gram news
ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU channel avatar

ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

@yasin_nuru

የ ያሲን ኑሩ ሐዲሶች Yasin Nuru "ወደ መልካም ነገር ያመላከተ ሰው የሰራውን ሰው ያህል አጅር ያገኛል" ረሱል (ﷺ) "የበጎ ስራ ምላሹ በጎ እንጂ ሌላ አይደለም " የብናኝ ክብደት ያክልም መልካምን የሰራ ሰው ያገኘዋል :>> { አል -ዘልዘለህ 7} UNOFFICIAL ለአስተያየት👇👇 @Hasabbbbot ሀዲሶችን ከፈለጋችሁ👇👇 @yasin_nuru_hadis

ProjectsARBlogs

42,400subscribers

Open the Channel

Latest posts

  • ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

    25 Sept, 14:16

    የዱሃ ሶላት...ነቢዩ (ﷺ) እንዳስተማሩን በሰውነታችን ውስጥ 360 መገጣጠሚያዎች ያሉ ሲሆን፣ በየቀኑ በሰላም ለተንቀሳቀሰበት ለእያንዳንዱ መገጣጠሚያችን ምስጋናና ሰደቃ ማቅረብ ይጠበቅብናል።ይሁን እንጂ የአላህ እዝነት ሰፊ ነውና—በረፋድ ሰዓት የምንሰግዳት ሁለት ረከዓ የዱሃ ሶላት ብቻዋን ለእነዚህ ሁሉ 360 መገጣጠሚያዎች እንደ ሙሉ ሰደቃና ምስጋና ሆና በቂ ሆና ትተካለች።የመስገጃ ወቅቱም ፀሐይ ወጥታ ከፍ ካለችበት (ረፋድ) ጀምሮ እስከ ዙህር ጥቂት ደቂቃዎች እስኪቀረው ድረስ ነው። በየቀኑ ጥቂት ደቂቃዎችን ሰጥተን ይህችን ውድ ሶላት በማዘውተር የሰውነታችንን ጤና ጸጋ እናመስግን!@yasin_nuru @yasin_nuru
    Image from a post by ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURUImage from a post by ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU
    3,120104151031Open in Telegram
  • ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

    24 Sept, 06:56

    ኻሊድ ቢን በርመክ እንዲህ ይላል፦ ❝ዝሙት የክፋት ፀባዮችን በሙሉ አጠቃልሎ የያዘ ነው። አንድ ዝሙተኛ ዘንድ አላህን መፍራት፣ ቃል ኪዳን ማክበርም ሆነ ለጓደኛ ታማኝ መሆንን አታገኝም።— ከኢብኑል ጀውዚ «አኽባሩ-ኒሳእ» ኪታብ የተወሰደوَلَا تَقْرَبُوا الزِّنَا ۖ إِنَّهُ كَانَ فَاحِشَةً وَسَاءَ سَبِيلًا"ዝሙትንም አትቅረቡ፡፡ እርሱ በእርግጥ መጥፎ ሥራ ነውና፡፡ መንገድነቱም ከፋ! "❝ከጋብቻ ያስፈራሩሃል፤ከዝሙት ግን አያስፈራሩህም።❞@yasin_nuru @yasin_nuru
    4,94080171251Open in Telegram
  • ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

    23 Sept, 13:37

    ረመዷን 4ወራት ከቀናት ይቀሩታል።#Terawih #Suhur #The doors of jannah will be open #Iftar #Shaytan❌#RAMADAN🥰❤@yasin_nuru @yasin_nuru
    6,170225258632Open in Telegram
  • ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

    22 Sept, 04:52

    ዐብዱላህ ኢብኑ ዑመር ( ረድየሏሁ ዓንሁማ) ከዕለታት አንድ ቀን ሚስቱን ፈታት።እሷም፦ «ከእኔ የምትጠላውን ነገር አይተህብኛልን?» ስትል ጠየቀችው።እሱም፦ «አልየሁም» አላት።እሷም፦ «ታዲያ ምን አግኝተህ ነው አንዲትን ንጹሕ እና ትእግስተኛ የሆነች ሙስሊም ሴት የምትፈታው?!» አለችው።ኢብኑ ዑመርም (የሷ ንግግር ልቡን ነክቶት) ከፍቺው ተመለሰ።📕ምንጭ-ሱነን ሰዒድ ኢብኑ መንሱር፡ 1099)@yasin_nuru @yasin_nuru
    5,9805620183Open in Telegram
  • ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

    19 Sept, 07:53

    አስተውል........👉‹‹ፍቅር ማለት በሀላል ተገናኝተህ የምትመሰርተው ትዳር ውስጥ የምታገኘው ምድራዊ ገነት ነው።› .......... 👉‹ባልሽ ግማሹን ኢማንሽን ሊሞላልሽ የሚፈልግ ሲሆን ከኒካህ በፊት የሚገኝ ጓደኛ ግን ቀሪውን ህይወትሽን ለማበላሸት የሚፈልግ ነው፡፡›› .......... 👉‹ዲኑንና ባህሪውን (አኽላቁን) የምትወዱለት ሰው ከጠየቃችሁ አጋቡት ( ካልሆነ በምድር ላይ ፈሳድ ጥፋትና ፊትናን እያንሰራፋችሁ መሆኑን ተገንዘቡ)፡፡›› ነብዩ ሙሀመድ (ሰ.ዐ.ወ) ....... 👉‹‹ጋብቻ በኔ ዘንድ የሚወደድ ተግባር ነው፡፡ እኔ ለምወደው ነገር ጀርባውን የሰጠ ለኔ ጀርባውን እንደሰጠ ነው፡፡›› ነብዩ ሙሀመድ (ሰ.ዐ.ወ) ........ 👉‹‹በኒካህ (ትዳር በመመስረት) አላህን ታዘዙት፤ቃል የገባላችኁን ይሰጣችኋልና› አቡበከር ሲዲቅ(ረዲያአላሁ.ዐንሁ). ....... 👉‹‹ከእናንተ መካከል በላጩ ሰው በሚስቱ መልካም አያያዝበላጫችሁ ነው›› ረሱል (አለይሂ ሠላቱ ወሠላም))@yasin_nuru @yasin_nuru
    6,43014822532Open in Telegram
  • ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

    18 Sept, 18:51

    በቁርኣን ውስጥ የመዲና ስም ማን ነው?@yasin_nuru @yasin_nuru
    Image from a post by ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURUImage from a post by ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU
    7,140591762Open in Telegram
  • ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

    17 Sept, 14:37

    "ወደ ቢሊየነርነት የሚያመሩ፣ በትንሽ ካፒታል ተጀምረው ትልቅ ተስፋ ያላቸውን 30 ዘመናዊ የቢዝነስ አማራጮች ለሚሊነሮች "1.ዘመናዊ የእንስሳት መኖ ማቀነባበሪያ 🔸ቦታ፦ የእንስሳት እርባታ ባለባቸው የከተማ ዳርቻዎች። 🔹ሰው መሳቢያ፦ "በ3 ወር የላምዎን ወተት በእጥፍ ይጨምሩ የሚል ቪዲዮ::2.ዘመናዊ የሸክላና የሴራሚክ ውጤቶች ማምረቻ 🔸ቦታ፦ የሸክላ አፈር በብዛት በሚገኝባቸው ገጠራማ ከተሞች። 🔹ሰው መሳቢያ፦ "ባህልና ዘመናዊነት በአንድ ላይ" በሚል ውብ የጌጥ እቃዎችን ማስተዋወቅ።3.የታሸገ የተፈጨ በርበሬና ቅመማ ቅመም ፋብሪካ 🔸ቦታ፦ ለጥሬ እቃ ምንጭ ቅርብ በሆነ የኢንዱስትሪ ዞን። 🔹ሰው መሳቢያ፦ "ከቆሻሻና ከቀለም ነፃ" በሚል ንፅህናውን በላብራቶሪ ምርመራ ማሳየት።4.የተጣራ የሱፍና የኑግ ዘይት ማምረቻ 🔸ቦታ፦ የሰሊጥና የኑግ ምርት ባለባቸው አካባቢዎች። 🔹ሰው መሳቢያ፦ "ለጤናዎ ቅድሚያ—ሳይቀላቀል የመጣ ዘይት" በሚል የምርት ሂደቱን ማሳየት።5.ዘመናዊ የዶሮ መፈልፈያ (Hatchery) 🔸ቦታ፦ መለስተኛ የአየር ንብረት ባለባቸው ቦታዎች።
    8,93011115311Open in Telegram
  • ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

    16 Sept, 09:08

    ⚠️ በኢስላም የሴት ልጅ ክብርና መብቶች[ኢስላም ሴትን ልጅ እንዴት አከበራት?]⁉️ብዙዎች "ስልጣኔ" ብለው በሚጠሩት ዓለም ውስጥ ሴት ልጅ እንደ ሸቀጥ ስትታይ፤ ኢስላም ግን ከ1,400 ዓመታት በፊት የሚከተሉትን መለኮታዊ መብቶች ሰጥቷታል፦1️⃣ ከታማኝነት አኳያ፦ አንድ ያገባ ወንድ ሚስቱን አታልሎ ዝሙት ቢፈጽም ቅጣቱ እስከ ሞት ድረስ ተቀጥቅጦ መገደል ነው። 2️⃣ ከፍትህ አኳያ፦ ከአንድ በላይ አግብቶ በመካከላቸው ፍትሃዊ ካልሆነ፤ በትንሣኤ ቀን አንድ ጎኑ ሽባ ሆኖ ይቀሰቅሳል። 3️⃣ ከመህር አኳያ፦ መህሯን (የጋብቻ ስጦታዋን) ወስኖ ካልሰጣት፤ አላህ ዘንድ እንደ "ሌባ" ይቆጠራል። 4️⃣ ከፍቺ በኋላ፦ ቢፈታት እንኳ የሰጣትን ስጦታዎች መልሶ የመውሰድ መብት የለውም። 5️⃣ ከውርስ አኳያ፦ የውርስ መብቷን የበላ የአላህን ድንበር ተላልፏል፤ ራሱንም በድሏል። 6️⃣ ከስነ-ምግባር አኳያ፦ ሚስቱን የሚያዋርድና የሚመታ እርሱ "ክፉ/ወራዳም" ነው፤ የሚያከብራት ደግሞ "ክቡር" የተከበረ ነው። 7️⃣ ከመብት አኳያ፦ ያላንዳች ምክንያት ከአራት ወር በላይ ትቷት ከራቀ፤ የመለያየት (የመፈታት) መብት አላት። 8️⃣ ከክብር አኳያ፦ እንደ እናቱ በመቁጠር (ዚሃር)አድርጎ ቢርቃት፤ ለቅጣቱ 60 ቀን መጾም ወይም 60 ምስኪን መመገብ አለበት። 9️⃣ በትዕግስት አኳያ፦ ቢጠላት እንኳ ይታገሳት፤ አላህ እርሷ ዘንድ ብዙ መልካም ነገርን ሊያደርግ ይችላልና ተብሏል። 🔟 ከመለያየት በኋላ፦ ቢፈታት እንኳ የነበራትን ውለታና መልካም ነገር መዘንጋት የለበትም። 11 ከልጆች አኳያ፦ ቢለያዩ እንኳ ልጆቿን ሊነጥቃት አይገባም፤
    8,9907551753Open in Telegram
  • ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

    14 Sept, 09:49

    🔆 #ካህሊል_ጂብራን 🔆🔱 ‹‹ ቁንጅና ያለው ፊት ላይ አይደለም፡፡ ቁንጅና በውስጣችን የሚገኝ የልብ ብርሃን ነው፡፡ ››🔱 ‹‹ አዋቂ ሠው ሁለት ልብ አለው፡፡ አንዱ ሲደማበት በሁለተኛው ይታገሳል፡፡››🔱 ‹‹ እምነት እውነትነቱን ከማረጋገጥ ባሻገር በልብ ውስጥ የሚገኝ እውቀት ነው፡፡ ››🔱 ‹‹ ኢምንቷ የደግነት ስራ ትልቁን ነገር ለማድረግ ከማሰብ በላይ ዋጋ አላት፡፡ ››🔱 ‹‹ ፍቅር የሚያንቀጠቅጥ ደስታ ነው፡፡ ››🔱 ‹‹ እውነት እርቃኑን በባዶው መራመድ ይችላል፡፡ ውሸት ግን ሁልጊዜ አምሮና ደምቆ መልበስን ይፈልጋል፡፡ ››🔱 ‹‹ ኩሩ መሆን ማለት ከምትፈልገው በታች መውሰድ ማለት ነው፡፡ ››🔱 ‹‹ ፍቅር የመለያያ ሠዓቱ እስኪደርስ ድረስ የራሱን ጥልቀት አይረዳም፡፡ ››🔱 ‹‹ ወንድ ሁለት ሴቶችን ይወዳል፡፡ አንደኛዋ በአዕምሮው የሚስላት ስትሆን ሁለተኛዋ ግን ገና አልተወለደችም፡፡ ››
    9,820115182221Open in Telegram
  • ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

    13 Sept, 12:44

    🪴ኢስቲቃማን እንዴት እናምጣ?በእስልምና ኢስቲቃማ (الاستقامة) ማለት በአላህ ትእዛዝ ላይ ጸንቶ መቆም፣ ከኃጢአት መራቅና በመልካም ሥራ ላይ መቀጠል ነው። በነገራችን ላይ ኢስቲቃማ ማምጣት በተለይ በችግር ጊዜ ትልቅ መፍትሔ ነው።💎ነገር ግን ኢስቲቃማ ማለት ችግር ፈጽሞ አይመጣም ማለት አይደለም፤ ችግር ሲመጣ በአላህ ላይ ተማምኖ፣ በትዕግሥትና በትክክለኛ መንገድ መቆም ነው።ኢስቲቃማን እንዴት እናምጣ?1. እምነትን ማስተካከል – ተውሂድን ማጠናከርና ልብን ከአላህ ጋር ማያያዝ። 2. ግዴታዎችን መጠበቅ – በተለይ አምስቱን ሶላቶች በጊዜያቸው መስገድ። 3. ኃጢአትን መተው – ትንሽ ነው ብሎ ኃጢአትን አለመናቅ።4. በቁርአንና በሱና ላይ መጠንከር።5. ዱዓን ማብዛት። ነቢዩ ﷺ በብዛት ይሉ ነበር፦ «يا مقلب القلوب ثبت قلبي على دينك» “የልቦች ቀያሪ ሆይ! ልቤን በዲንህ ላይ አጽናው።” 6. መልካም ጓደኞችን መምረጥ – ሰው በሚያደርገው አካባቢና ጓደኛ በጣም ይጎዳል ወይም ይጠቀማል።7. ትንሽ ትንሽ ቢሆንም በመልካም ሥራ መቀጠል። ዋናው ነገር ብዙ ጀምሮ ቶሎ መተው ሳይሆን በቀጣይነት መሥራት ነው።
    10,6009415722Open in Telegram
  • ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

    11 Sept, 07:06

    የተባረከ ጁምዓ ይሁንልን!@yasin_nuru @yasin_nuru
    Image from a post by ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURUImage from a post by ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU
    13,4001501791Open in Telegram
  • ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

    10 Sept, 07:27

    «አንዳንድ ዑለማዎች እንዲህ ብለዋል፦ አንድ ሰው ኻቲማው(የሂወቱ መጨረሻ) እንዲበላሽ ከሚያደርጉ ታላላቅ ምክንያቶች አራት ናቸው፦1.ለሰላት ግድየለሽነት ማሳየት።2.የሚያሰክር መጠጥ (ኸምር) መጠጣት።3.ወላጆችን መበደልና አለመታዘዝ።4.ሙስሊሞችን አዛ ማድረግ።»— አስ-ሱዩጢ رحمه الله@yasin_nuru @yasin_nuru
    14,800128291683Open in Telegram
  • ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

    9 Sept, 07:31

    الفوائد العشر لصلاة الفجر🔟 የሱብሒ ሰላት ጥቅሞች1. ቀኑን በሙሉ በአላህ ጥበቃ ስር ይውላልقال رسول الله ﷺ "من صلى الفجر فى جماعة فهو فى ذمه الله فلا تخسروا ذمه الله و من خسر ذمه الله طرده فكبه فى النار"“ሱብሒን ሰላት በጀምዓ የሰገደ ሰው በአሏህ ጥበቃ ስር ይውላል …….”2. አጅሩ(ምንዳው) ለሊቱን እንደቆመ ይቆጠርለታልقال ﷺ "من صلى العشاء فى جماعة فكأنما قام نصف الليل و من صلى الفجر فى جماعة كأنما قام الليل كلة"“የኢሻን ሰላት በጀመአ የሰገደ ግማሹን ለሊት እንደቆመ ሲሆን ሱብሂን በጀመአ የሰገደ ሙሉውን ለሊት እንደቆመ ይቆጠራል።”3. ከሙናፊቅነት ነጃ ይባላልقال ﷺ "ليس أثقل على المنافقين من صلاة العشاء والفجر ولو يعلمون ما فيهما لأتوهما ولوحبواً ليس صلاة أثقل على المنافقين من الفجر والعشاء ، ولو يعلمون ما فيهما لأتوهما ولو حبوا ، لقد هممت أن آمر المؤذن فيقيم ، ثم آمر رجلا يؤم الناس ، ثم آخذ شعلا من نار فأحرّق على من لا يخرج إلى الصلاة بعد" رواه البخاري
    16,10012820642Open in Telegram
  • ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

    7 Sept, 07:20

    ለዚህ ቪዲዮ እኔም ህያው ምስክር ነኝ! ሀቂቃ… ትዳር የሪዝቅና የበረካ በራፍ ነው።ሰራተኞች አሉኝ፤ ያገቡትም፣ ያላገቡትም፣ ልጆች ያላቸውም አሉ። የሁሉንም ወርሃዊ ደመወዝ እኔው ነኝ የምከፍለው፤ ክፍያቸውም በጣም ተቀራራቢ ነው። ነገር ግን እውነተኛው ልዩነት የሚታየው ደመወዝ ከተከፈለ በኋላ ባለው ህይወት ነው!ያገቡት ሰራተኞቼ ያቺኑ የምከፍላቸውን ደመወዝ አብቃቅተው፣ ቤታቸውን መርተው፣ የልጆቻቸውን ፍላጎት አሟልተው በሰላም ሲኖሩበት፤ ላጤዎቹ ሰራተኞቼ ግን ገና ወሩ አጋማሽ ሳይደርስ «እባክህ የቀጣይ ወር ደመወዝ ቅድሚያ ስጠኝ» እያሉ ማንኳኳት ይጀምራሉ!--ሀሀ--እናላችሁ… በትዳር ውስጥ ያለው ሚስጥር የገንዘቡ ብዛት ሳይሆን የበረካው ስፋት ነው ወላሂ! ትዳር ትንሹን አብዝቶ፣ ጎደሎውን ሞልቶ ያሳያል። ስለዚህ ያላገባችሁ… ከመበደር ወደ ማብቃቃት፣ ከላጤነት ወደ በረካው ጎጆ ተሻገሩ ለማለት ነው! 😉#AbuSufiyan@yasin_nuru @yasin_nuru
    14,300video10472231266Open in Telegram
  • ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

    5 Sept, 04:07

    ኢና ሊላሂ ወዒና ኢለይሂ ራጂዑንየወንድሜ ኡስታዝ አህመዲን ጀበል ወላጅ እናት ወደ አኼራ ሄደዋል::የእናታችን ስርዓተ ቀብርም ነገ ቅዳሜ ከዝሁር ሰላት ቡኃላ ሰናተል ጀናዛ ተሰግዶባቸው በኮልፌ የሙስሊሞች መካነ መቃብር የሚፈፀም ይሆናልአላህ ይዘንላቸው፣ ማረፊያቸውንም በጀነተል ፊርዶስ ያድርግላቸውለኡስታዝ አህመዲን ጀበል እና ለመላው ቤተሰቦቹ አላህ ሰብሩን ይወፍቃቸው@yasin_nuru @yasin_nuru
    15,60025711149775Open in Telegram
  • ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

    4 Sept, 06:07

    የተባረከ ጁምዓ ይሁንልን!@yasin_nuru @yasin_nuru
    Image from a post by ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURUImage from a post by ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU
    16,600130181622Open in Telegram
  • ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

    2 Sept, 09:45

    #ሱብሃን_አላህ #በግብፅ እጅግ ያልተለመደ የሕክምና ክስተት! 😢💔አንዲት ግብፃዊት ሴት የመውለጃ ቀኗ ከመድረሱ 10 ቀናት ቀደም ብሎ በልብ ችግር ምክንያት ትሞለች። ነገር ግን አስደንጋጩ ነገር መንታ ልጆቿ በማህፀኗ ውስጥ በሕይወት ነበሩ።በሚገርም ሁኔታ እናታቸው ከሞተች ከ15 ደቂቃ በሗላ ዶክተሮች ባደረጉት አስቸኳይ የቀዶ ጥገና (C.S) መንታ ህፃናት ከማህፀን ውስጥ በሕይወት መውጣት ችለዋል። ❤️ #አጂብ ህያውን ከሙት የሚያወጣ ጌታ ጥራት ይገባው‼﴿يُخْرِجُ الْحَيَّ مِنَ الْمَيِّتِ﴾ “ሕያውን ከሙት ያወጣል።” ቁ 6:95@yasin_nuru @yasin_nuru
    Image from a post by ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURUImage from a post by ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU
    18,600359542220127Open in Telegram
  • ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

    1 Sept, 07:22

    የባል እና ሚስት የሀላል ፍቅር ጨዋታ በግጥም🌹ባል :― አንቺ የኔ ፍቅር የህይወት ጨረቃ ልቤ ይከፋዋል ሳጣሽ ለደቂቃ ሴቶች ብዙ ናቸው አንቺ ግን ልዩ ነሽ ህይወቴን አድሻት ካጠገቤ ሁነሽ🌹ሚስት― አንተ የኔ ፍቅር የህይወት ነፀብራቅ ፍቅርክ ምግቤ ነው ከጎኔ አትራቅ ወንዶች ብዙ ናቸው አንተ ግን ልዩ ነክ ፍቅርክን መግበኝ ካጠገቤ ሁነክ።🌹ባል:― የትዳር አጋሬ የልጆቼ እናት ደስታዬ አለሜ የሀላል ሚስቴ ነች ጌታየ ይመስገን እሷን አድሎኛል ውዴን የመሰለ ከቶ የት ይገኛል።🌹ሚስት:― የልጆቼ አባት የትዳሬ አጋር ተስፋዬ ብሩህ እስካለሁ ካንተ ጋር መኖርክ መኖሬ መጥፋትክ መጥፋቴ ሳጣክ ቅር ይለኛል አትጥፋ ከፊቴ🌹ባል:― የሽቶ መኣዛ የቴምር ጭማቂ ሁቢ ማር ወለላ ሁሌም ተናፋቂ ጣፈጭ ነገር ሁሉ አንቺን ይመስሉኛል ብቻ ምን ልበልሽ… ቃላቶች ያጥሩኛል!🌹ሚስት:― የዐይኔ ማረፊያ የህይወቴ ፀደይ የፊትክ ብርሃን ይበልጣል ከፀሐይ የረህማን ፅጦታ የጀሊሉ ኒዕማ አንጀቴ ይርሳል ድምፅክን ስሰማ🌹ባል:― ሚስቱን የሚመታ የትዳር አጋሩን የፍቅር አይደለም ሳስበው ነገሩን ውዷ ባለቤቴ ክብርሽ ይከበር አንቺን የመታው ቀን እጄ ይሰበር🌹ሚስት:― እኔ እንክትክት ልበል እኔ ልሰባበር እሾክ አይውጋብኝ እንኳንስ መሰበር የፍቅር አርበኛ ፊትአውራሪ ጀግና አንተ መውድድ እንጂ ዱላ መች ታውቅና🌹ባል: እኔ እዚህ ጎራ አንቺ ወዲያ ማዶ ልቤ አረረልሽ በፍቅርሽ ማገዶ የልቤ በረዶ መዳኒቴ ነሽ ውዷ ባለቤቴ ሁቢ እንዴት ነሽ
    17,4001792817974Open in Telegram
  • ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

    29 Aug, 11:42

    የነቢዩ ﷺ ፍቅር 💔🥺አንድ ወጣት በመስጂደ ነበዊ አጠገብ በፖሊሶች ተያዘ። ምንም ሳይናገሩ እጆቹን ወደ ኋላ በካቴና አሰሩትወጣቱ እያለቀሰ፦ «ምን አድርጌ ነው? ሌባ አይደለሁም፣ ወንጀለኛም አይደለሁም… ለምን ትወስዱኛላችሁ?» አለ።አንድ አዛውንትም ሁኔታውን በርቀት ይከታተሉ ነበርና ወደ ፓሊሶቹ ጠጋ በማለት ፦«ይህን ወጣት አውቀዋለሁ። ሁልጊዜ በነቢዩ ﷺ ረውዳ ፊት ቆሞ ሰለዋት ሲያወርድ፣ እያለቀሰ ዱአ ሲያደርግ አየዋለሁ። ምን አድርጎ ነው የያዛችሁት?» ሲሉ ጠየቁ።ፖሊሶቹም ፦ «ሌባ አይደለም። ከአልባኒያ የመጣ ሰው ነው። ለ6 ዓመታት ሕጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ ሳይኖረው መዲና ውስጥ ኖሯል። ወደ አገሩ ለመመለስ ብዙ ጊዜ ሞክረናል፤ ግን ሁልጊዜ አምልጦ እንደገና በመስጂደ ነበዊ እናገኘዋለን» አሉ።ወጣቱም እንባውን እያፈሰሰ፦ «አልሰርቅም፣ አልዘርፍም፣ ማንንም አልጎዳም። እዚህ የመጣሁት የአላህን መልእክተኛ ﷺ ስለምወድ ብቻ ነው። ከዚህ ከተማ መለየት አልፈልግም» አለ።ከዚያም ከመስጂደ ነበዊ እያስወጡት ሳለ፣ ወደ አረንጓዴው ጉልላት (ቁበተል ኽድራ) እየተመለከተ ልብ ሰባሪ ንግግር ተናገረ፦«ያ ረሱለላህ ﷺ! በመካከላችን የነበረው ቃል እንዲህ ነበርን?!
    17,9001721282615124Open in Telegram
  • ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU

    28 Aug, 05:24

    እናቴም፣ አባቴም ነፍሴም ቤዛ ይሁንልዎ አንቱ የአላህ መልዕክተኛ اللَّهُمَّ صل عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ የተባረከ ጁምዓ ይሁንልን!@yasin_nuru @yasin_nuru
    Image from a post by ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURUImage from a post by ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU
    16,500175241751Open in Telegram