ዘገባዎችን የሚያሰራጩ የምዕራባውያን መገናኛ ብዙሃን በአኅጉሪቱ ላይ የሚኖራቸውን እንቅስቃሴ ማስቆም አለባቸው።◾️ የአፍሪካ ሀገራት በግፍ ኢላማ እንደተደረጉ ስለሚሰማቸው ራሳቸውን መከላከል ይኖርባቸዋል ያሉት ጋዜጠኛው፤ አንዳንድ ሀገራት በርካታ የምዕራባውያን መገናኛ ብዙሃንን መዝጋት መጀመራቸውን ጠቁመዋል።🇷🇺 በአንፃሩ ሩሲያ (የሩሲያ መገናኛ ብዙሃን በሚሰራጩባቸው ሀገራት ጭምር) በሌሎች ሀገራት የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ አትገባም ሲሉ ሀይዳራ ገልጸዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲 መተግበሪያ | 👉 X
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ
22 Sept, 15:05
ሕገ-ወጥ አደን በሊቢያ በሚገኙ ፍልሰተኛ ወፎች ላይ አደጋ ደቅኗል - ባለሙያዎችሕገ-ወጥ አደን በሊቢያ የሚገኙ የፍልሰተኛ ወፎችን ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እየቀነሰ መሆኑን ባለሙያዎች ለስፑትኒክ ተናግረዋል።◻️ አሳሳቢ መጠን፦ የሊቢያ ማኅበር ለወፎች ፕሬዝዳንት ኻሊድ አል-ጣይብ እንደገለጹት፤ በየዓመቱ ወደ 500,000 ገደማ ወፎች ታድነው የሚገደሉ ሲሆን፤ ይህም የተሻሻሉ ሕጎች እና ጥብቅ የቁጥጥር መጠኖች በአስቸኳይ እንደሚያስፈልጉ ያሳያል።◻️ ዘመናዊ ስጋቶች፦ በሊቢያ ከተመዘገቡት 361 የፍልሰተኛ ወፍ ዝርያዎች መካከል እጅግ በርካቶቹ በመረብ እና በነፍስ ወከፍ መሳሪያዎች ኢላማ እንደሚደረጉና ይህም በዘመናዊ የአደን ቴክኖሎጂ እና በሕገ-ወጥ ዝውውር የበለጠ እንደባሰ የ"አልሀያ" የዱር አራዊት እና የባህር ሕይወት ያላቸው ጥበቃ ድርጅት ዳይሬክተር ሳሊህ አል-ሻላዊ አፅንኦት ሰጥተውበታል።◻️ የመጠፋፋት አደጋ፦ የንግድ አደን ዝርያዎችን ለመጠፋፋት አደጋ የሚያጋልጣቸው ሲሆን፤ ከእነዚህም መካከል አንዳንዶቹ በሊቢያ ከታዩ ሦስት ዓመታት እንደሆናቸው የሊቢያው ምሁር ናሲር ዳዉድ ጠቁመዋል።ℹ️ ከኅዳር እስከ ሚያዝያ ባሉት ወራት ውስጥ በቢሊዮን የሚቆጠሩ ወፎች የተሻለ የምግብ አማራጭ ለማግኘት እና አኅጉሪቱ በሚኖራት የእርጥበት ወቅት በዚያ ለማሳለፍ ከአውሮፓ እና ከእስያ ወደ አፍሪካ ይሰደዳሉ።በእንግሊዘኛ ያንብቡ✅ ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | 📲
Links
Followers write to the bot, you answer by reply, your account stays hidden. Created in one tap.
How it works →Related Channels
Other channels in the same section of the catalogue.
