gram news
TIKVAH-MAGAZINE channel avatar

TIKVAH-MAGAZINE

@tikvahethmagazine

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያና የመረጃ መለዋወጫ መድረክ ነው። በ +251913134524 ላይ ያግኙን። ለማስታወቂያ @tikvahmagbot ላይ መረጃ ይጠይቁ።

ProjectsENReligion

193,000subscribers

Open the Channel

Latest posts

  • TIKVAH-MAGAZINE

    20 Sept, 11:45

    #እንድታውቁት: የቀድሞ የይዞታ ካርታ እያለ አዲስ ሕጋዊ የካዳስተር ምዝገባ ለምን ያስፈልጋል?የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ የቀድሞ የይዞታ ካርታ ያላቸው ባለይዞታዎች አዲሱን ሕጋዊ የካዳስተር ምዝገባ ማካሄድ ለምን እንደሚያስፈልጋቸው በሚል በገጹ ያቀረበውን መረጃ እንናጋራችሁ።ኤጀንሲው እንዳስታወቀው አዲሱ ምዝገባ የቀድሞውን ሰነድ ለመሻር ወይም ተመሳሳይ መብትን ለሁለተኛ ጊዜ ለመስጠት ሳይሆን፣ ያለውን የይዞታ መረጃ በዘመናዊና በተደራጀ የካዳስተር ሥርዓት ማረጋገጥን ዓላማ ያደረገ ነው።የመብት ሰጪ እና የመዝጋቢ ተቋማት ልዩነትነባሩ ካርታ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የመሬት ተጠቃሚነት መብት ሲፈቅድ የሚሰጠው የፈቃድ ሰነድ ሲሆን፤ በአዋጅ ቁጥር 1381/2017 መሠረት የመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ የሚሰጠው የካዳስተር ሰርተፊኬት ደግሞ የመሬቱ ወሰን በጂፒኤስ (GPS) እና በኦርቶ ፎቶ ቴክኖሎጂ ተለክቶ የመሬቱና የንብረቱ ባለቤትነት በሕግ መረጋገጡን የሚያሳይ የዋስትና ሰነድ ነው።አዲሱ የካዳስተር ምዝገባ የሚያካትታቸው ዝርዝሮችአዲሱ ሥርዓት የመሬት መብት፣ ክልከላ እና ኃላፊነትን በአንድ ላይ የሚያደራጅ ሲሆን የሚከተሉትን ያካትታል፦ የቁራሽ መሬቱ ትክክለኛ ወሰን፣ ስፋት፣ ርዝመት፣ ቅርጽና የኮኦርዲኔት መረጃ የወሰን መገናኛ ነጥቦች፣ የአጎራባች ይዞታዎች፣ የመንገድና የአድራሻ መረጃ
    Image from a post by TIKVAH-MAGAZINEImage from a post by TIKVAH-MAGAZINE
    23,000107121010Open in Telegram
  • TIKVAH-MAGAZINE

    20 Sept, 11:44

    ሀገራዊና አለማቀፋዊ እድሎችን ዩዝ ቱዩዝን ተቀላቅለው ይከታተሉ። በቻናሉ የየትምህርት ፣ ዓለም አቀፍ ስብሰባዎችና መድረኮች፣ የስራ፣ የስልጠና፣ የበጎ ፍቃድ ስራ እንዲሁም ሌሎች ዕድሎችም ይቀርቡበታል፡፡ቴሌግራም ቻናል ይጫኑ 👉🏼 @y2123 እኛ ሌሎችን ከፍ በማድረግ እንነሳለን !
    Image from a post by TIKVAH-MAGAZINEImage from a post by TIKVAH-MAGAZINE
  • TIKVAH-MAGAZINE

    20 Sept, 11:44

    ኢትዮጵያ በቴምር ልማት መስክ ያላትን እምቅ አቅም የምታሳይበት ሁለተኛው ዓለም አቀፍ የቴምር ፌስቲቫል በይፋ ተጀምሯል!የልምድ ልውውጦች፣ ሳይንሳዊ ውይይቶች እና የላቁ የግብርና ፈጠራዎች የቀረቡበትን ይህን ታላቅ ሁነት በአፋር ሰመራ አሰብ ሆቴል ይጎብኙ።📅 ቀን፦መስከረም 10 - 12፣ 2019 ዓ.ም. 📍 ቦታ፦ አፋር፣ ሰመራ — አሰብ ሆቴል#DatePalmFestivalEthiopia #AfarDatePalm #KhalifaAward #AgriculturalInnovation #EthiopiaEvents
    Image from a post by TIKVAH-MAGAZINEImage from a post by TIKVAH-MAGAZINE
    20,0001641Open in Telegram
  • TIKVAH-MAGAZINE

    19 Sept, 16:15

    አሜሪካ ለሶማሊያ ሰላም አስከባሪዎች የሚደረገው የሎጅስቲክስ ድጋፍ የሚቆምበትን ጊዜ አራዘመችአሜሪካ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሶማሊያ ድጋፍ ቢሮ (UNSOS) በኩል ለአፍሪካ ህብረት የሶማሊያ ሰላም ማስከበር ተልዕኮ (AUSSOM) የሚደረገውን የሎጅስቲክስ ድጋፍ ለማቋረጥ የያዘችውን የጊዜ ገደብ ለተጨማሪ አንድ ዓመት ለማራዘም ተስማምታለች።አሜሪካ ለዲፕሎማቶች ባሰራጨችው ረቂቅ ሰነድ መሠረት፣ በሶማሊያ የሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የድጋፍ ቢሮ ለአንድ ዓመት በሚቆይ የደረጃ በደረጃ ቅነሳ ሂደት አልፎ ሙሉ በሙሉ እንዲዘጋ ተስማምታለች።ይህ ውሳኔ ድጋፉ እ.ኤ.አ. በታህሳስ 2026 ማብቂያ ላይ በድንገት ይቋረጣል ተብሎ የተደቀነውን ስጋት ያስቀረ ነው ተብሏል።የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ዋሺንግተን ወደፊት ቢሮውን ሥራ በገንዘብ እንደማትደግፍ ገልጸው፣ የቅነሳው ዝርዝር ሂደት በታህሳስ ወር በሚካሄደው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ስብሰባ እንደሚወሰን አስረድተዋል።ቢሮው በየዓመቱ እስከ 500 ሚሊዮን ዶላር የሚደርስ በጀት ያለው ሲሆን፣ ለአፍሪካ ህብረት ሰላም አስከባሪዎች የምግብ፣ የውሃ፣ የነዳጅ፣ የሕክምና እና የትራንስፖርት አቅርቦቶችን ያመቻቻል።የደህንነት ተንታኞች እንደሚሉት ከሆነ የሎጅስቲክስ ድጋፉ መቋረጥ የአፍሪካ ህብረት ሰላም አስከባሪ ኃይልን ህልውና አደጋ ላይ የሚጥልና አል-ሸባብን በመታገል ላይ የሚገኘውን የሞቃዲሾ መንግሥት ሊያዳክም ይችላል የሚል ስጋት አስቀምጠዋል።አሜሪካ ባለፈው ዓመት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ለአፍሪካ
    Image from a post by TIKVAH-MAGAZINEImage from a post by TIKVAH-MAGAZINE
    22,20045Open in Telegram
  • TIKVAH-MAGAZINE

    19 Sept, 16:14

    የጉግል ምርት የሆነው «ጀሚኒ» ኤአይ የሦስት ኩባንያዎችን የሳይበር ደህንነት መጣሱ ተገለጸ።የጉግል የሰው ሠራሽ አስተውሎት ሞዴል የሆነው "ጀሚኒ" የሳይበር ደህንነት ብቃቱ በሚፈተሽበት ወቅት ያለምንም የሰው ልጅ ትዕዛዝ በራሱ ተነሳሽነት የሦስት ኩባንያዎችን የደህንነት ከለላ ሰብሮ መግባቱን ዎልስትሪት ጆርናል መዘገቡን ተከትሎ የዕለቱ መነጋገሪያ ዜና ሆኗል።በግንቦት ወር በተካሄደው በዚህ ሙከራ ጀሚኒ ለሕዝብ ይፋ የሆኑ መረጃዎችን እና የይለፍ ቃላትን በመገመት ወደ ድረ-ገጾቹ የገባ ሲሆን፣ ድርጊቱን የፈጸመው ድረ-ገጾቹ የሙከራው አካል እንደሆኑ በማሰብ መሆኑን የጉግል የደኅንነት ክፍል ምክትል ፕሬዝዳንት ሄዘር አድኪንስ ገልጸዋል።የኤአይ ሞዴሉ ወደ ኩባንያዎቹ የመረጃ ሥርዓት ከገባ በኋላ በራሱ ውሳኔ እንቅስቃሴውን ማቆሙና ጉግል ጥቃቱ ለደረሰባቸው ተቋማት መረጃ መስጠቱንና ክስተቱም በኤአይ ሥልጠና ወቅት ከፍተኛ ጥንቃቄ እንደሚያስፈልግ ማሳየቱን አስረድቷል ተብሏል።@TikvahethMagazine
    Image from a post by TIKVAH-MAGAZINEImage from a post by TIKVAH-MAGAZINE
    18,000291073Open in Telegram
  • TIKVAH-MAGAZINE

    19 Sept, 16:12

    ሀገራዊና አለማቀፋዊ እድሎችን ዩዝ ቱዩዝን ተቀላቅለው ይከታተሉ። በቻናሉ የየትምህርት ፣ ዓለም አቀፍ ስብሰባዎችና መድረኮች፣ የስራ፣ የስልጠና፣ የበጎ ፍቃድ ስራ እንዲሁም ሌሎች ዕድሎችም ይቀርቡበታል፡፡ቴሌግራም ቻናል ይጫኑ 👉🏼 @y2123 እኛ ሌሎችን ከፍ በማድረግ እንነሳለን !
    Image from a post by TIKVAH-MAGAZINEImage from a post by TIKVAH-MAGAZINE
    16,400832Open in Telegram
  • TIKVAH-MAGAZINE

    19 Sept, 16:10

    1 ቀን ቀረው!2ኛው ዓለም አቀፍ የቴምር ፌስቲቫል ነገ በሰመራ ይጀምራል2ኛው ዓለም አቀፍ የቴምር ፌስቲቫል ነገ መስከረም 10 ቀን 2019 ዓ.ም. በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ በሚገኘው አሰብ ሆቴል ይከፈታል።ለሦስት ቀናት በሚካሄደው በዚህ ዓለም አቀፍ ፌስቲቫል የግብርና መሪዎች፣ ባለሙያዎች፣ የቴምር አምራቾች፣ ባለሀብቶች እና የዘርፉ ተዋናዮች ይሳተፋሉ። ፌስቲቫሉ በተለይም በቴምር ምርትና ልማት ዙሪያ ያለውን ዕውቀትና ልምድ ለመለዋወጥ፣ የቴክኖሎጂና የፈጠራ ልምዶችን ለማስተዋወቅ እንዲሁም የንግድና የኢንቨስትመንት ትስስሮችን ለማጠናከር መድረክ ይፈጥራል። ፌስቲቫሉ በግብርና ሚኒስቴር፣ በአፋር ክልል መንግሥት እና በካሊፋ ዓለም አቀፍ ሽልማት በጋራ የሚዘጋጅ ሲሆን፣ ከመስከረም 10 እስከ 12 ቀን 2019 ዓ.ም. ይቆያል።📍 ሰመራ፣ አፋር | አሰብ ሆቴል 📅 መስከረም 10–22፣ 2019 ዓ.ም.#DatePalmFestivalEthiopia #AfarDatePalm #KhalifaAward #AgriculturalInnovation #EthiopiaEvents
    Image from a post by TIKVAH-MAGAZINEImage from a post by TIKVAH-MAGAZINE
    17,200212Open in Telegram
  • TIKVAH-MAGAZINE

    18 Sept, 16:08

    ደቡብ ሱዳን በናይል ወንዝ ላይ የፉላ ግድብን ለመገንባት በዝግጅት ላይ መሆኗን ገለጸችደቡብ ሱዳን በናይል ወንዝ ላይ የሚገነባውን የፉላ የውሃ ኃይል ማመንጫ ግድብ ፕሮጀክት ለማስጀመር ዝግጅት እያደረገች መሆኗን የሀገሪቱ የኃይል እና ግድቦች ሚኒስቴር አስታወቀ።በጁባ በተካሄደው 7ኛው ዓለም አቀፍ የሎጂስቲክስ ኮንቬንሽን (GLC 2026) ይፋዊ የሚዲያ ማስጀመርያ ስነ-ስርዓት ላይ የተናገሩት የኃይል እና ግድቦች ሚኒስትር አጎክ ማኩር፣ ሀገራቸው የግድቡን ግንባታ ለማካሄድ ከግብፅ በኩል የሚመጣ ምንም ዓይነት ፍራቻ እንደሌላት ገልጸዋል።ሚኒስትሩ አክለውም ደቡብ ሱዳን በአሁኑ ወቅት እየተጠቀመች ያለችው ከአጠቃላይ የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅሟ አንድ በመቶ ያህሉን ብቻ መሆኑን ጠቁመው፣ ይህም በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎችን ያለ አስተማማኝ የኃይል አቅርቦት ማቆየቱን አስረድተዋል።በዕቅድ ላይ ያለውና በኒሙሌ አካባቢ የሚገነባው የፉላ ግድብ 1,800 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅም ያለው ሲሆን፣ ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ የደቡብ ሱዳንን የሀገር ውስጥ ፍላጎት ሙሉ በሙሉ ማሟላት ከማስቻሉም በላይ ለጎረቤት ሀገራት የሚተርፍ ትርፍ ኃይል እንደሚያመነጭ ተገልጻል።አስተማማኝ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ለኢንዱስትሪ፣ ለኢንቨስትመንት፣ ለሎጂስቲክስ እና ለጠቅላላ የኢኮኖሚ ትራንስፎርሜሽን ወሳኝ መሆኑን ያመለከቱት ሚኒስትሩ፣ ሀገሪቱ በነሐሴ ወር 2018 ዓ.ም (August 2026) በጁባ በሚገኘው ፒራሚድ ኮንቲኔንታል ሆቴል የምታስተናግደው የሎጂስቲክስ ኮንቬንሽን የዘርፉን ባለሙያዎች፣ ኢንቨስተሮችን እና
    21,100video15363227Open in Telegram
  • TIKVAH-MAGAZINE

    18 Sept, 16:08

    የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከዘጠኝ ዓመታት በኋላ ወደ ደርባን የሚያደርገውን በረራ ዳግም ሊጀምር ነውየኢትዮጵያ አየር መንገድ በወቅታዊ የጉዞ ፍላጎት መቀነስ ምክንያት አቋርጦት የነበረውን ወደ ደቡብ አፍሪካዋ ደርባን ከተማ የሚያደርገውን የየዕለት በረራ ከዘጠኝ ዓመታት በኋላ እንደገና ሊጀምር መሆኑን አስታወቀ።በታህሳስ ወር ይጀምራል ተብሎ የሚጠበቀው ይህ አዲስ ቀጥታ የበረራ አገልግሎት፣ በደቡብ አፍሪካ የሚገኘውን ኪንግ ሻካ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ከአየር መንገዱ ዋና የበረራ ማዕከል አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ጋር በቦይንግ 737 MAX አውሮፕላን በቀጥታ የሚያገናኝ ይሆናል።አየር መንገዱ እ.ኤ.አ. በ2015 ወደ ደርባን ገበያ ሲቀላቀል በሳምንት ሦስት ጊዜ በረራ ያደርግ የነበረ ቢሆንም፣ በተጓዦች ቁጥር መዋዠቅ ምክንያት የሚደርስበትን የገንዘብ ጫና ለመቀነስ በነሐሴ 2017 አገልግሎቱን አቋርጦ ተጓዦች በጆሃንስበርግ በኩል እንዲጓዙ ሲያደርግ ቆይቷል።አሁን ላይ በኪንግ ሻካ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ የዓለም አቀፍ ተጓዦች ቁጥር ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ በኋላ እንደገና ማደጉን ተከትሎ፣ አየር መንገዱ ቀደም ሲል ይደረግ ከነበረው በረራ በበለጠ መጠን በሳምንት ሰባት ቀናት ሙሉ አገልግሎት ለመስጠት ዝግጅቱን አጠናቋል።ይህ በረራ ዳግም መጀመሩ በኩዋዙሉ ናታል ግዛት የሚገኙ ተጓዦችና የንግድ ተቋማት በጆሃንስበርግ ወይም በኬፕ ታውን በኩል ተጨማሪ በረራ ማድረግ ሳያስፈልጋቸው፣ የአየር መንገዱን ከ130 በላይ የዓለም አቀፍና የአፍሪካ መዳረሻዎች በቀጥታ እንዲጠቀሙ ዕድል የሚፈጥር ሲሆን፣
    Image from a post by TIKVAH-MAGAZINEImage from a post by TIKVAH-MAGAZINE
    17,600391Open in Telegram
  • TIKVAH-MAGAZINE

    18 Sept, 16:07

    2 ቀን ብቻ ቀረው!ሁለተኛው ዓለም አቀፍ የቴምር ፌስቲቫል በአፋር ሰመራ አሰብ ሆቴል ለመካሄድ 2 ቀናት ብቻ ቀሩት። የዘርፉ ተመራማሪዎች፣ አምራቾች እና የፈጠራ ባለቤቶች የሚሰበሰቡበትን ይህን ታላቅ ሁነት ለማስተናገድ አፋር ዝግጁ ናት! ይምጡ! ይሳተፉ! አዳዲስ ዕድሎችን ያግኙ!📅 ቀን፦መስከረም 10 - 12፣ 2019 ዓ.ም. 📍 ቦታ፦ አፋር፣ ሰመራ — አሰብ ሆቴል
    Image from a post by TIKVAH-MAGAZINEImage from a post by TIKVAH-MAGAZINE
    17,20012Open in Telegram
  • TIKVAH-MAGAZINE

    18 Sept, 16:07

    “ቤት ለመግዛት ብዙ ገንዘብ ያስፈልጋል” ብለው እያሰቡ ነው?🤔🔥 ቴምር ሪል እስቴት | መገናኛ ዲያስፓራ አደባባይ ፊት ለፊት ላይ አዲስ ዕድል! 🏠 💥40% ብቻ ከፍለው 60% ቤቱን ሲረከቡ እንዲከፍሉ እኛ አመቻችተንልዎታል! ✨💥 ልዩ ልዩ የክፍያ አማራጮች ✅ 40% ብቻ ይክፈሉ፤ 10% ቅናሽ ያግኙ! ቀሪውን 60% ቤትዎን ከተረከቡ በኋላ መክፈል ይችላሉ ✅ 20% ቅድመ ክፍያ ብቻ ቀሪውን 80% በ3 ዓመት የግንባታ ጊዜ ውስጥ በቀላሉ ይክፈሉ። ✅ 100% ለሚከፍሉ 35% ቅናሽ አለን🏠 60 ካሬ – ባለ1 መኝታ ጠቅላላ ዋጋ - 7,500,000 ብር 20% - 1.5 ሚሊየን 40% - 3 ሚሊየን 100% ከከፈሉ - 4,875,000 ብር🏠 90 ካሬ – ባለ2 መኝታ ጠቅላላ ዋጋ - 11,250,000 ብር 20% - 2.2 ሚሊየን 40% - 4.5 ሚሊየን
    Image from a post by TIKVAH-MAGAZINEImage from a post by TIKVAH-MAGAZINE
    13,90071Open in Telegram
  • TIKVAH-MAGAZINE

    18 Sept, 16:07

    🔥የከተማችን ታላቁ የንግድ ማዕከል መርካቶ ተክለሐይማኖት መገኛቸውን ያረጉ በልዩነት ቅናሽ የተደረገባቸው የንግድ ሱቆች ይዘንላቹ መጥተናል!👉በ 11 ፣ 16 ፣ 22 እና 32 ካ.ሜ አማራጭ ሲሆኑ💰የዋጋ መነሻቸውም:- 👉ግራወንድ ላይ ሙሉ ክፍያ : 4,950,000 ብር ቅድመ ክፍያ : 1,495,000 ብር👉1ኛ ወለል ሙሉ ክፍያ : 4,400,000 ብር ቅድመ ክፍያ : 1,320,000 ብር👉2ተኛ ወለል ሙሉ ክፍያ : 3,795,000 ብር ቅድመ ክፍያ : 1,138,500 ብር👉3ተኛ ወለል ሙሉ ክፍያ : 3,300,000 ብር ቅድመ ክፍያ : 990,000 ብር
    Image from a post by TIKVAH-MAGAZINEImage from a post by TIKVAH-MAGAZINE
    16,30013Open in Telegram
  • TIKVAH-MAGAZINE

    17 Sept, 19:50

    በኢትዮጵያ የተገኘው አዲስ የእባብ ዝርያ ምን አይነት ነው ?በኢትዮጵያ የወፍ እንቁላል ብቻ የሚመገብ አዲስ የእባብ ዝርያ መገኘቱ ተነግሯል። ይህ የእባብ ዝርያ ከሌሎች የእባብ ዝርያዎች ለየት ያለ የመጋገብ ሥርዓት እንዳለው ነው ሳይንቲስቶች የገለጹት።አዲሱ የእባብ ዝርያ ዳሲፔልቲስ አልቢጉላሪስ (Dasypeltis albigularis) ተብሎ የተሰየመ ሲሆን ይህ የእባብ ዝርያ ለምግብነት የሚጠቀመው የወፍ እንቁላልን ብቻ ነው።ሳይንቲስቶቹ ይህንን የእባብ ዝርያ ያገኙት በአፍሪካ ቀንድ ከሚገኙ ሰፊ ሽፋን ያላቸው የተፈጥሮ ደኖች አንዱ በሆነው የሀሬና የደን ውስጥ ነው።አዲስ የተገኘው እባብ ዳሲፔልቲስ ከሚባሉ የአፍሪካ እባቦች ዝርያ የሚመደብና ሰዎች ላይም ሆነ ሌሎች የእንስሳት ዝርያዎች ላይ ጥቃት እንደማያደርስ ተገልጿል።የምርምር ሥራው እስከ ሰባት ዓመታት የፈጀ መሆኑ ሲነገር መጀመሪያ ላይ እባቡ ከሌላ ቅርርብ ካለው ዝርያ ጋር ተመሳሳይ እንደሆነ ታምኖ የነበረ ቢሆንም እባቡ እያደገ ሲመጣ የታዩት የአካል ቅርጽ ለውጦች እና የዲ ኤን ኤ (DNA) ምርመራ ውጤቶች የተለየ እና አዲስ ዝርያ መሆኑን አረጋግጠዋል።የዚህ ዝርያ ሴቶቹ እባቦች እስከ 92 ሴንቲሜትር ሊረዝሙ የሚችሉ ሲሆን ወንዶቹ ግን ከ60 ሴንቲሜትር በታች አጭር ሆነው እድገታቸው ይጨርሳሉ።በአመጋገባቸውም እንቁላሉን ከዋጡ በኋላ የእንቁላሉን ቅርፊት ለመስበር በጉሮሮአቸው ውስጥ የሚገኙ አጥንቶችን ይጠቀማሉ። እንቁላሉ ከተሰበረ በኋላ ቅርፊቱን መልሰው እንደገና ያስወጡታል።አዲስ የተገኙት እነዚህ ዝርያዎች የሚኖሩት ከባህር ጠለል በላይ
    Image from a post by TIKVAH-MAGAZINEImage from a post by TIKVAH-MAGAZINEImage from a post by TIKVAH-MAGAZINE
    23,70015118161451Open in Telegram
  • TIKVAH-MAGAZINE

    17 Sept, 19:13edited

    How to Get Your First Job in MediaFree 3-Hour Career Starter Session for Fresh Journalism GraduatesThis practical session will help you move from graduation to your first media opportunity.See more https://t.me/concepthubeth/141Via @Concepthubeth
    Image from a post by TIKVAH-MAGAZINEImage from a post by TIKVAH-MAGAZINE
    24,60082Open in Telegram
  • TIKVAH-MAGAZINE

    17 Sept, 15:51

    የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጭነት አገልግሎቱን ለማዘመን ከካርጎ ኤአይ ጋር ተስማማየኢትዮጵያ አየር መንገድ የጭነት እና ሎጅስቲክስ አገልግሎት የዲጂታል አሰራሩን ለማዘመንና ለማቃለል የሚያስችለውን ስትራቴጂካዊ የትብብር ስምምነት ከዓለም አቀፉ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ካርጎ ኤአይ ጋር ተፈራረመ።​በዚህ ስምምነት መሠረት በአውሮፓ፣ በአፍሪካ፣ በመካከለኛው ምስራቅ እና በአሲያ የሚገኙ ከ30,000 በላይ የጭነት አስተላላፊዎች የአየር መንገዱን የጭነት ቦታ፣ የመጫኛ ዋጋ እና ክፍት በረራዎችን በቅጽበት በዲጂታል አማራጭ ማየትና ቦታ መያዝ ይችላሉ ተብሏል።መቀመጫውን በሲንጋፖር ያደረገው "CargoAi" ከ150 በላይ በሚሆኑ ሀገራት እና በ47 ሀገራዊ ገንዘቦች ክፍያዎችን የሚቀበል ኩባንያ ነው።ትብብሩ የጋራ ትስስር አቅምን በመጠቀም ከሌሎች አየር መንገዶች ጋር በዲጂታል አሰራር የበለጠ ውጤታማ እና ግልጽ የሆነ ትብብር እንዲፈጥር ያግዘዋል ተብሏል።@TikvahethMagazine
    Image from a post by TIKVAH-MAGAZINEImage from a post by TIKVAH-MAGAZINE
    23,00051124Open in Telegram
  • TIKVAH-MAGAZINE

    17 Sept, 15:49

    #AAU: የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ዘንድሮ የከፈተው ሞዴል ኮሚኒቲ ትምህርት ቤት በዛሬው እለት አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።@TikvahEthMagazine
    Image from a post by TIKVAH-MAGAZINEImage from a post by TIKVAH-MAGAZINEImage from a post by TIKVAH-MAGAZINEImage from a post by TIKVAH-MAGAZINE
    21,800278Open in Telegram
  • TIKVAH-MAGAZINE

    17 Sept, 15:48

    ታሪካዊቷ አፋር… በድጋሚ ታላቅ ዓለም አቀፍ የቴምር ፌስቲቫልን ለማስተናገድ ተዘጋጅታለች! በኢትዮጵያ ለሁለተኛ ጊዜ የሚካሄደው ዓለም አቀፍ የቴምር ፌስቲቫል ከመስከረም 10 እስከ 12 ቀን 2019 ዓ.ም. በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ አሰብ ሆቴል ይካሄዳል። ቀን፦መስከረም 10 - 12፣ 2019 ዓ.ም. ቦታ፦ አፋር፣ ሰመራ — አሰብ ሆቴል አዘጋጆች: የኢፌድሪ ግብርና ሚኒስቴር፣ የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት እና ካሊፋ ኢንተርናሽናል አዋርድ
    Image from a post by TIKVAH-MAGAZINEImage from a post by TIKVAH-MAGAZINE
    19,500389Open in Telegram
  • TIKVAH-MAGAZINE

    17 Sept, 13:21

    ፈረንሳይ በህጻናት የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ላይ እገዳ ጣለች የፈረንሳይ ሕግ አውጪዎች ከ15 ዓመት በታች ያሉ ህጻናት ማህበራዊ ሚዲያን እንዳይጠቀሙ የሚያግድ ሕግ በማጽደቅ የመጀመሪያዋ የአውሮፓ ሀገር ሆናለች። የፈረንሳይ መንግሥት ይህን ውሳኔ የወሰነው ህጻናትን ከማህበራዊ ሚዲያ ሊደርስባቸው ከሚችለው ጉዳት ለመጠበቅ መሆኑን ገልጿል። በአዲሱ ሕግ መሠረት ነሐሴ 26 ጀምሮ ከ15 ዓመት በታች ያሉ ህጻናት
    Image from a post by TIKVAH-MAGAZINEImage from a post by TIKVAH-MAGAZINEImage from a post by TIKVAH-MAGAZINE
    18,500763553Open in Telegram
  • TIKVAH-MAGAZINE

    17 Sept, 13:03

    በሱዳን በወርቅ ማዕድን ማውጫ ላይ በደረሰ የመደርመስ አደጋ የ82 ሰዎች ህይወት አለፈ።ባሳለፍነው ማክሰኞ በሱዳን ምዕራብ ኮርዶፋን ግዛት የወርቅ ማዕድን ማውጫ ላይ በደረሰ የመደርመስ አደጋ ቢያንስ 82 ሰዎች ሲሞቱ 50 ያህል ሰዎች ደግሞ የጉዳት ሰለባ ሆነዋል።የአደጋ መከላከል እና የነፍስ አድን ቡድኖች እና ሌሎች የማዕድን ሰራተኞች ሌሊቱን ሙሉ መሰረታዊ መሳሪያዎችን በመጠቀም 60 አስከሬኖችን ያገኙ ሲሆን ሌሎች 22 ደግሞ ረቡዕ እለት በሌላ ፍለጋ ተገኝተዋል።አንድ የአካባቢው አስተዳዳሪ 50 የሚጠጉ ሰዎች ቆስለዋል፣ ያሉ ሲሆን እስካሁን የጠፉት ሰዎች ቁጥር በወል አልታወቀም።አደጋው የሱዳን የማዕድን ዘርፍ በብዛት በግለሰቦች እጅ መግባቱን እና ከቁጥጥር ውጪ መሆኑን እንደሚያሳይ ተመላክቷል። አራተኛ አመቱን በያዘው የሱዱን የእርስበርስ ጦርነት የወርቅ ማዕድን ቁፋሮ ለሁለቱም ወገኖች እንደ መሰረታዊ የገቢ ምንጭነት እያገለገለ ይገኛል።በአደጋው ተቀብረው ያልወጡ አስክሬኖችን ለማግኘት ከባድ ማሽነሪዎች እንደሚያስፈልጉ ተገልጿል። የነፍስ አድን ሰራተኞች እስከ አሁን ድረስ ተቀብረው የቀሩ አስከሬኖችን ለማውጣት በጦርነት በተጎዳው ቀጠና ለመንቀሳቀስ ፈተና እንደሆነባቸው የቢቢሲ እና አፍሪካን ኒውስ ዘገባ ያመላክታል።@TikvahethMagazine
    Image from a post by TIKVAH-MAGAZINEImage from a post by TIKVAH-MAGAZINE
    18,9004613Open in Telegram
  • TIKVAH-MAGAZINE

    17 Sept, 13:01

    ​11 ኩባንያዎች የኢትዮጵያ የሰነደ-ሙአለዋይ ገበያን ሊቀላቀሉ ነው።የኢትዮጵያ የሰነደ-ሙአለዋይ ገበያ 11 አዳዲስ ኩባንያዎች ወደ አክሲዮን ገበያው እንዲገቡ በመርህ ደረጃ ማጽደቁን አስታወቀ።እነዚህ ኩባንያዎች ሙሉ በሙሉ ወደ ገበያው ሲቀላቀሉ ገበያ ውስጥ የሚገበያዩ ተቋማትን ቁጥር ወደ ሦስት እጥፍ ገደማ የሚያሳድገው ይሆናል።​ከእነዚህ 11 ኩባንያዎች መካከል በፋይናንስ ዘርፍ የሚሰራው የመጀመሪያው ተቋም በሚቀጥለው ሳምንት ይፋዊ የአክሲዮን ግብይት እንደሚጀምር የገበያው ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዮዲት ካሳ በናይሮቢ በሰጡት ቃለ-መጠይቅ ገልጸዋል፤ ሆኖም የኩባንያውን ስም ከመግለፅ ተቆጥበዋል።ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ አክለውም ሂደቱ በታቀደው መሠረት ከቀጠለ ቢያንስ ስድስት ኩባንያዎች በታህሳስ መጨረሻ ወይም በጥር ወር መጀመሪያ 2019 ዓ.ም ላይ ወደ ገበያው ሊገቡ ይችላሉ ብለዋል።በአሁኑ ወቅት በገበያው ተመዝግበው የሚገበያዩት ኩባንያዎች ስድስት ሲሆኑ፣ እነሱም ኢትዮ ቴሌኮም፣ አባይ ባንክ፣ አዋሽ ባንክ፣ አቢሲኒያ ባንክ፣ ገዳ ባንክ እና ወጋገን ባንክ ናቸው።እነዚህ 11 አዳዲስ ኩባንያዎች ሙሉ በሙሉ ወደ ገበያው ከገቡ፣ በሰነደ-ሙአለዋይ ገበያው ላይ የተመዘገቡ ተቋማት ቁጥር አሁን ካለው ስድስት ወደ 17 በማደግ አሁን ካለው በሦስት እጥፍ ገደማ ይጨምራል።​በአሁኑ ወቅት 22 የገበያ አገበያዮች / Trading Intermediaries ሲኖሩት ከእነዚህም ውስጥ ሰባቱ የኢንቨስትመንት ባንኮች ናቸው።ዘገባው የብሉምበርግ ነው።@TikvahethMagazine
    Image from a post by TIKVAH-MAGAZINEImage from a post by TIKVAH-MAGAZINE
    15,0002731Open in Telegram