Latest posts

TIKVAH-SPORT
22 Sept, 18:08edited
የሊቨርፑል ስፖርቲንግ ዳይሬክተር ማን ይሆናል ?የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል ከስፖርቲንግ ዳይሬክተሩ ሪቻርድ ሂውዝ ጋር መለያየቱ ይታወቃል።አሁን ላይ ሊቨርፑል በቀጣይ ማንን በስፖርቲንግ ዳይሬክተርነት ሊሾም እንደሚችል ታውቋል።የ " FSG " የቴክኒክ ዳይሬክተር የሆኑት ጁሊያን ዋርድ ቀጣዩ የሊቨርፑል ስፖርቲንግ ዳይሬክተር በመሆን ሊሾሙ መሆኑ ተገልጿል።ሀላፊው ከዚህ በፊት በ 2022/23 የውድድር ዘመን በተመሳሳይ ሀላፊነት አገልግለው ነበር።ጁሊያን ዋርድ በ 2012 ከማንችስተር ሲቲ ለቀው ነበር ሊቨርፑልን የተቀላቀሉት።@tikvahethsport @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
22 Sept, 16:43edited
የኢትዮጵያ እና ሴኔጋልን ጨዋታ ማን ይመራል ?ኢትዮጵያ ከሴኔጋል ጋር የምታደርገውን የ 2027 አፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ ሁለተኛ ጨዋታ የሚመሩት ዳኛ ታውቀዋል።በባሕር ዳር ስታዲየም የሚደረገውን ተጠባቂ ጨዋታ ካሜሮናዊው ዳኛ ዊሊ ሴቴፋን ንጋህ በመሀል ዳኝነት ይመሩታል።ዋና ዳኛው ባለፈው አመት የኢትዮጵያ ከ 17ዓመት በታች ቡድን ከሞሮኮ ጋር ያደረገውን የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ጨዋታ መርተው ነበር።ጨዋታው ቀጣይ ሳምንት ማክሰኞ ቀን 10:00 ሰዓት በባሕር ዳር ስታዲየም ይደረጋል።በሌላ በኩል ኢትዮጵያ ከሱዳን የምታደርገውን ጨዋታ ላይቤሪያዊው ዳኛ ዋሽንግተን ን ዶሎ እንዲመሩ ተመርጠዋል።ጨዋታው አርብ ምሽት 1:00 ሰዓት በደቡብ ሱዳን ጁባ ስታዲየም ይደረጋል።@tikvahethsport @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
22 Sept, 15:57edited
“ ማድሪድ ደርቢውን በዳኛ አልተሸነፈም ዳኛው አንዳች ስህተት አልሰራም “ ዣቪየር ቴባስ“ ቴባስ ተቋሙን ተጠቅሞ ክለባችንን እያጠቃ ነው ” ሪያል ማድሪድሪያል ማድሪድ የላሊጋው ፕሬዝዳንት ዣቪየር ቴባስ ስለ ክለቡ ለሰጡት አስተያየት ምላሽ ሰጥቷል።ፕሬዝዳንት ዣቪየር ቴባስ ሪያል ማድሪድ ከደርቢው በኋላ ዳኞችን ተጠያቂ ማድረጉን ተችተው ነበር።“ ማድሪድ ደርቢውን በዳኛ አልተሸነፈም “ ያሉት ቴባስ ዳኞች ላይ ጫና ማሳደር ነው አላማቸው ብለዋል።“ ሮሜሮ በቀይ መውጣት እንዳልነበረበት አምናለሁ ሁይሰን በቀይ መውጣቱ ትክክል ነው “ ሲሉ ነው የተናገሩት።ሪያል ማድሪድ በበኩሉ ባወጣው መግለጫ “ ቴባስ ማድሪድን ለማጥቃት ተቋሙን መጠቀሙ ተቀባይነት የለውም "ብሏል።አክሎም “ ቴባስ የሊጉን ገፅታ ማበላሸቱን ቀጥሎበታል ፣ የላሊጋ ፕሬዝዳንት የውድድሩ ባለቤት አይደለም "ሲል ገልጿል።@tikvahethsport @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
22 Sept, 14:48
የሲቲ የወሩ ምርጥ ተጨዋች ማን ይሆናል ?በአሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ የሚመራው ማንችስተር ሲቲ የወርሀ መስከረም የወሩ ምርጥ ተጨዋች ሶስት እጩዎችን ይፋ አድርገዋል።በዚህም መሰረት :-- ኤርሊንግ ሀላንድ- ማርክ ጉሂ እና- ኤሊዮት አንደርሰን በእጩነት መቅረብ ችለዋል።@tikvahethsport @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
22 Sept, 14:47
forwarded from @wanawsportwear
3ኛው_ዙር_ዋናው_የዶክተር_ብሩክ አማረ መታሰቢያ የእግር ኳስ ውድድር በአርባምንጭ ከተማ ዝግጅቱን በደማቅ ሁኔታ ተዘጋጅቷል።ከሶስት ዓመት በፊት መስከረም 10 ቀን በድንገት ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው ዶክተር ብሩክ አማረን ለማስታውስና መልካም ስራዎቹን ለመዘከር ቤተሰቡ ከዋናው ስፖርት ጋር በመተባበር ያዘጋጁት "ዋናው የዶ/ር ብሩክ አማረ ሦስተኛ ዓመት መታሰቢያ የእግርኳስ ውድድር" ከመስከረም 8 እስከ 10 በአርባምንጭ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል ።✍️ ለአሸናፊዎች አጓጊ ሽልማቶች የሚበረከቱ ሲሆን፤ በየአንዳንዱ ጨዋታም የላቀ ብቃት ላሳዩ ተጫዋቾች የ Man of the Match ስጦታ ተዘጋጅቷል! 📍ገርጂ መብራት ሃይል የካቲት ወረቀት ፊትለፊት፣ አለም ገብሬ ህንፃ፣ 2ተኛ ፎቅ። ⭐️ዋናው ወደፊት🔣🔣🔣
TIKVAH-SPORT
22 Sept, 13:28edited
የቶተንሀም ስፖንሰር ውሉን አቋረጠ !ጥሩ ያልሆነ የውድድር ዘመን እያሳለፈ የሚገኘው የሰሜን ለንደኑ ክለብ ቶተንሀም ስፖንሰሩን አጥቷል።የቶተንሀም ይፋዊ የፈርኒቸር ስፖንሰር ሲዲዝ ከቶተንሀም ጋር ያለውን ኮንትራት ማቋረጡ ተገልጿል።ተቋሙ ከቶተንሀም ጋር ያለውን ስምምነት የውል ማቋረጫ አንቀጽ ተጠቅሞ እንደሚያቋርጥ ተነግሯል።ተቋሙ ውሉን የሚያቋርጠው ቶተንሀም ደካማ የውድድር ዘመን ጅማሮ ማድረጉን ተከትሎ እንደሆነ ተገልጿል።እስካሁን ምንም ጨዋታ ማሸነፍ ያልቻለው ቶተንሀም በሊጉ በሁለት ነጥብ ሃያኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።@tikvahethsport @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
22 Sept, 13:16edited
“ የጆታ ህልፈት ለእግርኳስ ያለንን ፍቅር አሳጥቶን ነበር ” አንዲ ሮበርትሰንየቀድሞ የሊቨርፑል ተጨዋች አንዲ ሮበርትሰን የዲያጎ ጆታ ህልፈት ቡድኑ ላይ የስነ ልቦና ጉዳት ማድረሱን ገልጿል።“ ጆታ ለእኛ እግርኳስ ተጨዋች ብቻ አልነበረም ” ያለው ሮበርትሰን “ እሱ ጓደኛችን ፤ መልበሻ ቤት ውስጥ የቅርባችን ሰው ነበር "ብሏል።“ እጅግ በጣም የሚያም እና ልብ የሚሰብር ጊዜ ነበር ያሳለፍነው “ ሲል ሮበርትሰን ተናግሯል።አክሎም “ በወቅቱ የእግርኳስ ፍቅራችንን አጥተናል ፣ ቤተሰቡ እና ልጆቹ እንደዛ ሲጎዱ ስናይ ስለጨዋታ ማሰብ አልቻልንም "ብሏል።@tikvahethsport @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
22 Sept, 11:56
አርቴታ ውላቸውን ለማራዘም ተስማሙ !የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ኮንትራታቸውን ለማራዘም ከስምምነት መድረሳቸው ተገልጿል።አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ በአርሰናል ቤት ለረጅም ጊዜ ለመቆየት ከስምምነት እንደደረሱ ቢቢሲ ዘግቧል።ሚኬል አርቴታ በአርሰናል ያላቸው ኮንትራት በውድድር አመቱ መጨረሻ ያበቃ ነበር።አዲሱ ውል አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ በአርሰናል ከአስር አመት በላይ እንዲቆዩ ያስችላቸዋል ተብሏል።@tikvahethsport @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
22 Sept, 10:35edited
ቫልቬርዴ ለሳምንታት ከሜዳ ይርቃል !የሪያል ማድሪዱ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ፌዴ ቫልቬርዴ በማድሪድ ደርቢ የቁርጭምጭሚት ጉዳት አጋጥሞታል።ተጨዋቹ " ግሬድ ሶስት " የቁርጭምጭሚት ጉዳት እንዳጋጠመው ክለቡ ይፋ አድርጓል።በዚህም ምክንያት ቫልቬርዴ ለሁለት ሳምንታት ከሜዳ እንደሚርቅ ተገልጿል።ሪያል ማድሪድ ከብሔራዊ ቡድኖች ጨዋታ እረፍት በኋላ ከቪያሪያል ጋር የሊግ ጨዋታውን ያደርጋል።@tikvahethsport @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
22 Sept, 08:43edited
“ ባሎን ዶር ካሸነፍኩ መታሰቢያነቱን ለአፍሪካ አበረክታለሁ ” ኪሊያን ምባፔፈረንሳዊው ተጨዋች ኪሊያን ምባፔ ባሎን ዶር ካሸነፈ መታሰቢያነቱን ለአፍሪካ እንደሚያደርግ ገልጿል።የካሜሮን የዘረ ሀረግ ያለው ምባፔ " ፈረንሳይ ብወለድም አስተዳደጌ በአፍሪካ ባህል የተቃኘ ነው "ሲል ገልጿል።“ ወደ አፍሪካ ስሄድ ህዝቡ ከፍተኛ አቀባበል ያደርግልኛል ከህዝቡ ፍቅር ይሰማኛል “ ሲል ጨምሮ ተናግሯል።ለአፍሪካ የባሎን ዶር ድምፅ ሰጪዎች መልዕክት ያስተላለፈው ምባፔ “ በመጀመሪያ እስካሁን ለሰጡኝ ድጋፍ አመሰግናለሁ "ብሏል።አክሎም " አፍሪካን ለሁሉም ነገር አመሰግናለሁ እግሬ እዛ በሄደ ቁጥር የመወደድ ስሜት ይሰማኛል " ብሏል።ከአፍሪካ የተገኘ እንደመሆኑ ሰዎች ከባሎን ዶር ጋር ስሙን ሲጠሩ እንደሚደሰት ኪሊያን ምባፔ ተናግሯል።“ የባሎን ዶር ሽልማቱን አሸንፌ መታሰቢያነቱን ለአፍሪካ እንደማደርግ ተስፋ አደርጋለሁ ” ኪሊያን ምባፔ@tikvahethsport @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
21 Sept, 21:29edited
ሊዮኔል ሜሲ ለአርጀንቲና ጥሪ ቀርቦለታል ! አርጀንቲናዊው ኮከብ ሊዮኔል ሜሲ ከአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን ራሱን ማግለሉ ይታወቃል። ይሁን እንጂ አርጀንቲና ለተጨዋቾች ጥሪ ስታቀርብ ሊዮኔል ሜሲን በስብስቧ አካታለች። ሊዮኔል ሜሲ በአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን የመጨረሻ ጨዋታውን እንዲያደርግ እንደተዘጋጀለት ተገልጿል። አርጀንቲና ከሳምንታት በኋላ ከቤኒን በምታደርገው ጨዋታ ሊዮኔል ሜሲ በይፋ ይሸኛል ተብሎ
TIKVAH-SPORT
21 Sept, 19:47edited
ዎት ዌግሆርስት ለምን መነጋገሪያ ሆነ ?ኔዘርላንዳዊው አጥቂ ዎት ዌግሆርስት ከጨዋታ በፊት እጆቹን ተጠቅሞ ያልተለመደ ነገር ሲያደርግ ነበር።ዌግሆርስት በሰዓቱ ባደረገው ድርጊት ደጋፊዎች የቀለዱበት ሲሆን በማህበራዊ ሚዲያውም መነጋገሪያ ሆኖ ነበር።ይሁን እንጂ ዎት ዌግሆርስት ያደረገው አእምሮውን ይበልጥ ዝግጁ ለማድረግ የነርቭ ልምምድ ነበር።ተጨዋቹ ከጨዋታው በፊት አእምሮውን ለማንቃት የእጅ እንቅስቃሴዎችን እንደተጠቀመ ባለሙያዎች ይገልፃሉ።በኔዘርላንድ እውቅና ያላቸው የነርቭ ሳይኮሎጂ ፕሮፌሰር ኤሪክ ሼርደር ስለ ሁነቱ ሲያስረዱ “ እጅን ለማንቀሳቀስ የአንጎላችንን ብዙውን ክፍል ይፈልጋል “ ይላሉ።“ እጅ ሲንቀሳቀስ አብዛኛው የአንጎላችን ክፍል በቅንጅት ይሰራል “ ያሉት ባለሙያው “ ስለዚህ ያንን ሲያደርግ ብዙውን ክፍል ያነቃቃል " ብለዋል።“ በመሰረቱ ያንን ማድረግ ስርዓቱን እንደማዘጋጀት ነው አእምሮን እንደመክፈት ነው "በማለት ተናግረዋል።ዎት ዌግሆርስት ወደ ጨዋታው ከገባ በኋላ ወሳኝ የአቻነት ግብ በማስቆጠር ቡድኑ ቲዌንቴ ፒኤስቪን እንዲያሸንፍ ረድቷል።@tikvahethsport @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
21 Sept, 18:20edited
ቀይ ቀበሮዎቹ ተጋጣሚያቸውን መቼ ያውቃሉ ?የኢትዮጵያ ከ 17ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን የ 2027 አፍሪካ ዋንጫ ሴካፋ ዞን ማጣሪያ ተጋጣሚውን በዚህ ሳምንት ያውቃል።ቀይ ቀበሮዎቹ ከነገ በስቲያ ረቡዕ ታንዛኒያ ዳሬ ሰላም በሚደረግ የእጣ ማውጣት ስነ ስርዓት ተጋጣሚያቸውን ያውቃሉ።በማጣሪያ ውድድሩ ኢትዮጵያን ጨምሮ ኬንያ ፣ ታንዛኒያ ፣ ዩጋንዳ ፣ ሩዋንዳ ፣ ቡሩንዲ ፣ ጅቡቲ ፣ ሶማልያ ፣ ሱዳን እና ደቡብ ሱዳን ይሳተፋሉ።ውድድሩ ከመስከረም 30 እስከ ጥቅምት 10/2019 ዓ.ም በሩዋንዳ ኪጋሊ ይካሄዳል።በውድድሩ ከአንድ እስከ ሶስት ያለውን ደረጃ ይዘው የሚያጠናቅቁ ቡድኖች ለ 2027 አፍሪካ ዋንጫ ያልፋሉ።የ ኢትዮጵያ ከ 17ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ባለፈው አመት ለአፍሪካ ዋንጫው አልፎ እንደነበር አይዘነጋም።@tikvahethsport @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
21 Sept, 17:52edited
“ አንድም የፖርቹጋል ተጨዋች አያስፈራኝም ”በአውሮፓ ኔሽን ሊግ የፊታችን ሐሙስ ዌልስ ሊዝበን ላይ ከፖርቹጋል ጋር ጨዋታዋን ታደርጋለች።ስለ ጨዋታው አስተያየቱን የሰጠው የዌልስ አማካይ ጆርዳን ጄምስ ፍርሀት እንደማይሰማው ተናግሯል።“ ፖርቹጋል የአለም ምርጥ ተጨዋቾችን ይዛለች ይሄ ሊካድ አይችልም ” ያለው ጄምስ “ ነገርግን አንዳቸው አያስፈሩኝም ” ብሏል።አክሎም “ እነሱም ሰው ናቸው ፤ ሁለት እግር ብቻ ነው ያላቸው ስህተትም ይሰራሉ "ሲል ተናግሯል።በጨዋታው “ ሥራችን የሚሆነው የእነሱን ስህተት በመጠቀም ዋጋ ማስከፈል ነው ” ሲል ተደምጧል።@tikvahethsport @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
21 Sept, 16:08edited
“ የተኩላ ራት ሆንኩ ብዬ አስቤ ነበር ” ዲያጎ ኮስታስፔናዊው አጥቂ ዲያጎ ኮስታ ከአመታት በፊት ለዎልቭስ ሲፈርም ስለነበረው ገጠመኝ አስታውሷል።ዲያጎ ኮስታ በወቅቱ ለዎልቭስ መፈረሙ በተገለፀበት ቪድዮ ላይ ከተኩላዎች ጋር ታይቶ ነበር።“ ፈርቼ ነበር ” የሚለው ኮስታ " በውስጤ አንዱ ተኩላ እኔን ለማጥቃት ቢወስንስ ብዬ ማሰብ ጀምርኩ " ይላል።“ አሰልጣኛቸው ጠርቶ ዝለሉ ሲላቸው ምላሽ አልሰጥ ብለው ነበር እሱን አልሰማ ካሉ እኔማ አበቃልኝ ብዬ አስቤያለሁ "ሲል አስታውሷል።አክሎም “ ወደ እኔ ተመልሰው እግሬን ማነፍነፍ ሲጀምሩ የእኔ ነገር አበቃ ብዬ ነበር ውሻ አይደሉም እውነተኛ ተኩላ ነበሩ "ብሏል።@tikvahethsport @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
21 Sept, 16:08
forwarded from @wanawsportwear
ከሰፈር እስከ ሰፈር፤ እግር ኳስ አንድ ያደርገናል። ⚽🤝የቀበና ካፕ ዝግጅት በይፋ ተጀምሯል ይህ ከጤና ቡድኖች ውድድር በላይ የሆነው በአዲስ አበባ የሚገኙ ማህበረሰቦችን የሚያስተሳስረው፣ ለወጣቶች አዳዲስ ዕድሎችን የሚፈጥር እና በስፖርት አማካኝነት ጠንካራ ቁርኝትን የሚገነባ ትልቅ ዝግጅት አጋር የሆነው ዋናው ስፖርት ኩራት ይሰማዋል!ማልያስ ዋናው ይስራ! #ዋናውስፖርት
TIKVAH-SPORT
21 Sept, 15:25edited
ሳላህ የተቀመጠበት ድንጋይ የቱሪስት መዳረሻ ሆነ !የቱርኩን ክለብ ትራብዞንስፖር የተቀላቀለው ግብፃዊው ኮከብ ሞሀመድ ሳላህ በክለቡ ተፅዕኖ መፈጠሩን ቀጥሏል።አሁን ላይ ሞሀመድ ሳላህ በትራብዞን አካባቢ የተቀመጠበት ድንጋይ ከፍተኛ እውቅና ማትረፉ ተገልጿል።ሞሀመድ ሳላህ የተቀመጠበት ድንጋይ የቱሪስት ማዳረሻ ለመሆን የበቃ ሲሆን ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ ወደ ቦታው እያቀና ይገኛል።ሳላህ ለትራብዞንስፖር ባደረጋቸው ስምንት ጨዋታዎች 7️⃣ ጎል አስቆጥሮ ሁለት አመቻችቶ አቀብሏል።@tikvahethsport @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
21 Sept, 14:25edited
“ ሲቲ ሊጉን ማሸነፍ አይችልም ” ፖል ሜርሰንየቀድሞ ተጨዋች ፖል ሜርሰን ማንችስተር ሲቲ ፕሪሚየር ሊጉን ያሸንፋል የሚል እምነት እንደሌለው ገልጿል።“ ማንችስተር ሲቲ ሊጉን ሊያሸንፍ አይችልም ብዙ ግብ እያስቆጠርክ መቀጠል አትችልም “ ሲል ፖል ሜርሰን ተናግሯል።አክሎም " በዚህ መልኩ መጫወት አትችልም ፣ ትልቅ ክለቦች ከጨዋታ ውጪ ያደርጉሃል "ሲሉ ገልጿል።ሰንደርላንድ በሊጉ ብዙ ግብ የማያስቆጥር ቡድን መሆኑን የገለፀው ሜርሰን “ ሲቲ ላይ ግን ሶስት አስቆጥሯል አሳሳቢ ነው "ብሏል።“ ማንችስተር ዩናይትድን በአስር ተጨዋች አሸንፏል ነገርግን 11ለ11 በነበረ ስዓት ዩናይትድ የተሻለ ነበር ስለተከላከሉ ነው ጫና ስለቀነሰ ነው ያሸነፉት " ፖል ሜርሰን@tikvahethsport @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
21 Sept, 13:50edited
የዋልያዎቹ ዝግጅት ምን ይመስላል ?የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከፊቱ ለሚጠብቀው የ 2027 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ በአዲስ አበባ እና ሀዋሳ ከተሞች ላይ ዝግጅቱን ሲያደርግ ቆይቷል።ቡድኑ በዝግጅት ወቅቱ ሶስት የወዳጅነት ጨዋታ ሲያደርግ- ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ- ከ ኢትዮጵያ ከ 20ዓመት በታች ብሔራዎ ቡድን ( 2X )- ሀዋሳ ከተማ ጋር የአቋም መፈተሻ ጨዋታቸውን አድርጓል።ቡድኑ ዝግጅቱን አጠናቆ በነገው ዕለት የመጀመሪያ ጨዋታውን በሚያደርግበት ደቡብ ሱዳን ከተማ ጁባ ጉዞውን ያደርጋል።ዋልያዎቹ የፊታችን አርብ ከሱዳን 🇸🇩 ጋር እንዲሁም በቀጣይ ሳምንት ማከሰኞ ከ ሴኔጋል 🇸🇳 ጋር በባህርዳር ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።አፍሪካ ዋንጫ ለመግባት የሚደረግ ውድድር መሆኑን ያነሱት አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ “ የምንወዳደረው ለማሸነፍ ነው ፣ ይሄ የታዳጊ ቡድን አይደለም ” ብለዋል።“ ስምምነቴ ቡድኑን ለማሳለፍ ነው ከላሳለፍኩኝ ሌላ አዲስ አሰልጣኝ ይመጣል።” ሲሉ ጨምረው ተናግረዋል።
TIKVAH-SPORT
21 Sept, 12:54edited
“ በእኔና ዴምቤሌ መካከል የተፈጠረ ነገር የለም ” ምባፔፈረንሳዊው ተጨዋች ኪሊያን ምባፔ በእሱ እና ኡስማን ዴምቤሌ መካከል የተፈጠረ ነገር እንደሌለ ገልጿል።ሁለቱ ተጨዋቾች በባሎን ዶር ሽልማት ዘመቻዎች ዙሪያ አለመግባባት ውስጥ እንደሆኑ ሲነገር ነበር።ምባፔ ሲናገርም “ በዚህ ጉዳይ ከእሱ ጋርም አስቀድሜ ተነጋግሬ ነበር ምንም ነገር የለም ጓደኛዬ ነው ” ብሏል።"በብሔራዊ ቡድን ቆይታ ወቅት የተለያዩ ጉዳዮችን እየፈለጉ መከራከር የተለመደ ነው ነገርግን የተፈጠረ ነገር የለም " ሲል ተናግሯል።ምባፔ አያይዞም ከዚህ በኋላ ስለ ባሎን ዶር ሽልማት አስተያየት መስጠት እንደማይፈልግ ተናግሯል።@tikvahethsport @kidusyoftahe
Followers write to the bot, you answer by reply, your account stays hidden. Created in one tap.
How it works →Related Channels
Other channels in the same section of the catalogue.
