Latest posts

የገጣሚያን ማኅበር
23 Sept, 06:36
የ ኤርትራ ዋና ከተማ ማነች?
የገጣሚያን ማኅበር
23 Sept, 06:11
🎭መንፈሳዊ ትረካ-🎬🎨🎬ርዕስ- የጠዋት ፀሀይጸሀፊና ተራኪ ፦ ቦኤዝ ታምሬ @yegetamianmahiber @yegetamianmahiber
የገጣሚያን ማኅበር
23 Sept, 06:06
#መኖርና-ኑሮኮልታፋ ሆኜ ስረግጥ ኮሬብን ቃላቴ ሲያምር አልሻም ግብፅን ባገኝም እንኳን የኔን ሳሙኤል ሴሎን አልፌ ቤቴን አልረግጥም የልቤ ሚዛን ሁለት አይዝም አንዱን ካንተ ጋር አይመዛ'ዝንም ማር አፍልቆ ወተት ቢያዘንብም ከነዓን ለኔ መኖሪያ አደለምመፈለጌ የእዉነት ቢሆን በጌን ትቼ ባግድ ሰዉን ታላቅ ብሆን በተራራ ክብር ባገኝ ክብር ተራ እሺ ብለዉ ቢታዘዙኝ ደሞ አልፈዉም ቢቃወሙኝ ከመራሁት አርባ አመታት ሲጨመቁ አርባ ቀናት ያደርኩበት ባይኖችህ ፊት ኖርከዉ ካሉኝ መቶ አመታት እኔ ያመንኩት ያቺን ቀናትኦሪት ዘጸአት 24፤18 24፤18 ሙሴም ወደ ደመናው ውስጥ ገባ ወደ ተራራውም ወጣ፤ ሙሴም በተራራው ላይ አርባ ቀን አርባ ሌሊትም ቆየ።✍️እንደዚህ አይነት special timeዎች ከትክክለኛ መኖር ዉስጥ ይመደባሉ። @yegetamianmahiber @yegetamianmahiber


የገጣሚያን ማኅበር
22 Sept, 20:03
የ ኤርትራ ዋና ከተማ ማነች?
የገጣሚያን ማኅበር
22 Sept, 07:53
ማንበብ ትወዳላችሁ?
የገጣሚያን ማኅበር
22 Sept, 07:48edited
..❌አናምርም❌..እኩል መውደቃችን እኩል አሳበረን ጨዋታችን ደራ ሀፈረትን እረሳን ልክ ሆንን በውድቀት አቦካን ሀጢያትን ድፍረታችን በዛ እኛስ ወየውልን አውቀን ጨርሰናል ምኑንም ሳናውቀው የተግባባንበት እውቀት የውሸት ነው የተቃቀፍንበት ወደን የወደድነው እግዜር የጠላውን ጠላቱን እኮነው ምነው... ምነው አነስንበት አተልቆን ኖሮ ምነው ቀለልንበት ወርደን እንደ ድሮ ንስሀ እንደመግባት እንደመወቃቀስ ቡፌ ስንደረድር ለሀጢያታችን ድግስ ልባችንን ሰብረን በእንባ እንደመጥለቅለቅ ከየት አመጣነው ይህን ሳቅ መፍለቅለቅኧረ ለምን ሳቅን ስለምን ተመቸን
የገጣሚያን ማኅበር
22 Sept, 06:41
🎭መንፈሳዊ ትረካ-🎬🎨🎬ርዕስ- የነፍስ መሸሸጊያጸሀፊና ተራኪ ፦ ቦኤዝ ታምሬ @yegetamianmahiber @yegetamianmahiber
የገጣሚያን ማኅበር
22 Sept, 06:37
አያልቅብህ ትህትናህትሻው ነፍሴን ... እንዴት ልግለጥ፤ ከምቀዳው .... እንዴት ልብለጥ። ከምኔ ላይ ምኔን ጥዬ ላቅርብልህ ውሃ ብዬ። የለመንከኝ ፍጥረትህን .. የለመንከኝ የጋን ውሃ፤ ማቅረቢያዬ አዳፋ ልብ .. ያልታጠበ በንስሐ። ታውቀው የለ..ታሪክ ግብሬን ያልኖርኩትን ቡሩክ ኑሮ .. በአደባባይ መናገሬን። ታውቀኝ የለ እድፍ እንዳልኩ .. ምን እንዳጣሁ ምን እንዳለኝ፤ በኃጢአት ነትባ ያለች ነፍሴን .. የምሰጥህ እኔ ማን ነኝ። አንካሳ ነኝ ልበ ስንኩል.. ዛሬ ነገ የምቃጠር .. ለማፍቀርህ መልስ የማጣ፤


የገጣሚያን ማኅበር
21 Sept, 08:05
🎭መንፈሳዊ ትረካ-🎬🎨🎬ርዕስ-የአዲስ ኪዳን ባልንጀራጸሀፊና ተራኪ ፦ ቦኤዝ ታምሬ @yegetamianmahiber @yegetamianmahiber
የገጣሚያን ማኅበር
21 Sept, 08:05
ርዕስ: ምን ልከፍል ችላለሁ?ገጣሚ:- መክሊትአዳኝ እፈልጋለሁ ለሞት በተሰጠ ሰዉነት ተይዣለሁ ሀጢያትም ገዛኝ ባሪያዉ ሆኛለሁ መቆሚያ አርጎት ሰይጣን በኔ ላይ ህጉን ሰምቼ እንዳላረግ ከልካይ ተጥሎ ሳለ ከምድር በታች እኔን ሊወስደኝ ሊገለኝ ሲያመቻች ኩነኔም የለ የሞት ፍርሀት አዳኝ ተገኝቶ ለኔ የሚሞት ሀጢያቴን ወስዶ ፅድቅ አለበሰኝ ሞቱ ትንሳኤዉ ህያዉ አረገኝ ለመፅደቅ ሚሆን ባጣ ክፍያ ለክብሩ ሚሆን ፅድቁን ማሳያ ነፍሴ ተጣልቶ ከስጋዬ ጋር መንፈሴም ሆኖ የህግ አገልጋይ አዳኝ ተገኘ ከላይ ከሰማይ


የገጣሚያን ማኅበር
21 Sept, 07:36
❓❓❓❓❓❓❓❓❓❓❓❓❓❓ . 📖 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄ 📖🙋♂እግዚአብሔር ወደ ሸክላ ሰሪው የላከው ነብይ ማን ነው❓📌ትክክለኛ መልስ ምረጡ ቀጥሎም የሚመጣላቹ መንፈሳዊ ቻናል ተቀላቀሉ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇
የገጣሚያን ማኅበር
19 Sept, 19:06
ርዕስ:_ የዘመን ባለቤትለኔ በዝቶ ምህረት በዛ ሁሉ ቀናት ወራት ተደራርቦ አየዉ አዲስ አመት ሁሉን በአንተ አልፌ ከስንቱ ተርፌ ዛሬ ላይ መቆሜ ባንተ ተላልፌ. እጆች ከተያዙ መዉደቅስ የታለ. ማእበሉ እያለ ለካ መንገድ አለ በፈጣሪ ፍቃድ አምናን አሳለፍኩኝ እሱ ስላሰበዉ ዘንድሮን ደረስኩኝ ለንግግር እንኳን ቃላት ነዉ የሚያጥረዉ ዝም ብዬ ላመስግን እና ምን ልበለዉ ለኔ ስለሰጠ አዲስ ቀን አዲስ ወር ምንም አልልህም እ/ር ሆይ ክበር አንተዉ አቀናጅተ በሰጠኸኝ ዘመን አንተን ላመስግን ልቀኝ ነዉ ቅኔን ማን ችሎ ደረሰ በሀይል በብርታቱ ብዙዎች ሞተዋል የሚመስሉ ብርቱ እናማ እንዲ ነዉ ዘመን ከሰጠኸኝ አዚም እንዳይዘኝ በፀሎት አበርታኝ ለአንተ ብቻ ልኑር ለዘመን ባለቤት
የገጣሚያን ማኅበር
18 Sept, 19:07edited
እየሩሳሌምየዳዊት ከተማ ናት የተባለላት የሰለሞን አይነት ጥበብ የታየባት ከሰለሞን የሚበልጥ ከርሷ የወጣባት የነገሥታት ንጉስ ለሷ የመጣላት ያቺ ውብ ከተማ እየሩሳሌም ናትየሰላም ከተማ የሰላም መሰረት የቅዱሳን አባት ብርሃን የሆነላት የእረፍት ከተማ እየሩሳሌም ናትሊቀ ካህናችን በሰው አምሳል ሆኖ በበረት ተወልዶ 33 አመት ሰውነትን ለብሶ በሷ የኖረባት የዘለአለም አባት በርሷ የሚነግስባት የፍቅር ሁሉ ምንጭ የፍጥረታት ማማ ስምሽ ሁሉ መልካም የቅዱሳን ዜማ አለማት በሙሉ የተጠሩበት ቃል አንቺ እየሩሳሌም በአንቺ ይታያል
የገጣሚያን ማኅበር
17 Sept, 17:37
ልባም ሴት ንቁ በማለዳ እንቅልፍ የማይገዛት ታታሪ አስተዋይ ኗሪ በብልሃት ልባም ሴት አሳቢ አርቃ አላሚ ለክፋት የማትቆም ባለ ሙሉ መልካም ክንዷ የበረታ መታጠቂያዋ ሀይል ለስራ የፈጠነች ከሀሜት የራቀች እጇን የዘረጋች ለሌላቸው ድሆች ዝናብ አትፈራ በረዶ አይበግራት ለቤተሰብ ኗሪ ለልጆቿ እናት ለባሏ ውድ ሚስት የተመሰገነች የተነገረላት ልዩ እንደሆነች . ውበትም ሀሰት ነው ደም ግባት ከንቱ ነው ጌታን ምትፈራ ሴት ምስጋና ጌጧ ነው ልባም ሴት ማን ከቶ ሊያገኛት ባሏ ይታመናል ምርኮም አይጎድልበት ዋጋዋ ውድ ነው ከቀይ እንቁ በላይ
የገጣሚያን ማኅበር
17 Sept, 05:49
ላመስግን 🙏🌼በቀናቶቼ ላይ ቀን እየጨመረ በወራቶቼም ላይ ወርን እያኖረ አመት ደግሞ ሲሻር ሲመጣ ሌላ አመት እግዜር ቸርነቱ እንዲገለጥበት ከስንቱ እንዳወጣኝ አሰላስልና በደስታ በፊቱ ስቆም ለምስጋና ያለፍኩትን ሁሉ አስቤ ሳበቃ ዘውትር ይደንቀኛል የአምላኬ ጥበቃ✍ #አቤንኤዘር_ጥላሁን ጳጉሜን - 2017 አ.ም የተጻፈ@Ye_Getamian_Mahiber
የገጣሚያን ማኅበር
16 Sept, 05:30edited
አይለወጥም ዘመን ይቀየራል አመታት ያልፋሉ ውበትም ይረግፋል ቀናት ይጠፋሉ የምንወዳቸው ትተው ይሄዳሉ ቃልኪዳኖች ሁሉ ወድያው ይፈርሳሉ ፍቅርህ ወረት የለው ሁሌ ትወዳለህ ፍቅር ነህ ዘለአለም ደግሞም ታማኝ ነህ!! የሰው ፊት ሲጠቁር ፊትህ አይለወጥም የሰው ክንድ ሲዝል አንተ ግን አትዝልም ብንገፋህ እንኳን አንተ አትገፋንም አንተ አታረጅም ዘለአለም አትጥልም ፍቅር ነህ ዘለአለም አንተ አትለወጥም(2x)ገጣሚ ዲናኦል @yegetamianmahiber @yegetamianmahiber
የገጣሚያን ማኅበር
14 Sept, 19:50edited
ውዳሴከዘላለም የምትኖር ፣ ዘላለማዊ ክብር እና ውዳሴ ለስምህ ይሁን! የፍጥረት ሁሉ ፈጣሪ እና ባለቤት፤ ክብር እና ውዳሴ ለስምህ ይሁን ! ፧ ሁሉም በእጅ የሆነ ፤ የሁሉም ነገር ምንጭ የነገስታት ሁሉ ንጉስ የጌቶች ሁሉ ጌታ የሆንክ ግን ማንንም የማትንቅ ፣ ሁሉንም በእኩል የምትወድ። "ለክፉዎችም ለደጎችም ፀሐይህን የምታወጣ ፤ ለኃጥሁም ለፃዲቁም ዝናብህን የምታዘንብ" በሰማያትህ ላይ ከፍ ከፍ በል ! ክብርህ በምድር ሁሉ ይሁን ! ክብር እና ውዳሴ ለስምህ ይሁን ! ፧ እኛ የምንኖርለት ነገር ሁሉ ጠፊ ነበር ፤
የገጣሚያን ማኅበር
11 Sept, 14:22
በቃ አንዳቹም የበዓል ስጦታ አትሰጡኝም😔😐
የገጣሚያን ማኅበር
11 Sept, 05:47
እኔን ያዩ አይኖችህ ይባረኩ😍 አላንቀላፉም እኔን ስጠብቁ😍
የገጣሚያን ማኅበር
10 Sept, 21:10edited
ለመላው የቻናላችን ቤተሰቦች እንኳን ለ2019 ዓ.ም አዲስ አመት በሰላም አደረሳችሁ።አዲሱ አመት 🌻 የሰላም፣ የፍቅር፣ የስኬትና የመተሳሰብ ያድርግልን። 🌻 ሁላችንም የምንናፍቀውን የሀገራችንን ሰላም ይመልስልን።🌼🌼 መልካም አዲስ አመት 🌼🌼@yegetamianmahiber @yegetamianmahiber

Related Channels
Other channels in the same section of the catalogue.
