gram news
የሕያ ኢብኑ ኑህ | Yahya Ibnu Nuhe channel avatar

የሕያ ኢብኑ ኑህ | Yahya Ibnu Nuhe

@yahyanuhe

﷽ | Muslim | Theology | Comparative Religion | Philosophy | Student | ለንግድ፣ ለህክምና ወይም ለጉብኝት ወደ ቱርክ፣ ዱባይ እና የተለያዩ ሀገራት ለመጓዝ ካሰባችሁ ፈሲሩ ትራቭል የትኬት ጉዳያችሁን በኃላፊነት ያጠናቅቃል። እንግልት የሌለበት ጉዞ ለማድረግ ስትፈልጉ በዋትስአፕ አግኙን፦ https://wa.me/qr/5CWCIMYBZLCJB1

ProjectsENReligion

21,200subscribers

Open the Channel

Latest posts

  • የሕያ ኢብኑ ኑህ | Yahya Ibnu Nuhe

    22 Sept, 11:23

    በመድኃኒት እና በህክምና መገልገያ መሣሪያዎች አስመጪነት ስራ ላይ ኖዎት? ወይስ አዲስ ማስመጣት አስበዋል? ለስራዎ ስኬት የሚያግዝ አስተማማኝ የማማከር አገልግሎት ከፈለጉ በዚህ አድራሻ ያነጋግሩን። በተጨማሪም Single Window ላይ የሚሰሩ ስራዎችን በታማኝነት እንሰራለን።
    1,2802041Open in Telegram
  • የሕያ ኢብኑ ኑህ | Yahya Ibnu Nuhe

    22 Sept, 11:19

    forwarded from @abuyusra3

    በመድኃኒት እና በህክምና መገልገያ መሣሪያዎች አስመጪነት ስራ ላይ ኖዎት? ወይስ አዲስ ማስመጣት አስበዋል? ለስራዎ ስኬት የሚያግዝ አስተማማኝ የማማከር አገልግሎት ከፈለጉ በዚህ አድራሻ ያነጋግሩን።በተጨማሪም Single Window ላይ የሚሰሩ ስራዎችን በታማኝነት እንሰራለን።
    1,250154Open in Telegram
  • የሕያ ኢብኑ ኑህ | Yahya Ibnu Nuhe

    22 Sept, 10:59edited

    ​​ጳውሎስ ጽሑፎቹን ያዘጋጀው በመንፈስ ቅዱስ ተመርቶ ነው የሚለውን እምነት፣ የራሱ መልእክቶች በጥልቅ ሲመረመሩ ጥያቄ ውስጥ ይወድቃሉ። በቲቶ 1፡12-14 ላይ ጳውሎስ ኤፒሜኒደስ የተባለውን የቀርጤስ ሰው ጠቅሶ "የቀርጤስ ሰዎች ዘወትር ውሸታሞች ናቸው" ይልና፣ ይህንን ራሱን የሚያጠፋ የሎጂክ ስህተት ሳይረዳ "ይህ ምስክር እውነት ነው" ብሎ በማጽደቅ ግልጽ የሆነ ሰብዓዊ ስህተት ፈጽሟል። የቀርጤስ ሰዎች ዘወትር ውሸታሞች ከሆኑ፣ የቀርጤሱ ኤፒሜኒደስ የተናገረውም ቃል ውሸት መሆን አለበት፤ ቃሉ ውሸት ከሆነ ደግሞ የቀርጤስ ሰዎች እውነተኞች ናቸው ማለት ነው።​ይህን መሰረታዊ የሎጂክ ግጭት ጳውሎስ አለመረዳቱ፣ መጽሐፉ ከመለኮታዊ መነሳሳት የመጣ አለመሆኑን ያጋልጣል። በተጨማሪም ጳውሎስ በ1ኛ ቆሮንቶስ 7፡25 ላይ "ስላላገቡ ሰዎች ከጌታ የተቀበልኩት ትእዛዝ የለኝም፤ ነገር ግን በጌታ ምሕረት እምነት የሚጣልብኝ እንደ መሆኔ መጠን የራሴ ሐሳብ ከዚህ ቀጥሎ ያለው ነው፤" በማለት ትምህርቶቹ ከፈጣሪ የመጡ ሳይሆኑ የራሱ የግል ሀሳቦችና አስተያየቶች መሆናቸውን በግልጽ አረጋግጧል። ይህ ሁሉ የሚያሳየው ጳውሎስ ስህተት ሊሰራ የሚችል፣ በራሱ አእምሮ ብቻ የሚመራ ግለሰብ እንጂ መለኮታዊ ራእይ የተቀበለ ሐዋርያ አለመሆኑን ነው።​Footnotes:• ​Hyam Maccoby, The Mythmaker: Paul and The Invention of Christianity, Chapter 1: The Problem of Paul.• ​Thomas Fowler, The Elements of Deductive Logic: Designed Mainly
    Image from a post by የሕያ ኢብኑ ኑህ | Yahya Ibnu NuheImage from a post by የሕያ ኢብኑ ኑህ | Yahya Ibnu Nuhe
    1,380182Open in Telegram
  • የሕያ ኢብኑ ኑህ | Yahya Ibnu Nuhe

    19 Sept, 08:09

    በታዋቂው የፈረንሳይ ስነ-ጽሑፍ ሊቅ ቪክቶር ሁጎ በተጻፈው "The Hunchback of Notre-Dame" በተሰኘው መጽሐፍ ውስጥ፣ ሁለት ተቃራኒ ገጸ-ባህሪያት ይገኛሉ። አንደኛው በአካላዊ ተፈጥሮው የጎበጠውና በማህበረሰቡ የተገፋው፣ ነገር ግን እጅግ ንጹህና የዋህ ልብ ያለው ኳሲሞዶ ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ የቤተክርስቲያኗ ከፍተኛ የሃይማኖት አባትና ምሁር የሆነው፣ ነገር ግን በውስጡ የክፋት፣ የጥላቻና የጭካኔ ቁልል የተሸከመው ክላውድ ፍሮሎ ነው። ሁጎ በዚህ ስራው፣ እውነተኛው ጭራቅነት የአካል ወይም የአዕምሮ መዛባት ሳይሆን፣ በሃይማኖት ካባ የተሸፈነ የሞራል ውድቀት መሆኑን ለማሳየት ሞክሯል።ሰሞኑን ዘመድኩን በቀለ የተባለው ግለሰብ፣ በኦቲዝም በተጠቁ ምስኪን ህጻናት ላይ አፉን እያጣመመና እየጮኸ ሲያላግጥ የሚያሳየውን አሳዛኝ ድርጊት ስመለከት፣ የሁጎው የክፋት ገጸ-ባህሪ ነው ትዝ ያለኝ።ይህ ሰው እኮ እኛ "ችላ እንበለው" እንደምንለው አይነት ተራ ግለሰብ አይደለም። ከቤተ ክርስቲያኗ ታዋቂ ዩንቨርሲቲ ከሆነው ከቅድስት ስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ በቲዮሎጂ የተመረቀ፣ የሃይማኖት መምህር ነኝ ባይ ነው። ነገር ግን ምንም አይነት ፖለቲካዊ አላማና የትርክት ፍላጎት ቢኖርህ፣ ምንም በማያውቁና ልዩ እንክብካቤ በሚሹ የኦቲዝም ህጻናት ላይ ለማሾፍ ግን ከምንም በላይ የዘቀጠ ስብዕና እና የሞተ ህሊና ሊኖርህ ይገባል።የጥንት አበው "መምህሩ ኮሶ ቢጠጣ፣ ተማሪው ሬት ይልሳል" ይላሉ። መምህር እና የሃይማኖት አባት ነኝ የሚል አካል ይህን ያህል መግለጫ ወደሌለው የብልግና ሌቭል ውስጥ ከወረደ፣ እርሱን የሚያዳምጠውና
    3,010382217Open in Telegram
  • የሕያ ኢብኑ ኑህ | Yahya Ibnu Nuhe

    19 Sept, 08:08

    Image from a post by የሕያ ኢብኑ ኑህ | Yahya Ibnu NuheImage from a post by የሕያ ኢብኑ ኑህ | Yahya Ibnu Nuhe
  • የሕያ ኢብኑ ኑህ | Yahya Ibnu Nuhe

    18 Sept, 19:16edited

    ከሰሞኑ በአንዳንድ ጽንፈኛ አካላት ዘንድ፣ ቅዱስ ቁርኣን ማቃጠል እንደ ትልቅ ጀብዱ እና የድፍረት መገለጫ ተደርጎ ሲከወን አይተናል። ሙስሊሙ በስሜታዊነት ተገፋፍቶ መጽሐፍ ቅዱስን አፀፋውን ለመመለስ ሲያቃጥል ባለማየታቸው ግን ክፉኛ የተበሳጩ ይመስላሉ። ይህ የጥላቻ ጥማታቸው ስላላረካላቸውም፣ እራሳቸው መጽሐፍ ቅዱስን በማቃጠል "ሙስሊሙ አቃጠለ" የሚል የቂል ድራማ እስከመስራት ደርሰውም ተመልክተናል። ሙስሊሙ ይህንን የማያደርግበት ቀይ መስመር እንዳለው ግልጽ ነው፤ በእምነቱም ሆነ በስነ-ምግባሩ ሊያደርገው ፈጽሞ አይችልም!ለመሆኑ ሙስሊሙ ለምን አፀፋውን አይመልስም? ከተባለ አንደኛ፣ ይህ ተግባር ከእስልምና የሞራል እና የስነ-ምግባር መርህ ጋር ፈፅሞ ይጋጫል። የአንድ መጽሐፍ ይዘት ካልተመቸን፣ በሀሳብ እንሞግታለን፣ እንከራከራለን፣ እንወያያለን እንጂ ወረቀት አናቃጥልም። መጽሐፍን ማቃጠል የሀሳብ ድህነት እና የተሸናፊነት ምልክት ነው። ጥላቻም ቢሆን የራሱ የሆነ ልክና ገደብ አለው። ከዚህም ባሻገር፣ ሌላው አካል የሚያከብረውን ነገር በማበሻቀጥ ሰዎችን ወደ ቀናው መንገድ መጋበዝ አይቻልም።ሁለተኛው እና ዋነኛው ምክንያት ደግሞ ከእምነታችን መሰረት ጋር የሚያያዝ ነው። እኛ ሙስሊሞች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የገቡ የሰው እጆችና የተበረዙ ትምህርቶች አሉ ብለን ብናምንም፣ በተመሳሳይ መልኩ የቀደሙት መለኮታዊ መመሪያዎች (የተውራትና ኢንጂል) ቃላት አሁንም በውስጡ እንደሚገኙ ፅኑ እምነት አለን። ስለዚህ እነዚህን መጽሐፍት በጥላቻ ተገፋፍቶ ማቃጠልና ማዋረድ በእስልምና ፍፁም የተከለከለ ተግባር ነው።የእስልምና
    2,7406118211Open in Telegram
  • የሕያ ኢብኑ ኑህ | Yahya Ibnu Nuhe

    18 Sept, 19:15

    Image from a post by የሕያ ኢብኑ ኑህ | Yahya Ibnu NuheImage from a post by የሕያ ኢብኑ ኑህ | Yahya Ibnu Nuhe
  • የሕያ ኢብኑ ኑህ | Yahya Ibnu Nuhe

    15 Sept, 09:05

    forwarded from @hidayaic8212

    የሱና አስፈላጊነት የመጀመሪያ ዙር 4 ጥያቄዎችን በሚከተለው ሊንክ መመለስ ይችላሉ፦ለጥያቄው ሲስተሙ የሚሰጥዎት ጊዜ ⏱ 5 ደቂቃ ብቻ ነው።መልካም እድል፦t.me/QuizBot?start=1zuNVhJt
    Quiz Directoryየሱና አስፈላጊነት4 questions
  • የሕያ ኢብኑ ኑህ | Yahya Ibnu Nuhe

    14 Sept, 18:27

    forwarded from @hidayaic8212

    የስልጠናው ኦዲዮው አጭር ማብራሪያ፦ይህ የመጀመሪያው የድምጽ ክፍል ስለ 'ሱና' ምንነት እና የሐዲስ አጠባበቅ ታሪክ ጥልቅ ግንዛቤን የሚያስጨብጥ ነው። ፋይሉን በጉጉት እንድታዳምጡት የሚጋብዙ ዋና ዋና ነጥቦች የሚከተሉት ናቸው፦• ሱና በቋንቋ እና በሸሪዓዊ አገባቡ (ከነብዩ ንግግር፣ ተግባር እና ማጽደቅ አኳያ) ምን ማለት እንደሆነ በዝርዝር ያብራራል።• የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሐዲሶች ከመጀመሪያው ጀምሮ እንዴት በአራት ዋና ዋና መንገዶች (በማስታወስ/በመሸምደድ፣ በመጻፍ፣ እርስ በርስ በመማማር እና በተግባር በመተርጎም) ተጠብቀው እንደቆዩ ይተነትናል።• ገና በሶሓባዎች ዘመን (እንደ አብደላህ ኢብኑ አምር፣ አሊ ኢብኑ አቢ ጧሊብ፣ አቡ ሁረይራ እና አነስ ኢብኑ ማሊክ) የራሳቸው 'ሰሒፋ' (የጽሁፍ ስብስቦች) እንደነበሯቸው ታሪካዊ ማስረጃዎችን ያቀርባል።• ከሰሒፋዎች በመቀጠል የሐዲስ ስብስቦች እንዴት ወደ 'ሙሰነፍ' (በርዕስ የተከፋፈሉ)፣ 'ሙስነድ' (በሶሓባዎች ስም የተከፋፈሉ) እና 'ሱነን' (በፊቅህ ህግጋት የተከፋፈሉ) መጻሕፍት እንዳደጉ በሰፊው ይዳስሳል።• የሐዲስን ትክክለኛነት ለማረጋገጥ በዑለማዎች ስለተዘረጉት ጥብቅ ሳይንሶች (እንደ ዒልሙ ሪጃል፣ ዒልሙል ዒለል የመሳሰሉት) ያስገነዝባል።© ዳሩል ሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል
    3,540file2462Open in Telegram
  • የሕያ ኢብኑ ኑህ | Yahya Ibnu Nuhe

    11 Sept, 14:37

    forwarded from @hidayaic8212

    አዲስ እና ልዩ አጭር ኮርስ ከሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል | #1ኛ ዙር ስልጠና​“ቁርአን ብቻ ይበቃናል” የሚሉ አካላት መነሻቸው ምንድን ነው? የሱና (ሀዲስ) አስፈላጊነትና በኢስላም ውስጥ ያለው ድርሻስ ምን ያህል ነው?​እነዚህን እና ሌሎች ተያያዥ አንገብጋቢ ጥያቄዎችን በሰፊው የሚዳስሰውን 1ኛ ዙር የንፅፅር ትምህርት ኮርስ በማዕከላችን የቴሌግራም ቻናል ይዘንላችሁ ቀርበናል።• ​አዘጋጅ፦ ኢልያህ ማሕሙድ• ​የሚሰጥበት ቦታ፦ በሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል የቴሌግራም ቻናል​ይህንን ወሳኝ ኮርስ ሙሉ በሙሉ ተከታትለው በመጨረሻም የሚዘጋጀውን ፈተና ለሚወስዱ እና ለሚያልፉ ተሳታፊዎች በሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል በኩል የምስክር ወረቀት ይሰጣል።​እውቀትን ከትክክለኛው ምንጭ እንቅሰም! ትምህርቱን ለመጀመር የቴሌግራም ቻናላችንን አሁኑኑ ይቀላቀሉ፦https://t.me/Hidayaic8212
    Image from a post by የሕያ ኢብኑ ኑህ | Yahya Ibnu NuheImage from a post by የሕያ ኢብኑ ኑህ | Yahya Ibnu Nuhe
    4,760231511Open in Telegram
  • የሕያ ኢብኑ ኑህ | Yahya Ibnu Nuhe

    1 Sept, 14:16

    ስለ ወንድሜ አብዱረሒም አህመድ...ወንድሜ አብዱረሒም አህመድን በግል ቅርበት ያወቅኩት፣ የ"ድምፃችን ይሰማ" ንቅናቄ በጎመራበትና የሙስሊሙ ትግል ጫፍ በደረሰበት በዚያ ፈታኝ ወቅት ነበር። ጊዜው በመንግሥት በኩል ከፍተኛ አፈና የነበረበት ሲሆን፣ በግሌ የማውቃቸው በርካታ ጓደኞቼ በወቅቱ በነበረው እንቅስቃሴ ምክንያት ማረሚያ ቤት ወርደው ስለነበር፣ በሚዲያ ቀርቦ መናገር ከፍተኛ ስጋት ነበረው። በወቅቱ ደግሞ ቢቢኤን ሬዲዮ የትግሉ አንደበት ሆኖ በስፋት ይደመጥ ነበር።በዚህ ጭንቀት ውስጥ ሆኜ ነበር አብዱረሒም ለአንድ ቃለ-መጠይቅ ያናገረኝ። ስጋቴን ሲረዳ፣ ማንነቴ እንዳይታወቅ ድምፄን ቀይሮ ሊያቀርበኝ ቃል ገባ። በቃሉ መሠረት ኢንተርቪው አደረግን፤ ቃለ-መጠይቁንም አየር ላይ አዋለው። ያ አጋጣሚ ለረጅም ዓመታት የዘለቀው ወንድማዊ ወዳጅነታችን የመሠረት ድንጋይ ሆነ።ጊዜያት ነጉደው የ"ሀሩን ሚዲያ" ምዕራፍ ሲከፈት፣ አብዱረሒም ለኡማው ያለው ተቆርቋሪነት ይበልጥ ያስተዋልኩበት ነበር። በተለይም ለዲን ሲሉ ዋጋ የሚከፍሉ ሰዎች ጉዳይ እንቅልፍ ይነሳው ነበር። የዳዕዋው ሥራ አቅም እንዲያገኝና ሕዝበ ሙስሊሙም ትኩረት እንዲሰጠው በማስተባበር፣ "አይዟችሁ" በማለት ከጎናችን ቆሞ ከፍተኛ ትግል አድርጓል። በዚህ ሒደት ውስጥ ስህተት ነው ብሎ ያመነውን ያለምንም ፍርሀት በግልጽ ከመናገር ወደኃላ አይልም።የእሱ በጎነት ግን በእኛ የንጽጽር ዳዕዋ ላይ በሚደረግ አይዟችሁ ባይነት ብቻ የተገደበ አልነበረም። ለሙስሊሙ ኡማ ተብለው ከተቋቋሙ የትኞቹም ተቋማትና ድርጅቶች ጋር በነበረው ግንኙነት እጅግ ቀና አመለካከት
    6,450106389Open in Telegram
  • የሕያ ኢብኑ ኑህ | Yahya Ibnu Nuhe

    1 Sept, 14:16

    Image from a post by የሕያ ኢብኑ ኑህ | Yahya Ibnu NuheImage from a post by የሕያ ኢብኑ ኑህ | Yahya Ibnu Nuhe
    4,77018Open in Telegram
  • የሕያ ኢብኑ ኑህ | Yahya Ibnu Nuhe

    25 Aug, 13:51edited

    በ20ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ ላይ በሚሽነሪዎች ዓለም ከተፈጠሩት እጅግ አወዛጋቢና የረቀቁ ስትራቴጂዎች አንዱ "የውስጥ እንቅስቃሴ" (The Insider Movement - IM) የተሰኘው ስልት ነው። የዚህ ስልት ዋነኛ ፍልስፍና "አንድ ሙስሊም ክርስቲያን ለመሆን ዲናዊ የነበረውን አኗኗሩን፣ ማህበረሰቡንና ሃይማኖታዊ መለያውን መተው የለበትም" የሚል ነው።ከዚህ ቀደም ሰዎች እምነታቸውን ሲቀይሩ ስማቸውን ለአብነት ከ'መሀመድ' ወደ 'ጳውሎስ' ይቀይራሉ፣ ከመስጊድ ወጥተው ወደ ቤተክርስቲያን ይሄዳሉ። ይህ ግን በማህበረሰቡ ዘንድ መነጠልንና ከፍተኛ ተቃውሞን ስለፈጠረባቸው፣ አዲሱ ስልት ሰውዬው ራሱን "ሙስሊም" ብሎ እየጠራ፣ ነገር ግን በውስጡ የክርስትናን ዶክትሪን ተሸክሞ በማህበረሰቡ ውስጥ "የውስጥ አርበኛ" ሆኖ እንዲቀጥል የሚያደርግ የረቀቀ የስነ-ልቦና ስልት ነው።​ይህ ስልት መሬት ላይ እንዴት እንደሚተገበር የሚያሳየውን የመጀመሪያውን ተጨባጭ ምሳሌ እንመልከት፦ "የኢሳ ተከታይ ሙስሊሞች" (Messianic Muslims) የሚባለው አደረጃጀት ነው። በእነዚህ ሚሽነሪዎች የተጠመቀ አንድ ሙስሊም፣ የሙስሊም ስሙን አይቀይርም፣ የቀድሞ አለባበሱን አይተውም፣ አልፎ ተርፎም በቀን አምስት ጊዜ ወደ መስጂድ መሄዱን እና በረመዳን መጾሙን ሁሉ እንዲቀጥል ይደረጋል። ሆኖም መስጂድ ውስጥ ግንባሩን መሬት ላይ አስደግፎ ሱጁድ ሲያደርግ፣ ዱዓውን የሚያደርገው በአዲሱ ሚስጥራዊ እምነቱ መሠረት ለ"ጌታ ዒሳ" (ኢየሱስ) ነው። ሲጠየቅም "እኔ ክርስቲያን አይደለሁም፤ እኔ ዒሳ አል-መሲህን የምከተል ሙስሊም ነኝ" ይላል።ጆን ትራ
    6,980832053Open in Telegram
  • የሕያ ኢብኑ ኑህ | Yahya Ibnu Nuhe

    25 Aug, 13:50

    Image from a post by የሕያ ኢብኑ ኑህ | Yahya Ibnu NuheImage from a post by የሕያ ኢብኑ ኑህ | Yahya Ibnu Nuhe
    5,10092Open in Telegram
  • የሕያ ኢብኑ ኑህ | Yahya Ibnu Nuhe

    24 Aug, 17:28

    በቅርቡ የምክክር ኮሚሽኑ በሀገራችን የዘመን አቆጣጠር ላይ ሲውል የነበረውን እና ሃይማኖታዊ አንድምታ ያለውን "ዓ.ም." (ዓመተ ምህረት) በመተው፣ ሁሉንም አቃፊና ገለልተኛ እንደሚሆን በተስማሙበት "ዓ.ል." (ዓመተ ልደት) ወይም "እ.ኢ.አ." (እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር) እንሸጋገር የሚል ሀሳብ አቅርቧል። ይህን ተከትሎ ግን በአንዳንድ የኦርቶዶክስ እምነት አክቲቪስቶች ዘንድ ሰማይ ምድሩን የሚያቀልጥ ጩኸት እየሰማን ነው። አንዳንዶችም "ለምን የኛን ተውት ትላላችሁ? ሂጅራስ ለምን ሆነ?" እያሉ እያማረሩ ነው።​እዚህ ላይ ግን በግልጽ መነጋገር ያለብን እጅግ አስገራሚ ደብል ስታንደርድ አለ። ​በመጀመሪያ ደረጃ፣ ሙስሊሙ የራሱ የሆነ የ"ሂጅራ" ዘመን አቆጣጠር አለው። ሂጅራ የሚያመለክተው የነብዩ ሙሐመድን (ሰ.ዐ.ወ) ከጥቃት ለመሸሽ ያደረጉትን ታሪካዊ ስደት እንጂ፣ በማንም እምነት ላይ ጣልቃ የሚገባ (ቲዮሎጂያዊ) ትርክት የለውም።ይህን የሂጅራ አቆጣጠር "የኛን አይወክልም" በማለት እንዳንጠቀምበት ሲያወግዙ የነበሩ ወገኖች፣ ዛሬ ላይ ደግሞ ተመልሰው "ሙስሊሙን ጨምሮ ሁሉም ሰው 'ዓመተ ምህረት' ብሎ ካልጠራ ሞቼ እገኛለሁ" ማለታቸው የግብዝነት ጥግ ነው። የራስህን ሃይማኖታዊ መለኪያ በሌላው ላይ መጫን መብት አይደለም! ፈልገህ "ዓ.ም" ብለህ መጠቀም መብትህ እንደሆነው ሁሉ፣ የሌላውን አለመጠቀምም ማክበር ግዴታህ ነው።​እኛ ሙስሊሞች "ዓ.ም" (ዓመተ ምህረት) የሚለውን ለምን አንቀበለውም?ይህ ጉዳይ ከእልህ ወይም ከፖለቲካ ሳይሆን፣ ቀጥታ ከእስልምና ዐቂዳ ጋር የሚያያዝ ነው። እስልምና የነብዩላህ ዒሳን
    6,17096272Open in Telegram
  • የሕያ ኢብኑ ኑህ | Yahya Ibnu Nuhe

    24 Aug, 17:27

    Image from a post by የሕያ ኢብኑ ኑህ | Yahya Ibnu NuheImage from a post by የሕያ ኢብኑ ኑህ | Yahya Ibnu Nuhe
  • የሕያ ኢብኑ ኑህ | Yahya Ibnu Nuhe

    21 Aug, 18:42

    እፎይ የተሰኘው የካራ እምነት ተከታይ በሰሒሕ ሙስሊም ላይ የሰፈረውን ይህንን ሐዲስ አንስቶ ያቀረበው ትችት፣ የአላህን መሐሪነትና የሰውን ተፈጥሮ በቅጡ ካለመረዳት የመነጨ ነው። ሐዲሱ እኮ ሰዎችን ለኃጢአት የሚያነሳሳ ሳይሆን፣ በተቃራኒው ተስፋ መቁረጥን የሚያክም ታላቅ ነብያዊ መድኃኒት ነው። የሰው ልጅ እንደ መላእክት ኃጢአት የማይሠራ ፍጹም ፍጡር ሆኖ አልተፈጠረም፤ ስህተት ሰርቶ መመለስ የሚችል ነጻ ፍቃድ የተሰጠው ፍጡር ነው። አላህ እጅግ መሐሪ በመሆኑ፣ ይህ መለኮታዊ ባሕሪው ይቅርታ ጠያቂዎችን በምህረት የሚመለከትበት ማንነቱ ነው። ሰዎች ፈጽሞ የማይሳሳቱ ቢሆኑ ኖሮ፣ የመላእክትን ባህሪ ይላበሱ ነበር እንጂ የሰው ልጅ የመፈጠሩ ዓላማ በተግባር ባልታየ ነበር። ስለዚህ ሐዲሱ "ኃጢአት ሥሩ" እያለ ሳይሆን፣ "ብትሳሳቱም የአላህ እዝነት ከኃጢአታችሁ ይሰፋልና በተስፋ ወደ እርሱ ተመለሱ" የሚል የጠለቀ የውዴታና የተስፋ ቋንቋ ነው። [1]​ይህ ግለሰብ ይህንን መለኮታዊ የእዝነት ቋንቋ ከማጣጣሉ በፊት፣ እስኪ የራሱን መጽሐፍ ቅዱስ ቢያስተውለው ኖሮ ልክ እንደ ሐዲሱ ዓይነት ተመሳሳይ ትምህርት ባገኘበት ነበር። ኢየሱስ በሉቃስ ወንጌል ላይ፦ "ንስሐ ከማያስፈልጋቸው ከዘጠና ዘጠኝ ጻድቃን ይልቅ ንስሐ በሚገባ በአንድ ኃጢአተኛ በሰማይ ደስታ ይሆናል" በማለት ያስተምራል። [2] ታዲያ መጽሐፍ ቅዱስ "ከጻድቃን ይልቅ በኃጢአተኛው ንስሐ በሰማይ ትልቅ ደስታ ይሆናል" ሲል፣ አምላክ ሰዎች ጻድቅ ከመሆን ይልቅ ኃጢአት እንዲሠሩ ይፈልጋል ማለት ነውን? ብለን ብንጠይቀው አይደለም እንደሚል ግልጽ ነው፤ የንስሐን እና
    7,200934233Open in Telegram
  • የሕያ ኢብኑ ኑህ | Yahya Ibnu Nuhe

    21 Aug, 18:41

    Image from a post by የሕያ ኢብኑ ኑህ | Yahya Ibnu NuheImage from a post by የሕያ ኢብኑ ኑህ | Yahya Ibnu Nuhe
  • የሕያ ኢብኑ ኑህ | Yahya Ibnu Nuhe

    17 Aug, 10:47edited

    አላህ የፍጥረታትን መጨረሻ አስቀድሞ ያውቃል። ይህ መለኮታዊ ዕውቀቱ ፍጹም መሆኑን ያሳያል። ነገር ግን "አስቀድሞ አወቀ" ማለት "አስገድዶ አሠራ" ማለት አይደለም። ለምሳሌ፣ አንድ ብቁ መምህር የትኛው ተማሪው እንደሚያልፍና የትኛው በስንፍናው ምክንያት እንደሚወድቅ አስቀድሞ ሊያውቅ ይችላል፤ ወረቀት ላይም ሊጽፈው ይችላል። ተማሪው ሲወድቅ ግን የወደቀው መምህሩ አስቀድሞ ስላወቀና ስለጻፈው ሳይሆን፣ የራሱ ምርጫና ስንፍና ስላመጣበት ነው። አላህም ሰዎች በነጻ ምርጫቸው ምን እንደሚሠሩ አስቀድሞ ያውቃል፤ አዋቂነቱ ግን የሰዎችን ነጻ ምርጫ አይነጥቅም።አስተያየት ሰጪው ያነሳው ጥያቄ አዲስ አይደለም፤ ከ1400 ዓመታት በፊት ታላላቆቹ ሰሐባዎች ልክ እንደዚሁ ነብዩን (ﷺ) ጠይቀዋቸው ነበር። "የአላህ መልእክተኛ ሆይ! መጨረሻችን አስቀድሞ የታወቀ ከሆነ፣ ለምን ሥራን ትተን በውሳኔያችን ላይ ብቻ አንደገፍም?" አሏቸው። የነብዩ (ﷺ) ምላሽ እጅግ ድንቅ እና ሎጂካዊ ነበር፦ "ሥሩ! (መልካም ተግባርን ፈጽሙ)፤ ሁሉም ሰው ለተፈጠረለት (ለተዘጋጀለት) ነገር ይገራል (ይመቻችለታል)።" [1]​ይህ ማለት፣ አንተ የጀነት ሰዎች ከሚሠሩት መልካም ተግባር ጋር ራስህን ካገኘኸው፣ አላህ ለጀነት እያገራህ መሆኑን ታውቃለህ ማለት ነው። የገሀነም ሰዎች መጨረሻቸው የማይታወቀው እኮ፣ በምርጫቸው የገሀነምን ተግባር (ክህደትንና አመጽን) ስለፈጸሙ ነው። ስለዚህ አንድ ሙስሊም "ለገሀነም አለመወሰኔን በምን አወቅኩ?" ብሎ ተስፋ አይቆርጥም፤ ይልቁንም በአላህ እዝነት ተስፋ እያደረገ ወደ ጀነት የሚያደርሰውን ተግባር ይፈጽማል።​ይህ
    7,960492133Open in Telegram
  • የሕያ ኢብኑ ኑህ | Yahya Ibnu Nuhe

    17 Aug, 10:46

    Image from a post by የሕያ ኢብኑ ኑህ | Yahya Ibnu NuheImage from a post by የሕያ ኢብኑ ኑህ | Yahya Ibnu Nuhe
    5,11072Open in Telegram