gram news
Zemedkun Bekele (ዘመዴ) channel avatar

Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

@zemedkunbekelez

"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ 👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና 👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

ProjectsENBlogs

201,610subscribers

Open the Channel

Latest posts

  • Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

    13 Nov, 18:41

    • ቋራ ~ ዳግማዊ ወለጋ• ጎንደር ~ መዝገበህ ያዝልኝማ… ይሄ ሟርት አይደለም ዝግጅቱን ነው የምነግርህ።"…ከላይ ከወልቃይት ጀምረህ በቋራ በኩሉ አድርገህ ቤኒሻንጉልን አልፈህ እስከ ጋምቤላ ድረስ ሀገር በቀል ዜጎች እንዲኖሩ አይፈቀድም።• ሸጋ ጌታቸው ሰፋሪ ያላችሁ ጎንደሬዎች ሁለት ምርጫ አላችሁ። አንደኛው መፈናቀል፣ መሰደድ፣ መንከራተት። ሌላኛው ደግሞ ከእነነአርበኛ ባዬ ቀናው፣ ከእነ ሳሚ ባለድል ጋር አንድነት ፈጥረህ መታገል። ይኸው ነው።• እያብላችሁት ጠብቁኝ። በሰፊው እመለስበታለሁ።
    11,6003111255312116Open in Telegram
  • Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

    13 Nov, 12:36edited

    • ነፍስ ይማር ተወዳጅ አባታችን 😭😭😭"…መርካቶ አውቶቡስ ተራ ሳይደርሱ በስተ ግራ ማርስ ሙዚቃ ቤት ብለው ሥራ ጀምረው ኋላ አርያም መንፈሳዊ መዝሙር ቤት ወደሚል ስያሜውን ቀይረው፣ መዝሙር ማሳተም ጀምረው ዛሬ በእያንዳዳችሁ ቤት የሚገኙ የብዙ ታላለቅ ዘማርያንን መዝሙሮች እና ሰንበት ትምሕርት ቤት መዝሙሮችን ለቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በግለሰብ ደረጃ አበርክቶ የፈጸሙ ታላቅ አባት ታላቅ ወንድማችን፣ በወቅቱም ለሁላችንም ሰብሳቢያችን ነበሩ ጋሽ ጉልላት ብሥራት። ዛሬ ማረፋቸውን እንደዋዛ ሰማሁ።"…እነ ኪነጥበብን፣ እነ ዘማሪ ይልማ ኃይሉ፣ ፋንቱ ወልዴ፣ ተስፋዬ ኢዶ፣ ታዲዮስ ግርማ ምንዳዬ ብርሃኑ እና ሌሎችንም ታላላቅ ዘማርያንን ከሕዝብ እንዲተዋወቁ ምክንያት የነበሩት ታላቅ ወንድማችን፣ መካሪ ሰብሳቢያችን አቶ ጉልላት ብሥራት እኛ ጋሼ የምንላቸው ባለ ማዕተብ ደግ፣ የዋህ ልበቀና ወንድማችን ከዚህ ዓለም ድካም፣ እጅግ ውጣ ውረድ ከበዛበት ከሚያለፈው ዓለም ወደማያለፈው ዘላለማዊ ወደሆነው ዓለም ተሸጋገሩ አሉኝ።"…ልጆቻቸው አዳሙ ጉልላት፣ ኤርሚያስ ጉልላትም አባታቸውን በመርዳት፣ ዘማርያንን በመመልመል፣ በመለየት፣ በማብቃት ከኅትመት እስከ ስርጭት በሽያጭም ሱቅ በመጠበቅ ያለውን ሂደት በሙሉ አባታቸውን በመርዳት፣ ከጎናቸው ቆመው በማገዝ፣ ኋላም በማሳረፍ በብዙ ያገለገሉአቸው ልጆቻቸው ናቸው። እኔና ቀሲስ እንግዳወርቅ በቀለ ጌልገላ መንፈሳዊ መዝሙር ቤትን በጋራ ስንከፍት የመጀመሪያ ሥራ ማስጀመሪያ ካሴት የነበረው 42 የቅጂ ካሴት በየጊዜው ወደ መዝሙር ቤታቸው ጎራ ባልኩ ቁጥር የሚሰጡኝን የተለያዩ መዝሙራት እና የእንግዳወርቅን ቁር ሁለት መዝሙር፣ ሰላምለኪ ለኖኅ ሐመሩ በሚለው የመዝሙር ካሴት ነበር ሥራ የጀመርነው።"…አቶ ጉልላት ከመንፈሳዊ ሕይወታቸው ባሻገር በስፖርቱ ዓለምም ቀጥተኛ ተሳታፊም ቁጥር 1 ታማኝ የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ ደጋፊም ነበሩ። እሳቸው፣ የመቅደላ መዝሙር ቤት ባለቤት አቶ ታዬ፣ እነ እሸቴ ዕፁብድንቅ የቅዱስ ጊዮርጊስ የእግር ኳስ ክለብ ቀንደኛ ደጋፊ ሲሆኑ እኔ ደግሞ ቀንደኛ ባልባልም በስም ግን ለበዓሉ ድምቀት ሲባል እንዲሁ ጭር ከሚል ያልተመዘገበ፣ ፋይል ላይ የሌለ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከኢትዮጵያ ቡና አልያም ኢትዮጵያ ቡና ከውጭ ክለብ ጋር በተለይም ከግብፅ ክለብ ጋር ግጥሚያ ሲኖረው ከጨዋታው ይልቅ የደጋፊውን ህብረ ዝማሬ፣ ለማየት የኢትዮጵያ ቡና የእግር ካስ ክለብ ደጋፊ ነኝ በማለት የኳሱ ነገር ባይገባኝም ባገኘኋቸው ቁጥር ግን እንደ ዐዋቂ ትንኮሳ በመፍጠር እነ ጋሼ የመጨረሻ ኃይላቸውን ተጠቅመው፣ የግምባራቸው ደምስር እየተገታተረ፣ ላባቸው ጨፍ እያለ፣ ክለባቸው እንዴት ኃያል እንደሆነ እኔን በማስረዳት የሚያወጡት ድምጽና ጉልበት ልክ አሁን እንደሆነ ነው ትዝ የሚለኝ። (ዘመዴ የቅዱስ ጊዮርጊስን ፊልም ሽጠህ እየበላህ የቡና ደጋፊ ነኝ ስትል ምንም አይሰማህም? እያሉም ጫን ስልባቸው ከሰማእቱ ጋር ሊያቀሳስሩኝም ይዳዳቸው ነበር።"…አቶ ጉልላት ብሥራት በተወለዱ በ76 ዓመታቸው ሕዳር 3/2019 ዓም አርፈው በዛሬው ዕለት ወዳጅ ዘመዶቻቸው በተገኙበት በወይብላ ማርያም ሥርዓተ ቀብራቸው መፈጸሙን ሰማሁ። በአካል ተገኝቼ መቅበር ባለመቻሌ እንደዛሬ ተሰምቶኝ አያውቅም።በሉ እናንተ ሂዱ የእኛም ወደዚያው ነው ድሮም መንገደኛ ፊትና ኋላ ነው።• የተክለ ጊዮርጊስን ነፍስ ይማር።
    25,700558277197431911Open in Telegram
  • Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

    13 Nov, 08:07

    • አርብ ሕዳር 4/2019 ዓመተ ምሕረት• እንደምን አደራችሁ?
    28,100594173881275Open in Telegram
  • Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

    12 Nov, 16:14

    • ሕዝቡ እና እነርሱ…"…የጎንደር ገበሬ ከላይ ዝናብ ፈጣሪ ከልክሎት፣ ከታች ምድር እህል አላበቅልለት ብላው፣ ከብቶቹ የሚግጡት ሳር፣ የሚጠጡት ውኃ አጥተው፣ ሰዉም፣ እንስሳውም በራብ ደቅቋል። በጠኔ ተመትቷል። ጫጭቷል፣ ከስቷል። ስደትም ጀምሯል።"…እዚያው ገጠር ነፃ እናወጣሃለን ብለው ነፍጥ አንግበው የሄዱት በስም ዐማራ፣ በትውልድ ጎንደሬ ነን የሚሉ ጎረምሶች ደግሞ ይኸው ተመልከቷቸው የሚመስሉትን። ድሮ ድሮ በእኔ ዘመን ያለ ሜካፕ፣ ያለ ቡቶክስ በተመጣጠነ ምግብ፣ በምቾት ብቻ የሚያምሩትን እነዚያ የቦሌ ልጆች፣ የዲታ የሀብታም ልጆች የምንላቸው ቆነጃጅት እንኳ በሜካፕ አብደው እንዲህ እንደነዚህ የፋኖ መሪዎች አይጸዱም። እነዚህ የጎንደር ነፃ አውጪዎች መሆናቸው ነው። እነዚህን አይቶ ወደፋኖ ትግል የሚገባ ካለ ከእነሱ በላይ ተርቦ ከርሱን ለመሙላት የሚወድ ብቻ ነው የሚሆነው። ምናቸውም ለትግል አይገፋፋም። እዚያ ከተማ በሥራ እጦት፣ በገቢዮች፣ በደንብ አስከባሪዎች ምን አጨናነቀው። በቀላሉ ያለው አዱኛን፣ ዮሐንስ ንጉሡን መሆን እየተቻለው ምን አደከመው። ከምር ቀን የወጣውማ ለእነዚህ ወጠጤዎች ነው።"…መኪና ዘርፈው፣ ሰው አግተው፣ መቀጮ ክፈል፣ ግብር አምጣ ብለው። የገበሬውን የራስ መጠበቂያ የግል መሳሪያ ገፍፈው እየሸጡ፣ በገንዘቡ እየበሉ፣ እየጠጡ፣ እየሰከሩ፣ እየዞመቱ፣ የትግል በረሃውን የኤልሳ የውበት ሳሎን፣ ሲቲ ላውንጅ፣ ኩሪፍቱ መዝናኛ አስመስለውት ይኖራሉ።"…አንድም ቦታ አይዋጉም። አንድም ቀበሌ አያስለቅቁም። ትግላቸው ጎንዮሽ ነው። እነ አሻራ ሚዲያ ላይ ሰበር ዜና ቱሪናፋቸውን ይተሮንፋሉ በቃ። ከመከላከያው ጋር በስምምነት ነው ያሉት። ፍየል፣ በግ ቀለባቸው ነው። ቢራ፣ ወይን ውስኪ መታጠቢያቸው ነው። አልባሳታቸው የአሜሪካ ኤርፎርስ ነው የሚያስመስላቸው። የእጅ ሰዓታቸው በሚልዮን ብር የሚገመት ነው። ትግሉ በቶሎ እንዲጠናቀቅ የማይፈልጉት እነዚህ ደናቁርት በተረጋጋ መንግሥት እና የመንግሥት ሥርዓት ውስጥ ሥፍራ እንደሌላቸው የሚያውቁ "ሀ" ገደሉዎች ስለሆኑ ነው።"…ከሃሎ እንዴት ነህ? ማሬ ደናነሽ? በቀር፣ ፌስቡክ፣ ዩቲዩብ፣ ቲክቶክና ቴሌግራም ከሚኮመክሙበት በቀር፣ ከፍ ካለ በሰከሩ ጊዜ መግለጫ የሚሉትን የድርኳዜ ማላገጫ ከሚቀርጹበት፣ ፎቶም የሚነሱበት ካልሆነ በቀር ሌላ ምንም ፋይዳ ለማይሠሩበት ገዝተው የሚይዙት ስልክ ግን አይፎን ምናምንትስዬ የሚባለውን ነው። የፀጉር ቁርጣቸው፣ የጺም ስታይላቸው። ሜካፑ ሁሉ የከተማ አርቲስቶች አይጠቀሙትም። ልጠቀምም ቢሉ እንደ ጃኒና ጆዬ አዶናይ ቲክቶከር ካልሆኑ በቀር አቅማቸው አይፈቅድም። በፋኖ መሪዎች አይን የሪልስቴት ባለቤት የሆነ አንድ ሰው እንደነሱ ተረጋግቶ ተመችቶት የሚኖር አይመስለኝም።"…በየትኛውም ዓለም በረሃ የሚገቡ የነፃነት ታጋዮች ምቾት አይታይባቸውም። ጎስቁለው፣ ቆሽሸው፣ ፂማቸውን፣ ፀጉራቸውን አጎፍረው ነው የሚታዩት። በየዋሻው እየተንከራተቱ፣ እየተደበቁ፣ እየተሸሸጉ ነው የሚታገሉት። እነዚህ አረቄያም ግን እንደምታዩአቸው ነው። የቀደሙ ታጋዮች በራብ፣ በተመጣጣኝ ምግብ እጦት፣ በእንቅልፍ እጦት፣ በክረምት ዝናቡ፣ በበጋ ፀሐዩ እየተፈራረቀባቸው ነው ታግለው፣ አታግለው፣ ሕዝባቸውን አደራጅተው መልሰው ሕዝባቸውን ነፃ የሚያወጡት። የእነዚህ ግን ይለያል። እረኞቹ ሰብተው፣ ወዝተው፣ ጠብድለው ነው የሚታዩት። በጎቹ ግን ጫጭተው፣ መንምነው ማለቃቸው ነው።"…እነዚህ ነውረኞች እንዲህ ዓይነት ስታይሊሽ የሆነ አክተር የሚያስመስላቸውን ፎቶ ሲለጥፉ፣ ሲያስለጥፉ ቅሽሽ አይላቸውም። የሚያየን፣ የሚሰማን ምንይለናል፣ ይታዘበናል አይሉም። ሼም አያውቁም። የተመቱ ናቸው። አእምሮ የተነሡ። ጭራሽ የአረብ፣ የአውሮጳና የአሜሪካ ሴቶች ይራኮቱባቸዋል። በእሷ ቤት ጀግና አግኝታ፣ ወንድ አግኝታ፣ ዳግማዊ አፄ ቴዎድሮስን፣ ገብሬዬ ጀግናውን አግኝታ ልቧ ውልቅ ብሏል። እነዚህ የኢንተርኔት ላይ ጀግኖች፣ የፌስቡክ ላይ ወንድኛ አዳሪዎች የሴቱን ልብ አውቀው ይጫወቱባቸዋል። እንደከበት ይነዷቸዋል።"…ብር አንሶኝ ነው ወንድምዋ ይለዋል ከተማ ያለው ጎረምሳ ጫካ ላለው የፋኖ መሪ ተብዬው ቴክሳስ፣ ዜንጦ ጆሊ የፋኖ መሪ።• ባለፈው የላኩልህስ?~ እሱማ አለቀ። ኑሮ እኮ ተወዷል አብዋ።• ምን እየበተንከው ነው እንጂ?~ ማርያምን፣ ወላሂ በትኜው አይደለም።• በቃ እሺ ፈልጌ እልክልሃለሁ።~ እሺ ወንድምዓለም።"…ከዚያ መኪና ይታገታል፣ ሰው ይታገታል፣ ገበሬ ከብቱን ይዘረፋል። ነጋዴ ይገፈዳል። ወደ ሱዳን የሚሰደዱ ሱማሌዎች ይሸጣሉ። ይቸበቸባሉ። መሳሪያ ተዘርፎ ይሸጣል። ኮንትሮባንዱ ይጧጧፋል። ኩላሊት ይሸጣል። ባሪያ ይፈነገላል። ዳያስጶራ ይቀፈላል። ያ የተፈለገው ብር ሲሞላ ብሩ ለወንድም ለእህት ይላካል። የአፋብኑ የጎንደር ገንዘብ ያዥ ወደ መንግሥት ከድቶ ሲገባ 35 ሚልዮን ብር ነው እምጷ ቀሊጦ ያደረጋቸው።"…አሁን ላይ በኦሮሚያ ሸኔ መሆን፣ በዐማራ ክልል ጎንደር በእነዚህ ስር መሆን፣ በጎጃምም የእነ ማርሸት አስረስ ጥላሁን፣ በይፋትም የእነ መከታው ፋኖ መሆን ዲቪ ሎተሪ እንደወጣልህ ቁጠረው። በአንፃሩ ደግሞ ላስታ ያሉ ፋኖዎች የሚበሉት የላቸውም። የጎጃም ተዋጊ ፋኖው ቅማል ፈልቶበታል። መሪዎቹ የወርቅ ጉድጓድ ነው የሚያስቆፍሩት። ጎንደር ያለ ፋኖ በመከላከያ ተዋግቶ ይገደላል። እንደ ገና ደግሞ ከሸጋው ጌታቸው እና ከደረጄ ተባብሎ እርስ በእርሱ ይጠዛጠዛል። ይገዳደላል። መሪዎቹ ግን ጌታቸውን የገደሉ ባሪያዎች መስለው እንደምታዩአቸው የፌልም አክተር፣ ሞዴላ ሞዴል መስለው ፏ ሽር ብትን ዘጭ ብለው ይኖራሉ።"…ሁለዜ እንደምለው ዛሬም እደግመዋለሁ። የዐማራ ፋኖ ድብን አድርጎ አሳምኖ ያሸንፋል። እንዲህ ዓየነቶቹን የቋንጃ እከኮች አራግፎ ያሸንፋል። ደግሞም ማንም ሳይነካቸው ነው እርስ በእርሳቸው ተበላልተው ተጠፋፍተው የሚያልቁት። እደግመዋለሁ የዐማራ ፋኖ ትግል ቅዱስ ትግል ነው። ምክንያታዊም ነው። ወንፊት ማበጠሪያ ሰፌዱ ከሁሉም ፊት ቀርቧል። እያንዳንድህ ትበጠራለህ፣ ትጸዳለህ። የዐማራ ፋኖ ትግል ግን ጥርት፣ ኩልልል ብሎ እየፈሰሰ በድል ይጠናቀቃል።• ይኸው ነው።
    33,800video83223468331712Open in Telegram
  • Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

    12 Nov, 14:46

    "…መልካም"…እንደተለመደው እንደቤታችን ጠባይ በሌላ ቤት የማይገኘውን እና እንደኮሶ መራራ ጨክነው ቢጠጡት ፈዋሽ የሆነውን ነጭ ነጯን እውነት ማውጋት እንጀምር አይደል?
    31,1005621625916102Open in Telegram
  • Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

    12 Nov, 09:58edited

    • ሐሙስ ህዳር 3/2019 ዓመተ ምሕረት"…በድሮን ወላጆቻቸውን አጥተው እነርሱ ቆሳስለው በሕይወት የተረፉት የወለጋዎቹ ሕጻናት አሁንም በበረሃ መንገድ ላይ ናቸው። መንገዱ አድካሚ ነው። ገና ጎጃም አልገቡም። የቦንቡ ፍንጣሪ ቁስሉና የእሳቱ ቃጠሎ ማብረጃ ባይኖርም፣ ራብና ጥሙ የቁስል ጥዝጠዛው እንዳለ ቢሆንም እስከ አሁን ድረስ ግን ነፍሳቸወወ አለች። መጥፎ ዜናም የለም። ትናንት ደክምክም ብላ የነበረችውም ሕፃን እስከአሁን በሕይወት አለች። ከሃኪም፣ ከእህልና ውኃም እንዲያደርሳቸው ጸልዩላቸው።"…የእናንተ ርብርብ ግን ይገርማል። እጅግም አስደንቆኛል። እግዚአብሔር ያክብራችሁ። እግዚአብሔር ይስጣችሁ። ከሃኪም ዘንድ በሰላም ይድረሱ እንጂ በዚያ ሁሉም ነገር ዝግጁ ሆኖ እንዲጠብቃቸው በእህታችን በኩል ዝግጁ ተደርጓል። ማረፊያቸው ጭምር ተዘጋጅቷል። ሁላችሁንም እግዚአብሔር ይስጣችሁ። ከእንዲህ ያለ ከባድ አሰቃቂ ከሆነ ኀዘን መከራ ይሰውራችሁ።• አሜን እናንተ ግን እንደምን አደራችሁ…?
    34,000video614412185511712Open in Telegram
  • Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

    11 Nov, 18:31

    "…ለምወደው እጅግ ለማከብረው ለማደንቀው ለቦለጢቃ ሊቁ፣ የጎጃምን ትግል አፈር ደቼ ላበላው፣ ጀግኖችን አጥፍቶ፣ የበላይ ዘለቀን ልጆች ሽባ ላደረገው፣ ለማርሸት ታዛዥ ለጠበቃዬ አስረስ መዓረይ እኔ ነጠላ ለባሹ፣ ሥዕለ አድህኖ ፊት ቆሜ ሻማ እያበራሁ ሕዝቡን አቢዩዝ የማደርገው ዘመዳችሁ የሰጠሁት መልስ ያነበባችሁትን ይመስላል።"…በነገራችን ላይ እኔና አስረስ ከተነጋገርንባቸው፣ ከተጨቃጨቅንባቸው፣ ዝም ጭጭ ካስባልኩበት ትንቅንቃችን 0.0001 % እስከአሁን አልተነፈስኩም።"…ፈልጎኝ፣ አስፈልጎኝ፣ ከአንተ ጋር ማውጣት አልፈልግም። አንተ የቦለጢቃ ሊቅ ነህ፣ እኔ ደግሞ እልም ያልኩ ማይም ነኝ። እናም ከአንተ ጋር ማውራት አልፈልግም እያልኩት በግድ ፈልጎኝ የመጣው እሱ ራሱ ነው። መጥቶም ግን እኔ እንደነ መሳይ አይደለም ያስተናገድኩት። እንዴ ይሄን ደግሞ ማን ነገረህ? ብሎ እስኪደነቅብኝ ድረስ ነው ገትሬ ያናዘዝኩት። መንጋው ይሄ አይገባውም።"…በጫጫታ ስብዕና አይገነባም። በቲፎዞ መክበር የለም። እንደ ባዬ ደስታ ያሉ በትግሉ ሜዳ ላይ ተቀምጠው ወንድማቸውን የአንበሳ ጫማ አከፋፋይ፣ ባለ ኤንትሬ መኪና ባለቤት የሚያደርጉ ዘራፊዎችን አጠገቡ ኮልኩሎ "ተስፋችን፣ መዳኛችን፣ አምባ መጠጊያ አለታችን እያለ ሲያንቆለጳጵሰው ውሎ ቢያድር የአስረስን ሾተላይነት መቀየር አይቻልም። ዲያብሎስን መልአክ ለማድረግ አይሞከርም። ዲያብሎስን መገሰፅ፣ ማዘዝ፣ ልቀቅ፣ ውጣ ማለት ብቻ ነው ትግሉን ጤነኛ የሚያደርገው። የዐማራ ትግል እንዲፈወስ ከተፈለገ የጎጃሙን ፋኖ አመራር ከጥቂቶቹ በቀር ጠራርገህ አውጥተህ በዘመድ፣ በጓደኛ ሳይሆን በሙያ፣ በብቃት፣ በችሎታና በጀግንነታቸው እየተመዘኑ የሚመሩ ከታች ያሉ የተደበቁ ዕንቁዎችን መማምጣትና መተካት ሲቻል ብቻ ነው።"…ፈንዳ፣ ጧ በል እኔን ከዳንኤል ክብረት ጋር አታነጻፅረኝ። ዳንኤል ክብረትን አፈር ደቼ ያበላሁት እኔው ዘመዴ ነኝ። ከጃዋር መሀመድ ጋር አታመሳስለኝ። እንደው ቢጠፋ ቢጠፋ ከጠወልዋሌ፣ ከተልባ ስፍር፣ ከገበቴ ውኃይ በሞቀበት ከሚፈላው መርቃኙ ባለ ሜንጫ ጋር ታወዳድረኛለህ እንዴ? ሥነ ሥርዓት። የእኔ ውለታ ዛሬ ላይ ላይታይህ ይችላል። የእኔ ተጋድሎ የሚፈነዳው፣ የሚያብበው ነገ ነው። ነገ ስታጣኝ ነው የሚገባህ። ለማንኛውም የዐማራ ትግል መዳኛዬ ነው። የምጸድቅበት። እናም ለጽድቄ ነው እንዲህ ወጥሬ የምታገለው።• ለዘመድኩን ከፍዬዋለሁ የሚል ካለ በአናትህ ተገልበጥ በሉት። ንገሩልኝ። የእነ አዝማሪት ጋለሞታ አልማዝ ባለጭራዋን ተቅማጥ በተቅማጥ የሚያደርግ ስድብ እየጠጣሁ ግግም ብዬ ባላየ፣ ባልሰማ እየተፈጣፈጥኩ ያለሁት። የዐማራ ትግል የጽድቅ አክሊል ስለሚያስገኝልኝ ብቻ ነው። ለዐማራ በማገዝህ የምታተርፈው ስድብ ብቻ ነው። ዐማራ የሚገባው ውሎ አድሮ ነው። ወይኔ ዘመዴ እኮ ነግሮን ነበር የሚለው ከሁለት ዓመት በኋላ ሁላ ነው። ገንዘብ ለማግኘት የኦሮሞ እና የትግሬን ቦለጢቃ ነው መደገፍ። ትንበሸበሻለህ በፈረንካ። ዐማራ ጋር ወፍ የለም። በሰማይ ነው የሚከፈልህ። አለቀ።https://t.me/ZemedkunBekeleZ/37110"…ለማንኛውም ለምወደው፣ እጅግም ለማከብረው ለመዓረይ እኔ ነጠላ ለባሹ ዘመዴ የሰጡህትን መልስ እንዴት አያችሁት? ሓሳብ አስተያየታችሁን በነፃነት ✍✍✍
    34,800video78423259292517Open in Telegram
  • Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

    11 Nov, 17:20

    • ይድረስ…"…እጅግ ለምወደው እና ለማከብረው ለታላቁ ጠበቃ ለአይቶ አስረስ መዓረይ…• መስመር ላይ አግኝቼዋለሁ… አለ መሳይ መኮንን"…አሸባሪ፣ ታጋዮች፣ የመንግሥት ተቀናቃኝ ፅንፈኛ ኃይሎች ተብለው ከተፈረጁት የትግል መሪዎች መካከል 24/7 በኢትዮ ቴሌኮም ኔትወርክ ፌስቡክ ላይ ተጥዶ፣ የኋትስአፕ ስብሰባ እየመራ፣ ከኦነጉ ሞገስ ዘውዱ ጋር ሳይቀር ኢንተርቪው እየሰጠ ድሮን የማይፈራው ጠበቃ አስረስ መዓረይ ምን እንዳደረኩት እንጃ ብቻ ለሁለተኛ ጊዜ ከግንቦቴው መሳይ መኮንን ጋር ሆኖ ስሜን አንስቶታል። እናም ለወዳጄ እጅግ አድርጌ ለማከብረው ለእኔ ሾተላይ፣ መሰሪዬ መዓረይ አጠር ብላ ረዘም ያለች ምላሽ እሰጠው ዘንድ ወደድኩ። ወደድኩናም ዛሬ።ላቅርብ ወይስ ነገ ስላችሁ እናንተው ዛሬ ይቅረብ አይደርብን ስላላችሁ እነሆ በእናንተ ምርጫ ለዛሬ አቀረብኩላችሁ። መልካም ንባብ።• ከመስመር ላይ የማይጠፋውን አስረስን መሳይ መኮንን መስመር ላይ አግኝቼዋለሁ በማለት ጥያቄውን ጀመረ። መሳይ የጠየቀው ስለ ጃዋር፣ጃዋር ስለ ደቡብ ጎንደሩ ትግሬ ስለ አያሌው መንበር ወዘተ ነበር። አስረስ ግን በንዴት የተጠየቀውን ትቶ እሁድ ለት በነጭ ነጯን ከዘመዴ።መርሀ ግብሬ ላይ ስለገባሁለት አጋጣሚውን ተጠቅሞ ሊገባልኝ ስለፈለገ እንዲህ በማለት ጀመረ…"…የብልፅግና ዲጅታል ሚሊሻዎች ብቻ ሳይሆኑ… በዐማራ ትግል ስም የተደበቁ፣ ማንነታቸው የማይታወቅ፣ ይሄንን ትግል በተለያየ ስልት በመከፋፈል፣ የግል ጥቅማቸውን ለማሳደድ የሚፈልጉ፣ ምስኪኑን ሕዝብ በሃይማኖታዊ መንገድ ነጠላ ለብሰው፣ ሥዕለ አድህኖ አስቀምጠው ሻማ እያበሩ ምስኪኑን ማኅበረሰብ አቢዩዝ የሚያደርጉ፣24 ሰዓት የእኛን ስም በማንሣት፣ ቤተ ሰቦቻችንን በማንቋሸሽ፣ በጎ ምግባራችን ክፉ እንደሠራን አድርገው፣ በጣም በጣም በከፍተኛ ደረጃ የሚዘምቱብን ግለሰቦች እና ቡድኖች አሉ። የእነሱን ሁሉ ዘመቻ ተቋቁመን ነው ጸንተን ያለነው…• ከዚህ ንግግሩ ተነሥተን እንተንነው እንግዲህ…ሀ፦ በዐማራ ትግል ስም የተደበቁ፣ሁ፦ ማንነታቸው የማይታወቅ፣ሂ፦ ይሄንን ትግል በተለያየ ስልት በመከፋፈል፣ የግል ጥቅማቸውን ለማሳደድ የሚፈልጉ፣ሃ፦ ምስኪኑን ሕዝብ በሃይማኖታዊ መንገድ ነጠላ ለብሰው፣ ሥዕለ አድህኖ አስቀምጠው ሻማ እያበሩ ምስኪኑን ማኅበረሰብ አቢዩዝ የሚያደርጉ፣ሄ፦ 24 ሰዓት የእኛን ስም በማንሣት፣ህ፦ ቤተሰቦቻችንን በማንቋሸሽ፣ሆ፦ በጎ ምግባራችን ክፉ እንደሠራን አድርገው፣ በጣም በጣም በከፍተኛ ደረጃ የሚዘምቱብን ግለሰቦች እና ቡድኖች አሉ።• ከሀ እንጀምር… ሀ፦ በዐማራ ትግል ስም የተደበቁ፣ይሄ እኔን አይመለከተኝም። እኔ በዓማራ ትግል ውስጥ አልተደበቅኩም። ስሜን እና አድራሻዬን፣ የስልክ ቁጥሬን ሳይቀር በግልጽ አስቀምጬ ነው የዐማራ ትግል ውስጥ የገባሁት። ሠራዊት የለኝም። ብርጌድ የለኝም። ግን የዐማራ ትግል መዳኛዬ ነው ብዬ በግልጽ ተናግሬ ነው ሓሳብ በመሸጥ ተሳትፎ እያደረግኩ ያለሁት። ሃሳቤ ገዢ እስካገኘ ድረስ ደግሞ ከዐማራ ፋኖ ትግል አልወጣም። የከሰረ ነጋዴ፣ አጭበርባሪና ሾተላይ ብቻ ነው ከዘመኑ የተቀደሰ የዐማራ ፋኖ ትግል የሚወጣው።ሁ፦ ማንነታቸው የማይታወቅ፣ አለ…"…ዘመድኩን በቀለ እባላለሁ፣ የሐረርጌ ቆቱ ነኝ ካልኩ ቆየሁ። አክሊለ ገብርኤል ክርስትና ስሜ ነው። የምሥራቅ ሰው ነኝ ያውም የሐረርጌ መራታ፣ ባለ ማዕተብ የተዋሕዶ ልጅ፣ የሥላሴ ባርያ የድንግል አሽከር ብዬ እኮ ደጋግሜ በአፍም፣ በመጣፍም ተናገርኩ። ሀገረ ጀርመን ከራየን ወንዝ ማዶ የስደት ሀገሬ ነው። +4915216158791 በእጄ የምይዘው የእጅ ስልኬ ነው። ከዚህ በላይ ማንነቴን እንዴት ልገለጽ መዓረይ ወንድሜ?ሂ፦ ይሄንን ትግል በተለያየ ስልት በመከፋፈል፣ የግል ጥቅማቸውን ለማሳደድ የሚፈልጉ፣ አለ…"…በተቃራኒው አወራህ። እኔማ ከፋፋዮቹን አስቀድሜ አናት አናታቸውን እሳት በሚተፋ ብዕሬ ደብድቤ ከፋፈልኳቸው። መዶሻ ሆኜ ሾተላዮቹን ከቅዱሱ የዐማራ ፋኖ ትግል ነቃቅዬ አወጣኋቸው። ጣልኳቸው። የምስኪኑ የዐማራ አምላክ በእኔ በደካማው የሐረርጌ ቆቱ፣ ነፍጠኛ የደብተራ ልጅ ላይ አድሮ እሬቻቸውን አበላቸው። መከፋፈል እኔን አይመለከትም። የግል ጥቅም ያልከውም አይመለከተኝም። የግል ጥቅም ከተነሣ አንተ በብዙ የምትጠየቅበት ወንጀል ገና ይጠብቅህሃል። መርጦለማርያም ላይ ብቻ የገዳሙ አባቶች ከ30 ሚልዮን ብር በላይ መልስ ሲሉህ እሺ ብለህ ለጥዋት ቀጥረህ፣ ብሩን ይዘህ እነ ዝናቡ ጋር የተደበቅከው፣ በዚያ ላይ መርጦለማርያም ያሳረድካቸው እነዚያ ወጣቶች ደም ገና ይፋረድሃል። ከእንግሊዝ እነ ኢንጂነር አሜሪካ ላለችው ሚስትህ እና ልጆችህ ለፋኖ የተሰበሰበ ዶላር የሚከፍሉት እኮ ጥቅም ስላለህ ነው። በእነ መዓዛ መሀመድ፣ በእነ ተስፋዬ ወልደ ሥላሴ በኩል እየተለመነ አንተ እና ማርሸት የምትጫወቱበት ዶላር ቢደርቅም ከጎጃም ባለሀብቶች የምትዘርፈው ብር መች አርክቶህ ያውቅና አባቴ። ቢያንስ ከአርበኛ ውባንተ ሚስት ላይ የዘረፈከው 20 ሚልዮን ብር መች እንቅልፍ ይሰጥህና መዓረይ። እነዚያን የጎጃም ሴቶች ያስረሸንከው መች ይፋታህና አስረሴ? የጎጃም ዐማራን ጀግና ጀግና ፋኖ አስረሽናችሁ፣ አስወግዳችሁ ስታበቁ፣ በጎጃም የዐማራ ፋኖን ትግል እንኩትኩቱን አውጥታችሁ ስታበቁ የምን ስለ ጥቅም ማውጣት ነው? እኔን በተመለከተ ከዐማራ ትግል በተለይ ከዐማራ አክቲቪስት በተለይ ከአክስትህ ከአልማዝ ባለ ጭራ የተረፈኝ ስድብ ነው። ተቅማጥ የሚያስመጣ ስድብ። "ዘመዴ ግርማን እና ቤተልሄምን ከሰው አትቁጠራቸው" ብትለኝም ያተረፍኩት ውርደት ነው።
    34,3001,08021974202020Open in Telegram
  • Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

    22 Sept, 16:44edited

    👆②✍✍✍ "…በአላማጣ ዙሪያ ዛሬ ውሎውን ይልማ መርዳሳ አቢይ የፈረመበትን ከ17 ጊዜ በላይ የድሮን ጥቃት ፈጽሟል። በዚህም ወያኔ የተለያዩ ተተኳሾችን እና አንዳንድ ነገሮችን ትሸከማላችሁ ብላ በአንድ ቦታ ላይ ያስቀመጠቻቸው የቀን ሠራተኞች፣ ለሸክም ይሆናሉ ብላ የገዛቻቸው አህያ፣ ግመል እና የተለያዩ እንስሳት በአንድ ላይ አከማችተውት የነበረ የተለያዩ ተተኳሾች እና መሳሪያዎች በድሮን ተመትቷል። በነገራችን ላይ ዘመዴ ሕወሓት መችም አትማርም። እንዴት ብትለኝ ፋኖን ተመልከተው ትግሉ ከተጀመረ ጀምሮ በዚህ መጠን በድሮን ተመትተው አያውቁም። እነዚህ ግን ሁሌም በጅምላ እንደተጨፈጨፉ ነው። ለምን ከፋኖ እንደማይማሩ አይገባኝም? ሌላው ደግሞ ዐማራ ጥብቅ ዲሲፕሊን ስላለው ምስጢር ጠባቂ ሆኗል፣ ትግሬ ግን ስለተከፋፈለ አስተኳሹ የትየለሌ ሆኗል። ለዛሬ ይኸው ነው በቀጣይ ነገሮችን እየተከታተልኩ አሳውቅሃለሁ። ሰላም እደር ፊልድ ማርሻል ሃኒ ባጀር ዘመዴ ብላኛለች።"…እሺ የርግቤን ሪፖርት እንዴት አያችሁት። ሪፖርት መረጃዋ ከተመቻችሁ አስተያየታችሁን ጻፉላት። ቤተ መንግሥት እና መከላከያ፣ ብሔራዊ መረጃ አገልግሎት የሄዱት ወፎችና እርግቦቼም በስራ ላይ ተጠምደዋል። በተለይ ኮምፒዩተር አካባቢ ያሉቱ ጉድ ነው እያሳዩኝ ያሉት።• ስምምነ ‼
    15,000388169118444Open in Telegram
  • Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

    22 Sept, 16:44edited

    • ወቅታዊ የሸዋና የራያ ሁኔታ፦"…ፊልድ ማርሻል ሃኒባጃር ዘመዴ ሆይ ! እኔ ወደ ወሎ ወደ ቤተ ዐምሓራ ከመሄዴ በፊት ገና መንገድ ስጀምር ብዙ መኪና ከቤተ ክህነት ሲወጣ ስላየሁ ወዴት ነው የሚሄዱት ብዬ እስቲ ልከተላቸው ብዬ መከተል ጀመርኩ። የምሥራቁን አዲስ አበባ በር ይዘው መጓዙ ጀመሩና ሞጆ ላይ ወደ ዝዋይ መስመር ሲሄዱ ተከተልኳቸው። ከሰዓታት በኋላ ሻሸመኔ ደረሱ። ዝቅ ብዬ ሳይ የቤተ ክርስቲያን ምረቃ ነው አሉኝ። የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ እንዳይሰቀል የኦሮሞ ወሀቡያ እስላሞች እና የኦሮሞ ጴንጤና ዋቄፈና ባለ ሥልጣናት መከልከላቸውን፣ የተሰቀለውንም ማውረዳቸውንም ሰማሁ።"…ቆይቶም የሀገረ ስብከቱ ሊቀጳጳስ ነፍሰ ገዳዩ አቡነ ዜና ማርቆስ እኔም እኮ እሮሞ ነኝ፣ ስለዚህ ሰንደቅ ዓላማው መሰቀል አለበት ብለው ቆመው ቢያሰቅሉም እስላሞቹ ባለ ሥልጣናት፣ አንተ ኦሮሞ ብትሆንም የቱለማ ኦሮሞ ነህ። ከኦሮሞነትህም ዐማራነትህ ነው የሚጎላው። የቱለማ ኦሮሞ የኦሮሞነትንም መስፈርት አያሟላም። የዓለም ስምህም አሰፋ ነበር። አሰፋ ደግሞ የኦሮሞ ስም አይደለም። የጵጵስና ስምህም ዜና ማርቆስ ነው። ዜና ማርቆስ ደግሞ የቡልጋ ሰው ናቸው። እናም በኦሮሞ ጉዳይ አያገባህም። መብቱ የእኛ ነው። የፋኖ ባንዲራ አንሰቅልም። የኦሮሞ ባንዲራ የእኛን የአባ ገዳንም ባንዲራ አንስቀልም፣ የግድ ጨርቅ መሰቀል አለበት ካላችሁ የአርጀንቲናነ እና የእስራኤልን ሰማያዊና ነጭ ስንሰቅልላችሁ ነበር። እሱ ደግሞ እስራኤል ፍልስጤምንና ኢራንን ስለደበደበች ድጋሚ በኦሮሚያ እኛ የወሀባ እስላሞች እያለን አይሰቀልም። ባይሆን የስልጤ ባንዲራ
    15,000376625421Open in Telegram
  • Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

    22 Sept, 15:05

    • ዴየሞ።መጣች…"…የሸዋና የራያ ወቅታዊ ሪፖርት ይዣለሁ ነው የምትለው። እኔ በሰሜን በኩል በሱሉልታ በደራ መስመር ወደ አምባሰል ስሔድ ርግቤ ደግሞ በሸዋ ለ ወደ ራያ ነበር የበረረችው። ያየችውን እና የታዘበችውን እያስረከበችኝ ነው።• መልእክቷን ከፍቼ ላንብበውና ቀሽሬ እንደወረደ ላቅርብላችሁ አይደል?
    17,8004801459113127Open in Telegram
  • Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

    22 Sept, 13:50

    • ግሸን ደርሻለሁ…"…ግሸን ከአዲስ አበባ ደሴ 400 ኪሎ ሜትር ከተጓዙ በኋላ ከደሴ 82 ኪሎ ሜትር ተጉዘው በአጠቃላይ ከኢትዮጵያ ዋና ከተማ ከአዲስ አበባ በ482 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኝ የጌታችን የአምላካችን እና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ግማደ መስቀሉ የሚገኝባት ተራራ ናት።"…በአሁን ሰዓት የግሸን ደብረ ከርቤ ገዳም በዐማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ወሎ ቤተ ዐምሓራ ምኒልክ ዕዝ ቁጥጥር ስር ነው። ባለፈው ሳምንት የአገዛዙ አንድ ሙሉ ክፍለጦር በደቡብ ወሎ በዳውንት ያለቀው እና የተደመሰሰው በቆረጣ ገብቶ ግሸንን አስለቅቆ አለሁ፣ ሁሉ በእጄ ሁሉ በደጄ ነው ለማለት ነበር። ግን አልተሳካም። አሁን ግሸን በቆንጆዎቹ ቁጥጥር ስር ናት።"…የኦሮሙማው መንግሥት በትእቢት ተሞልቶ፣ በእብሪት አብጦ፣ ያጎረሱትን እጆች በሙሉ ነክሶ፣ ውለታ ቢስ ሆኖ፣ የበላበትን መሶብ ገበታ ገልብጦ፣ ወጪት ሰባሪ ሆኖ ተወጣጥሮ በዐማራ ላይ የሠራው ግፍ አሁን ተግባራዊ ዋጋ ወደማስከፈሉ ገብቷል። በሀገረ ኢትዮጵያ ብዞ ሚልዮን ሰዎች ከሚሳተፉባቸው ክብረ በዓላት በቁጥር ጥቂት እንደሆኑ ይታወቃል። የቁልቢው ቅዱስ ገብርኤል፣ የአክሱም ጽዮን፣ አዲስ አበባ የመስቀል ደመራ፣ የጎንደር እና የአዲስ አበባ የጥምቀት በዓል፣ ደብረ ሮሐ ቅዱስ ላሊበላ እና ግሸን ደብረ ከርቤ ማርያም ናቸው።"…ከእነዚህ ውስጥ ሙሉ ክልል ትግራይ በትግሬዎቹ እጅ ነው። ብልፅግና ምንም ዓይነት ቁጥጥር የለበትም። ግሸን ደብረ ከርቤም ከአገዛዙ ቁጥጥር ውጪ ነው። የአካባቢውንም፣ የገዳሟንም ፀጥታ የሚያስከብረው የዐማራ ፋኖ ነው። ይሄ ማለት ለአገዛዙ
    20,800video6621361071676Open in Telegram
  • Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

    22 Sept, 12:34edited

    ማስታወሻ…"…እኔና ወፎቼ በነበረን ስብሰባ በጊዜ የተገደበ ሹመትም እንደተሰጠኝ ላሳውቃችሁ እወዳለሁ። ከዛሬ መስከረም 12/2019 ዓመተ ምሕረት ከዕለተ ቅዱስ ሚካኤል ጀምሮ አስቸኳይ ጉዳይ ገጥሞኝ ወደ አጎት ሀገር ጀርመን ወደ መጠለያ ዋሻዬ እስክመለስ ድረስ በኢትዮጵያ ቆይታዬ አዲሱ መጠሪያ ስሜ የሚከተለው ይሆናል።• ፊልድ ማሽራል ሃኒ ባጀር ዘመዴ• አከተመ።"…ከተቻለ እንዲያው ደስስ እንዲለኝ ለበአሉ ድምቀትም ሲባል በአዲሱ ማእረጌ አሁኑኑ መጥራት ብተጅምሩ ብዬ አሳስባችኋለሁ። ማን በጀር ነበር ያሉኝ እኔኑ ጠፋኝ ስሜ። አዲስ ስም ስለሆነ እስክትለምዱት ድረስ ብትቸገሩ ነው።• ዘመዴ ከራየን ወንዝ ማዶ ስመለስ ነው ይሄኛው ማን ባጀር የሚለው ግን በሃገር ቤት ቆይታዬ ወቅት የምጠራበት ስሜ ነው። ሰምታችኋል። 😂 …ዘና ፈታ እያልን ነው የምንዘግበው። መጨናነቅ ብሎ ነገር የለም።• እንዴት ነኝ ግን ፊልድ ማረሻነቱ ተስማምቶኛል?
    21,300510224401087Open in Telegram
  • Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

    22 Sept, 11:55

    • መልካም…"…የተወደዳችሁ የቴሌግራም መንደር ነዋሪዎች ሆይ! እኔ ተወዳጁ፣ ተናፋቂው፣ የሥላሴ ባርያ የድንግል አሽከሩ የምሥራቁ ሰው የሐረርጌው ቆቱ ባለ ማዕተቡ የተዋሕዶ ልጅ የተነከሩት ፊልድ ማረሻ ዘመዴ እና ተወዳጆቹ ታማኞቹ ወፎቼ እንደተለመደው ለእናንተ ትኩስ፣ ትኩስ የሆኑ መረጃዎችን ልናካፍላችሁ በማሰብ ረዘም ካለ የእረፍት ጊዜ በኋላ አሁን ወደ እናንተ ተመልሰናል።"…እኔና ወፎቼ ረዘም ላሉ ቀናት በመጪው ጊዜ ለሚጠብቀን ከፊታችን ላለው የጦርነት እና የራብ ጊዜ ሕዝብ መረጃ በሚያገኝበት አግባብ ላይ ለመመካከር በማሰብ ሌት እና ቀን ግሩም የሆነ ስብሰባ እና ውይይት ስናደርግ ከርመን ሁላችንም ለእረፍት ከሄድንበት ተመልሰን የሥራ ስምሪት ወስደን ወደ መሬት ወርደን ሥራ ለመጀመር እንቅስቃሴ ጀምረናል። ንስሩ ብቻ ነው ለጊዜው አሜሪካ ላይ በምሥራቀ ፀሐይ አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የተፈጠረን ነውር ለማጽዳት፣ ሴራ ለማክሸፍ የሚቆየው እንጂ ሌሎቹ ወፎቼ እና ርግቦቼ በሙሉ የሥራ ስምሪት ወስደው በየቦታው እንቅስቃሴ ጀምረዋል። የቤተ መንግሥቱ ሌባም መረጃ ለመስጠት ዝግጅቱን ጨርሷል።"…እኔም ከነ ሙሉ የፊልድ ማረሻ የማእረግ ልብሴ በቀጥታ በርሬ ዛሬ ንጋት ላይ አዱ ገነት አዲስ አበባ የገባሁ ሲሆን፣ መንገዱም፣ መንደሩም ፍርስርስ ብሎ አበባና ሳር ብቻ ሆኖብኝ ቅብዥርዥር ቢልብኝም ለትንሽ ሰዓት ዞር ዞር ብዬ አዱ ገነትን አይቼ፣ ከመስቀል በዓል በፊት ለጠቋር ዋቃ ጉራቻ በአል የቱለማ ኦሮሞዎቹ ከወርሀ ነሐሴ ጀምረው በ4 ቢልዮን ብር የኦሮሙማው በጀት በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ላይ የሚጨፍሩ
    22,100576184522543Open in Telegram
  • Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

    22 Sept, 09:09

    "…የእኛ እግዚአብሔር በተለይ ደግሞ የእኔ እግዚአብሔር ይችላል። አምላኬ ይችላል። የእውነት፣ የሐቅ፣ ልብና ኩላሊትን የሚመረምር አምላክ ሁሉን ማድረግ ይችላል። እግዚአብሔር አሸናፊ ነው።"…ዘወትር ከፊት ከኋላዬ ቅደሚ የምላት የእኔ አማላጅ፣ የእኔ እናት፣ የአምላክ እናት እመቤታችን ቅድስት ድግል ማርያም ለአፍታም ያህል ለሰከንዶች ተለይታኝ የለማወቋነ የማረጋግጠው በዚህ በዚህ ጊዜ ነው።"…የተወረወረብኝን ጦር አምላኬ አበባ አደረገልኝ። አዲስ ዘመንም፣ አዲስ የሥራ በርም ከፈተልኝ። የተወረወረብኝን ድንጋይ ሰብስቤ ምርጥ ቪላ፣ ምርጥ ሃውልት እንዳንፅም ሁሉን አመቻቸልኝ። ወጥመድ ተሰበረ። እኔም አመለጥኩኝ። እግዚአብሔር ይመስገን። እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ከሆነ ሁሉም ነገር ይለወጣል። እግዚአብሔር ይመስገን። ዳይ ወደ ሥራ ተንቀሳቀስ። ይቅርታ ነገሩን ሁሉ ከትቶታል። አለቀ፣ ሃላስ።• እናንተ ግን እንደምን አደራችሁ?
    25,60060328577885Open in Telegram
  • Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

    21 Sept, 20:02edited

    • ልዩ ዝግጅት…• በዮፍታሔ ሾው የቲክቶክ አዳራሽ https://www.tiktok.com/t/ZTy1mV8UR/• ኢትዮ ቤተሰብ ሚዲያ… https://www.youtube.com/live/gAGwW9brldw?is=XEOhWZZH8Ky44hGS"…ሁላችሁም ተጋብዛችኋል
    31,2003269945964Open in Telegram
  • Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

    21 Sept, 08:41

    መስከረም 11/2019 ዓመተ ምሕረት"…የጥምረቱ ክርክር፣ ሙግት ይቀጥል። የአገዛዙም ሆነ የተቃዋሚው ኃይል ደጋፊዎች ጎራ ለይታችሁ በቃላት መጠዛጠዙን ቀጥሉ። ይበጀኛል ያላችሁትን ደግፋችሁ የራሳችሁን ጻድቅ፣ ሌላውን ኃጥእ፣ ቡልጉ፣ ጭራቅ አድርጋችሁ ኡኡ፣ ወየው ወየው ማለታችሁማለታችሁም ሆነ ለምትደግፉት አካል ሽንጥን ይዞ መከራከር ተፈጥሮአዊ ነው ቀጥሉበት። ሄዶ ሄዶ አንደኛችሁ በፈሊጥም ሆነ በፍልጥ ማሸነፋችሁ አይቀርም። እናም ተሟገቱ። ግን ደግሞ የድርቁ ነገር እንዳይረሳ።"…ድርቁ ከመጣ፣ ከሰፋ መከላከያም ፋኖም፣ ጥምረቱም ሊያስቆመው አይችልም። ለመዋጋትም፣ ለመከራከርም ምግብ ወሳኝ ነው። ያለምግብ ክርክርም፣ ጦርነትም ዋጋ የለውም። ለመዋጋትም ሆነ ለመከራከር በቅድሚያ መብላት አለብህ። በባዶ ሆድ ጦርነትም ክርክርም ከንቱ ነው። የራበው ሰው አቅመቢስ ነው የሚሆነው። እናም ተዋጊዎችም፣ ተከራካሪ ደጋፊዎችም ከውጊያችሁ እና ከክርክራችሁ ጎን ለጎን ስለ ድርቁ፣ ስለራቡ እየጸለያችሁ ቢሆን ይመከራል።"…እግዚአብሔር ሊቀጣን የመጣበት መንገድ እየገረመኝ ነው። ከመላ ሀገሪቱ የሚደርሱኝ መረጃዎች እያስደነገጡኝ ነው። ተመስገን እዚህ እዚህ ቦታ እንኳን ቢሆን ድርቁ እዚህ እዚህ አከባቢ ምርት ስላለ ይካካሳል ብዬም እንዳልፅናና የሚያደርግ ነገር ነው እያየሁ ያለሁት። እናም አገዛዙም ቅድመ ዝግጅት ቢያደርግ፣ ሕዝቡም ቢጸልይ መልካም ነው።"…ወለጋ ኦሮሞዎቹ ዐማራን ጎዳን ብለው እህል ከጎተራ፣ ለንግድ የሚሄደውን ከመኪና አውርደው እሳት ለቀቁበት። የዐማራ አምላክ ደግሞ በሌላው የኦሮሞ ግዛት፣ ትርፍ አምራች
    38,400video72334083531310Open in Telegram
  • Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

    20 Sept, 21:05

    መልካም…"…ዛሬም እንደ ወትሮው በቲክቶክ መንደራችን ከ60 ሺ በላይ ሕዝብ መርሀ ግብራችንን ተከታትሎዘል። እግዚአብሔር ይመስገን። 🙏🙏🙏• ምሽቱ እንዴት ነበር?
    39,700572212691486Open in Telegram
  • Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

    20 Sept, 16:08edited

    "…ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር"…በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ምሽት ልክ 01:30 ሲሆን በዘመድ ቴቪ መርሀ ግብሩ ይጀምራል። እንደተለመደው ገባ ገባ በሉና ጠብቁን።• ZemedTv 👉 zemedtv.com/live.html• በትዊተር (×) 👉 x.com/i/broadcasts/1OGwbnAbbLPKB• በራምብል 👉 rumble.com/v7fqulu--zemede-september-20-2026.html?e9s=src_v1_cbl%2Csrc_v1_upp_a• ቲክቶክ 👉 tiktok.com/@zemedkun.b• በሳታላይት ቴሌቭዥን 👉 Zemed TV Yahsat 52.5° East 11977 H 27500• በሳታላይት ቴሌቭዥን 👉 Mereja TV Niesat / Eutelsat 8 B Freq. 11.636 Vertical SR: 27.500
    41,700313155231663Open in Telegram
  • Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

    20 Sept, 15:20

    • በዛሬው መርሀ ግብራችን…"…ልጅቷ " ፀረ ኢትዮጵያ የጨረቃ ጳጳሱን ለምን ራሷን ለአደጋ አጋልጣ እንደቀረጸቻቸው ከራሷ ከልጅቷ አንደበትም ትሰማላችሁ" ።• ዛሬ ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር ቃሪያ በሚጥሚጣ የመሰለ ዝግጅት ነው።• ዝግጁ?
    40,7004531992723128Open in Telegram
Download the series as CSV
A feedback bot for your channel — free

Followers write to the bot, you answer by reply, your account stays hidden. Created in one tap.

How it works →
Create the bot