Latest posts

Wolaita Sodo University
7 Apr 2025, 14:15
በበሌ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ኢንጂነርንግና ሂሳብ (STEM) ስልጠና መስጠት ተጀምሯል፡፡ወሶዩ፤ 29/07/2017 ዓ.ም የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ስቴም( STEM) ማዕከል ከኢንፎርማቲክ ት/ቤት ጋር በመተባበር በወላይታ ዞን ኪንዶ ኮይሻ ወረዳ በሌ ሀዋሳ ከተማ በሌ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለሚገኙ ተማሪዎች የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፡ ኢንጂነርንግና ሂሳብ ትምህርቶች እንዲሁም የቢዝነስና ስራ እድል ፈጠራ ላይ ያተኮረ ስልጠና በትምህርት ቤቱ ግቢ እየተሰጠ ይገኛል።«ዕውቀትን በተግባር!!»የዩኒቨርሲቲው ህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ቢሮወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟላ መረጃ ለማግኘት ትክክለኛውን የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!!ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/Wolaita-Sodo-University-246568056057804/ ቴሌግራም፡https://t.me/WolaitaSUniversity ዩቲዩብ፡ https://www.youtube.com/.../UC6VukdZbl5iVgZGXG8BkMdw/videos ዌብሳይት፡ http://www.wsu.edu.et/ ትዊተር፡ https://twitter.com/WSodoUniversity... ኢንስታግራም፡ https://instagram.com/wolaita_sodo_university?igshid=YmMyMTA2M2Y=አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን




Wolaita Sodo University
5 Apr 2025, 16:55
በዩኒቨርሲቲው፣ በቻይና መንግስት እና በኢትዮጵያ ማዕድንና ኢነርጂ ሚኒስቴር በሶስትዮሽ የጋራ ትብብር ተገንብቶ በመጠናቀቅ ላይ ስለሚገኘው የባዮጋዝ ሃይል ማመንጫ አጠቃቀም ዙሪያ ለዘርፉ ባለሙያዎች ስልጠና ተሰጠ።የባዮጋዝ የኃይል ማመንጫ ፕሮጀት ግንባታ በቅርቡ ሙሉ በሙሉ ተጠናቅቆ መደበኛ የሃይል ማመንጨት ስራውን እንደሚጀምርም ተጠቁሟል።በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ግቢ እየተገነባ ያለው ባዮጋዝ የኃይል ምንጭ ሆኖ ለአካባቢው ማህበረሰብ ከሚሰጠው ጥቅም በተጨማሪ ለዘርፉ ተማሪዎች ሰርቶ ማሳያ እንደሚሆንና የተለያዩ የምርምር ስራዎችን ለመስራት እንደሚያግዝ የዩኒቨርሲቲው ምርምር ዘርፍ ዳይሬክተር የሆኑት ዶክተር ዳዊት ዳልጋ ገልጸዋል።ዶክተር ዳዊት አክለውም ስልጠናው ለዘርፉ ባለሙያዎች ያለው ጠቀሜታ ከፍተኛ መሆኑን በማንሳት ሰልጣኞች ከስልጠና ያገኙትን ዕውቀትና ክህሎት በአግባቡ ተግባራዊ በማድረግ የኅብረተሰቡ ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ መሥራት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።በስልጠና መርሀ ግበር ላይ የዩኒቨርሲቲው ተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጂ ዲን ዶክተር ሰለሞን ጉንታ በበኩላቸው ዩኒቨርሲቲው ይህንን ግዙፍ የባዮጋዝ ፕሮጀክት የመስራት ዕድል በማግኘቱ መደሰታቸውን ገልጸው ፕሮጀክቱ በቅርቡ በተጨባጭ ሀይል ከማመንጨት ባለፈ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በተግባር የሚማሩበትና ምርምር የሚያደርጉበት የሙከራ ቦታ ይሆናል ብለዋል።የየባዮጋዝ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ዋና አስተባባሪ የሆኑት መምህርና ተመራማሪ ረዳት ፕሮፌሰር አሸናፊ አበበ የባዮጋዝ ግንባታ ፕሮጀት የእስካሁኑ አፈፃፀም ከ90% በላይ የደረሰ መሆኑ ተናግረው
Wolaita Sodo University
5 Apr 2025, 16:55





Wolaita Sodo University
5 Apr 2025, 16:55
የኢ. ፌ. ዴ. ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ያዘጋጀው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚዎች ፎረም መካሄድ ጀምሯል።በፎረሙ የኢ. ፌ. ዴ. ሪ ትምህርት ሚኒስቴር የሚኒስትር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጌታቸው ተፈራ፣ የህዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ቦጋሌ፣ የኢትዮጵያ መገነኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሳምሶን መኮንን፣ የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት እንዲሁም አጠቃላይ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚዎች ተገኝተዋል።በፎረሙ የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መሠረታዊ ሀሳብ (Principles of public Relations)፣ Contemporary public Relations and Communicatin Strategy፣ Leveraging Digital Media for Public Relations፣ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት KPIs እና የኮሚዩኒኬሽን ሚናና ኃላፊነት በተመለከተ ገለጻ እንደሚደረግ እንዲሁም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚዎች ፎረም የመመስረቻ ፕሮግራም ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል።➭ «ዕውቀትን በተግባር!!»የዩኒቨርሲቲው ህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ቢሮ➤ የካቲት 16/2017 ዓ.ምወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟላ መረጃ ለማግኘት ትክክለኛውን የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/Wolaita-Sodo-Universi
Wolaita Sodo University
5 Apr 2025, 16:55



10,800Open in Telegram
Wolaita Sodo University
5 Apr 2025, 16:53
በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ድጋፍ በህዝብ አስተያየት፣ በሚዲያ ሞኒተርንግ፣ በሚዲያና ህዝብ ግንኙነት እና በዲጂታል ሚዲያ ዙሪያ በወላይታ ዞን ለሚገኙ የዘርፉ መራሮችና ባለሙያዎች ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቀቀ።በስልጠና መድረክ ላይ በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የኮሚኒኬሽንና ህዝብ ግንኙነት ትምህርት ክፍል መምህርና ተመራማሪ ዶ/ር ተሻለ ተገኔ መንግስት የኮሚዩኒኬተሮችን አቅም እያጎለበተ የተደራጀ መረጃ ለህዝብ እንዲደርስ እየሠራ ያለው ሥራ የሚደነቅ ነው ብለዋል።ሚዲያ አራተኛ መንግስት እንደሆነ የተለያዩ ጥናቶች ያነሳሉ ሲሉ የገለጹት ዶ/ር ተሻለ ዘርፉ በብቃት፣ በዕውቀት እና በሰለጠነ የሰው ኃይል ካልተመራ ሀገር አፍራሽ መረጃዎች ሊሠራጩ ስለሚችሉ የዘርፉ አመራሩም ሆነ ባለሙያ የተጣለበትን ኃላፊነት በአግባቡ መወጣት አለባቸው ሲሉም አንስተዋል።ውስብስብ በሆነ የመረጃ ልውውጥ ጊዜ ላይ ነን ያሉት ዶክተር ተሻለ የህዝብ ግንኙነት ሥራ በህዝብና መንግስት መካከል ድልድይ በመሆን እንደሚያገለግል ገልጸው የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በዘርፉ ያለውን ክፍተት በመገንዘብ በዞኑ ውስጥ በኮሚዩኒኬሽን፣ በህዝብ ግንኙነትና በሚድያ ለሚሰሩ አመራሮችና ባለሙያዎች ስልጠና መስጠቱ የመረጃው ጥራትና ተደራሽነት አግባብነት ያለው እንዲሆን ያደርጋል ብለዋል።በስልጠና ማጠቃለያ ላይ የተሰጠው ሥልጠና ለቀጣይ ሥራ አቅም የሚሰጥ በመሆኑ በሥልጠና የተገኘውን ዕውቀት ወደ ተግባር በመቀየር የተፈለገው የተግባቦትና የመረጃ ፍሰት እንዲኖር ከአመራሩም ሆነ ከባለሙያው ቁርጠኝነት ይጠበቃል ተብሏል።አመራሮች የመሪነት ሚናቸውን መወጣት እንዲሁም
Wolaita Sodo University
5 Apr 2025, 16:53




Wolaita Sodo University
5 Apr 2025, 16:52
የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ እና በቻይና አገር የሚገኘው ይብን (Yibin) ዩኒቨርሲቲ በአጋርነት በሚሰሩ ጉዳዮች ዙሪያ በበየነ መረብ (Online Discussion) ውይይት አደረጉ።በውይይቱ ሁለቱ ተቋማት በትኩረት መስካቸው መስረት የጋራ የመግባቢያ ስነድ (MoU) ተዘጋጅቶ በመፈራረም ለመሥራት መስማማታቸውም ተመላክቷል።በውይይቱ ላይ የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት ዶክተር አክበር ጩፎ በኢ. ፌ . ዴ. ሪ ትምህርት ሚኒስቴር በምክንያታዊነት ልየታ (Justification) መረረት የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በግብርና፣ በምህንድስናና ቴክኖሎጂ፣ በከርሰ ምድር ጥናት እና በሥነ ሰብ የትኩረት መስኮች ላይ የተፈለገው ውጤት እንዲመዘገብ ሰፊ ተግባራትን እያከናወነ መቆየቱን አብራርተዋል።ዶክተር አክበር አክለውም ዩኒቨርሲቲው እ አ አ 2030 ቴክኖሎጂ መሪ የግብርና ልህቀት ማዕከል ሆኖ የማየት ራዕይ ሰንቆ እየሠራ መሆኑን ጠቁመው በሀገር አቀፍም ሆነ በዓለም አቀፍ ከሚገኙ አካዳሚክ ተቋማት ጋር መሥራት ለራዕይው ስኬት የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ ስለሆነ ከይብን (Yibin) ዩኒቨርሲቲ ጋር በትብብር በትጋት ለመሥራት ዩኒቨርሲቲው ቁርጠኛ መሆኑን ተናናግረዋል።በበየነ መረብ በተደረገው ውይይት የቻይናው ይብን (Yibin) ዩኒኒቨርሲቲ ተወካዮች ስለወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በተደረገው ገለፃ መደሰታቸውን ገልጸው ሁለቱ ተቋማት ተጨባጭ ለውጥ ለማስመዝገብ በጋራ ለመሥራት ዝግጁ መሆናቸውን አስረድተዋል።በውይይቱ የይብን (Yibin) ዩኒቨርሲቲ ስለቻይና ባህልና ቋንቋ ትምህርት በመስጠት የሁለቱን ሀገራት
Wolaita Sodo University
5 Apr 2025, 16:52





Wolaita Sodo University
1 Apr 2025, 15:34
#ማስታወቂያበወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ #መርሃ #ግብሮች በመደበኛና በተከታታይ ፕሮግራሞች ለመማር ለሚፈልጉ ሁሉ፡-ዩኒቨርሲቲው ከታች በተመለከቱ መርሀ ግብሮች በመደበኛና በሳምንት መጨረሻ ለመማር የሚፈልጉትን ለማስተናገድ ዝግጅቱን ጨርሶ ተመዝጋቢዎችን እየተጠባበቀ ይገኛል፡፡በመሆኑን የ2017 ዓ.ም NGAT ተፈትኖ የማለፊያ ውጤት ያስመዘገበ እስከ 26/07/2017 ዓ.ም ድረስ መመዝገብ የሚችል መሆኑን እናስታውቃለን፡፡ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲዕውቀትን በተግባር!




Wolaita Sodo University
1 Apr 2025, 15:02





Wolaita Sodo University
1 Apr 2025, 15:02
ወቅታዊ አስጊ የሆነውን የትራፊክ አደጋ ለመቀነስ እንዲቻል በመንገድ ደህንነት ሥራ ላይ በጎ ፈቃደኛ ተማሪዎችን ለማሰማራት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና (ንድፈ ሀሳብ ማብራሪያ) ተሰጥቶ ወደ ሥራ መገባቱ ተገለፀ፡፡ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በየደረጃው የማህበረሰብ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችሉ የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነ ማህበረሰባዊ ኃላፊነት (SocialResponsibility) እየተወጣ እንደሆነም ተገለጸ፡፡የዩኒቨርሲቲው ምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክት ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዘውድነህ ቶማስ በዩኒቨርሲቲው ተነሳሽነት የተለያዩ ሙያዊ በጎ አድራጎት ተግባራት በትምህርት፣ በጤና፣ በግብርና እና በሌሎችም ዘርፎች እየተከናወኑ እንደሆነ ገልፀው በከተማው በትራፊክ ፍሰት ምክንያት እየተንፀባረቀ የሚገኘው የሞትና የንብረት ውድመት ምጣኔ እንዲቀንስ በዘርፉ በጎ ፈቃደኛ ተማሪዎችን ለማሰማራት የተሰጠ ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ትርጉሙ ብዙ ነው ብለዋል፡፡ዶክተር ዘውድነህ አክለውም በሀገር አቀፍ ደረጃ እጅግ አሳሳቢ እየሆነ የመጣውን የመንገድ ትራፊክ አደጋ ለመከላከል ሊወሰዱ በሚገቡ የመንገድ ትራፊክ ደህንነት እርምጃዎች ዙርያ የባለድርሻ አካላት ተቀናጅተው መስራት ይኖርባቸዋል ብለዋል።ዩኒቨርሲቲው ዘንድሮ የጀመረው በጎ አድራጎት (Professional volunteerism) ሥራዎች አንዱ የሆነው ለ12ኛ ክፍል መልቀቂያ (ዩኒቨርሲቲ መግቢያ) ፈተና ለሚዘጋጁ ተማሪዎች ፈቃደኛ በሆኑ የዩኒቨርሲቲው መምህራን በሳምንት መጨረሻ የማጠናከሪያ ትምህርት መስጠት መጀመሩን ያወሱት ዶክተር ዘውድነህ በአሁን ወቅት ደግሞ በመንገድ ትራፊክ
Wolaita Sodo University
1 Apr 2025, 12:40




Related Channels
Other channels in the same section of the catalogue.
