gram news
tewhidnasuna channel avatar

tewhidnasuna

@tewhidnasuna

ቁርአንና ሐዲስን በሰለፎች ግንዛቤ ለመረዳት የሚያስችሉ ተውሂድ፣ሲራ አጠር አጠር ያሉ የነብዩ ﷺ ሓዲሶችን እና የሰለፎችን ንግግሮች የሚያገኙበት ቻናል ነው።ቻናሉን ይቀላቀሉ ኪታቦችን ይቅሩ

ProjectsENReligion

24,500subscribers

Open the Channel

Latest posts

  • tewhidnasuna

    23 Sept, 03:52edited

    ሁሉም ነፍስ ሞትን ትቀምሳለች እኛ ግን ዘንግተናታል።
    569video9Open in Telegram
  • tewhidnasuna

    22 Sept, 16:43

    ፈጥኖ ማን ይመልስ ! ✈️✈️ትክክለኛውን መልስ ያገኝ ሰው add የሚለውን በመጫን ስጦታ ያገኛል።📝 ጥያቄጂብሪል ዐለይሂ ሰላም ስንት ክንፎች አሉት ?
  • tewhidnasuna

    22 Sept, 05:17edited

    "የጊዜ ሰይፍ" ​ነቢዩ ሙሐመድ (ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፦ ​«ሁለት ጸጋዎች አሉ፤ በርካታ ሰዎች በእነርሱ ይታለላሉ (ዋጋቸውን አይረዱትም)፦ ጤና እና (ትርፍ ጊዜ) ናቸው።» (ቡኻሪ ዘግበውታል) ​💡 ትልቅ ትምህርት በትንሹ ​ጊዜ አይመለስም፦ ያለፈችው እያንዳንዷ ሰከንድ ከሕይወታችን የተቀነሰች ገፅ ናት። ​ትርፍ ጊዜህን ባዶ አታድርገው፦ አላህን በማውሳት፣ ጠቃሚ እውቀት በመቅሰም ወይም ቤተሰብንና ሰዎችን በመርዳት አሳልፈው። ​ጤናህን ተጠቀምበት፦ መቆምና መስገድ የምትችለው፣ መፆም የምትችለው ዛሬ ጤና እያለህ ነው። ነገ በህመም ወይም በእድሜ መግፋት ምክኒያት ሳትፈልግ ልትገደብ ትችላለህ። ​✨ የዕለቱ መልእክት፦ "ጊዜ ሰይፍ ነው፤ ካልቆረጥከው ይቆርጥሃል። ዛሬ የምትዘራውን ነገ ታጭዳለህና አሁን የምታሳልፍባትን እያንዳንዷን ሰከንድ ለነገው ዓለምህ ስንቅ አድርጋት!"
    1,33017Open in Telegram
  • tewhidnasuna

    21 Sept, 15:25

    ጥያቄ ? 📮📮ትክክለኛውን መልስ ያገኝ ሰው add የሚለውን በመጫን ስጦታ ያገኛል።📝 ጥያቄአል አቅሷ መስጂድን የገነባው ነብይ ማን ነው ?
  • tewhidnasuna

    21 Sept, 11:43edited

    ቃኢዳን በአማርኛ
    Image from a post by tewhidnasunaImage from a post by tewhidnasuna
  • tewhidnasuna

    20 Sept, 18:49

    "ነገ ሰኞ ነው የቻለ ይፁም ያልቻለ ያስታውስ#ሼር ያድርግ
    1,79028Open in Telegram
  • tewhidnasuna

    20 Sept, 17:42edited

    🕌ከውዱዑ በኋላ የሚሰገድ ሁለት ረከዓ ያለው ትልቅ ምንዳ!ረሱል (ሰዐወ) እንዲህ ብለዋል፦﴿مَن تَوَضَّأَ نَحْوَ وُضُوئِي هذا، ثُمَّ صَلّى رَكْعَتَيْنِ لا يُحَدِّثُ فِيهِما نَفْسَهُ، غُفِرَ له ما تَقَدَّمَ مِن ذَنْبِهِ﴾👉“ውዱዑን አሳምሮ ያደረገ፤ ልክ እኔ እደማረገው አይነት ውዱዑ ከዛም በውስጡ ነፍሱን ሳያወራ (ሳይወሰወስ) ሁለት ረከዓ የሰገደ፤ ያለፈው (ጥቃቅን) ወንጀሎቹ ይማርለታል።”📚ቡኻሪ (159) ሙስሊም (226) ዘግበውታል
    1,87013Open in Telegram
  • tewhidnasuna

    20 Sept, 08:10

    ተውሂድ ማለት በቋንቋ ደረጃ «አንድ ማድረግ» ወይም «ብቸኛ ማድረግ» ማለት ሲሆን፣ በሸሪዓ (በእስልምና ህግ) ትርጉሙ ደግሞ አላህን በጌታነቱ፣👉በአምልኮቱ እንዲሁም በስሞቹና በባህሪያቱ ብቻውን ማድረግ (ማንኛውንም አጋር አለማቀላቀል) ማለት ነው።​ ተውሂድ በሦስት ዋና ዋና ክፍሎች ይከፈላል፦👉​ተውሂዱ አር-ሩቡቢያህ (የጌታነት ተውሂድ)፦ አላህ በፈጣሪነቱ፣ በሲሳይም ሰጪነቱ፣ በሁሉም ነገር ላይ አዛዥና አስተዳዳሪነቱ ብቻውን እንደሆነ ማመንና መመስከር ነው።👉​ተውሂዱ አል-ኡሉሂያህ (የአምልኮ ተውሂድ)፦ ማንኛውንም የአምልኮ ዓይነት (እንደ ዱዓ፣ ሰላት፣ እርድ፣ ስለት፣ ተወኩል ወዘተ) ለአላህ ብቻ ማድረገና ከእሱ ውጭ ላለ ማንኛውም አካል አለመገዛት ነው።👉​ተውሂዱ አል-አስማእ ወስ-ሲፋት (የስሞችና የባህሪያት ተውሂድ)፦ አላህ በቁርዓን ወይም ነቢዩ (ሶ.ዐ.ወ) በሐዲስ የገለጹትን የአላህ ስሞችና ባህሪያት ያለ ቅርጽ ማመሳሰል (ተሽቢህ)፣ ያለ ማስተባበል (ተዕጢል) እና ያለ ትርጉም ማዛባት (ታዕዊል) እንዳሉ አምኖ መቀበል ነው። ​የተውሂድ ጥቅሞች👉​የሰው ልጅ የተፈጠረበት አላማ ነው፦ አላህ ሰዎችንና ጂኖችን የፈጠረበት ዋና ምክንያት እሱን ብቻ እንዲገዙና ተውሂድን እንዲተገብሩ ነው።👉​የስራዎች ሁሉ መቅበያ መስፈርት ነው፦ ማንኛውም መልካም ስራ በአላህ ዘንድ ተቀባይነት የሚያገኘው በተውሂድ ላይ ከተመሰረተ ብቻ ነው።👉​የጀነት መግቢያና ከእሳት መዳኛ ነው፦ ተውሂድን ጠብቆ የሞተ ሰው የጀነት መግቢያ መንገድ ይከፈትለታል።
    2,00014Open in Telegram
  • tewhidnasuna

    19 Sept, 14:58

    የምሽት አዝካሮች (አዝካሩል መሳእ) የሚከተሉት ናቸው። እነዚህን አዝካሮች በየቀኑ ምሽት (ከዐስር ሶላት በኋላ እስከ መግሪብ ወይም ከኢሻእ በፊት ባለው ጊዜ) ማለት ትልቅ ጥበቃና አጅር ያስገኛል፦ ​1. አያተል ኩርሲይ (አንድ ጊዜ) ​«اللَّهُ لَا إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ الْحَيُّ الْقَيُّومُ...» (አል-በቀራህ፡ 255) ​ጥቅሙ፦ እስከ ጠዋት ድረስ ከአሸይጣን ጥበቃ ይሆንልሃል። ​2. ሱረቱል እክላስ፣ አል-ፈልቅ እና አን-ናስ (3 ጊዜ) ​ሱረቱል እክላስ (ቁል ሁወላሁ አሐድ) — 3 ጊዜ ​ሱረቱል ፈልቅ (ቁል አዑዙ ቢረቢል ፈልቅ) — 3 ጊዜ ​ሱረቱል ናስ (ቁል አዑዙ ቢረቢን-ናስ) — 3 ጊዜ ​ጥቅሙ፦ ከማንኛውም ጎጂ ነገር ሁሉ በቂ ጥበቃ ይሆናሉ። ​3. ሰይዱል እስቲግፋር (የምህረት መጠየቂያ መሪ) (አንድ ጊዜ) ​«اللَّهُمَّ أَنْتَ رَبِّي لَا إِلَٰهَ إِلَّا أَنْتَ، خَلَقْتَنِي وَأَنَا عَبْدُكَ، وَأَنَا عَلَىٰ عَهْدِكَ وَوَعْدِكَ مَا اسْتَطَعْتُ، أَعُوذُ بِكَ مِنْ شَرِّ مَا صَنَعْتُ، أَبُوءُ لَكَ بِنِعْمَتِكَ عَلَيَّ، وَأَبُوءُ بِذَنْبِي فَاغْفِرْ لِي فَإِنَّهُ لَا يَغْفِرُ الذُّنُوبَ إِلَّا أَنْتَ» ​(አላሁመ አንተ ረቢ ላ ኢላሀ ኢላ አንተ፣ ኸለቅተኒ ወአና ዐብዱከ፣ ወአና ዐላ ዐህዲከ ወወዕዲከ መስ-ተጠዕቱ፣ አዑዙ ቢከ ሚን ሸሪ ማ ሶነዕቱ፣ አቡኡ ለከ ቢኒዕመቲከ ዐለየ፣ ወአቡኡ ቢዘንቢ ፈግፊር ሊ፣ ፈኢነሁ
    1,96014Open in Telegram
  • tewhidnasuna

    18 Sept, 14:37edited

    ሌትም ቀንም ይቺን ዚክር ያለ ሰው ጀነት ገባ ሰይዱል እስቲግፋር ረሱል ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇اللهم أنْتَ رَبِّي لَا إلَهَ إلَّا أنْتَ، خَلَقْتَنِي وَ أنَا عَبْدُكَ، وَ أنَا عَلَى عَهْدِكَ وَ وَعْدِكَ مَا اسْتَطَعْتُ، أعُوذُ بِكَ مِنْ شَرِّ مَا صَنَعْتُ، أبُوءُلَكَ بِنِعْمَتِكَ عَلَيَّ، وَ أبُوءُ بِذَنْبِي فَاغْفِرْ لي فَإنَّهُ لَا يَغْفِرُ الذُّنُوبَ إلَّا أنْتَ.አላህ ሆይ አንተ አምላኬ ነህ፡፡ ከአንተ ውጭ ሌላ አምላክ የለም፡፡ ፈጥረህኛል፡፡ እኔ ባሪያህ ነኝ፡፡ እኔ የቻልኩትን\ያክል ያንተን ቃልዳኪን ለመሙላት እሞክራለሁ፡፡ ከስራሀው ነገር ከክፉው በአንተ እጠበቃለሁ፡፡\በኔ ላይ ለዋልከው ጸጋህ እውቅና እሰጣለሁ፡፡ ሐጢአቴም እናዘዛለሁ፡፡ ማረኝ፡፡ ከአንተ ውጭ ሐጢአትን የሚምር የለም፡፡ �አልሏሁምመ አንተ ረብቢ ላኢላህ ኢልላ አንተ፤ ኸለቅተኒ ወአነ ዐብዱከ ወአነ ዐለ ዐሕዲከ ወወዐዲከ መስተጠዕቱ አዑዙ ቢከሚን ሸርሪ ማስነዐቱ አቡዑ ለከ ቢኒዐመቲክ ዐለይየ ወአቡኡ ቢዘንቢ ፈግፈርሊ ፈኢንነሁ ላየግፍሩዝኑቡ ኢልላ አንተ
    2,25030Open in Telegram
  • tewhidnasuna

    18 Sept, 09:02

    ♦️ከጁሙዓ ቀን ሱናዎች ▪️ገላን መታጠብ ▪️ጥሩ ልብስ መልበስ ▪️ሽቶ መቀባት(ለወንዶች ብቻ) ▪️በጊዜ ወደመስጂድ መሄድ ▪️በነብዩ - ﷺ - ላይ ሰለዋት ማብዛት ▪️ሱረቱል ከህፍን መቅራት ▪️ዱዓ የሚያገኝበትን ሰአት መጠባበቅ _ 🔻በተጨማሪ አርፍደው ከመጡ የሰው ትከሻ ላይ እየተረማመዱ ሶፍ ውስጥ ከመግባት መቆጠብ, ኹጥባን በጥሞና ማዳመጥ, ሌላ ሰው ቢያወራም ዝምበል አለማለት እና ሶላት ካለቀ በኋላ ያመለጣቸውን ሰዎች ሶላት ሳይቆርጡ ረጋ ብሎ መውጣት ያስፈልጋል። ____ ©ዲን መመካከር ነው
    2,24016Open in Telegram
  • tewhidnasuna

    17 Sept, 08:39

    Image from a post by tewhidnasunaImage from a post by tewhidnasuna
    2,83038Open in Telegram
  • tewhidnasuna

    17 Sept, 07:40edited

    ቃኢዳ በአማርኛ
    2,75029Open in Telegram
  • tewhidnasuna

    16 Sept, 15:16

    Image from a post by tewhidnasunaImage from a post by tewhidnasuna
    2,89032Open in Telegram
  • tewhidnasuna

    16 Sept, 07:48edited

    የማለዳ መልእክት (49) ~ ልጆቻችን አካዳሚ ትምህርት መማራቸው እና በዚህ ላይ መጎበዛቸው ይበል የሚያሰኝ ነው። በዚህ ላይ ማገዝና ሞራል መስጠትም ተገቢ ነው። ይሄ የሚሆነው በዲናዊ ትምህርት ሂሳብ ከሆነ ግን ትርፍ ሳይሆን ኪሳራ ነው።ልጆቻችን ሶላት ይሰግዳሉ ወይ? ቁርኣን እና ሌሎችም ኢስላማዊ ትምህርቶችን ይማራሉ ወይ? በዚህ በኩል ከሌሉ በአካደሚ ትምህርት ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገባቸው ትርጉም የለውም። እንዲያውም ሊጎዳቸው ይችላል። ዲናቸውን ካላወቁ በየትምህርት ዓይነቶቹ ውስጥ የተሰነቀሩ ብልሹ አስተሳበቦችን ሳያመዛዝኑ ይውጣሉ። የዲንን ዋጋ እና የአለማመንን አደጋ በቅጡ ስለማይለዩ እንደዋዛ ከኢስላም ሊወጡ ይችላሉ። ስማቸው የሙስሊም የሆኑ ግን ሙስሊም ያልሆኑ ምሁራን በየዩኒቨርሲቲው ውስጥ አሉ። የአካደሚ ትምህርት ደረጃቸው የሚያላብሳቸው ትእቢት ስላለ ምክር ለመስማትም ዝግጁ አይደሉም። (አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ስማቸው የሙስሊም የሆኑ፣ ግን ከነ ጭራሹ እስልምና ውስጥ የሌሉ፣ ሰው ግን ሙስሊም አድርጎ የሚያስባቸው ሁለት ዶክተሮችን አውቃለሁ።)በሃገር አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያመጡ ልጆችን ማበረታታትና መሸለም ጥሩ ሆኖ ሳለ መነጋገሪያ ያደርግንበት መንገድ ግን በጣም የተጋነነ ነው። ቁርኣን ሒፍዝ የጨረሱ፣ በተለያዩ ሃገራት ለአመታት ተንከራተው ጥሩ የዒልም ደረጃ ላይ የደረሱ ደረሶችን ግን ዞሮም የሚያያቸው የለም። ከስር እየመጡ ላሉት ተተኪዎች ምንድነው እያስተላለፍን ያለነው? ይህንን የተራራቀ አቀራረባችንን እያዩ ለዲናቸው ትኩረት ይሰጣሉ ወይ?የዲን ትምህርት ለምን
  • tewhidnasuna

    15 Sept, 18:29

  • tewhidnasuna

    14 Sept, 14:02

    3,620poll22Open in Telegram
  • tewhidnasuna

    14 Sept, 04:38

    ​«ጌታዬ ሆይ! የቁርኣንን በረካ፣ የቁርኣን መጅሊሶችን እና የቁርኣን ወዳጅነትን አትንሳን። »
    Image from a post by tewhidnasunaImage from a post by tewhidnasuna
    3,56045Open in Telegram
  • tewhidnasuna

    13 Sept, 14:37

    የድሮ ስርዓት ናፋቂው የከላላ ከተማ ከንቲባው ህገ ወጥ እስርና ወከባ!የከላላ ከተማ ከንቲባ አቶ አስናቀ ጥላሁን የክርስትና እምነት ተከታይ ናቸው። ከላላ በአብዛኛው ሙስሊም ማህበረሰብ ያለበት ከተማ ቢሆንም የህዝበ ክርስቲያኑ መብት ተከብሮ የሚኖርበት አካባቢ መሆኑ ይታወቃል። ከዚህ በተቃራኒው በሙስሊሙ ማህበረሰብ የውስጥ ጉዳዮች ውስጥ ጣልቃ በመግባት የኢስላማዊ ዳዕዋ ይዘትን ጭምር ካልወሰንኩና ለምን ዳዕዋ ታደርጋለህ በሚል ከንቲባው የመጅሊስ አባል የሆነውን ወንድም ኢዘዲን ሻፊን አስሮና አስፈራርቶ ከለቀቀው በኋላ በድጋሜ ሌሎት 5:00 አፍነው ለመውሰድና ለመግደል ሙከራ ቢያደርጉም አልሳካላቸው ሲል የከለላ ከተማ መጅሊስ ም/ኃላፊ የሆነውን ሸህ ሙሀባ ሰኢድን አስረውት የወገኛሉ።የከተማው ከንቲባ ይህንን ኢህገመንግስታዊ፣ አሳፋሪና ህዝብን የሚያቃቅር ተግባር በአስቸኳይ እንዲያቆሙና ሸህ ሙሀባ ሰኢድን በአስቸኳይ ከእስር እንዲለቁት እንጠይቃለን!የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤትም በየደረጃው ከሚገኙ የመንግስት አመራር ጋር በመነጋገር መሠል ድርጊቶችን እንዲቃወምና የወንድማችንን መብትና የመጅሊስ ክብር እንዲያስጠብቅ እንጠይቃለን።ከከላላ ሙስሊሞች
    3,39014Open in Telegram
  • tewhidnasuna

    12 Sept, 03:31edited

    ጭንቅ ጥብብ ብሎሃል ብሎሻል እንግዲያውስ እናዳምጣው
    3,790video33Open in Telegram